No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 253A6 ኀዳር 12 ቀን 2AAA ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ፍስሐ ወርቅነህ መስፍን Eቁበዮናስ ተሻገር ገ/ሥላሴ Aብዱራሂም Aህመድ Aመልካች፡- Aቶ ተስፋዬ ገለቴ - ጠበቃ በፀሎት መኮንን ቀረበ።
መልስ ሰጪ፡- የIትዮጵያ ንግድ ባንክ - ነ/ፈጅ ታሪኳ ላEከ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
የAሁኑ Aመልካች ሐምል 4 ቀን 1995 ዓ.ም. በAሁኑ መልስ ሰጭ Eና በሥር ጣልቃ ገብ በነበሩት በAቶ ሃይደር ከቢር Eና በፈንታል ወረዳ ፍ/ቤት ላይ መስርቶት የነበረው ክስ፣ በመልስ ሰጭ ባንክ Aዲስ ከተማ ቅርንጫፍ በሂሣብ ቁጥር 1A11 ከነበረው የተንቀሳቃሽ ሂሣቤ ውስጥ ሳይፈረድብኝና በAፈፃፀምም ሳልገደድ ባንኩ ከፈንታል ወረዳ ፍ/ቤት ታዝዤ ከፍያለሁ በማለት ብር 135‚912.08 /Aንድ መቶ ሰላሣ Aምስት ሺህ ዘጠኝ መቶ Aስራ ሁለት ብር ከዜሮ ስምንት ሳንቲም/ ወጭ በማድረግ ከፍሐል።
በመጨረሻም ከፈንታል ወረዳ ፍ/ቤት የተሰጠ የክፍያ ትEዛዝ የልለ መሆኑና ባንኩ የከፈለው በተጭበረበረ ሰነድ መሆኑን ገልጨ ያለAግባብ የከፈለውን ገንዘብ ወደ ሂሣቤ Eንዲያስገባልኝ ብጠይቅ Eምቢተኛ በመሆኑ፣ የሥራ ግድታውን ባለመወጣት የከፈለውን ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ከወለዱና ከወጭና ኪሣራ ጋር Eንዲከፈለኝ በማለት ጠይቋል። የAሁኑ መልስ ሰጭ በበኩሉ በሰጠው መልስ፣ ክፍያ የፈፀመባቸው ትEዛዞች የመጡት ከፍርድ ቤት መሆኑንና ማኀተሞቹም ትክክለኛ መሆናቸውን Aምኖ የከፈለ መሆኑን ገልፆ ፊርማው የዳኛው ስለመሆኑ የማረጋገጥ ግድታ የልለበት መሆን በመግለጽ መልስ ሰጥቷል። የሥር ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ ባንኩ ሐሰተኛ ነው ተብሎ ላታወቅ በማይችል የፍርድ ቤት ትEዛዝ መሰረት የከፈለ በመሆኑ በኃላፊነት የሚጠየቅበት ምክንያት የለም በማለት በነፃ Aሰናብቶታል። ይግባኝ የቀረበለት የፍ/ከፍተኛ ፍ/ቤትም ውሣኔውን Aጽንቶታል።
ይህ ችሎት በጥቅምት 3A ቀን 1999 በዋለው ችሎት ጉዳዩ ለሰበር Eንዲቀርብ ትEዛዝ ሰጥቶ የግራ ቀኙን መልስ Eና የመልስ መልስ Eንዲሁም የቃል ክርክሩን Aሰምቷል።
በዚህ ጉዳይ በዋነኛነት ታይቶ ላወሰን የሚገባው የሕግ ጥያቄ፣ የAሁኑ መልስ ሰጭ በAደራ ተቀብሎ ያስቀመጠውንና ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ብር 135‚912.08 ለልላ ግለሰብ ከፍሎ በመገኘቱ ገንዘቡን ለመመለስ በኃላፊነት Aይጠየቅም መባሉ በAግባቡ መሆን Aለመሆኑን መመርመር ይሆናል።
በመሰረቱ በAሁኑ Aመልካችና በመልስ ሰጭው መካከል በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1779 Eና በሚቀጥሉት Aንቀጾች Eንዲሁም ከተያዘው ጉዳይ ጋር ቀጥተኛ Aግባብነት ባለው በንግዱ ሕግ ቁጥር 896 Eስከ 9A2 ባሉት ድንጋጌዎች መሰረት የAደራ ውል ስምምነት ያለ መሆኑ ይታወቃል። በዚህ የውል ግንኙነት ተቃራኒ የሆነ ስምምነት ከልለ በቀር Aደራ ተቀባዩ ባንክ በተጠየቀ ጊዜ በAደራ የተቀበለውን ገንዘብ የመመለስ ግድታ ያለበት መሆኑ ሳይቀር በAደራ የተቀበለውን ገንዘብ Aስፈለጊ ለሆኑ ስራዎቹ Eንዲገለገልበት መብት የሚያገኝ መሆኑን የንግድ ሕግ ቁጥር 896 በግልጽ ደንግጓል። በተመሣሣይ ሁኔታ ተቃራኒ ስምምነት በልለበት ሁኔታ Aደራ Aስቀማጩ በAደራ ተቀባዩ ዘንድ ያስቀመጠውን ገንዘብ በማንኛውም ጊዜ በሙሉ ወይም በከፊል ላያዝበት የሚችል መብት ያለው ስለመሆኑም በዚሁ ንግድ ሕግ ቁ. 898/1/ ላይ ተመልክቷል። በያዝነው ጉዳይ የAሁኑ መልስ ሰጭ በAደራ የተቀበለውን የAመልካችን ገንዘብ Aደራ Aስቀማጩ ወይም በሕግ Aግባብ ሥልጣን የተሰጠው ክፍል ሳያዘው ገንዘቡን Aሳልፎ ለልላ ከፍሎ ተገኝቷል። ለክፍያውም ምክንያቱ የማጭበርበር ተግባር ድርጊት መሆኑ ተረጋግጧል። Aቶ ሐይደር ከዲር በተባለ ሰው ተፈፀመ በተባለው የማጭበርበር ተግባር የተጭበረበረው የAሁኑ መልስ ሰጪ ባንክ Eንጂ የAሁኑ Aመልካች Aይደለም። የAሁኑ መልስ ሰጭ ተጭበርብሮ ከሆነ ያጭበረበረውን ሰው በሕግ Aግባብ ከሶ ከሚጠይቅ በቀር ተቃራኒ ስምምነት በልለበት ሁኔታ የተቀበለውን የAደራ ገንዘብ Aደራ Aስቀማጩ በተጠየቀ ጊዜ የማይመልስበት ሕጋዊ ምክንያት የለም። የማጭበርበር ተግባሩ ሕጋዊ ስርዓቱን ባልተከተለ የፍርድ ቤት ማኀተም መሆኑ የAደራ ተቀባዩን ባንክ ኃላፊነትም Aይቀንሰውም።
በመጨረሻ በዚህ የማጭበርበር ተግባር ላጎዳ የሚችል ክፍል ቢኖር በቀጥታ የማጭበርበር ተግባሩ ሰለባ የሆነው መልስ ሰጪ ባንክ Eንጂ በምትኩ ያልተጭበረበረው Aደራ Aስቀማጭ ላሆን የሚችልበት የሕግ Aግባብ Aይኖርም።
በAጠቃላይ ተቃራኒ ስምምነት በልለ ጊዜ የAደራ ገንዘብ Eንደተጠየቀ የሚከፈል ገንዘብ ነው። Aደራ ተቀባዩ ተጭበርብሬ ነው በማለት የሚያነሳው መቃወሚያ ገንዘቡ Eንዲከፈል በተጠየ ጊዜ ከመክፈል የሚያግደው Aይደለም።
የሥር ፍ/ቤት በAደራ ተቀባይና በAደራ Aስቀማጩ መካከል የተደረገ ተቃራኒ ስምምነት መኖሩን ሳያረጋገግጥ “መልስ ሰጪ ሐሰተኛ ነው ተብሎ ላታወቅ በማይችል የፍርድ ቤት ትEዛዝ መሰረት የከፈለ በመሆኑ በኃላፊነት የሚጠየቅበት ምክንያት የለም” በማለት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ብለናል።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ
3381A የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
መልስ ሰጭ ባንክ ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ብር 135‚912.08 /Aንድ መቶ ሰላሣ Aምስት ሺህ ዘጠኝ መቶ Aስራ ሁለት ብር ከዜሮ ስምንት ሣንቲም/ ክስ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ ከሚታሰብ ሕጋዊ ወለድ ጋር ለAመልካች ይክፈል፤
Aመልካች ለዳኝነት የከፈለውን ገንዘብ መልስ ሰጪ ይተካ፤ የጠበቃ Aበል 1A% ይክፈል፤ ኪሣራ በቁርጥ ብር 2AAA /ሁለት ሺህ/ ለAመልካች ይከፈል።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት።
ነ/ዓ