No summary available.
ሐምል 24 ቀን 1999 ዓ.ም.
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ መስፍን Eቁበዮናስ Aሰግድ ጋሻው ተሻገር ገ/ሥላሴ ብርሃኑ Aመነው Aመልካች፡- የጅማ ከተማ የAካባቢ Aስተዳደር ጽ/ቤት ተወካይ ቲጃኔ Aባቡልጉ ቀረቡ።
ተጠሪ፡- Aቶ ሸዋረገድ Aባድር ቀረቡ።
መዝገቡን መርምረን ፍርድ ሰጥተናል።
የሰበር Aቤቱታ የቀረበው የOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚው ችሎት በሰጠው ትEዛዝ ላይ ነው።
የAሁን ተጠሪ በወረዳው ፍ/ቤት ከሳሽ Aመልካች ደግሞ ተከሣሽ በመሆን ተከራክረዋል።
ተጠሪ የተፈጠረው ሁከት ይወገድልኝ በማለት በጠየቀው ዳኝነት መነሻ Aድርጎ ያቀረበው ምክንያት Eናቴ በካርታ ቁጥር 928 1392 ካሬ ሜትር 295 296 በሆነው ቦታ ላይ የቤት ቁጥር 156 የሆነ ቤት Aላቸው የEናቴ ወራሽ መሆኔን Aረጋግጫለሁ ሆኖም ተከሣሽ የAሁን Aመልካች ለልላ ግለሰብ ስለሸጠብኝ ሁከት ተፈጥሮብኛል የሚለውን ነው።
Aመልካችም ይህ በካርታ ቁጥር 928 የተመዘገበው ካርታ የተሰጠው በ1954 ዓ.ም. ነው። የከተማ ቦታ Eና ትርፍ ቤትን የመንግሥት ባደረገው Aዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት ይህ ክስ የቀረበበት ንብረት የተወረሰ ነው፤
የተፈጠረ ሁከት የለም በማለት ተከራክሯል።
የሥር የወረዳ ፍ/ቤትም በውርስ Aግኝቼ የEራሴ ሆኗል በማለት ከሳሽ ይከራከር Eንጂ ይህ ስለመሆኑ ማስረጃ Aላቀረበም። ንብረቱ በAዋጅ ቁጥር 47/67 የተወረሰ ስለሆነ የተፈጠረ ሁከት የለም በማለት ወስኗል። ይህም ውሣኔ በከፍተኛው ፍ/ቤት ፀንቷል።
የOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ግራ ቀኙን በይግባኝ ካከራከረ በኋላ የAሁን Aመልካች ተወርሷል ይበል Eንጂ ስለመወረሱ ማስረጃ Aላቀረበም። ንብረቱ በከሳሽ በAሁን ተጠሪ ስም መሆኑን Aልካደም የወራሽነት ማስረጃ ቀርቦ Eያለ የሥር ፍ/ቤት መልስ ሰጭ የባለቤትነት ማስረጃ የለውም ማለቱ ተገቢ Aይደለም ስለሆነም ካርታ Eና ፕላን ያለውን ንብረት በላዝ መሸጡ ተገቢ Aይደለም በማለት በሥር ፍ/ቤቶች የተሰጠውን ውሣኔ ሽሮታል።
የሰበር Aቤቱታ የቀረበለት የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ይኸው የጠቅላይ ፍ/ቤት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት Aመልካችን Aሰናብቷል።
የሰበር Aቤቱታ የቀረበውም የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት Eና ሰበር ሰሚ ችሎት በጉዳዩ ላይ የሰጡት ዳኝነት መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ ላታረምልን ይገባል በማለት ነው።
ግራ ቀኙም በዚህ ሰበር ችሎት የቃል ክርክር Aድርገዋል።
Eኛም ጉዳዩን ተመልክተናል። Eንደተመለከትነውም ተጠሪ ሁከት ተፈጠረበት በተባለው ንብረት መብት ወይም ጥቅም ያለው መሆኑን ለማሣየት መሰረት ያደረገው ወራሽ ነኝ በማለት ነው። ንብረቱም የAውራሽ የEናቴ ነው ለማለት ያበቃው በካርታ ቁጥር 928 የተመዘገበውን ካርታ ነው። ይሁን Eንጂ ይህ ካርታ በ1954 ዓ.ም. የተሰጠ ነው በማለት Aመልካች ላቀረበው ክርክር ማስተባበያ Aላቀረበበትም። ክዶም Aልተከራከረም። Aመልካች ይህ የንብረቱ የባለቤትነት ማረጋገጫ የተሰጠው Aዋጅ ቁጥር 47/67 ከመውጣቱ በፊት ሲሆን ይህ Aዋጅ ከወጣ በኋላ ግን ተወርሷል በማለት ይህንኑ ሕግ መሰረት Aድርጎ ለቀረበው ክርክር ተጠሪ Aልተወረሰም በማለት ተከራክሯል:: የቤቱ ካርታ የተሰጠበት ጊዜ Eና Aዋጁ የወጣበት ጊዜ Eንደ መነሻ ፍሬ ነገር በመያዝ ንብረቱ የተወረሰ መሆኑን የግምት መነሻ በመስጠት Aመልካች ያስረዳ ሲሆን ተጠሪ በበኩሉ ይህ ንብረት ያልተወረሰ መሆኑን በሚያመለክት ሁኔታ ማስረጃ በማቅረብ Aላረጋገጠም:: ይልቁንም በቃል በተደረገው ክርክር Aዋጅ ቁጥር 47/67 ሲወጣ Eኔ Eስር ቤት ነበርኩኝ፤ የደርግ መንግሥት በAምባገነንነት በቀበል Aማካኝነት ለልሎች ሰዎች በኪራይ ተሰጠብኝ የሚለውን መግለጽ ንብረቱ በEርግጥም የተወረሰ መሆኑን የሚያመለክት ነው።
ስለሆነም ንብረቱ ተወርሷል ወይስ Aልተወረሰም የሚለውን ነጥብ በሚመለከት ማን ክርክሩን መጀመርና ማስረዳት Eንዳለበት የሚያመለክተውን ድንጋጌ ባለመከተል Eና ይህም ሥርዓት ቢዛነፍም Eንኳ ከግራ ቀኙ ማን የተሻለ ማስረጃ Aቅርቧል የሚለውን ነጥብ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ከግምት ውስጥ ሳያስገባ የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ Aግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
Aመልካች ክርክር ባስነሳው ንብረት ላይ የፈፀመው ሁከት የለም ብለናል።
No topics extracted.
የOሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 22312 በሐምል 14 ቀን 1997 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ Eና የሰበር ሰሚው ችሎት በሰበር መ/ቁ.
3264A በህዳር 21 ቀን 1998 ዓ.ም. የሰጠው ትEዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁ 348 /1/ መሰረት ተሽሯል።
Eንዲሁም የከፍተኛው ፍ/ቤት በመ/ቁ A5349 በታህሣሥ 21 ቀን 1997 ዓ.ም. የሰጡት ውሣኔ ፀንቷል።