No summary available.
መጋቢት 25 ቀን 2AAA ዓ.ም.
ዳኞች፡- Aብዱልቃድር መሐመድ ሒሩት መለሰ ፀጋዬ Aስማማው ዓላ መሐመድ መድኀን ኪሮስ Aመልካች፡- ወ/ሮ የሻረግ Aባትኩን ቀረቡ።
ተጠሪ፡- ወ/ሮ መሰረት Aድማሱ ቀረቡ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ክርክሩ የተጀመረው በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ሲሆን የAሁንዋ ተጠሪ የAቶ ኪዳነወርቅ ብርቁ ሚስት ስለመሆናቸው መጋቢት 16 ቀን 1996 ዓ.ም. በመ/ቁ.
12185 በዚሁ ፍ/ጠ/ፍ/ቤት ቄራ ምድብ 1ኛ ፍትሐብሕር ችሎት የተወሰነላቸው ሲሆን የAሁንዋ Aመልካች የሟች Aቶ ኪዳነወርቅ ብርቁ ሚስት Eኔ ነኝ፤ ወ/ሮ መሰረት Aድማሱ የሟች ሰራተኛ Eንጂ ሚስት Aልነበሩም በማለት ተቃውመዋል።
ተቃውሞው የቀረበለት ፍ/ቤትም ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ ወ/ሮ መሰረት Aድማሱ Aቅርበው ያሰሙዋቸው ምስክሮች Aቶ ኪዳነወርቅ ብርቁ ድግስ ደግሰው ለተጠሪው ሕዝብ ወ/ሮ መሰረት Aድማሱ ሚስቴ ናት፤
ከEንግዲህ ባልና ሚስት ነን ብለው መናገራቸውንና ከዚያም በኋላ Aብረው በመኖር ልጆች መውለዳቸውን ያስረዱ በመሆኑና ተቃዋሚዋ ያሰሙዋቸው ምስክሮች ደግሞ የሰጡት ምስክርነት ይህን የሚያፈርስ ባለመሆኑ ተቃውሞው ተቀባይነት የለውም በማለት ቀደም ብሎ የተሰጠውን ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 36A/2/ መሰረት Aጽንቷል።
የAሁንዋ Aመልካች ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ Aቅርበዋል።
የፍ/ከ/ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ የወ/ሮ መሰረት Aድማሱ ምስክሮች ሟች ድግስ ደግሰው ባልና ሚስት ነን ብለው ተናግረዋል ብለው ቢያስረዱም ይህ Aባባል በጽሁፍ በሽማግልዎች ፊት Eስካልተደረገ ጊዜ ድረስ ተደረገ የተባለው ጋብቻ በባሕላዊ ጋብቻ ሥር Aይወድቅም። የሥር ፍ/ቤት የወ/ሮ መሰረት Aድማሱ” ሚስትነት የወሰነው ጋብቻው በሰርተፍኬት ወይም በትዳር ሁኔታ ሳይረጋገጥ ነው በማለት ውሳኔውን በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ሽሮታል።
የAሁንዋ ተጠሪ ደግሞ በፍ/ከ/ፍ/ቤት ውሣኔ ላይ ቅር በመሰኘት ለፍ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ሲሆን ጠቅላይ ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ካዳመጠ በኋላ ይግባኝ ባይዋ በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ያሰሙዋቸው ምስክሮች ሟች ድግስ ደግሰው ሰው ጠርተው በሕዝብ ፊት ከEንግዲህ ከወ/ሮ መሰረት Aድማሱ ጋር ባልና ሚስት ነን በማለት በመናገር የጋበቻውን መመሥረት ያበሰሩና Aብረው በመኖርም ልጆች መውለዳቸውን ያስረዱ በመሆኑ የጋብቻው መኖር በቤተሰብ ሕግ Aንቀጽ 97/1/ መሰረት በሁኔታ ተረጋግጧል። ይህ ሁኔታ ደግሞ በመልስ ሰጭ ማስረጃ በAንቀጽ 97/2/ መሰረት Aልተስተባበለም። የሥር ፍ/ቤት ለባሕላዊ ጋብቻ የሰጠው ትርጉምም የተሳሳተ ነው በማለት የፍ/ከ/ፍ/ቤት የሰጠውን ፍርድ በመሻር የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ Aጽንቷል።
የAሁንዋ Aመልካች ያቀረቡት የሰበር Aቤቱታም የፍ/ጠ/ፍ/ቤት የሰጠውን ፍርድ በመቃወም ነው። Aመልካች በAቤቱታቸው ያካተቱት ቅሬታም ተጠሪ የሟች ሰራተኛ Eንጂ ሚስት Aይደሉም። ሕጋዊ ሚስት Eኔው ነኝ።
የተሰሙት የተጠሪ ምስክሮች የሰጡት ምስክርነት በሟችና በተጠሪ መካከል ባሕላዊ ጋብቻ ስለመመስረቱ Aያስረዳም። ወቅቱ በ1976 ዓ.ም. ቦታውም Aዲስ Aበባ በመሆኑ በዚህ ጊዜ የሚፈፀም ባሕላዊ ጋብቻ በሽማግልዎች ፊትና በጽሁፍ ሰፍሮ የግራ ቀኙንና የሽማግልዎችን ፊርማ ባረፈበት ሁኔታ መሆን ነበረበት። በሟችና በተጠሪዋ መካከል ተደረገ የተባለው ጋብቻ ይህን የሚያሟላ Aይደለም።
የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት Eና የፍ/ጠ/ፍ/ቤት የመልስ ሰጭ ምስክሮች በድግስ ወቅት ሟች ሚስቴ ናት ሲሉ ሰምተናል በማለት የሰጡትን ምስክርነት ብቻ መነሻ በማድረግ የEኔ ምስክሮች ተጠሪዋ ሚስት ሳይሆኑ የሟች ሰራተኛ ናቸው ደመወዝም ይቀበሉ ነበር በማለት ያስረዱትን ባለመቀበል ተጠሪዋ የሟች ሚስት ስለመሆናቸው በሁኔታ ተረጋግጧል በማለት የሰጡት ውሣኔ በቤተሰብ ሕግ Aንቀጽ 4 Eና 97/2/ የተመለከተውን ድንጋጌ ያላገናዘበ በመሆኑ ውሣኔው መሰረታዊ የሕግ ስህተት Aለበት። ተጠሪዋ ባሰሙዋቸው ምስክሮች ከሟች ጋር በባሕላዊ ሥነ ሥርዓት ጋብቻ የፈፀሙ ስለመሆኑ Aላስረዱም Eንጂ ፍ/ቤቱ Aስረድተዋል Eንኳን ቢል ተጠሪዋ ከ1977 ዓ.ም. Eስከ 198A ዓ.ም. ድረስ የሟች ኪዳነወርቅ ብርቁ የጽዳት ሰራተኛ Eንደነበሩ የሚያሳይ ማስረጃ መቅረቡ Eንዲሁም ሟች ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ጥር ወር 1994 ዓ.ም. ሲሆን ተጠሪዋ ከ198A ዓ.ም. ጀምሮ ከሟች በመለየት Aቶ ሽፈራው መንክር የተባሉትን ሰው Aግብተው ሁለት ልጆች ወልደዋል። ከዚህ ሁኔታም ተጠሪዋ ከሟች ተለያይተው ሟች ከዚህ ዓለም Eስከተለዩበት ጊዜ ድረስ የየራሳቸውን ኑሮ ይኖሩ የነበረ ስለመሆኑ መረዳት ይቻላል። Eንዲህ ዓይነቱ ሁኔታ ባለበት ተጠሪዋ የሟች ሚስት ናቸው መባሉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነው። በመሆኑም የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት Eና ፍ/ጠ/ፍ/ቤት የሰጡት ውሣኔ ተሽሮ የፍ/ከ/ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ Eንዲፀና Eንዲወስንልኝ የሚል ነው።
No topics extracted.
ተጠሪዋ ደግሞ በሰጡት መልስ የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ሚስትነቴን ያረጋገጠልኝ ጥቅምት 15 ቀን 1976 ዓ.ም. ዘመድ ጠርተን ድግስ ደግሰንና ጋብዘን ከዚህ በኋላ ባልና ሚስት ነን ተጋብተናል በማለት መጋባታችንን በማሳወቅ የጋብቻ ሥነ ሥርዓት መፈፀማችንን ከዚህ በኋላም ባልና ሚስት ሆነን ልጅ መውለዳችንን በማስረጃ በመረጋገጡ ነው። Aመልካች በወቅቱ ተጠሪ የሟች ባለቤት Aይደለችም ሰራተኛው ናት ከማለት በስተቀር በማስረጃ ያረጋገጥኩትን የጋብቻ ሁኔታ ስላለመኖሩ Aላስረዱም። የከፍተኛው ፍ/ቤት የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤቱን ውሣኔ የሻረው ባሕላዊ ጋብቻን በሽማግልና በፊርማ ሥነ ሥርዓት መከናወን Aለበት የሚል በጣም ጠባብ ትርጉም በመስጠት ነው።
የፍ/ጠ/ፍ/ቤትም የከፍተኛው ፍ/ቤት የሰጠውን ትርጉም ሲሽር ሕጉ በAማራጭ ያስቀመጣቸውን ሁኔታዎች ከግምት ያስገባ Aይደለም። ከዚህም Aልፎ በጽሑፍና በውል Aባት ሽማግል ፊት መደረግ Aለበት የሚለው ድምዳሜ የA/Aበባ ከተማ ማኀበረሰብ ላወክል የሚችል ባሕላዊ Aመራር ነው ብሎ ለመደምደም በቂ መነሻ Aይሆንም በማለት ያስቀመጠው ትንታኔ የሕጉን መንፈስ በትክክል የሚገለጽ በመሆኑ ውሣኔው Aንዳችም የሕግ ስህተት የለበትም በማለት ተጠሪ መልስ ሰጥተዋል።
በተጨማሪ ተጠሪ ከሟች ጋር የተዋወቅነውና የትዳር ጥያቄም ቀርቦልኝ የተጋባነው ሟች በሚያንቀሳቅሱት የባሕል ሕክምና ድርጅት ውስጥ በረዳት ሐኪምነት ተቀጥሬ በነበረበት ወቅት ስለመሆኑ Aልክድም ብለዋል።
ሆኖም ከሟች ጋር ከተጋባን በኋላ ተለያይተን ኖረን Aናውቅም። ሟች ከመሞታቸው በፊት ተለያይተው ተጠሪዋ ልላ ባል Aግብታ ነበር የተባለው በስር ፍ/ቤት ያልቀረበና በማስረጃም ያልተረጋገጠ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም። ከሟች ባለቤቴ የወለድኩትን ልጅ ያሳደግነውና በAዲስ Aበባ ከተማ በወረዳ 19 ቀበል 49 ክልል የቤት ቁጥር AA8 Eና AA9 የሆነውን ድርጅትና የመኖሪያ ቤት ያፈራነው በጋራ ነው። በሰበር መ/ቁ. 2A938 የተሰጠው ውሣኔም Aሁን ከቀረበው ክርክር ጋር ተዛማጅነትና ተመሣሣይነት የለውም።
በመሆኑም የፍ/ጠ/ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ ምንም የሕግ ስህተት የልለበት በመሆኑ ውሣኔው Eንዲጸናልኝ በማለት ተከራክረዋል። Aመልካችም የመልስ መልሳቸውን በማቅረብ ከመዝገቡ ጋር Aያይዘዋል።
በበኩላችን ደግሞ ተጠሪዋ የጋብቻ ሁኔታን Aረጋግጠዋል ወይስ Aላረጋገጡም? Aመልካችስ የጋብቻ ሁኔታውን Aስተባብለዋል ወይስ Aላስተባበሉም? የሚሉት ጭብጦች በመያዝ መዝገቡን መርምረናል።
መዝገቡን Eንደመረመርነውም ግራ ቀኙ በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ባካሄዱት ክርክር የተጠሪ ምስክሮች ያስረዱት ሟችና ተጠሪዋ ድግስ ደግሰው ሰው ጠርተው ሟች ከዛሬ ጀምሮ ከተጠሪዋ ጋር ባልና ሚስት ሆነዋል ብለው ማሳወቃቸውን ከዚያም በኋላ ልጅ ወልደው Aብረው የኖሩ መሆናቸውን ነው።
ይህ ዓይነቱ ማስረጃ ደግሞ ጋብቻው በቤተሰብ ሕግ Aንቀጽ 4 መሰረት በባሕላዊ ሁኔታ የተፈፀመ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው። በAንፃሩ የAሁንዋ Aመልካች ያሰሙዋቸው ምስክሮች የሰጡት ምስክርነት ተጠሪዋ የሟች ሰራተኛ መሆናቸውንና ከሟች ጋር ስለመጋባታቸው ግን የሚያውቁ መሆናቸውን ነው ያስረዱት። መጀመሪያ ተጋብተው ግን ደግሞ ሟች ከመሞታቸው በፊት የተፋቱ ስለመሆኑም Eንዲመሰክሩ Aልተጠየቁም። Eነሱም ይህን Aስመልክተው ያሉት ነገር የለም። ይህ የAመልካች ምስክሮች ምስክርነት ደግሞ ተጠሪዋ ከሟች ጋር የትዳር ጋብቻ ያላቸው መሆኑን በቤተሰብ ሕግ Aንቀጽ 97/1/ ያስረዱትን የሚያስተባብል Aይደለም። ይህን መሰረት በማድረግ የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በተጠሪዋና በሟች መካከል ጋብቻ ነበር በማለት የሰጠው ውሣኔ የሚነቀፍበት የሕግ ምክንያት Aልነበረም።
የፍ/ጠ/ፍ/ቤትም በሰጠው ውሣኔ በAሁንዋ ተጠሪና በሟች መካከል ባሕላዊ ጋብቻ ሰለመመስረቱ በማስረጃ ተረጋግጧል። በAዲስ Aበባ ከተማ ውስጥ የሚፈፀም ባሕላዊ ጋብቻ በሽማግል ፊት በጽሑፍና በፊርማ ነው የሚከናወነው በማለት የፍ/ከ/ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ መንደርደሪያ የሆነውን የሕግ ትርጉምም ተቀባይነት የለውም ሲል በውሣኔው ላይ ያሰፈረውን ትንታኔ ስንመለከትም ውሣኔውና ለውሣኔው መሰረት ተደርጎ የተወሰደው ትንታኔ የሚነቀፍበት ምክንያት የለም። ምክንያቱም ተጠሪዋ ከሟች ጋር ፈፀምኩት የሚሉትን ባሕላዊ ጋብቻ ስለመመሥረቱ ለማስረዳት የሚጠበቅባቸው የAመሰራረቱን ሁኔታ ማስረዳት ነው። በምስክሮቻቸው ያስረዱትም ጋብቻውን ለልሎች ለማሳወቅ ታስቦ ድግስ መዘጋጀቱንና ሰዎች መጠራታቸውን የተጠሩት ሰዎች ከተገኙ በኋላ ሟች ከEንዲህ ከወ/ሮ መሰረት Aድማሱ ጋር ባልና ሚስት ሆነናል Eወቁልን በማለት የተናገሩ መሆናቸውን ከዚያም በመቀጠል ባልና ሚስት ሆነው Aብረው መኖራቸውንና ልጅም መውለዳቸውን ነው። ይህ ዓይነቱ ጋብቻ ደግሞ በAዲስ Aበባ ከተማ ውስጥም የሚፈፀም ነው። በዚህ ሁኔታ ባሕላዊ ጋብቻ Eንዳይፈፀምም የሚከለክል ምክንያት የለም። ተጋቢዎች ከፈለጉ ጋብቻውን በጽሑፍ በመፈራረም ላያደርጉት ይችላሉ። ከፈለጉ ደግሞ በቃል ለማኀበረሰቡ Eወቁልን ብለው በመናገር ላመሰርቱት ይችላሉ።
በመሆኑም የፍ/ጠ/ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ ምንም ዓይነት የሕግ ስህተት ያለበት ባለመሆኑ የቀረበው የሰበር Aቤቱታ ተቀባይነት ያለው ሆኖ Aላገኘነውም።
ው ሣ ኔ
የፍ/ጠ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 26737 ጥቅምት 4 ቀን 2AAA ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ፀንቷል። ይፃፍ።
ወጪና ኪሣራን በተመለከተ ግራ ቀኙ ይቻቻሉ ብለናል።