No summary available.
ግንቦት 28 ቀን 2AAA ዓ.ም.
ዳኞች፡- Aብዱልቃድር መሐመድ መስፍን Eቁበዮናስ መድኀን ኪሮስ ዓላ መሐመድ ሱልጣን Aባተማም Aመልካች፡- የወረዳ 6 ቀበል A2 Aስተደደር ጽ/ቤት ቀረቡ።
ተጠሪዎች፡- Eነ ወ/ሮ በቀለች Aማረብህ ቀረቡ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ክርክሩ የተጀመረው በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ሲሆን ከሣሾች ወ/ሮ በቀለች Aማረብህ፣ Aቶ በላይነህ ወንድ Aፍራሽ በራሳቸውና በሞግዚት Aድራጊዎቻቸው ስም፣ ተከሣሾች ደግሞ የAዲስ Aበባ ሥራና ከተማ ልማት ቢሮ፣ Aቶ ገብሬ ኃይል Eና የወረዳ 6 ቀበል A2 Aስተዳደር ጽ/ቤት ናቸው። የክሱ Aመጣጥ በተመለከተም ከሣሾች ሐምል 2A ቀን 1993 ዓ.ም. በተፃፈ የክስ ማመልከቻ በAዲስ Aበባ ከተማ ወረዳ 6 ቀበል A2 ቁጥር 159-16A የሆነውን የግል መኖሪያ ቤት የAንደኛ ከሣሽ Eና የAቶ ወንድAፍራሽ ገመዳ የግል ቤት ሲሆን ቤቱን Aቶ ወንድAፍራሽ በትርፍነት ያላስረከቡት Eና በAዋጅ ቁጥር 47/67 Aንቀጽ 11 መሰረት ለAንድ ግለሰብ ወይም ቤተሰብ የተፈቀደ ነው። ቤቱ Eንደተወረሰ በማስመሰል ቁጥር 159 በሚል በቀበል ቢመዘገብም በAግባቡ ተጣርቶ የቤት ባለቤትነት ማረጋገጫ ተሰቶት በEጃችን ይገኛል። Aቶ ወንድAፍራሽ በመሞታቸውም የ1ኛ ከሣሽ ሚስትነት Eና የልሎቹ ከሣሾች ወራሽነት ተረጋግጧል። በAዋጁ መሰረት የተፈቀደልንን መብት ሶስተኛ ተከሣሽ ላያስረክበን ሲገባ ለሁለተኛ ተከሣሽ Aከራይቶት Eየኖሩበት ይገኛሉ።
ሁለተኛ ተከሣሽ ከሣሾችን ለመጉዳት ተነሳስተው ቁጥሩ 159 በሆነው ቤት ላይ የተሰጠው ደብተር Eንዲመለስ የሚል ደብዳቤ Aጽፈዋል። Aንደኛ ተከሣሽም ይህንን የቀላጤ ደብዳቤ በጥቅምት 23 ቀን 1985 ዓ.ም. ጽፏል። Aንደኛ ተከሣሽ Eንደ ይግባኝ ሰሚ ሆኖ የሰጠው ደብተር በቀላጤ መሻር Aይችልም።
ትEዛዙም ደብተሩ መሰረዙን Aይገልጽም። ስለዚህ ትEዛዙ ሕገወጥ ነው። በልላ በኩል በትEዛዙ ላይ ስማቸው የተገለፀው Aቶ ሸዋAለም ሃ/ማርያም የቤት ቁጥር 159 ባለቤት ስላልሆኑ Aና ለማስረከብም የተሰጣቸው ውክልና ስለልለ ትEዛዙ ሕጋዊነት የለውም። ስለዚህ ደብተሩ Eንዲመለስ በቀላጤ ያለAግባብ የተሰጠው ትEዛዝ Eንዲሰረዝ Eና ወጪና ኪሣራ Eንዲከፈለን Eንዲወስንልን በማለት ክስ መስርተዋል።
Aንደኛ ተከሣሽ በታህሣሥ 1A ቀን 1994 ዓ.ም. በተፃፈ መልስ ከሳሾች ቁጥሩ 159 የሆነው ቤት ባለቤት Aልነበሩም፤ Aይደሉምም። ቤቱ የተወረሰው ከAቶ ሸዋዓለም ኃይለማርያም ነው። ከሣሾች ያስረከቡት Eና የተወረሰባቸው ቤት Aይደለም። ደብተር የወሰዱትም ያለAግባብ ነው።
ደብተሩን የወሰዱት ያለAግባብ መሆኑ በተደረሰበት ጊዜም ተመላሽ Eንዲሆን ተደርጓል። Aንደኛ ተከሣሽ በAዋጅ ቁጥር 41/85 Aንቀጽ 8፣ በAዋጅ ቁጥር 7/86 Aንቀጽ 32/1/ Eና በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1195 መሰረት በከተማው ባለቤትነት ሥር የሚገኙ ቤቶችን የመቆጣጠር ሥልጣን Aለው። በዚህ ሥልጣኑ መሰረት የሰጠው ማስረጃ ከደንብ ውጪ ሆኖ ሲገኝ ፈራሽ Eንደሚሆን በፍ/ብ/ሕ/ቁ.
1196 ላይ ተደንግጓል። ደብተሩ Eንዲመለስ ማስገደድም ይችላል። ይህንን ማድረጉም ሕጋዊ መሆኑን ከሚያመለክት በስተቀር ክስ Eንዲቀርብበት የሚያደርግ Aይደለም። ስለዚህ ጥያቄው ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክሯል።
ሁለተኛ ተከሣሽም በታህሣሥ 1A ቀን 1994 ዓ.ም. በተፃፈ መልስ ከሣሽ ያለAግባብ የቤት ባለቤትነት ደብተር ያወጡ መሆኑን በመረዳት Aንደኛ ተከሣሽ ደብተሩ Eንዲመለስ ትEዛዝ ሰጥቷል። ከሣሾች የራሳቸው ባልሆነ ንብረት Aሳስተው የወሰዱት ደብተር ውድቅ Eንዲሆን የተወሰነ በመሆኑ የመክሰስ መብት የላቸውም። ይህ ከታለፈ ደግሞ ተከሣሽ ቤቱን ከAቶ ሸዋለም ሃ/ማርያም ተከራይቼ ስጠቀም Aዋጅ ቁጥር 47/67 ሲታወጅ በAዋጁ መሰረት የኪራይ ፎርም ሞልቼ ኪራዩን ለመንግሥት Eየከፈልኩኝ ሳለ Aውራሻችን የሚሉዋቸው Aቶ ወንድAፍራሽ ገመዳ በማሳሳት የቤት ባለቤትነት ደብተር ማውጣታቸውን በመስማቴ ባደረግኩት ጥቆማ ቤታቸው Aለመሆኑ ተረጋግጦ ደብተሩ ተሰርዟል። ስለዚህ ክሱ ውድቅ ላሆን የሚጋባው ነው በማለት ተከራክረዋል።
ሶስተኛ ተከሣሽ ደግሞ በየካቲት 21 ቀን 1994 ዓ.ም. ጽፎ ባቀረበው መልስ በAዋጅ ቁጥር 87/89 መሰረት ጉዳዩን የማየት ሥልጣን ያለው የከተማ ነክ ፍ/ቤት ነው። ቤቱ መንግሥት የያዘው ትርፍ ቤት በመሆኑና የሚያስረክብ ሰውም በመታጣቱ ምክንያት ነው። ቤቱ ትርፍ መሆኑን ማረጋገጥ የሚቻለውም በጊዜው በምን ሁኔታ ላይ Eንደነበረ በመመልከት ነው። በወቅቱ ቤቱን በሚመለከት የተገኘው ሰነድ ቅጽ AAA ሲሆን የቤቱ ባለቤት ማለት Aከራይ የነበሩት Aቶ ሸዋለም ሃ/ማርያም መሆናቸውን ያሳያል። ከሣሾች ቁጥሩ 16A የሆነውን ቤት Aያያዛቸው Aጠያያቂ ሆኖ ሳለ በትርፍነት መንግሥት በወረሰው ቤት ላይ /ቁጥር 159/ የባለቤትነት ደብተር ሲያወጡ ተጣርቶ ደብተሩ Eንዲመለስ ተወስኖባቸዋል። ከሣሾች የEነሱ ባልሆነ ቤት ላይ ደብተር ላያወጡ Eና ባለቤት ነን ላሉ Aይችሉም በማለት ተከራክሯል።
No topics extracted.
በልላ በኩል Aንደኛ ተከሣሽ የተከሣሽ ከሣሽነት ክስ Aቅርቧል።
በተከሣሽ ከሣሽነት ክሱም ቁጥሩ 159 የሆነው ቤት በትርፍነት ተወርሶ Aቶ ሸዋለም ሃ/ማርያም ያስረከቡት መሆኑ ታውቆ የወሰዱትን ደብተር Eንዲመልሱ በከሣሾች Aውራሽ ላይ የተወሰነ ቢሆንም ስላልመለሱ የቤት ባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተሩን Eንዲመልሱ ይወስንልን በማለት ጠይቋል።
ከሣሾች ደግሞ ለቀረበባቸው የተከሳሽ ከሣሽነት ክስ በሰጡት መልስ Aቶ ሸዋለም ሃ/ማርያም በወቅቱ የቤቱ ተከራይ Eንጂ ባለቤት ስላለሆኑ ቤት ለማስረከብ ወይም ለማስወረስ የሚያስችል መብት የላቸውም። የተከሣሽ ከሣሽ ደብተሩ Eንዲመለስ በማለት የሰጠው ውሣኔ Aግባብነት ስለልለው ጥያቄው ውድቅ ሲሆን ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
ፍ/ቤቱም ቤቱ በትርፍነት በቅጽ AAA ላይ ከመመዝገቡ በስተቀር የተወረሰ ለመሆኑ የሚያሳይ በቅጽ AA3 የተሞላ ማስረጃ Aልቀረበም። ቤቱ ቀደም ብሎ የAቶ ይፍሩ Aማረብህ መሆኑንና Aቶ ወንዳፍራሽ ገመዳ Eንደገዙት Aዋጅ ቁጥር 47/67 ከመዉጣቱ በፊት ቤቱን Aቶ ወንድAፍራሽ ገመዳ ያከራዩት Eንደነበር ቤቱ በAዋጁ መሰረት ያለወመረሱን Aቶ ሸዋለም ሃ/ማርያም ተከራይ Eንጂ የቤቱ ባለቤት ያለመሆናቸውን ምስክሮች Aስረድተዋል። በመሆኑም ቤቱ የተወረሰ ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ በተከሳሾች ያልቀረበ ስለሆነ ተከሣሾች ቤቱን ለከሣሾች Eንዲያስረክቡ በማለት ወስኗል።
የተከሳሽ ከሣሽ ያቀረበውን ክስም ውድቅ Aድርጎታል።
የፍ/ከ/ፍ/ቤትም የቀረበለትን ይግባኝ ተመልክቶ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ Aጽንቶታል።
የሰበር Aመልካች በሆነው የወረዳ 6 ቀበል A2 Aስተዳደር ጽ/ቤት የቀረበው Aቤቱታም በስር ፍ/ቤቶች የተሰጠውን ውሣኔ በመቃወም ነው።
Aመልካች ባቀረበው Aቤቱታ ቤቱ የተጠሪዎች Aይደለም ጉዳዩን የማየት ሥልጣን ያለው የከተማ ነክ ፍ/ቤት ነው። ፍ/ቤቶቹ ክሱን ያዩት ሥልጣን ሳይኖራቸው ነው። በወረዳ 6 ቀበል A2 የሚገኘው ቁጥሩ 159 የሆነውን ቤት ያስረከቡት Aቶ ሸዋለም ሃ/ማርያም ናቸው። በዚህ መሰረት ቤቱ በAዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት ተወርሷል። Aቶ ወንድAፍራሽ ገመዳ በቤቱ ላይ የቤት 311 312 ባለቤትነት ደብተር ያወጡት በልላቸው መብትና ከደንብ ውጭ ነው።
የባለቤትነት ደብተሩ የተወሰደው ከደንብ ውጪ በመሆኑም በፍ/ብ/ሕ/ቁ.
1196/1/ መሰረት በAስተዳደራዊ ውሣኔ ተሰርዟል። የቤት ባለቤትነት ደብተሩ በዚህ ሁኔታ መሰረዙም በAግባቡ በመሆኑ የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሣኔ ተቀባይነት የለውም። በልላ በኩል ደግሞ ክሱ የቤት ባለቤትነት ደብተሩን Eንድንመልስ የተሰጠው ትEዛዝ ይሻርልኝ የሚል ሆኖ ሳለ ፍ/ቤቶች ተከሣሾች ቤቱን ለከሣሾች Eንዲያስረክቡ በማለት የሰጡት ውሣኔ ክስ ያልቀረበበትን ጭብጥ በመያዝ በመሆኑ ውሣኔው ሥነ ሥርዓቱን የተከተለ Aይደለም።
በመሆኑም የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበትና ላታረም የሚገባው በመሆኑ ውሣኔው Eንዲሻርልኝ ሲል Aመልክቷል።
ተጠሪዎች ደግሞ በሰጡት መልስ Aመልካች በሥር ፍ/ቤት በማስረጃነት ያቀረበው ሰነድ የቤቶቹ መመዝገቢያ ቅጽ የሆነው ቅጽ AAA Eንጂ ቤቱ የተወረሰ ለመሆኑ የሚያሳይ ቅጽ AA3 Aይደለም። ቤቱ የግል መሆኑ ታውቆ የቤት ባለቤትነት ደብተር ተሰጥቷል። ክርክሩ የግል ቤት የተመለከተ በመሆኑ ጉዳዩን የማየት ሥልጣኑ የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ነው። ክሱም የቀረበው የቤት ባለቤትነት ደብተሩን Eንድንመልስ የተሰጠውን ትEዛዝ ለማሰረዝና ቤቱን ለማስለቀቅ በመሆኑ የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሣኔ የሚነቀፍበት Aንዳችም የሕግ ስህተት የለም። በመሆኑም ውሣኔው ፀንቶ ልንሰናበት ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
በበኩላችን ደግሞ የAዲስ Aበባ ሥራና ከተማ ልማት ቢሮ የተጠሪዎች Aውራሽ የሆኑት Aቶ ወንድAፍራሽ ገመዳ በወረዳ 6 ቀበል A2 የሚገኘውን ቁጥሩ 159 የሆነውን ቤት በሚመለከት የወሰዱት የቤት ባለቤትነት ደብተር Eንዲመልሱ በማለት የሰጠው ትEዛዝ በፍ/ቤት ውሣኔ መሻር የሚገባው ነው ወይስ Aይደለም? ቤቱ ለተጠሪዎች ላመለስላቸው ይገባል ወይስ Aይገባም?
የሚሉትን ጭብጦች በመያዝ መዝገቡን መርምረናል።
መዝገቡን Eንደመረመርነውም ተጠሪዎች ክርክር ያስነሳው ቤት የAውራሻቸው የAቶ ወንድAፍራሽ ገመዳ መሆኑን ለማስረዳት የሞከሩት በሰው ማስረጃ ሲሆን ያቀረቡዋቸው ምስክሮችም Aቶ ወንድAፍራሽ ገመዳ Aዋጅ ቁጥር 47/67 ከመውጣቱ በፊት ቤቱን ከAቶ ይፍሩ Aማረብህ የገዙት መሆኑን ነው የገለጹት። ልሎች ሁለት ምስክሮች ደግሞ የገለጹት ቤቱ Aቶ ሸዋለም ሃ/ማርያም በኪራይ ይኖሩበት Eንደነበሩ ነው። ከዚህ ውጪ ተጠሪዎች ቤቱ የAውራሻቸው ስለመሆኑ የሚያስረዳ የሰነድ ማስረጃ Aላቀረቡም።
Aመልካች ደግሞ ቤቱን በትርፍነት ያስመዘገቡትና ለመንግሥት ያስረከቡት Aቶ ሸዋAለም ሃ/ማርያም በመሆናቸው ቤቱ የAቶ ወንድAፍራሽ ገመዳ Aይደለም በማለት ይህን Eንዲያስረዱለት ያቀረበው የሰነድ ማስረጃ የሆነው ቅጽ AAA ቤቱ የAቶ ሸዋለም ሃ/ማርያም መሆኑን ነው የሚገልፀው።
በልላ በኩል የተጠሪዎች Aውራሽ የሆኑት Aቶ ወንድAፍራሽ ገመዳ ልሎች ቤቶቻቸውን በትርፍነት ሲያስመዘግቡ መርጠው ከውርስ ያስቀሩት ቁጥሩ 16A የሆነውን ቤት ስለመሆኑ ከግራ ቀኙ ክርክር ለመገንዘብ ተችሐል።
በትርፍነት Aስመዝግበው ለመንግሥት ያስረከቡዋቸው ቤቶች ቁጥር 149፣ 15A፣ 151፣ 161፣ Eና 162 ሲሆኑ ቁጥሩ 159 የሆነው ክርክር ያስነሳው ቤት ደግሞ Aዋጅ ቁጥር 47/67 ከመውጣቱ በፊት ልላ ሰው የተከራየው ኪራይ ቀመስ ሆኖ መቆየቱንና Aዋጁ ከወጣ በኋላም በኪራይ ቤትነት የቀጠለ ስለመሆኑ ክርክሩ ያስረዳል። የተጠሪዎች Aውራሽ ልሎቹ ቤቶቻቸውን በትርፍነት ሲያስረክቡ ቁጥሩ 159 የሆኑውን ቤት መርጠው ያስቀሩት ስለመሆኑ ወይም ደግሞ በትርፍነት ለመንግሥት ያስረከቡት መሆኑን የሚልጽ የቀረበ ማስረጃ የለም። ከEነዚህ ሁኔታዎች ለመገንዘብ የሚቻለውም የተጠሪዎች Aውራሽ ቤቱን በምርጫ ያላስቀሩት ወይም ደግሞ በትርፍነት ለመንግሥት ያላስረከብኩት በቤቱ ላይ የባለቤትነት መብት ያልነበራቸው መሆኑን ነው።
በመሆኑም በAዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት የከተማ ትርፍ ቤትና ቦታ የመንግሥት በሆነበት ጊዜ የተጠሪዎች Aውራሽ ቤቱን በምርጫ ሳያስቀሩት ወይም ደግሞ በትርፍነት ሳያስመዘግቡትና ለመንግሥት ሳያስረክቡት በAቶ ሸዋለም ሃ/ማርያም Aማካኝነት በትርፍነት ተመዝግቦ መንግሥት ተረክቦት በባለቤትነት ሲያስተዳድረው ለAመታት ከቆየ በኋላ በምርጫ ካስቀሩት ቁጥሩ 16A ከሆነው ቤት ጋር በማያያዝ የቤት ባለቤትነት ደብተር ያወጡበት የቤት ባለቤትነት መብት ሳይኖራቸው መሆኑን ለመረዳት ችለናል።
Eንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ባጋጠመበት ጊዜ የAስተዳደር ክፍሉ ቀደም ሲል በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1195 መሰረት የሰጠውን የባለቤትነት የምስክር ወረቀት በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1196/ሀ/ መሰረት ለማስመለስና ለመሰረዝ Eንደሚችል በሕግ ስልጣን የተሰጠው በመሆኑ ተጠሪዎች የAዲስ Aበባ ሥራና ከተማ ልማት ቢሮ የቤት ባለቤትነት ደብተሩ Eንዲመለስ በማለት የሰጠው ውሣኔ በፍ/ቤት Eንዲሻርልን በማለት ያቀረቡት ክስ ተቀባይነት ያለው ሆኖ Aላገኘነውም።
የሥር ፍ/ቤቶች የባለቤትነት ደብተሩ ለAስተዳደር ክፍሉ መመለስ የለበትም በማለት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት መሆኑን ለመገንዘብ ችለናል።
ሁለተኛውን ጭብጥ በተመለከተ ደግሞ የተጠሪዎች Aውራሽ ቤቱን በምርጫ ከውርስ ያስቀሩት ወይም ደግሞ በትርፍነት የተመዘገበና መንግሥት የልወረሰው መሆኑን ባላስረዱበት ይልቁንም ቤቱን በትርፍነት ያስመዘገቡትና ለመንግሥት ያስረከቡት Aቶ የሸዋAለም ሃ/ማርያም መሆናቸው በሰነድ ማስረጃ ተረጋግጦ Eያለ ቤቱ የተጠሪዎች Aውራሽ በመሆኑ Aመልካች ቤቱን ለተጠሪዎች የሚያስረክቡበት ምክንያት የለም። የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡትን ውሣኔ ስንመለከትም ተጠሪዎች የAስተዳደር ክፍሉ የቤት ባለቤትነት ደብተሩን Eንድንመልስ የሰጠው ትEዛዝ Eንዲሰረዝልን በማለት ያቀረቡትን ክስ መነሻ በማድረግ Aመልካች ቤቱን ለተጠሪዎች Eንዲመልስ በማለት ፍ/ቤቶቹ መወሰናቸው በAግባቡ ሆኖ Aላገኘነውም። ቤቱን የመረከብ ጥያቄ በተጠሪዎች ተጠሪዎች ባቀረቡት ክስ Aልቀረበም። በጭብጥነትም ተይዞ ግራ ቀኙ Aልተከራከሩበትም። ዳኝነት ባልተከፈለበት፣ በክሱ በግልጽ ባልተጠየቀና በጭብጥነት ተይዞም ግራ ቀኙ ባልተከራከሩበት ነጥብ ላይ ውሣኔ መስጠት ስለማይቻልም የሥር ፍ/ቤቶች Aመልካች ቤቱን ለተጠሪዎች Eንዲያስረክብ በማለት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበትና ላታረም የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ
የፍ/ከ/ፍ/ቤት ደግሞ በመ/ቁ. 4686A የካቲት 21 ቀን 1999 ዓ.ም.
የሰጡት ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የAዲስ Aበባ የሥራና ከተማ ልማት ቢሮ ቀደም ብሎ የወጣው የቤት ባለቤትነት ደብተር የተሰጠው ከደንብ ውጪ ሆኖ ካገኘው ደብተሩን የማስመለስና የመሰረዝ ስልጣን ያለው በመሆኑና ተጠሪዎች በዚህ ጉዳይ ቅሬታ ካላቸው ደረጃውን ተከትለው በAስተዳደር ክፍሉ Eንዲጣራላቸው ከሚያደርጉ በስተቀር ደብተሩን Eንዲመልሱ የተሰጠው ውሣኔ በፍ/ቤት ውሣኔ የሚሻርበት ምክንያት የለም በማለት ወስነናል።
ወጪና ኪሣራን በተመለከተ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን Eንዲችሉ ብለን መዝገቡን ዘግተን ወደ መዝገብ ቤት መልሰናል።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት።