No summary available.
ግንቦት 14 ቀን 2AAA ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልዱ ታፈሰ ይርጋ መድሕን ኪሮስ ሡልጣን Aባተማም Aመልካች፡- ወ/ሮ ዘውዲቱ ጌታቸው ቀርባለች ተጠሪ፡- ተመስገን ደሣለኝ ቀርቧል።
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዳይ የጋብቻ ውልን የሚመለከት ነው።
የግራ ቀኙ ጋብቻ በፍቺ ከፈረሰ በኋላ የቀጠለውን የንብረት ክፍፍል በተመለከተ Aመልካች ጥያቄያቸውን ለጃቢ ጠህናን ወረዳ ፍ/ቤት Aቅርበዋል ተጠሪም በመሃከላችን የጋብቻ ውል Aለ በዚህም መሰረት Aመልካችን ያገባኋት በAመት 12A.AA /መቶ ሃያ/ ብር ልከፍላት ልብስ ከዛው ከደሞዟ ላታሰብ የሕክምና ወጪ ልሸፍን Eንጂ በEኩል ባለመብት Eንድትሆን Aልተስማማሁም በማለት Aመልካች ንብረት ለመካፈል ያቀረቡትን ጥያቄ ተቃውመዋል። ጉዳዩ የቀረበለት ወረዳ ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ተመልክቶ የጋብቻ ውሉ ሕጋዊ Aይደለም በማለት Aመልካች ያቀረቡትን ጥያቄ ተቀብሎ ንብረቶቹን የግራ ቀኙን የጋራ ስለሆኑ Eኩል ይካፈሉ በማለት ወስኗል። ተጠሪ በውሣኔው ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለምE/ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት Aቅርበው ፍ/ቤቱ የወረዳ ፍ/ቤቱ ውሣኔ ስህተት የለውም በማለት የይግባኝ ቅሬታውን ውድቅ Aድርጎታል። ተጠሪ በመቀጠል ለAማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሁለተኛ ይግባኝ ያቀረቡ ሲሆን ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን ከAከራከረ በኋላ ግራ ቀኙ የንብረት ግንኙነታቸውን በተመለከተ ተጠሪ ለAመልካች በወር ከሚያገኘው ገቢ ውስጥ ለዓመት ብር 12A.AA (መቶ ሃያ) ላከፍላት ከዚህ ውጪ ልላ ንብረት ግንኙነት Eንደማይኖር መስማማታቸው ሕጉን Aይቃረንም በማለት ተጠሪ Aመልካች ሳትገባ የሰራውን ሆነ ከገባች ወዲህ ታድሷል የተባለውን ቤት Eንድትካፈል መወሰኑ ተገቢ Aይደለም በማለት የሥር ፍ/ቤትን ውሣኔ ሽሮ Aመልካች ቤቱን ልትካፈል Aይገባም በማለት ወስኗል።
የAሁኑ የሰበር Aቤቱታ የቀረበውም በዚህ ውሣኔ ላይ ነው። ይህ ችሎትም ግራ ቀኙ ባደረጉት የጋብቻ ውል ላይ ተጠሪ ለAመልካች በዓመት ብር 12A.AA (መቶ ሃያ) ላከፍላትና ከዚህ ውጪ ልላ የንብረት ግንኙነት Eንደማይኖር መስማማታቸው ሕግን Aይቃረንም መባሉን ለመመርመር Aቤቱታው ለሰበር ችሎት ቀርቦ Eንዲታይ በማድረጉ ተጠሪ ቀርበው መልሣቸውን በጽሑፍ Aቅርበዋል።ችሎቱም መዝገቡን Eንደሚከተለው መርምሯል።
ከመዝገቡ Eንደተረዳነው ግራ ቀኙ ባልና ሚስት መሆናቸው ያልተካደ ጉዳይ ነው። Aከራካሪው ነጥብ የንብረት ክፍፍል ነው። Aመልካች በጋብቻ ጊዜ የተገኘ ንብረት የግል Eስካልተባለ የጋራ ነው ሲሉ የሚከራከሩ ሲሆን ተጠሪ ደግሞ ተጋቢዎቹ የንብረት ግንኙነታቸውን በተመለከተ ላስማሙ ስለሚችሉ በዚሁ መሰረት የተስማሙና የጋብቻ ውሉም ሕግን የሚቃረን ባለመሆኑ የA/ብ/ክ/መ ጠቅላይ ፍ/ቤት ውሣኔ ስህተት የለውም ብለዋል።
የA/ብ/ክ/መ የቤተሰብ ሕግ ልክ Eንደ የፍድራሉ የቤተሰብ ሕግ ተጋቢዎቹ የንብረት ግንኙነታቸውን Aስመልክቶ ላስማሙ Eንደሚችሉ ያመለክታል። በመሆኑም የንብረት ግንኑነታቸውን በመሰላቸው መንገድ ላወስኑ ይችላሉ። ነገር ግን ስምምነቱን በሚወስኑበት ጊዜ መሰረታዊ የEኩልነት መብትን በሚጥስ መልክ ላፈፀም Aይገባውም። በሕገ- መንግሥቱ Aንቀፅ 34(1) ሴቶች በጋብቻ Aፈፃፀም በጋብቻ ዘመንና በፍቺ ግዜ Eኩል መብት Eንዳላቸው ያመለከተ ሲሆን Aንቀጽ 35/2/ም ቢሆን ሴቶች በጋብቻ ከወንዶች ጋራ Eኩል መብት Eንዳላቸው ተደንግጓል።
በመሆኑም በጋብቻ ዘመን በተፈራ ንብረት ላይ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች Eኩል መብት Eንዳላቸው መገንዘብ ይቻላል። ሆኖም ግን በተያዘው ጉዳይ ግራ ቀኙ ባደረጉት የጋብቻ ውል ተጠሪ ለAመልካች በዓመት ብር 12A.AA Eንደሚከፍላትና ከዚህ ውጭ Aመልካች በጋራ ንብረታቸው ላይ ምንም ዓይነት መብት Eንዳይኖራት ያደረጉት ስምምነት ከላይ የተጠቀሰውን የሕገመንግሥቱን የEኩልነት መብት ድንጋጌን የሚፃረር ነው።ማንኛውም ሕግ ወይንም ልማዳዊ Aሰራር ከሕገመንግሥቱ ጋር የሚቃረን ከሆነ ተፈፃሚነት Eንደልለው በሕገመንግሥቱ Aንቀጽ 9(1) ላይ ተመልክቷል።
ከዚህም ልላ Aንድ የውል ግድታ በሕግ Aግባብነት ባልተቋቋመ ጊዜ በዚህ ውል መሰረት Eንዲፈጽም ጥያቄ የቀረበለት ወገን ውሉ የማይረጋ ስለሆነ ተፈፃሚነት የለውም በማለት ይህንን ውል Aልፈጽምም ማለት Eንደሚችል በፍ/ብ/ሕ/ቁ.18A9 የተመለከተ ሲሆን Aመልካችም ከተጠሪ ጋር የተደረገው ውል ሕግን የሚፃረር ስለሆነ ተፈፃሚነት የለውም በማለት የተከራከሩ Eንደመሆኑ መጠን በዚህ ስምምነት መሰረት ላገደዱ የማይገባ ሆኖ ሣለ የAማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሥር ፍ/ቤቶችን ውሣኔ በመሻር የAመልካችን የንብረት ክፍፍል ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ
የAማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ.ቁ. 1111A ሐምል 3 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ከላይ Eንደተጠቀሰው መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
Aመልካችና ተጠሪ ንብረት ላካፈሉ ይገባል ተብሎ በጃቢ ጣህናን ወረዳ ፍ/ቤት በ14.4.99 ዓ.ም የተሰጠው ውሣኔ Eንደዚሁም የምEራብ ጎጃም ዞን ከ/ፍ/ቤት ይግባኙ Aያስቀርብም በማለት በጥር 9 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ትEዛዝ በAግባቡ ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት Aጽንተነዋል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።