No summary available.
ሚያዝያ 21 ቀን 2AAA ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልዱ ታፈሰ ይርጋ መድኀን ኪሮስ ሡልጣን Aባተማም Aመልካች፡- ወ/ሮ ኪሮስ ገ/ማርያም - ጠበቃ ሰለሞን ገ/ሚካኤል ተጠሪ፡- Aቶ ግርማ ገብረስላሴ - ጠበቃ Aያልው ካሕሳይን መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥሎ የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ ጉዳይ የተጀመረው በAዲስ Aበባ የከተማ ነክ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን በቅድሚያ የAሁን ተጠሪ የሟች ወ/ሮ ኪሮስ ውቤ ልጅ ነኝ በማለት የወራሽነት ማስረጃ ካገኙ በኋላ የAሁን Aመልካች Eዚሁ ፍ/ቤት ቀርበው ሟች Eህቴ ወ/ሮ ኪሮስ ውቤ ልጅ ሳትወልድ የሞተችና ከተጠሪውም ጋር ምንም ዓይነት ዝምድና የልላቸው ስለሆነ ተጠሪ የሟች ወራሽ ነው ተብሎ በዚህ መዝገብ የተሰጠው ማስረጃ ላሰረዝ ይገባል የሚል መቃወሚያ Aቅርበው ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን Aከራክሮ ልጅነትን በተመለከተ የከተማ ነክ ፍ/ቤት ለመወሰን በሕግ ሥልጣን ያልተሰጠው ስለሆነ ተጠሪ የሟች የወ/ሮ ኪሮስ ውቤ ልጅነትን በተመለከተ ሥልጣን ላለው ፍ/ቤት Aቤቱታ Aቅርበው ውሣኔ በተገኘ ጊዜ መዝገቡን የማንቀሳቀስ መብታቸው የተጠበቀ ነው በማለት መዝገቡን ዘግቷል።
ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተውም የከተማ ነክ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በበኩሉ ግራ ቀኙን Aከራክሮ ልጅነት የልደት የምስክር ወረቀት በማቅረብ ማስረዳት Eንደሚቻል በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ በAንቀጽ 154 ላይ የተመለከተ ሲሆን ከዚህ ድንጋጌ ማንኛውም ፍ/ቤት የሕግ ግምት uመውሰድ ልጅነትን ማረጋገጥ የሚችል በመሆኑ ሥልጣን ላለው ፍ/ቤት Aቤቱታው ይቅረብ ላባል የሚችለውም የልደት የምስክር ወረቀት ሳይቀርብ Aመልካች ልጅ መሆኑን በሁኔታና በሰው ምስክር ለማስረዳት በጠየቀ ጊዜ ነው ካለ በኋላ ይግባኝ ባይ የAሁን ተጠሪ የሟች የወ/ሮ ኪሮስ ውቤ ልጅ ስለመሆኑ በልደት የምስክር ወረቀት የተረጋገጠ ስለሆነ የሥር ፍ/ቤት የይግባኝ ባይ ልጅነት በቅድሚያ ሥልጣን ባለው ፍ/ቤት ላረጋገጥ ይገባል በማለት Aቤቱታውን ሳይቀረበል መቅረቱ በAግባቡ ስላልሆነ ይግባኝ ባይ የሟች ወ/ሮ ኪሮስ ውቤ ልጅ ከሆነ የመጀመሪያ ደረጃ ወራሽ ስለሚሆን መ/ሰጭ ላወርሱ ስለማይችሉ በመ/ቁ.
52A5/98 ኀዳር 1 ቀን 1998 ዓ.ም. ወራሽ ናቸው ተብሎ የተሰጠው ውሣኔ ተሰርዟል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
የAሁን Aመልካች በዚሁ ውሣኔ ቅሬታ Aድሮባቸው ለከተማ ነክ ፍ/ቤት ሰበር ችሎት የሰበር Aቤቱታ ቢያቀርቡም የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ውሣኔ መሰረት የሕግ ስህተት Aልተፈፀመበትም በማለት Aቤቱታውን ሳይቀበለው ቀርቷል።
ይህ ሰበር ችሎትም የቀረበለትን Aቤቱታ መርምሮ በተጠሪ ልጅነት ላይ ተመስርቶ የቀረበውን ክርክር የከተማ ነክ ይ/ሰሚ ፍ/ቤት ተመልክቶ ውሣኔ መስጠቱ በሕግ በተሰጠው ሥልጣን ሥር የሚሸፈን ስለመሆኑ ተጣርቶ ላወሰን የሚገባው መሆኑን በማመኑ ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
የሰበር Aቤቱታውም ያስቀርባል ከተባለበት ነጥብ Aኳያ Eንደሚከተለው ተመርምሯል።
የAዲስ Aበባ ከተማ ነክ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በውሣኔው ላይ Eንዳሰፈረው ልጅነት የሚረጋገጥበት ዋናው ማስረጃ የልደት ምስክር ወረቀት Eንደሆነ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ በAንቀጽ 154 ላይ ተመልክቷል። ይህ ማለት ግን የልደት ምስክር ወረቀት ክርክር ላነሳበት የማይችል ሙሉ Eምነት ላጣልበት የሚችል /Conclusive/ ማስረጃ ነው ማለት ግን Aይደለም።
Aመልካችም ተጠሪ የሟች ወ/ሮ ኪሮስ ውቤ ልጅ መሆኔን ያረጋግጥልኛል በማለት ያቀረቡት የልደት ምስክር ወረቀት በተጭበረበረ መንገድ የተገኘ ከመሆኑም በላይ ሟች በሕይወት ዘመናቸው ልጅ Aልወለዱም በማለት ተከራክረዋል። በተጠሪ ልጅነት ላይ በዚህ መልኩ ክርክር የተነሳበት ከሆነም የተጠሪ ልጅነት ሥልጣን ባለው ፍ/ቤት ክርክር ተደርጎበት ውሣኔ የሚሻ ጉዳይ ነው።
በዚሁ መሰረትም የከተማ ነክ የመ/ደ/ፍ/ቤት ክርክር የተነሳበት የተጠሪ ልጅነት ጉዳይ በቅድሚያ ሥልጣን ባለው ፍ/ቤት Eልባት ላሰጠው ይገባል ማለቱ Aግባብነት ያለው ሆኖ ሳለ የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ግን የልደት ምስክር ወረቀቱ በማስረጃ ላስተባበል Eንደማይችል በመቁጠር የተጠሪ ልጅነት ጉዳይ ከዚህ በኋላ ክርክር ላደረግበት Aይችልም በማለት የሥር ፍ/ቤት የሰጠውን ትEዛዝ መሻሩ Eንደዚሁም የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ሰበር ችሎት ይህንን ስህተት ሳያርም መቅረቱ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ
No topics extracted.
A4714 በሐምል 12 ቀን 1999 ዓ.ም. የሰጠው ትEዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
259 260 2. የAዲስ Aበባ ከተማ ነክ መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 4979/97 በታህሳስ 4 ቀን 1999 ዓ.ም. የሰጠው ብይን ጸንቷል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።