No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 3A959 ታህሣሥ A1 ቀን 2AAA ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ፍስሐ ወርቅነህ ሒሩት መለሰ ተሻገር ገ/ሥላሴ ታፈሰ ይርጋ Aመልካቾች፡- 1. ወሮ ተወዳጅ ገ/ሥላሴ - ቀረቡ።
ተጠሪዎች፡-
በዚህ መዝገብ የተያዘው ጉዳይ የጀመረው በፍ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የAሁን Aመልካቾች የሟች ል/ኮ ገ/ስላሴ በሻህ ልጆች ለመሆናቸው Eንዲረጋገጥላቸው ያቀረቡትን Aቤቱታ ፍ/ቤቱ ተመልክቶ ልጅነታቸውን Aረጋግጧል። ከዚህ በኋላ Aመልካቾች የሟች ልጆች Aለመሆናቸውን ተጠሪዎች ተቃውመው ወደ ክርክሩ ገብተዋል። ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ Aይቶ በAመልካቾች Eና በሟች መካከል የልጅነት ሁኔታ መኖሩ ተረጋግጧል በማለት ቀድሞ የሰጠውን ውሣኔ Aጽንቷል። ተጠሪዎች ይህንን ውሣኔ በመቃወም ይግባኛቸውን ለፍ/ከፍተኛ ፍ/ቤት Aቅርበዋል። ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን Aከራክሮ በAመልካቾችና በሟች መካከል የልጅነት ሁኔታ የለም ሲል የሥር ፍ/ቤትን ውሣኔ ሽሯል። በዚሁ ውሣኔ ላይ Aመልካቾች ለፍ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ቢሆንም ይግባኛቸው ተቀባይነት ሣያገኝ ቀርቷል።
የAሁኑ የሰበር Aቤቱታም የቀረበው በዚህ ውሣኔ ላይ ነው።
ይህ ችሎትም Aመልካቾች የሟች ልጆች Aይደሉም መባሉ ከተሻሻለው የቤተሰብ ሕጉ ድንጋጌዎች Aኳያ Aግባብ መሆን Aለመሆኑን ለመመርመር Aቤቱታው በሰበር ችሎት Eንዲቀርብ Aድርጓል። ግራ ቀኙም ክርክራቸውን በጽሁፍ Aቅርበዋል። ችሎቱም መዝገቡን Eንደሚከተለው መርምሯል።
ከመዝገቡ ላይ Aመልካቾች የሟች ል/ኮ ገ/ስላሴ በሻህ ልጆች ለመሆናቸው የልጅነት ሁኔታ መኖሩ ተረጋግጦ ማስረጃ Eንዲሰጣቸው ጥያቄ ማቅረባቸውን ተረድተናል። ተጠሪዎች ደግሞ Aመልካቾች የሟች ልጆች Aለመሆናቸውን ተቃውመው ተከራክረዋል።
በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ Aንቀጽ 154 Eና ተከታዮቹ ሥር ልጅነት የሚረጋገጥባቸው መንገዶች ተዘርዝረዋል። ልጅነት የልደት ምስክር ወረቀት በማቅረብ፣ የልደት ምስክር ወረቀት ከልለ የልጅነት ሁኔታ መኖሩን በማረጋገጥ የልጅነት ሁኔታ ከልለ ደግሞ ተወላጅነትን በማስረዳት ማረጋገጥ Eንደሚችል ተመልክቷል። ከነዚህ ሁኔታዎች ለተያዘው ጉዳይ Aግባብነት ያለው የልጅነት ሁኔታ መኖሩን በማረጋገጥ ልጅነት የሚታወቅበት ሁኔታ ነው። በቤተሰብ ሕጉ ቁጥር 156 Aንድ ሰው የልጅነት ሁኔታ Aለው የሚባለው በማኀበረሰቡ ዘንድ የEርሱ ወይም የEርሷ ልጅ ነው Eየተባለ የሚገመት ሲሆን Eንደሆነ ተመልክቷል። ይህ ሁኔታ መኖሩን ማስረዳት ከተቻለ ፍ/ቤቱ ልጁ ነው ሲል የሕግ ግምት Eንደሚወስድና ይህንን ግምት ግን ልጅ ነው የተባለው ሰው ላሆን Eንደማይችል በማስረዳት ማፍረስ Eንደሚችል የቤተሰብ ሕጉ Aንቀጽ 157 ያመለክታል።
በተያዘው ጉዳይ በሥር ፍ/ቤቶች የተረጋገጠውን ፍሬ ነገር ስንመለከት ሟች Aመልካቾችን Eንደ ልጆቻቸው ያሳድጓቸው Eንደነበር ትምህርት ቤትም Aባት በመሆን Eንዳስመዘገቧቸው፣ በመረዳጃ Eድር ቅጽ ውስጥ ልጆች ብለው Eንዳስመዘገቧቸው፣ በሰፈርም በት/ቤትም የሟች ልጆች ሆነው Eንደሚታወቁ 233 234 ተገንዝበናል። የፍ/ከፍተኛ ፍ/ቤት የልጅነት ሁኔታ የለም ያለው Aመልካቾች በጋብቻ ውስጥ ወይም ከጋብቻ ውጪ መወለዳቸው Aልተገለፀም፣ ሟች Aመልካቾች የሟች ልጆች Eንዳልሆኑ ገልፀው የተውት ኑዛዜ Aመልካቾች Eንዲፀድቅ መጠየቃቸው ልጆች Aለመሆናቸውን ያመኑ መሆኑን ያሣያል በማለት ነው። ነገር ግን የልጅነት ሁኔታን ለማረጋገጥ ልጁ በማኀበረሰቡ ዘንድ የEርሱ ወይም የEርሷ ልጅ ነው Eየተባለ የሚገመት መሆኑን ከማረጋገጥ ባለፈ ልጁ በጋብቻ ውስጥ ወይም ከጋብቻ ውጪ የተወለደ ለመሆኑ ማስረዳት Aስፈላጊ Aይደለም። በመሆኑም ሕጉ የማይጠይቀውን ተጨማሪ ሁኔታ Aመልካቾች Aላስረዱም በሚል የተሰጠው ውሣኔ Aግባብነት የለውም።
ልላው ሟች በተውት ኑዛዜ ላይ Aመልካቾች ልጆች Aለመሆናቸውን መግለፃቸው በራሱ የልጅነት ሁኔታ መኖሩን ለማፍረስ የሚያበቃ Aይደለም።
የልጅነት ሁኔታ Aለመኖሩን ለማስረዳት በቤተሰብ ሕጉ Aንቀጽ 157/2/ መሰረት ልጅ የተባለው ሰው ልጅ ላሆን Eንደማይችል ማስረዳት ያስፈልጋል።
በመሆኑም ኑዛዜውን Aመልካቾቹ Eንዲፀድቅ መጠየቃቸው Aመልካቾች የሟች ልጆች Aይደሉም ወደሚለው መደምደሚያ Aያደርስም።
በAጠቃላይ በሥር ፍ/ቤቶች የተረጋገጠው ፍሬ ነገር Aመልካቾች የልጅነት ሁኔታ ያላቸው መሆኑ” Eያdየ ሕጉ የማይጠይቀውን ተጨማሪ ሁኔታ Aመልካቾች Aላስረዱም በማለት የልጅነት ሁኔታ የለም በሚል የተሰጠው ውሣኔ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ
የፍ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 4487 በሐምል 21 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ Eና የፍ/ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ በሚያዝያ 29 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ትEዛዝ ተሽሯል።
የፍ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 2A534 በጥር 22 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
ወጪና ኪሣራ ይቻቻሉ።