No summary available.
ግንቦት 14 ቀን 2AAA ዓ.ም.
ዳኞች፡- Aብዱልቃድር መሐመድ መስፍን Eቁበዮናስ መድሕን ኪሮስ ዓላ መሐመድ ሡልጣን Aባተማም Aመልካች፡- Aቶ ከበደ ሙሕ ቀረቡ።
ተጠሪ፡- ወ/ሮ ፋናዬ ብዙነህ ቀረቡ።
መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ነበር። መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዳዩ የቀረበው Aመልካች የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ግንቦት 6 ቀን 1999 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔና የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በይግባኝ መዝገብ ቁጥር 32A29 ጥቅምት 18 ቀን 2AAA ዓ.ም.
የሰጠው ትEዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስላለበት በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ 269 270 በማለት የሰበር Aቤቱታ ስላቀረቡ ነው። የክርክሩ ፍሬ ጉዳይ Aመልካችና ተጠሪ በሕጋዊ ጋብቻ ተሣሥረው ለበርካታ ዓመታት በባልና ሚስትነት የኖሩ ሲሆን፣ ጋብቻቸውን በፍች Aፍርሰዋል። ከዚህ በኋላ የጋራ ንብረታቸውን ለመካፈል በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የጋራ ንብረት ዝርዝር Aቅርበው ትEዛዝ ተሰጥቶበታል። Aከራካሪው ጉዳይ ተጠሪ Eስከ ጥር 29 ቀን 1998 ዓ.ም. Aመልካች የተቀበሉት የጡረታ Aበል ታስቦ Eንዲከፈለኝ ትEዛዝ ይሰጥልኝ በማለት ጥያቄ ማቅረባቸው ነው። የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪ የጡረታ Aበል ይሰጠኝ ጥያቄ የሕግ ድጋፍ የለውም በማለት ውድቅ Aድርጎታል። ተጠሪ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት በከፍተኛው ፍርድ ቤት ይግባኝ Aቅርበው፣ ፍርድ ቤቱ በይግባኝ Aመልካችና ተጠሪ ያቀረቡትን ክርክር ከሰማ በኋላ Aመልካች የሚያገኙት የጡረታ Aበል የጋራ ንብረት ነው በማለት የጡረታና ማኀበራዊ ዋስትና ባለስልጣን ከግንቦት ወር 1999 ጀምሮ ግማሽ የጡረታ Aበል ለተጠሪ Eንዲከፍል በማለት ወስኗል።
Aመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ያቀረቡ ሲሆን ይግባኙን የሰማው የጠቅላይ ፍርድ ቤት ችሎት የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ የሚነቀፍበት የሕግ ወይም የፍሬ ጉዳይ ስህተት የለም በማለት ይግባኙን በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል። Aመልካች Aሁን የTገኘው Aንድ መቶ ሰላሣ Aምስት ብር የጡረታ ገንዘብ ወታደር ቤት EያለG< በAይኔ ላይ ጉዳት ደርሶብኝ በቦርድ በመውጣቴ የማገኘው ነው። ስለሆነም የሥር ፍርድ ቤት የባልና የሚስት የጋራ ሀብት ነው በማለት ተጠሪዋ ግሣሹን Eንድትወስድ የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ይታረምልኝ በማለት ያመለከተ ሲሆን ተጠሪª በበኩሐ የጡረታ Aበሉ በትዳራችን ጊዜ የተጠራቀመ በመሆኑ ግማሹን EንÉወስድ መወሰኑ በAግባቡ ነው በማለች ተከራክራለች።
በሥር የቀረበው ክርክርና በሰበር ግራ ቀኙ የሚያነሱት የመከራከሪያ ነጥብ ከላይ የተገለፀው ሲሆን Eኛም የከፍተኛው ፍርድ ቤት ተጠሪዋ ከግንቦት 1999 ጀምሮ ግማሽ የጡረታ Aበል ልታገኝ ይገባታል በማለት የሰጠው ውሣኔ ሕግን መሰረት ያደረገ ነው ወይስ Aይደለም የሚለውን ነጥብ Aይተናል።
የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሣኔውን በሚሰጥበት ወቅት የተከተለውን ሥርዓት ስንመረምረው፣ ተጠሪ የጡረታ Aበል፣ ታስቦ ላሰጠኝ ይገባል በማለት ክስ ያቀረቡት Eስከ ጥር 29 ቀን 1998 ዓ.ም. Aመልካች የወሰዱትን የጡረታ Aበል መሆኑን የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በውሣነው በግልጽ Aስፍሮታል። ይህ ከሆነ ተጠሪ የጠየቁትን ጋብቻቸው ከመፍረሱ በፊት ተለያይተው Eያለ Aመልካች ተቀብለው የተጠቀሙበት የጡረታ Aበል ታስቦ Eንዲሰጣቸው Eንጂ ጋብቻው ከፈረሰ በኋላ Aመልካች ከሚያገኙት የጡረታ Aበል ግማሹን Eንዲወስንላቸው በሥር ፍርድ ቤት Aልጠየቁም። ተጠሪ ለፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ያላቀረቡትንና በሥር ያልተከራከሩበትን Aዲስ ነገር በይግባኝ ደረጃ ለማንሣትና ለመጠየቅ Eንደማይችሉ የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 328 ንUስ Aንቀጽ 2 ይደነግጋል። ስለሆነም ተጠሪ በሥር ያልጠየቁትና ያልተከራከሩትን ጉዳይ በማንሣት የከፍተኛው ፍርድ ቤት ተጠሪ ከግንቦት ወር 1999 ዓ.ም. ጀምሮ Aመልካች ከሚያገኙት ጡረታ ግማሹን ላከፍላት ይገባል በማለት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሥነ ሥርዓት ግድፈት ያለበት ሆኖ Aግኝተነዋል።
ከዚህ በተጨማሪ Aመልካች የሚያገኙት የጡረታ Aበል፣ የመንግሥት ሰራተኛ በነበሩበት ሰዓት ከደመወዛቸው ተቆርጦ የተጠራቀመ ነው የሚለው Aባባል መሰረታዊ ስህተት ያለበትና የጡረታ Aበሉ መንግሥት በኩል ተቀማጭ የሚሆን ገንዘብ ያለ በመሆኑ ለAንድ ሰራተኛም የጡረታ Aበል የሚከፈለው Eድሜው በገፋበት“ ጉልበቱ በደከመበት ጊዜ መጦሪያ የሚሆነውና ለመኖር የሚያስፈልገውን ወጭ በከፊልም ቢሆን በመሸፈንና ለማኀበራዊ ደህንነቱ ዋስትና ለመስጠት መንግሥት ካለው የማኀበራዊ ደህንነትና ዋስትና ፖላሲ የመነጨ በመሆኑ Eንደማንኛውም ገቢ ¾ጋራ ንብረት ነው የሚባል Aይደለም። የAንድ ሰው የጡረታ Aበል በማናቸውም መልኩ በEዳ ላያዝ ወይም ላታገድና ላቀነስ Eንደማይችል የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 4A4/ሰ/ በግልጽ የሚደነግግ ሲሆን የከፍተኛ ፍርድ ቤት ይህንን በመተላለፍ Aመልካች የሚከፈለው የጡረታ Aበል ግማሹ Aየተቆረጠ ለተጠሪ Eንዲከፈል የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ፍርድ ሰጥተናል።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ
የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይግባኝ መዝገብ ቁጥር 32A29 ጥቅምት 18 ቀን 2AAA ዓ.ም. የሰጠው ትEዛዝ ተሽሯል። ይፃፍ።
የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ