No summary available.
/መ/ቁ. 29343 ሚያዝያ 7 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ መስፍን Eቁበዮናስ ሒሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ መድህን ኪሮስ Aመልካች፡- 1. ወ/ሮ Aምሳለ ተፈራ 2. ወ/ት ልንሳ Iላላ ተጠሪ፡- ወ/ት Aበባ Aድማሱ ጠበቃ ጥጋቡ ጌጤ ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥሎ የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ ጉዳይ የተጀመረው በፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን የAሁን Aመልካቾች በተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ 1ኛ ከሳሽና ሟች Aቶ Iላላ Iብሳ በጋብቻ ሥርዓት ግድታ ውስጥ Eያሉ 2ኛዋን ከሳሽ ወልደዋል። ሟች Aቶ Iላላ Iብሳ የካቲት 29 ቀን 1995 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ ሲሆን ተከሳሽ የሟች ልጅ ናቸው። ሟች Eና 1ኛ ከሳሽ ታህሣሥ 18 ቀን 1962 ዓ.ም በAዲስ Aበባ ከተማ ተጋብተው በቂርቆስ ክ/ከተማ ቀበል A9 ቁጥር 836 በሆነ መኖሪያ ቤት Eየኖሩ በካርታ Aቶ Aክላሉ Aጥላባቸው ከተባሉ ግለሰብ የገዙትን መኖሪያ ቤት Eያከራዩ ለትዳር ጥቅም Aውለዋል። የከተማ ቦታና ትርፍ ቤት ለመንግስት ያደረገው Aዋጅ ቁጥር 47/67 ሲታወጅ ባልና ሚስቱ ተነጋግረው ለዚህ ክስ ምክንያት የሆነውን በቂርቆስ ክ/ከተማ ቀበል 09 ቁጥር 836 የሆነውን ቤት በጋራ ሀብትነት መርጠው የኪራይ ገቢ ይሰበስቡበት የነበረውን ከላይ የተገለፀውን መኖሪያ ቤት በትርፍነት ለመንግሥት Aስረክበዋል።
የ1ኛዋ ከሳሽ Eና የሟች የጋራ ሀብት የሆነውን Eንዲሁም የ2ኛዋ ከሳሽ የውርስ ድርሻ የተቋቋመበትን መኖሪያ ቤት ሟች Aቶ Iላላ Iብሳ በሞት ከተለዩበት ከየካቲት 29 ቀን 1995 ዓ.ም ጀምሮ ተከሳሽዋ በይዞታቸው ሥር Aድርገው በወከሐቸው ግለሰቦች Aማካይነት Eያከራዩ በኪራዩ ገቢ Eስካሁን በብቸኝነት ይጠቀሙበታል። ይሄው ቤት በAነስተኛው በወር ብር 3.500 ላከራይ የሚችል ሲሆን ሟች ሕይወታቸው ካለፈበት ጊዜ ጀምሮ ክስ Eስከቀረበበት ጊዜ ድረስ በብቸኝነት በመሰብሰብ ያለAግባብ የበለፀጉ ስለሆነ የ2 ዓመት ከ5 ወር ገቢው ብር 101.500 /Aንድ መቶ Aንድ ሺህ Aምስት መቶ/ ስለሚሆን የ1ኛ ከሳሽ ድርሻ ብር 50.750 የ2ኛ ከሳሽ ብር 25.375 ተከሳሽ Eንዲከፍሉና ቤቱም በሐራጅ ተሸጦ Eንድንከፋፈል ይወሰንልን በማለት ጠይቀዋል።
የከሳሾች ክስና ማስረጃ ለተከሳሽ ደርሶ በሰጡት መልስ 1ኛ ከሳሽ ከሟች ጋር በጋብቻ ተቆራኝተው በነበረ ጊዜ በካርታ የተመዘገበውን ቤት ከAቶ Aክላሉ Aጥላባቸው ገዝተው ለጋብቻ ጥቅም ሲያውሉት Eንደነበር ያቀረቡት ከሀቅ ያፈነገጠ ነው። የተጠቀሰው ቦታና ቤት Aቶ Iላላ Iብሳና Aቶ ለማ Iብሳ በጋር ገዝተውት የነበረ ሲሆን Aቶ Iላላ Iብሳ በመሬቱና በቤቱ ላይ በግላቸው ሙሉ መብት Aልነበራቸውም። ቤቱ በጋራ ሐብትነት ተመርጦ ነው በማለት ከሳሾች በክሳቸው የጠቀሱትም ሐሰት ነው። ሟች Aቶ Iላላ Iብሳ ለመንግስት ያስረከቡትን ቤት ከAቶ ለማ Iብሳ ጋር የጋራ ስለነበር የግል ነው ብሎ ለመምረጥ የሚያስችል መብት ስላልነበራቸው ቤትና መሬቱን ከማስረከብ በስተቀር ምንም ማድረግ የማይችሉ ስለነበርና ቤቱም ተከፍሎ ባላለቀ የባንክ ብድር Eዳ ተይዞ የነበረ በመሆኑ በEነዚህ ምክንያቶች ቤትና ቦታውን መንግሥት በትርፍነት ወረሰው Eንጂ ባልና ሚስቱ መክረው Aላስረከቡትም።
ጠበቃ ተስፋዬ ዘውድ ቀረቡ 223 224 በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቀበል A9 የሚገኘውና መለያ ቁጥሩ 836 የሆነው መኖሪያ ቤት ሟች Eና 1ኛ ከሳሽ ጋብቻ ከፈፀሙበት ታህሣሥ 18 ቀን 1962 ዓ.ም በፊት በ1957 ዓ.ም የተሰራና በጋብቻ ወቅትም የጋራ Eንዲሆን የፈቀዱበት ውል የልለ ስለሆነ የሟች የAቶ Iላላ Iብሳ የግል ንብረት ነው።
Aቶ ለማ Iብሳ ለረጅም ዘመን የሟች ወኪል በመሆን ንብረታቸውን ያስተዳድርላቸው የነበረ ሲሆን ሟች ሲሞቱ ተከሳሽ Aሜሪካን Aገር Eኖር ስለነበር የሟችን ቤት Eኔ Aልተረከብኩም፤ Aላከራየሁም። Aቶ ለማ Iብሳን የወከልኩት ለወደፊቱ በውርስም ሆነ በልላ ምክንያት ለማገኘው ንብረት ወኪል Eንዲሆነኝ Eንጂ የሟችን ቤት Eንዲያስተዳድርልኝ Aልወከልኩም በማለት ሙሉ መልስ በመስጠት ተከራክረዋል።
የግራ ቀኙ ክርክር በዚህ መልኩ የቀረበለትም የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ክሱን ከሰማ በኋላ የክርክሩ መሰረት የሆነው ቤት የሟች Aቶ Iላላ Iብሳና የ1ኛ ከሳሽ የጋራ ሐብት ነው ወይንስ Aይደለም?
ተከሳሽ ይህንኑ ለክሱ ምክንያት የሆነውን ቤት በወኪላቸው Aማካይነት ይዘውታል ወይ? ቤቱን በተመለከተ የተጠየቀውን ገንዘብ ተከሳሽ ለመክፈል ይገደዳሉን? የሚሉትን ጭብጦች መሥርቶ ጉዳዩን መርምሯል።
በዚህም መሰረት የመጀመሪያው” ጭብጥ በተመለከተ በቂርቆስ ክ/ከተማ ቀበል A9 ክልል የሚገኘው የመ/ቁጥር 836 የሆነው ቤት ሟችና 1ኛ ከሳሽ ከመጋባታቸው በፊት በ1957 ዓ.ም የተሰራና በሟች Aቶ Iላላ Iብሳ ስም የተመዘገበ ስለመሆኑ በተከሳሽ በኩል ማስረጃ የቀረበ ከመሆኑም በላይ ከሳሾችም በክርክር ወቅት ይህንን ያላስተባበሉ ሲሆን ሟች Aቶ Iላላ Iብሳና 1ኛ ከሳሽ ይህን ከጋብቻ በፊት የተሰራውን ቤት የጋራ የጋብቻ ንብረት ያደረጉበት የጋብቻ የውል ሰነድ የለም።
No specific laws extracted.
No topics extracted.
1ኛ ከሳሽ ክስ የቀረበበት ቤት የጋራ ንብረት ነው በማለት ያቀረቡት ልላ የመከላከያ ነጥብ ሟች Aቶ Iላላ Iብሳና 1ኛ ከሳሽ በጋብቻቸው ወቅት ያፈሩትን በካርታ የሚታወቀው ቤት በAዋጅ ቁጥር 47/67 Aንቀጽ 11/1/ መሰረት ለመንግስት Aስወርሰው /Aስረክበው/ ለAሁኑ ክርክር መሰረት የሆነው” ቤት በስምምነት መርጠው ያስቀሩት ቤቱ በAዋጁ መሰረት የጋራ ንብረት ሆኗል የሚል ነው። ነገር ግን የAዋጁ ድንጋጌ ሲታይ ቤተሰብ ወይንም ግለሰብ Aንድ ቤት Eንደሚፈቀድለት Eንጂ ይህ Aንድ ቤት ከንብረት ሕግ Aንፃር የማን ንብረት ነው የሚለውን Aይመልስም። በAጠቃላይ ከሳሽ ቤቱን በስምምነት መርጠን ይበሉ Eንጂ የግል ንብረት የሆነውን የጋራ ንብረት ለማድረግ በሕግ ተቀባይነት ያለው ማስረጃ በማቅረብ ያላስረዱ ስለሆነ 1ኛ ከሳሽ ቤቱ የጋራ ንብረት ነው በማለት ያቀረቡት ክስ ተቀባይነት የለውም ብሐል።
የኪራይ ክፍያን Aስመልክቶ በክስ የተጠየቀውን በተመለከተም ተከሳሽ Aከራይተው ሲጠቀሙ የነበረ ስለመሆኑ በማስረጃ ያልተረጋገጠ ስለሆነ ጥያቄው በAግባቡ Aልቀረበም በማለት ሳይቀበለው ቀርቷል።
በመጨረሻም 2ኛ ከሳሽ በቤቱ ላይ የውርስ ድርሻ ያላቸው መሆኑ ስለተረጋገጠ 2ኛ ከሳሽና ተከሳሽ የሚስማሙ ከሆነ ቤቱ ተገምቶ Aንዱ ለልላው የግምቱን ግማሽ በመክፈል ቤቱን Eንዲያስቀረው በዚህ መልኩ ስምምነት ካልተገኘ ቤቱ ተገምቶ በሐራጅ ተሸጦ የሽያጩን ውጤት ገንዘብ Eኩል Eኩል Eንዲካፈሉ በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
ከሳሾች በዚህ ውሣኔ ቅሬታ Aድሮባቸው የይግባኝ ቅሬታቸውን ለፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት Aቅርበው ፍ/ቤቱም በበኩሉ ግራ ቀኙን Aከራክሮ የሥር ፍ/ቤት ውሣኔ ጉድለት የልለው ነው በማለት በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/ 348/1/ መሰረት Aጽንቶታል።
የሰበር Aቤቱታው የቀረበው ይህንኑ በመቃወም ሲሆን ይህ ችሎትም Aቤቱታው ያስቀርባል በማለት ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
ምላሽ ማግኘት የሚገባውም የጉዳዩ ጭብጥ በቂርቆስ ክ/ከተማ ቀበል 08 ክልል የሚገኘውና ቁጥር 836 የሆነው ቤት የ1ኛ Aመልካችና የሟች Aቶ Iላላ Iብሳ የጋራ ሀብት ነው ወይንስ Aይደለም? የሚለው በመሆኑ ይህንኑ ጭብጥ በመያዝ Aቤቱታው ተመርምሯል።
ሟች Aቶ Iላላ Iብሳና 1ኛ Aመልካች የተጋቡት ታህሳስ 18 ቀን 1962 ዓ.ም ሲሆን ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት ደግሞ ሁለቱ ከመጋባታቸው በፊት በ1957 ዓ.ም በሟች Aቶ Iላላ Iብሳ የተሰራ ስለመሆኑ ግራ ቀኙን Aላከራከረም።
Aመልካቾች Aጥብቀው የሚከራከሩት ሟች Aቶ Iላላ Iብሳና 1ኛ Aመልካች በጋብቻ ተሳስረው Eያሉ በካርታ በAቶ Aክላሉ Aጥላባቸው ስም የተመዘገበውን ቤት ገዝተው Aከራይተው ሲጠቀሙ ቆይተው የከተማ ቦታና ትርፍ ቤትን የመንግሥት ሀብት የሚያደርገው Aዋጅ ቁጥር 47/67 ሲታወጅ ይህንኑ በጋብቻ ጊዜ የገዙትን ቤት በትርፍነት ለመንግስት Aስረክበዋል። በልላ በኩልም ሟች Aቶ Iላላ Iብሳ ከጋብቻ በፊት የነበራቸውን ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት በባንክ ብድር ተሰርቶ የነበረ ስለሆነ ብድሩ በጋብቻ ጊዜ ተከፍሎ የተጠናቀቀ ከመሆኑም በላይ ባልና ሚስቱ በAዋጅ ቁጥር 47/67 Aንቀጽ 11/1/ መሰረት Eንደ Aንድ ቤተሰብ መቆጠር Eንዳለባቸው ሕጉ ስለሚያስገድድ ምርጫቸው መሆኑን Aሳውቀው መንግስት በትርፍነት Eንዳይወርሰው በማድረግ የጋራ ሀብት Aድርገውታል በማለት ነው።
ተጠሪም በበኩላቸው በካርታ የተመዘገበውን ቤት 1ኛ Aመልካችና ሟች Aቶ Iላላ Iብሳ ስለመግዛታቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ ካለማቅረባቸውም በላይ ቤቱን ከAቶ Aክላሉ Aጥላባቸው ላይ ታህሳስ 16 ቀን 1965 ዓ.ም በተደረገ ውል የገዙት ሟች Aቶ Iላላ Iበሳና Aቶ ለማ Iብሳ ናቸው። ከAቶ Aክላሉ Aጥላባቸው ላይ የተገዛው ቤት በAንድ በኩል የ1ኛ Aመልካችና የAቶ Iላላ Iብሳ በልላ በኩል የAቶ ለማ Iብሳ ንብረት የነበረ ሲሆን ይህን ቤት በትርፍነት ለመንግስት Aስረክበዋል ቢባል Eንኳ በሟች Aቶ Iላላ Iብሳ ስም የተመዘገበውንና ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት ግን የጋራ ንብረት ስለመደረጉ በAመልካቾች ማስረጃ Aልተረጋገጠም በማለት ተከራክረዋል።
በካርታ የተመዘገበው ቤት ሟች Aቶ Iላላ Iብሳና 1ኛ Aመልካች በጋብቻ ተሳስረው በነበረ ጊዜ የተገዛ ስለመሆኑ ተጠሪ Aምነው ነገር ግን የተገዛው 1ኛ Aመልካች ከሟች ባለቤታቸው ጋር በመሆን ሳይሆን ሟች Aቶ Iላላ Iብሳና Aቶ ለማ Iብሳ የገዙት ነው በማለት ክርክር ቢያቀርቡም የከተማ ቦታና ትርፍ ቤትን የመንግስት ሀብት ለማድረግ በወጣው Aዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት ይህንኑ ቤት ለመንግስት በትርፍነት ያስረከቡት 1ኛ Aመልካችና ሟች ባለቤታቸው Eንደነበሩ በAስረጂነት የቀረበው የመረካከቢያ ቅጽ የሚያረጋግጥ ከመሆኑም በላይ ቤቱን በትርፍነት ያስረከቡት ሟች ብቻ ናቸው ቢባል Eንኳን ይህ ሁኔታ የAቶ ለማ Iብሳን የጋራ ባለሀብትነት ላያረጋግጥ የማይችል በመሆኑ ይህ ችሎት በካርታ የተመዘገበው የ1ኛ Aመልካችና የሟች ባለቤታቸው የነበረ መሆኑን ለማረጋገጥ ችሐል።
በልላ በኩልም Aንድ ሰው ወይንም Aንድ ቤተሰብ ከAንድ መኖሪያ ቤት በላይ በባለቤትነት መያዝ Eንደማይችል በተጠቀሰው Aዋጅ ቁጥር 47/67 Aንቀጽ 11/1/ ላይ የተመለከተ ሲሆን ይህ Aዋጅ በወጣበት ጊዜ 1ኛ Aመልካችና ሟች ባለቤታቸው Aቶ Iላላ Iብሳ በጋብቻ ተሳስረው ይኖሩ የነበረ Eንደመሆኑ መጠን ከAዋጁ Aኳያ Eንደ Aንድ ቤተሰብ መቆጠራቸው ስለማይቀር በጋብቻ ጊዜ ካፈሩት ቤትና ከጋብቻ በፊት ከተሰራውና የሟች የግል ንብረት ከነበረው ቤት መካከል Aንዱን መርጠው በትርፍነት ለመንግሥት ማስረከብ ግድ ስለሚሆን በዚሁ መሰረት በጋብቻ ጊዜ ያፈሩትን ቤት መርጠው ማስረከባቸው ልላውን በሟች ስም ተመዝግቦ የሚገኘውንና ለዚህ ክርክር ምክንያት የሆነውን ቤት የጋራ ማድረጋቸውን Eንደሚያስገነዝብ መረዳት Aያዳግትም።
በEርግጥ የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በፍርዱ ላይ Eንዳሰፈረው ከተጋቢዎች መሀል Aንዱ የግሉ የሆነውን ቤት የጋብቻው የጋራ ንብረት ማድረግ ቢፈልግ በቀድሞውም ሆነ በAዲሱ የቤተሰብ ሕግ መሰረት የዚህ ዓይነት ስምምነት ወይንም የጋብቻ ውል ላኖር Eንደሚገባ መደንገጉን 227 228 መገንዘብ ቢቻልም 1ኛ Aመልካችም ሟች ባለቤታቸው በጋብቻ ጊዜ ያፈሩትን ቤት በትርፍነት ለመንግሥት ማስረከባቸው Eስከተረጋገጠ ድረስ የሟች የግል ንብረት የነበረውንና ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ቤት ከAዋጁ መንፈስ Aኳያ ያለምንም ልላ ተጨማሪ ስምምነት ይህ ሁኔታ በEራሱ ቤቱን የጋራ ማድረጋቸውን ስለሚያስገነዝብ የሥር ፍ/ቤቶች ለክሱ ምክንያት የሆነው ይሄው ቤት የ1ኛ Aመልካችና የሟች ባለቤታቸው Aይደለም በማለት የሰጡት ውሣኔ ከAዋጁ ጋር ያልተጣጣመና የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ
23027 በየካቲት 9 ቀን 1999 ዓ.ም የከፍተኛ ፍ/ቤትን ውሣኔ በማጽናት የሰጠው ትEዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
በቂርቆስ ክ/ከተማ ቀበል 09 ክልል የሚገኘው የቤት ቁጥር 836 የሆነው ቤት የ1ኛ Aመልካችና የሟች ባለቤታቸው Aቶ Iላላ Iብሳ የጋራ ንብረት ነው ተብሎ ተወስኗል።
ከላይ የተጠቀሰውና የ1ኛ Aመልካችና የሟች Aቶ Iላላ Iብሳ ቤት ተገምቶ በ1ኛ Aመልካችና የሟች ወራሾች በሆኑት 2ኛ Aመልካችና በተጠሪ መካከል ስምምነት ከተገኘ Aንዱ ለልላው የግምቱን ግማሽ በመክፈል ቤቱን Eንዲያስቀረው ተወስኗል። በዚህ መልኩ መስማማት ካልቻሉ ቤቱ ተገምቶ በሐራጅ Eንዲሸጥና የሽያጩን ገንዘብ ግማሹን 1ኛ Aመልካች Eንዲወስዱ ግማሹን ደግሞ 2ኛ Aመልካችና ተጠሪ Eኩል Eንዲካፈሉ ተወስኗል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።