No summary available.
መጋቢት 18 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ ሂሩት መለሰ Aብዱራሂም Aህመድ መድህን ኪሮስ ዓላ መሐመድ Aመልካች፡- ወ/ሮ Aስናቀች ሲሻው ቀረቡ ተጠሪ፡-
መዝገቡ የቀረበው የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመዝገብ ግንቦት 9 ቀን 1996 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔና የፍ/ጠ/ፍ/ቤት በይግባኝ መዝገብ ጥር 21 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ስላለበት በሰበር ታይቶ Eንዲታረምልን በማለት ሚያዝያ 1 ቀን 1999 ዓ.ም በተፃፈ Aቤቱታ በመጠየቃቸው ነው።
የክርክሩ መሰረታዊ ጉዳይ በዚህ መዝገብ ተጠሪ የሆኑት ሰዎች Aንደኛ ተጠሪ የሟች ፊታውራሪ Aየነው ገብረመድህን ሚስት ከሁለተኛ Eስከ ሶስተኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱት ተጠሪዎች ደግሞ ልጆች መሆናቸውን በመግለጽ ሟች ፊታውራሪ Aየነው ገብረመድህን ለወ/ሮ ወለተኪዳን በህይወት Eስካሉ ድረስ ብቻ Eንዲኖሩበት መስከረም 22 ቀን 196A ዓ.ም ባደረጉት የስጦታ ውል በወረዳ 11 ቀበል 2 የቤት ቁጥር 631 የሆነውን ቤት ሰጥተዋቸው ነበር። ወ/ሮ ወለተኪዳን በህይወት በመኖራቸው በዚሁ ቤት ውስጥ ሲኖሩ ቆይተው የሞቱ ስለሆነ ቤቱን ያስረክቡን ብለው Aመልካችን በመክሰሳቸው ሲሆን የግራ ቀኙን ክርክር የሰማው የሥር ፍርድ ቤት ለተጠሪዎች ቤቱን ማስረከብ Aለባችሁ በማለት ወስኗል። Aመልካች ይግባኝ ብለው በፍ/ከ/ፍ/ቤት ይግባኙ ከተሰማ በኋላ የከፍተኛው ፍርድ ቤት የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ውሣኔን ሽሮታል። ተጠሪዎች ይግባኝ ለፍ/ጠ/ፍ/ቤት Aቅርበው ፍርድ ቤቱ የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ በመሻር የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ውሣኔን Aጽንቷል። Aመልካችና ተጠሪዎች በዚህ ፍርድ ቤት ክርክር በተነሳበት ቤት ላይ Aዋጅ ቁጥር 47/67 Eና የፍትሐብሕር ህጉ የንብረት ድንጋጌዎችና Eና የይርጋ ድንጋጌዎችን ስላላቸው ተፈፃሚነት የቃልና የጽሑፍ ክርክር Aቅርበዋል።
Eኛም መዝገቡን መርምረናል። መዝገቡን Eንደመረመርነው ወ/ሮ ወለተኪዳን ቤቱን ከያዙት በኋላ የከተማ ቦታና ትርፍ ቤትን የመንግስት ንብረት ለማድረግ Aዋጅ ቁጥር 47/1967 ታውጇል። በዚህ Aዋጅ Aንቀጽ 2/3/ሀ/ መሰረት ትርፍ ቤት ማለት Aንድ ቤተሰብ ወይም ግለሰብ ለመኖሪያ ከሚያስፈልገው ወይም ከያዘው Aንድ መኖሪያ ቤት ውጪ ያለ መሆኑ ተመልክቷል። ሟች ፊታውራሪ Aየነው ለወ/ሮ ወለተኪዳን በቤቱ የመጠቀም መብት ብቻ በውል ያስተላለፉ በመሆናቸው Aዋጁ ሲታወጅ በወረዳ 11 ቀበል 2 የቤት ቁጥር 631 Eና በወረዳ 11 ቀበል 02 የቤት ቁጥር 634 ባለቤት Eንደሆኑ ከህጉ ድንጋጌ ለመረዳት ይቻላል።
በAዋጅ ቁጥር 47/1967 Aንቀጽ 16 ንUስ Aንቀጽ 1 መሰረት ሟች ፊታውራሪ Aየነው የቤት ቁጥር 634 በምርጫ ይዘዋል። ይህ ከሆነ ወ/ሮ ወለተ ኪዳን ይኖሩበት የነበረው ቁጥሩ 631 የሆነው ቤት በAዋጁ Aንቀጽ 2/3/ሀ/ መሰረት ትርፍ ቤት ነበር። ፊታውራሪ Aየነው ይህንን የመጠቀም መብት ለወ/ሮ ወለተኪዳን በውል ያስተላለፉትን ቤት በAዋጅ ቁጥር 47/1967 Aንቀጽ 13 ንUስ Aንቀጽ 2 መሰረት Aዋጁ በታወጀ በሰላሣ ቀን ውስጥ ማስመዝገብና ማሣወቅ ሲገባቸው በዚህ የህግ ድንጋጌ መሰረት ግድታቸውን Aልተወጡም። ሆኖም ፊታውራሪ Aየነው ቤቱን በAዋጁ Aንቀጽ 13 ንUስ 2 መሰረት Aለማሣወቃቸው የቤቱ ባለቤት ይዘው ለመቆየት የሚያስችላቸው Aይደለም። ምክንያቱም በAዋጅ ቁጥር 47/1967 Aንቀጽ 13 ንUስ Aንቀጽ 1 መሰረት በAንቀጽ 11 ንUስ Aንቀጽ 1፣2 Eና 3 የተደነገገው Eንደተጠበቀ ሆኖ በማዘጋጃ ቤት ወይም በከተማ ክልል ውስጥ የሚገኝ ትርፍ ቤት ይህ Aዋጅ ከፀናበት ቀን ጀምሮ የመንግስት ንብረት Eንደሆነ በግልጽ ስለሚደነግግ ነው።
በመሆኑም የቤት ቁጥር 631 Aዋጅ በሚታወጅበት ጊዜ ትርፍ ቤት የነበረ በመሆኑ ከነሐሴ 1 ቀን 1967 ዓ.ም ጀምሮ በAዋጅ ቁጥር 47/1967 Aንቀጽ 13 ንUስ Aንቀጽ 1 መሰረት የመንግስት ንብረት ሆኗል። ስለሆነም ፊታውራሪ Aየነው ከነሐሴ 1 ቀን 1967 ዓ.ም ጀምሮ በፊት በነበረው ስያሜ በAዲስ Aበባ ከተማ Aስተዳደር ወረዳ 11 ቀበል 02 የቤት ቁጥር 631 ላይ የነበራቸው የባለቤትነት መብት በህግ ተቋርጧል። ይህ ከሆነ የተጠሪዎቹ መብት በሟች ፊታውራሪ Aየነው መሞት ምክንያት የማይቋረጡ መብትና ግድታዎች ጋር የተገናኘ ነው። ይህም በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 826 ንUስ Aንቀጽ 2 በግልጽ ተመልክቷል። በመሆኑም ሟች ፊታውራሪ Aየነው ክርክር በተነሳበት ቤት ላይ የባለቤትነት መብት የልላቸውና በAዋጅ ቁጥር 47/1967 Aንቀጽ 13 ንUስ Aንቀጽ 1 መሰረት ወደ መንግስት የዞረ ስለሆነ ተጠሪዎች በቤቱ ላይ ወ/ሮ ወለተኪዳን ከያዙት ከሰላሣ ዓመት በኋላ የይገባኛል ጥያቄ የማቅረብ መብት የላቸውም የሥር ፍርድ ቤቶች ጉዳዩን ከAዋጅ ቁጥር 47/1967 Aንፃር በመመልከት ተጠሪዎችን በቤቱ ላይ የይገባኛል ጥያቄ ለማቅረብ የሚያስችላችሁ በቂ ምክንያት የለም ብለው ማሰናበት ሲገባቸው ጉዳዩን ከፍታብሕር ህግ ቁጥር 1168 Aንፃር ብቻ በመመልከት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው። የሥር ፍርድ ቤቶች Aመልካች የቤቱ ባለቤት ሆነዋል ወይስ Aልሆኑም የሚለውን ነጥብ የወሰኑት የቤቱ ባለቤት ፊታውራሪ Aየነው Eንደሆኑ በመቁጠር ነው። ነገር ግን ከነሐሴ 1 ቀን 1967 ዓ.ም. ጀምሮ በAዋጅ ቁጥር 47/1967 Aንቀጽ 13 ንUስ Aንቀጽ 1 መሰረት የባለቤትነት መብታቸው በህግ ለመንግስት የተላለፈ በመሆኑ በፍርሐብሕር ህግ ቁጥር 1168 መሰረት ወ/ሮ ወለተኪዳን የቤቱ ባለቤት መሆን Aይችሉም የሚለውን መከራከሪያ ለማንሳትና Aመልካችን ለመሟገት የሚችለው የሚመለከተው የመንግስት Aካል Eንጂ ተጠሪዎች Aይደሉም።
No topics extracted.
በመሆኑም የሥር ፍርድ ቤቶች የክርክሩን መሰረታዊ ጭብጥ ወደ ጐን በመተውና የከተማ ቦታና ትርፍ ቤትን ለመንግስት ለማድረግ የወጣውን Aዋጅ ቁጥር 47/1967 ድንጋጌዎች ሳያገናዘቡ የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት Aለበት በማለት ፍርድ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመዝገብ ግንቦት 9 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል። ይፃፍ።
የፍ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመዝገብ ጥር 21 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል። ይፃፍ።
የፍ/ከ/ፍ/ቤት በመዝገብ ህዳር 1 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በውጤት ደረጃ ፀንቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻቻሉ።
ይህ ፍርድ መጋቢት 18 ቀን 2000 ዓ.ም በሙሉ ድምጽ ተሰጠ።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት።
319 320 ነ/ዓ