No summary available.
ጥቅምት 18 ቀን 1997 ዓ.ም.
Eንዲሁም የከፍተኛው ፍ/ቤት በመ/ቁ A5349 በታህሣሥ 21 ቀን 1997 ዓ.ም. የሰጡት ውሣኔ ፀንቷል።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት።
ነ/ዓ የሰበር መ/ቁ. 236A8 ኀዳር 3 ቀን 2AAA ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ፍስሐ ወርቅነህ ሐጎስ ወልዱ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- የIትዮጵያ øራይቬታይዜሽንና የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጂንሲ ነ/ፈጁ መስፍን በሻህ ተጠሪ፡- የAቶ ኑር በዛ ተረጋ ወራሾች ጠበቃ ስንታየሁ ባህሩ መዝገቡን መርምረን ቀጥሎ የተመለከተውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር Aቤቱታ ላቀርብ የቻለው የAሁን ተጠሪዎች Aውራሽ በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ መነሻነት ሲሆን የክሱም ይዘት ባጭሩ በወረዳ 18 ቀበል 34 ክልል ቁጥራቸው ከAA1 -AA7 የሆኑት ቤቶች ያለAግባብ በመንግሥት የተወሰዱ መሆናቸው ታምኖበት በሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር በኩል Eንዲመለስልኝ ተወስኖ በዚሁ ውሣኔ መሰረት ቤቶቹን Eንድረከብ ታህሣሥ 3 ቀን 1988 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ ለተከሣሽ (ለAሁን Aመልካች) Aመልክቼ Eንዳለሁ በኀዳር ወር 1991 ዓ.ም Aካባቢ በቤቶቹ ውስጥ የነበሩት ተከራዮችን ሲለቁ ከሣሽ ቤቶችን የተረከብኩኝ ቢሆንም ያቀረብኩት Aቤቱታ Aስቀድሞ ቤቶቹ ላመለሱልኝ Eንደሚገባ ታምኖበት በተወሰነልኝ መሰረት Eንዲመለሱልኝ የሚል ሆኖ ሳለ Aቤቱታዬን በትክክል ባለመረዳት ለቤቶቹ የቤት ባለቤትነት መብት Eንዲሰጠኝ Eንዳመለከትኩኝ ቆጥሮ የሚመለሱት ቤቶች በሙሉ ሣይሆን በከፊል ብቻ ነው በማለት በመወሰኑ ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለኤጀንሲው የሥራ Aመራር ቦርድ ይግባኝ ያቀረብኩ ቢሆንም ቦርዱ የኤጀንሲውን ውሣኔ በመሻር መዝገቡን የዘጋ ስለሆነ የኤጀንሲውም ሆነ የቦርዱ ውሣኔ ከሥልጣናቸው ውጭ ስለሆነ በፍርድ ላሰረዝልኝ ይገባል የሚል ነው።
የከሣሽ ክስና ማስረጃ ለተከሣሽ (ለAሁን Aመልካች) ደርሶ በሰጠው መልስ ከሣሽ በክስ Aቤቱታቸው በጠቀሷቸው ቤቶች ትርፍነታቸው ተረጋግጦ በAዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት የተወረሱ ንብረቶች ናቸው በመሆኑም በመጀመሪያ የኤጀንሲው ሥራ Aስኪያጅ በመቀጠልም የኤጀንሲው ሥራ Aመራር ቦርድ ይህን ጉዳይ ለማየት ሥልጣን Eንደልለው በመግለጽ የመጨረሻ ውሣኔ በመስጠት መዝገቡ Eንዲዘጋ ወስኗል። በAዋጁ ቁጥር 11A/87 መሰረት ተከሣሽ የሚሰጣቸውን ውሣኔዎች በፍ/ቤት Eንደገና ላታዩ /Review/ Eንደሚችሉ የተደነገገ ድንጋጌ ስለልለ ፍ/ቤቱ ይህንን Aቤቱታ ተቀብሎ የማየት ሥልጣን የለወም። በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረበ ሲሆን በፍሬ ጉዳዩም ሙሉ መልስ በመስጠት ክሱ ከበቂ ኪሣራ ጋር ላሰረዝ ይገባል በማለት ተከራክሯል።
የግራ ቀኙ ክርክር በዚህ መልኩ የቀረበለትም የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ክርክሩን መርምሮ በተከሣሽ በኩል የፍ/ቤቱን ሥልጣን Aስመልክቶ የቀረበውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በተመለከተ A.ፍ.ዲ.ሪ ሕገመንግሥት በAንቀጽ 79(1) ላይ የዳኝነት ሥልጣን የፍ/ቤቶች ብቻ Eንደሆነ በAንቀጽ 37(1) ላይ ደግሞ ማንኛውም ሰው በፍርድ ላወሰን የሚገባውን ጉዳይ (Justieable matter) ለፍ/ቤት የማቅረብና ውሣኔ የማግኘት መብት Eንዳለው የተደነገገ ከመሆኑም በላይ በAስተዳደር Aካላት የተሰጡ ውሣኔዎችን ፍ/ቤቶች Eንደገና ለማየት ተፈጥሯዊ /inherent/ የሆነ ሥልጣን ያላቸው ስለሆነ ፍ/ቤቱ ጉዳዩን ለማየት ሥልጣን የለውም ተብሎ በተከሣሽ በኩል የቀረበው መቃወሚያ በAግባቡ የቀረበ Aይደለም በማለት ውድቅ Aድርጎ በፍሬ ጉዳይ ረገድ ግራ ቀኙ ያደረጉትን ክርክር መርምሮ በAዋጅ ቁጥር 11A/87 Aንቀጽ 4(1) Eና Aንቀጽ 3(2) መሰረትና ይህን Aዋጅ ለማስፈፀም በወጣው መመሪያ ቁጥር AA1/88 Aንቀጽ 3(1) Eና (2) መሰረት ከAዋጁ ቁጥር 47/67 ውጭ የተወሰዱ ንብረቶች ይመለሱልኝ የሚሉ Aቤቱታዎችን Eንደዚሁም ከAዋጅ ውጭ በተወረሰ ንብረት ላይ Aዋጅ ቁጥር 11A/87 ከመጽናቱ በፊት በልላ Aካል የመጨረሻ Aስተዳደራዊ ውሣኔ የተሰጠ ቢሆንም ይህ ውሣኔ Eንደገና Eንዲመረመር Aቤቱታ ሲቀርብ ኤጂንሲው ከዚያም ቦርዱ የማየት ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል።
ሆኖም በAዋጁና በመመሪያው መሰረት ከEነርሱ በፊት ልላ የAስተዳደር ባለሥልጣን ከAዋጁ ወጭ የተወረሱ ናቸው የተባሉ ንብረቶች ላይ የሰጠውን የመጨረሻ Aስተዳደራዊ ውሣኔ ኤጀንሲውም ሆነ ቦርዱ በመመርመር ተገቢውን ውሣኔ ለመስጠት የሚችሉት Aቤቱታ ሲቀርብላቸው Eንጂ በገዛ ፈቃዳቸውና በEራሣቸው ጊዜ Aይደለም በማለት በውሣኔው ላይ Aስፍሮ፤ በተያዘው ጉዳይ የኤጀንሲው ሥራ Aስኪያጅና የሥራ Aመራር ቦርድ ከላይ የተጠቀሱትን የAዋጁንና የመመሪያውን ድንጋጌዎች ጥሰው ከሥልጣናቸው በማለፍ ከሣሽ ቤቶቹን ለመረከብ በተወሰነልኝ መሰረት ርክክቡ ይፈፀምልኝ በማለት ያቀረቡትን Aቤቱታ ያለAግባብ የተወረሱ ቤቶች ይመለስልኝ በማለት Aዲስ Aቤቱታ ያቀረቡ በማስመሰል ውሣኔ የሰጡ ስለሆነ የኤጂንሲው ሥ/Aስኪያጅም ሆነ ቦርዱ ከሥልጣናቸው ውጭ ውሣኔ ስለሰጡ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2121 መሰረት ተሰርዟል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
No topics extracted.
ጉዳዩ በይግባኝ የቀረበለትም የፍ/ከ/ፍ/ቤት በበኩሉ ግራ ቀኙን Aከራክሮ የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ጉዳዩን ለማየት ሥልጣን የልለው መሆኑን Aስመልክቶ የቀረበውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሣይቀበለው የቀረው በAግባቡ Eንደሆነና በዚህ ረገድ የቀረበው የይግባኝ ቅሬታ ተቀባይነት የልለው ነው ካለ በኋላ በፍሬ ጉዳይ ክርክር ረገድም ኤጀንሲውም ሆነ የኤጀንሲው የሥራ Aመራር ቦርድ የሰጡት ውሣኔ ከAዋጁም ሆነ ከመመሪያው Aኳያ ሲታይ ከሥልጣናቸው ውጭ ስለሆነ የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ውሣኔው ላሰረዝ Eንደሚገባ የሰጠው ውሣኔ የሚነቀፍ Eንዳልሆነ ነገር ግን የኤጂንሲው ሥራ Aስኪያጁ ውሣኔ በቦርዱ ተሽሮ ባለበት ሁኔታ ፍ/ቤቱ በድጋሚ የኤጀንሲውን ሥራ Aስኪያጅ ውሣኔ መሻሩ በAግባቡ Aይደለም በማለት በዚህ መልኩ የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤትን ውሣኔ በማሻሻል Aጽንቷል።
የሰበር Aቤቱታውም የቀረበው ይህንኑ በመቃወም ሲሆን ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት የቀረበውን Aቤቱታ መርምሮ የøራይቬታይዜሽን ኤጂንሲ የሰጠው ውሣኔ Eንደገና ለማየት ፍ/ቤቶች ተፈጥሯዊ /inherent/ ስልጣን Aላቸው በማለት ኤጀንሲው የሰጠውን ውሣኔ የሥር ፍ/ቤቶች በድጋሚ Aይተው ውሣኔ መስጠታቸው Aግባብነቱ ለሰበር ቀርቦ ላጣራ Eንደሚገባ በማመኑ ተጠሪዎችን በመጥራት ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
በAጠቃላይ የክርክሩ ነጥብ ከላይ የተመለከተው ሲሆን የሰበር Aቤቱታውም Eንደሚከተለው ተመርምሯል።
የተጠሪዎች Aውራሽ በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ የጠየቁት ዳኝነት /Relief/ ኤጂንሲውም ሆነ ቦርዱ የቀረበላቸው Aቤቱታ ከAዋጁ ውጭ የተወሰደ ቤት Eንዲመለስልኝ ይወሰንልኝ የሚል ባልሆነበት ሁኔታ ከተጠየቀው ውጭ ልላ ጭብጥ በመያዝ ውሣኔ የሰጡ ስለሆነ ይሄው ውሣኔ ላሰረዝ ይገባል በማለት ነው።
ከAዋጅ ውጭ ስለተወሰዱ ንብረቶች በወጣው Aዋጁ ቁጥር 11A/87 Aንቀጽ 4(1) Eና (2) መሰረት ከAዋጅ ውጭ የተወሰዱ ንብረቶችን የባለቤትነት ሁኔታ የማጣራትና የመወሰን ሥልጣን ለAመልካች የተሰጠ ሲሆን የባለቤትነትን ጥያቄ በሚመለከት ኤጀንሲው በሚሰጠው ውሣኔ ላይ ቅሬታ ያለው ወገን Aቤቱታውን ለኤጀንሲው የሥራ Aመራር ቦርድ ማቅረብ Eንደሚችል በዚሁ Aዋጅ በAንቀጽ 5/3/ ላይ ተመልክቷል።
በEርግጥ የተጠሪዎች Aውራሽ ታህሣሥ 3 ቀን 1988 ዓ.ም ለAመልካች ያቀረቡት Aቤቱታ ለክርክሩ ምክንያት የሆኑት ቤቶች ከAወጁ ውጭ የተወሰዱ ስለሆነ ይመለስልኝ በማለት ሣይሆን የቤቶቹ ባለቤትነቴ በሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር Aማካይነት ተረጋግጦ ተወስኖልኝ ርክክቡ የዘገየ ስለሆነ ቤቶቹን Eንድረከብ ይወሰንልኝ በማለት ነው።
የተጠሪዎች Aውራሽ ለክርክሩ ምክንያት የሆኑት ቤቶች Eንዲመለሱልኝ በልላ Aካል ተወስኖልኛል የሚሉ ከሆነ ቀድሞውንም ቢሆን ቤቶቹን ለመረከብ Aቤቱታ ማቅረብ የነበረባቸው ለፍ/ቤት Eንጂ ለኤጀንሲው Aልነበረም።
በልላ በኩልም ለኤጀንሲው የቀረበው Aቤቱታ ይዘቱ ምንም Eንኳን የቤቶቹን ርክክብ የሚመለከት ቢሆንም ኤጀንሲው የተቋቋመው ከAዋጁ ውጭ የተወሰዱ ንብረቶች የባለቤትነት ሁኔታ Aጣርቶ ለመወሰን Eስከሆነ ድረስ የEነዚህንም ቤቶች የባለቤትነት ሁኔታ ከAዋጁ Aኳያ መርምሮ ውሣኔ ቢሰጥ ከሥልጣኑ ውጭ በማለፍ ውሣኔ ሰጥቷል ወደሚል ድምዳሜ ላወሰድ Aይችልም። ይልቁንም ኤጀንሲው የተቋቋመበትን A/ቁ/11A/87 ለማስፈፀም በወጣው መመሪያ ቁጥር AA1/88 መሰረት Aዋጅ ቁ. 11A/87 ከመውጣት በፊት ከAዋጅ ቁጥር 47/67 ውጭ በተወሰደ ንብረት ላይ በልላ Aስተዳደራዊ Aካል የመጨረሻ Aስተዳደራዊ ውሣኔ ተሰጥቶ ባለበት ሁኔታም የውሣኔው Aግባብነት Eንዲመረመር Aቤቱታ ሲቀርብ ኤጀንሲውም ሆነ ቦርዱ መርምረው ውሣኔ መስጠት Eንደሚችሉ የተመለከተ Eንደመሆኑ መጠን የተጠሪዎች Aውራሽ በዚህ መልኩ ያቀረቡትን Aቤቱታ ኤጀንሲውም ሆነ ቦርዱ መርምረው ውሣኔ መስጠታቸው ከስልጣናቸው ውጭ ነው ላባል Aይችልም።
ከዚሁ ጋር በተያያዘም በሕገ መንግሥታችን Aንቀጽ 37/1/ ላይ ማንኛውም ሰው በፍርድ ላወሰን የሚገባውን ጉዳይ ለፍ/ቤት ወይም ለልላ በሕግ የዳኝነት ሥልጣን ለተሰጠው Aካል የማቅረብና ውሣኔ ወይም ፍርድ የማግኘት መብት Eንዳለው ተመልክቷል።
ከዚህ የሕገመንግሥቱ ድንጋጌ በግልጽ መገንዘብ የሚችለው ፍ/ቤቶች Aንድን Aቤቱታ ተቀብለው ውሣኔ መስጠት የሚችሉት ዳኝነት የተጠየቀበት ጉዳይ በሕግ ለልላ Aካል ያልተሰጠ ጉደይ በሚሆንበት ጊዜ Eንደሆነ ነው።
የተያዘውም ጉዳይ በተጠቀሰው A/ቁጥር 11A/87 መሰረት የዳኝነት ሥልጣኑ በግልጽ ለልላ Aካል ማለትም ለAመልካች የተሰጠ ስለሆነና ኤጀንሲውም በሰጠው ውሣኔ ቅር የተሰኘ ወገን ቅሬታውን ለኤጀንሲው የሥራ Aመራር ቦርድ ማቅረብ Eንደሚችልና የቦርዱም ውሣኔ የመጨረሻና Aሳሪ /Final and binding/ Eንደሆነ በAዋጁ ላይ ስለተመለከተ Aቤቱታው ይህንን ሥርዓት ካለፈ በኋላ በኤጀንሲውም ሆነ በቦርዱ የተሰጠው ውሣኔ ከሥልጣን ውጭ ስለሆነ ውሣኔው ላሰረዝ ይገባል የሚለው የተጠሪዎች Aቤቱታ በAንድ በኩል በዚህ መልኩ የተሰጠው ውሣኔ በፍ/ቤት በድጋሚ ለማየት የሚያስችል የሕግ ማEቀፍ /legal frame work/ በልለበት ሁኔታ ከመሆኑም በላይ በልላም በኩል የፍ/ቤቶች የዳኝነት ሥልጣን በEኛ Aገር ሁኔታ ከሕግ የመነጨ Eንጂ ተፈጥሯዊ /inherent/ ባልሆነበት ሁኔታ ስለሆነ የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት የፍ/ቤቱን ሥልጣን Aስመልክቶ በቀረበለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ ተመስርቶ ፍ/ቤቱ ጉዳዩን ለማየት ሥልጣን የለውም በማለት መመለስ ሲገባው የፍ/ከ/ፍ/ቤትም ይህንኑ ስህተት ሣያርም መቅረቱ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ሆኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ