No summary available.
የሰ/መ/ ግንቦት 7 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ ተገኔ ጌታነህ መድሕን ኪሮስ ዓላ መሐመድ ሱልጣን Aባተማም Aመልካች፡- የባህር ዳር ጨርቃጨርቅ Aክስዮን ማሕበር Aልቀረቡም ተጠሪዎች፡- 1ኛ/ የባህር ዳር ልዩ ዞን Aስተዳደር Aልቀረቡም 2ኛ/ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ባለAደራ ቦርድ ነገረፈጅ Aቶ Aዳነ መጋቡ ቀረቡ።
መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ነበር። መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
መዝገቡ የቀረበው Aመልካች የAማራ ብሕራዊ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጥር 4 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት የካቲት 5 ቀን 1999 ዓ.ም 289 290 ባቀረበው የሰበር Aቤቱታ Aጣርቶ ለመወሰን ነው። ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በAማራ ብሕራዊ ክልል የምEራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን፣ ፍሬ ጉዳዩም Aንደኛ ተጠሪ የAማራ ብሕራዊ ክልል ባወጣው ደንብ መሰረት በ1988 ዓ.ም የቦታ ኪራይ ብር 497,943.54 /Aራት መቶ ዘጠና ሰባት ሺ ዘጠኝ መቶ Aርባ ሦስት ብር ከሀምሣ Aራት ሣንቲም/ Eንዲከፍል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት ያልከፈለ በመሆኑ Eንዲከፍል ውሣኔ ይሰጥልኝ በማለት በAመልካች ላይ ክስ Aቅርቧል። Aመልካችም ይህ Eዳ የባህርዳር ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ የመንግሥት የልማት ድርጅት Eንደነበርና ወደ ባህርዳር ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ Aክስዮን ማሕበር ከመቀየሩ በፊት የነበረ ስለሆነ፣ ሁለተኛው ባለEዳ፣ ሦስተኛ ወገን ተከራካሪ፣ /ተከሣሽ/ ሆኖ ጣልቃ Eንዲገባ በጠየቁት መሰረት ፍ/ቤቱ 2ኛ ተጠሪ ጣልቃ Eንዲገባ ትEዛዝ ሰጥቷል።
የከፍተኛው ፍርድ ቤት Aንደኛ ተጠሪ ያቀረበውን ክስና Aመልካቹና ሁለተኛው ተጠሪ ያቀረቡትን ክርክርና ማስረጃ ከሰማ በኋላ ሁለተኛው ተጠሪ የቦታውን ዋና ግብር 454,511.99 /Aራት መቶ ሀምሣ Aራት ሺ Aምስት መቶ Aሥራ Aንድ ብር ከዘጠና ዘጠኝ ሣንቲም/ Eንዲከፍል ወስኗል።
ሁለተኛው ተጠሪ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበ ሲሆን የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሁሉንም ተከራካሪ ወገኖች ክርክር ከሰማ በኋላ ሁለተኛ ተጠሪ ብር 56,159.44 /ሀምሣ ስድስት ሺ Aንድ መቶ ሀምሣ ዘጠኝ ብር ከAርባ Aራት ሣንቲም/ ብቻ Eንዲከፍል ቀሪውን Eዳ Aመልካች Eንዲከፍል በማለት ወስኗል። Aመልካች በክሱ ተከሳሽ የሆነው የባህርዳር ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ Aክስዮን ማሕበር የተመሰረተው 1992 ዓ.ም ነው። ስለዚህ ፋብሪካው ወደ Aክስዮን ማሕበርነት ከመለወጡ በፊት የነበረው Eዳ Eኛን የሚመለከት ባለመሆኑና ሁለተኛው ተጠሪ ይህንን Eዳ የመክፈል ግድታ በAዋጅ ቁጥር 182/1992 የተጣለበት ሆኖ Eያለ Aክስዮን ማሕበሩ Eዳውን Eንዲከፍል የAማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ ስህተት ያለበትና Aክስዮን ማህበሩን ለኪሣራ የሚዳርግ በመሆኑ በሰበር ይታረምልን በማለት Aመልክቷል።
ሁለተኛው ተጠሪ በበኩሉ ወደ Aክስዮን ማሕበሩ የሚተላለፉና የማይተላለፉ Eዳዎችን የመወሰን ሥልጣን ያለው የIትዮጵያ ፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ መከፈል ያለበት Eዳ ነው በማለት ያሣወቀን 56,159.44 /ሃምሣ ስድስት ሺ Aንድ መቶ ሃምሣ ዘጠኝ ብር ከAርባ Aራት ሣንቲም/ በመሆኑ ከዚህ ውጭ ያለውን Eዳ Aመልካች መክፈል ይገባዋል የሚል ክርክር Aቅርቧል። Aንደኛ ተጠሪ በበኩሉ Eዳው መከፈል ያለበት Eዳ መሆኑን ሁለተኛ ተጠሪና Aመልካች Eንዳልካዱ ገልፆ በሁለቱ መካከል በሚደረገው ክርክር የከተማው Aስተዳደር ማግኘት የሚባውን ክፍያ ሣያገኝ ጉዳዩ Eየተጓተተ በመሆኑ በAጭር ጊዜ ታይቶ Eዳውን ከነወለዱ Eንዲከፍሉ ውሣኔ ይሰጥልን በማለት ተከራክሯል።
ከሥር የክርክሩ Aመጣጥና የAመልካችና ተጠሪዎች በሰበር ያቀረቡት ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን Eኛም መዝገቡን መርምረናል። መዝገቡን Eንደመረመርነው Aመልካች ያለበት Eዳና Aጠቃላይ Eሴቱ Eና መንቀሳቀሻ ካፒታሉ ተለይቶ የባህርዳር ጨርቃጨቅ ፋብሪካ Aክስዮን ማህበር ተብሎ በAዲስ መልክ በAክስዮን ማህበርነት ከመደራጀቱ በፊት ለAንደኛ ተጠሪ መክፈል የሚገባውን የቦታ ግብር Eዳ የመክፈል ኃላፊነት Aለበት ወይስ የለበትም የሚለው ነጥብ መታየት ያለበት ሆኖ Aግኝተነዋል። ከዚህ Aንፃር ስንመዝነው መንግሥት Aመልካች ድርጅት ወደ Aክስዮን ማህበር ከመቀየሩ በፊት የነበሩበትን Eዳዎች በኃላፊነት የሚረከብ Aንድ ተቋም ማቋቋም በማስፈለጉ ምክንያት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ባለ Aደራ ቦርድን ሥልጣንና ኃላፊነት Eንደገና በመወሰን ሕግ ያወጣ መሆኑን ከAዋጅ ቁጥር 208/1992 መግቢያ ለመረዳት ይቻላል። የባለAደራ ቦርዱ መሰረታዊ ዓላማም የመንግሥት የልማት ድርጅት ወደግል ይዞታ በሚዛወርበት ወይም ወደ Aክስዮን ማህበር በሚለወጥበት ወይም ወደ ቀድሞ ባለቤቱ በሚመለስበት ጊዜ ወደ Aዲሱ ባለቤት ወደ Aክስዮን ማህበሩ ወይም ወደ ቀድሞ ባለቤቱ የማይተላለፉ ሂሣቦችን መሰብሰብ Eዳዎችን መረከብና ከዚሁ ጋር የተያያዙ የፍርድ ቤት ጉዳዮችን መከታተል Eንደሆነ በAዋጅ ቁጥር 208/1992 Aንቀጽ 5 ንUስ Aንቀጽ 1 በግልጽ ተደንግጓል። ከዚህ በተጨማሪ የባለAደራ ቦርዱ ወደ Aክስዮን ማህበርነት የተቀየሩ ወደ ግል የተዛወሩ ወይም ለቀድሞ ባለቤታቸው የተመለሱ የመንግሥት የልማት ድርጅት Eዳዎችን ለመንግሥት Eያቀረበ Eንዲከፈሉ የማድረግ ሥልጣንና ኃላፊነት ያለበት መሆኑን Aዋጅ ቁጥር 208/1992 Aንቀጽ 6 ንUስ Aንቀጽ 1/ሐ/ ይደነግጋል። በዚህ መዝገብ የባህርዳር ከተማ Aስተዳደር የጠየቀው የመሬት ኪራይ የባህርዳር ጨርቀጨርቅ ፋብሪካ ወደ Aክስዮን ማህበርነት ከመቀየሩ ከAራት ዓመት በፊት የነበረና የባህርዳር ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ የመንግሥት የልማት ድርጅት በነበረበት 1988 ዓ.ም መክፈል የሚባው Eዳ ነው። Aሁን ያለው የባህር ዳር ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ Aክስዮን ማህበር 1992 ዓ.ም ህጋዊ ሰውነት ያገኘ ድርጅት በመሆኑ ከጅምሩ በፈረሰውና ወደ Aክስዮን ማህበርነት በተቀየረው የባህርዳር ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ስም ያቀረበውን ክስ በኃላፊነት ይዞ መከራከር የሚገባው የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ባለAደራ ቦርድ Eንደሆነ ከAዋጅ ቁጥር 208/1992 Aንቀጽ 5 ንUስ Aንቀጽ 1 ድንጋጌዎች ለመረዳት ይቻላል።
No topics extracted.
ሁለተኛ ተጠሪ Eዳውን ላለመክፈል የሚያቀርበው ምክንያት የIትዮጵያ ፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ Aላሳወቀኝም የሚል ነው። ሆኖም የመንግሥት የልማት ድርጅቱ ወደ Aክስዮን ማህበርነት ሲቀየር በፕራይቬታይዜበሽን ኤጀንሲ ያልታወቀና ውሣኔ ያልተሰጠበት Eዳ ሁሉ ወደ Aክስዮን ማህበሩ ይተላለፋል የሚል ግልጽ የህግ ድንጋጌ ካለመኖሩም በላይ የዚህ Aይነት የህግ Aተረጓጐም Aክስዮን ማህበሩን ለከፍተኛ ኪሣራ የሚዳርግና የባለAደራ ቦርዱ የተቋቋመበትን መሰረታዊ ዓላማ ጋር የሚቃረን ሆኖ Eናገኘዋለን። በመሆኑም Eዳው Aክስዮን ማህበሩ ከመቋቋሙ በፊት የነበረ Eስከሆነ ድረስ ፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ በወቅቱ ያላወቀውና ውሣኔ ያልሰጠበት Eዳ በAክስዮን ማህበሩ መከፈል ይገባዋል በማለት የAማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠው ትርጉምና ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት Aለበት በማለት ፍርድ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የፍርዱ ግልባጭ ይተላለፍ።
የፍርዱ ግልባጭ ይተላለፍ።
ሁለተኛው ተጠሪ ብር 454,511.99 /Aራት መቶ ሀምሣ Aራት ሺ Aምስት መቶ Aሥራ Aንድ ብር ከዘጠና ዘጠኝ ሣንቲም/ Eና የከፍተኛው ፍርደ ቤት ውሣኔ ከሰጠበት ከሐምል 27 ቀን 1997 ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ ዘጠኝ ፐርሰንት /9%/ ህጋዊ ወለድ ለAንደኛው ተጠሪ ይክፈል ብለናል።
Aመልካችና ተጠሪዎች ያወጡትን ወጪና ኪሣራ ለየራሳቸው ይቻሉ።
ይህ ፍርድ ግንቦት 7 ቀን 2000 ዓ.ም በፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሙሉ ድምጽ ተሰጠ።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት።
ነ/ዓ u›ªÏ ¾}¨[c< u?„‹