No summary available.
ኀዳር 12 ቀን 2AAA ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ፍስሐ ወርቅነህ መስፍን Eቁበዮናስ ተሻገር ገ/ሥላሴ Aብዱራሂም Aህመድ Aመልካች፡- Aቶ ኤልያስ ከፈለ - Aልቀረበም።
ተጠሪ፡- Eነ Aቶ ከድር Aህመድ /4 ሰዎች/ ቀረቡ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር Aቤቱታ የቀረበው Aመልካች ጥቅምት 3 ቀን 1999 ዓ.ም. ጽፎ ባቀረበው ማመልከቻ መነሻነት ነው።
የጉዳዩን የሥር Aመጣጥ የAሁን ተጠሪዎች በፍድራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በAመልካች ላይ ያቀረቡት ክስ በቂርቆስ ክ/ከተማ የሚገኘውን የንግድ ቤት ለኑሮAቸው መቋቋሚያ ተፈቅዶላቸው መንቀሳቀሻ ገንዘብ በማጣት ላሁኑ Aመልካች ቦታውን ለ4 ዓመት ማከራየታቸውን፣ ውሉ ከተደረገ በኋላ ቦታው የተሰጣቸው ለዘለቄታው ሣይሆን ለ3 ዓመት ብቻ መሆኑን መገንዘባቸውንና በቦታው ላይ ከብረታ ብረት ወርክሾፕ በስተቀር ልላ ሥራ መሥራት Eንደማይችሉ፣ ከዚህ ውጭ ሰርተው ከተገኙ የላዝ ውሉ የሚሰረዝ መሆኑ በAስተዳደር Aካል የተነገራቸው መሆኑን፣ Aመልካች ግን ከላዝ ውሉ ውጭ Eየሰሩ ስለሚገኙ በውሉ ለመቀጠል Aስቸጋሪ ሁኔታ ከመፈጠሩም በላይ ከክ/ከተማው ጋር ባረደረጉትም ውል ለልላ ሶስተኛ ወገን ቦታውን Aሣልፎ መስጠት የተከለከለ በመሆኑ ባጠቃላይ ውሉ የተሣሣተ ውል ነው ተብሎ Eንዲሰረዝ የሚል ነው። Aመልካችም መልስ Eንዲሰጡ በተታዘዙበት Eለት ባለመቅረባቸው በጽሁፍ መልስ የመስጠት መብታቸው ታልፏል። ከዚህ በኋላ ግራ ቀኙ የቃል ክርክር Eንዲያቀርቡ ተደርጎ ፍርድ ቤቱ Aመልካችና ተጠሪዎች ያደረጉት ውል ከላዝ ውሉ ጋር የማይጣጣም ነው በማለት ውሉን ሰርዞ ግራ ቀኙ ወደየነበሩበት Eንዲመለሱ ሲወሰን የከፍተኛው ፍርድ ቤትም በይግባኝ ውሣኔውን Aጽንቷል። Aመልካች ይህን የሰበር Aቤቱታ ያቀረቡት በዚህ መነሻነት ሲሆን ፍ/ቤቱም Aቤቱታውን መርምሮ መልስ ሰጪን በማስቀረብ ግራ ቀኙን Aከራክሯል። ክርክራቸውንም ከሕጉ ጋር በማገናዘብ መርምሯል።
በዚህም መሰረት ግራ ቀኙ ያደረጉት ውል ከሕዳር 6 ቀን 1996 ዓ.ም. ጀምሮ ለAራት ዓመት ማለትም Aስከ ኀዳር 6 ወይም 7 ቀን 2AAA ዓ.ም. ድረስ የሚዘልቅ መሆኑን ፍርድ ቤቱ ተረድቷል።
በልላም በኩል ተጠሪዎች ከቂርቆስ ክ/ከተማ ጋር ያደረጉት የላዝ ውል ለሶስት ዓመታት የሚዘልቅ መሆኑን ተጠሪዎች በክሣቸው ላይ ገልፀዋል ተጠሪዎች ካቀረቡት ክስ በመነሣት ፍርድ ቤቱ ለመገንዘብ የቻለው ጉዳይ በክርክር ሒደት ላይ Eያለ የላዝ ውሉ የጊዜ ገደብ ያበቃ መሆኑን ነው። የላዙ የጊዜ ገደብ ካለቀ ደግሞ ተጠሪዎች የነበራቸውን የክስ መሰረት ያጡ ለመሆኑ Aጠያያቂነት የለውም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 28A ላይ Eንደተመለከተው ክሱ በማንኛውም ደረጃ ባለ ጊዜ የክሱ መሰረት ማክተሙን ፍርድ ቤቱ ከተረዳ ክሱን Eንደሚሰርዝ በግልጽ ተደንግጓል። በተያዘውም ጉዳይ ተጠሪዎች ለሶስት ዓመት ከክፍለ ከተማው ጋር ያደረጉት ውል ማብቃቱ የተረጋገጠ ስለሆነና በዚህም ሣቢያ በቦታው ላይ ምንም Aይነት መብት ስለልላቸው፣ በልላም በኩል Aመልካችም በውሉ ከተመለከተው የAራት ዓመት ጊዜ በላይ በቦታው የተጠቀመ ስለሆነ ግራ ቀኙን መብት በልላቸው ጉዳይ Eየተከራክሩ መሆኑን ፍርድ ቤቱ በመገንዘቡ የሥር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት መሆን Aለመሆኑን ማየት ሣያስፈልግ የሰበር Aቤቱታውን ሰርዘናል በተመሣሣይ ሁኔታም ተጠሪዎችን ተጠቃሚ ያደረገው የሥር ፍርድ ቤቶች ውሣኔም ከላይ በተመለከተው ምክንያት ከEንግዲህ ተፈፃሚ ላሆን Aይችልም ብለናል።
ው ሣ ኔ
የሰበር Aቤቱታው ተሰርዟል፣ የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና በዚህ ጉዳይ የተጀመረው የAፈፃፀም መዝገብ Eንዲዘጋ ታዟል።
ግራ ቀኙ ወጪያቸውን ይቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.