No summary available.
ጥቅምት 19 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ፍስሐ ወርቅነህ ሐጎስ ወልዱ ሒሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- Aቶ ርEሶም ገ/መድኀን - ጠበቃ Aበበ ኃይል ተጠሪ፡- ወ/ሮ Aልማዝ ጊላሚካኤል - ቀረቡ።
መዝገቡን መርምረን ቀጥሎ የተመለከተውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር Aቤቱታ ላቀርብ የቻለው Aመልካችና ተጠሪ ጋብቻቸው ጸንቶ ባለበት ጊዜ ተሸጧል የተባለን መኪና ዋጋው ለትዳር ጥቅም ስለመዋሉ በማስረጃ Aልተረጋገጠም በማለት የሽያጩን ገንዘብ ግማሹን Aመልካች ለተጠሪ ይክፈሉ በማለት የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት Aለበት ሲሉ ተጠሪ ቅሬታ በማቅረባቸው ነው።
የጉዳዩ Aመጣጥም ሲታይ በግራ ቀኙ መካከል የነበረው ጋብቻ በፍቺ ከፈረሰ በኋላ ተጠሪ የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በሰጠው ትEዛዝ መሰረት ባቀረቡት የንብረት ዝርዝር ከቤት በወጣሁ ጊዜ የግል Aልባሳቶቼን ይዤ ስላልወጣሁ Aመልካች Eነዚህን Aልባሳቶቼን Eንዲሰጠኝ፣ የሰ/ቁ 3-38794 የሆነው መኪና ከጋብቻ በኃላ የተገዛና የጋራ ንብረት ስለሆነ የመኪናውን ዋጋ ግማሽ ድርሻዬን Eንዲሰጠኝ Eንደዚሁም በጋብቻ ወቅት ያፈራናቸው የቤት Eቃዎች ተቆጥረው የሚገኙ ስለሆነ ግማሽ ድርሻዬን Eንዲሰጠኝ ይወሰንልኝ በማለት ጠይቀዋል።
በፍድራል መ/ደ/ፍ/ቤት ተጠሪ የነበሩት የAሁን Aመልካች በበኩላቸው በሰጡት መልስ Aመልካችና ተጠሪ ጋብቻቸውን የፈጸሙት ግንቦት 27 ቀን 1987 ዓ.ም. Eንደነበረና ጋብቻቸውን በፈጸሙ ጊዜም ተጠሪ ከጋብቻ በፊት የነበራቸው Aንድ መኪና Eና Aንድ ቤት በጋብቻ ውሉ የግላቸው ሆኖ Eንደተመዘገበና የቀድሞው መኪና ተሸጦም Aቤቱታ የቀረበበትን የሰ/ቁ 3- 38794 መኪና ተጠሪ Eንደገዙና ይህም መኪና በመካከላቸው ክርክር ከመጀመሩ በፊት በመስከረም 8 ቀን 1991 ዓ.ም በተፃፈ ውል Eንደተሸጠና ገንዘቡም ለምን ጥቅም Eንደዋለ በመዘርዘር በAጠቃላይም ተጠሪ ለAመልካች የሚያካፍሉት ምንም ንብረት Eንደልለ በመጥቀስ መልስ ሰጥተዋል።
የንብረት ክርክሩ በዚሁ መልኩ የቀረበለትም የፍድራል መ/ደ/ፍ/ቤት ክርክሩን መርምሮ Aመልካች የጠየቋቸው የግል Aልባሳትና የቤት ቁሳቁሶችን በተመለከተ ተጠሪ ክደው ያልተከራከሩ ስለሆነ የግል Aልባሳቶቻቸውን Eንዲያስረክቧቸው የቤቱ ቁሳቁሶቹንም ከተቻለ በዓይነት Eንዲከፋፈሉ ካልተቻለም ተገምተው በግምቱ መሰረት Eንዲከፋፈሉ በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
መኪናውን በተመለከተ ከጋብቻ በፊት ተጠሪ የነበራቸው መኪና በጋብቻ ውሉ የግል ተደርጎ የነበረ ቢሆንም ይህንኑ መኪና በጋብቻ ጊዜ ሸጠው ልላ መኪና ሲገዙ ይሄው መኪና የግል ሀብታቸው Eንዲሆን በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ Aንቀጽ 58/2/ መሰረት ተጠሪ በፍ/ቤት ያላስመዘገቡ ስለሆነ በAንቀጽ 62/2/ መሰረትም የጋራ ሀብት ስለሚሆን መኪናው ተሸጧል የተባለበትን ብር 24A ሺህ ግማሹን ብር 12A ሺህ ከነወለዱ ተጠሪ ለAመልካች ላከፍሉ ይገባል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
የሥር ተጠሪ የAሁን Aመልካች በዚሁ ውሣኔ ቅሬታ Aድሮባቸው የይግባኝ ቅሬታቸውን ለፍድራል ከ/ፍ/ቤት Aቅርበው ፍ/ቤትም በበኩሉ ግራ ቀኙን Aከራከሮ መ/ሰጭ ከቤት በወጣሁ ጊዜ የግል Aልባሳቶቼን ይዤ ስላልወጣሁ ይግባኝ ባይ ላሰጠኝ ይገባል በማለት ያቀረቡትን Aቤቱታ በተመለከተ የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በይ/ባይ በግልጽ ያልተካደ ስለሆነ የግል Aልባሳቶቻውን ላያስረክብ ይገባል ተብሎ ቢወሰንም ይ/ባይ ለመልስ ሰጪ ላያስረክቡት የሚገባ ምንም ንብረት Eንደልለ በግልጽ ከመካዳቸውም በላይ በዚህ ረገድ መ/ሰጭ የቆጠሩት ማስረጃ ይ/ባይ የመሃላ ቃላቸውን Eንዲያወርዱ በመጠየቅ ሲሆን በሥር ፍ/ቤት ክርክር ሲደረግ ይ/ባይ የመሐላ ቃላቸውን Eንዲያወርዱ ባለመደረጉ በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት መሐላ Eንዲያወርዱ ተደርጎ መ/ሰጭ የግል Aልባሳታቸውን ጥለው Eንዳልሄዱ ያረጋገጡ ስለሆነ በዚህ ሁኔታ የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ይ/ባይ የመ/ሰጭን የግል Aልባሳቶችን ላያስረክቡ ይገባል በማለት የሰጠው ውሣኔ በAግባቡ Aይደለም በማለት ሽሯል።
የሰ/ቁ. 3-38794 ¾J’¨<” መኪና በተመለከተ ይግባኝ ባይ የሚያቀርቡት ክርክር መኪናው የተሸጠው ግራ ቀኙ ከመፋታታቸው ከ11 ወራት በፊት Aካባቢ በመሆኑ ከፊሉ ገንዘብ በጋራ ለጋራ ችግራቸው Eንዳዋሉትና በቀሪው ገንዘብም ብዛት ያለው ወርቅ ገዝተው በመ/ሰጭ Aክስት ቤት ማስቀመጣቸውን ቢሆንም ይህንን ለማስረዳት ያቀረቧቸው ምስክሮች ቀርበው Eንደተሰሙት ይግባኝ ባይና መ/ሰጭ ተጣልተው በሽማግልዎች ፊት Eርቅ በፈጸሙበት ጊዜ የተገዛበትን ዋጋና ግራሙን የማያውቁት ወርቅ በመ/ሰጭ Aክስት ቤት ሲያስቀምጡ ማየታቸውን Eንጂ ለመ/ሰጭ Aክስት በAደራ ተሰጥቷል የተባለው ወርቅ uመኪናው ሽያጭ ገቢ የተገዛ ስለመሆኑ ካለመሆኑም በላይ ወርቁ የመ/ሰጭ Aክስት ቤት ስለመቀመጡም ቢሆን በምስክርነት ማቅረብ ይገባቸው የነበረው የመ/ሰጭ Aክስትን ነበር የሚል ትችት በውሣኔው ላይ Aስፍሮ የመኪናው ሽያጭ ገንዘብ ለግራ ቀኙ ጥቅም መዋሉን ይግባኝ ባይ ተቀባይነት ያለው ማስረጃ Aላቀረቡም በማለት ይግባኙን ባለመቀበል የፍድራል መ/ደ/ፍ/ቤት” ውሣኔ Aጽንቷል።
No topics extracted.
የሰበር Aቤቱታውም የቀረበው ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ሲሆን ይህ ሰበር ችሎት የቀረበውን Aቤቱታ መርምሮ Aመልካችና ተጠሪ በፍቺ ከመለያየታቸው በፊት በAንድነት Eየኖሩ ተሸጠ የተባለው መኪና የሽያጭ ገንዘብ ለግራ ቀኙ መጠቀሚያ ስለመዋሉ በማስረጃ Aልተረጋገጠም ተብሎ የሽያጩን ገንዘብ ግማሹን Aመልካች ለተጠሪ ላከፍሉ ይገባል ተብሎ በሥር ፍ/ቤቶች የተሰጠው ውሣኔ ተጠሪ ባሉበት ተጣርቶ ላወሰን Eንደሚገባው በማመኑ ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙን Aከራክሯል። የሰበር Aቤቱታውም ከሕጉ Aኳያ Eንደሚከተለው ተመርምሯል።
Aመልካችና ተጠሪ ጋብቻቸውን የፈጸሙት ግንቦት 27 ቀን 1987 ዓ.ም. Eንደሆነ ይሄው ጋብቻቸው በፍቺ የፈረሰው ደግሞ ኀዳር 7 ቀን 1992 ዓ.ም. Eንደሆነና Eንደዚሁም ለክርክሩ መነሻ ምክንያት የሆነው የሰ/ቁ. 3- 38794 የሆነው መኪና የተሸጠው መስከረም 1 ቀን 1991 ዓ.ም. መሆኑ Eነዚህ ፍሬነገሮች ግራ ቀኙን Aላከራከ[ም።
የተጠቀሰው መኪና ጋብቻው በፍቺ ከመፍረሱ 1 ዓመት በፊት ጋብቻው ጸንቶ ባለበት ጊዜ መሸጡና ጋብቻው በፍቺ በፈረሰ ጊዜ የመኪናው ሽያጭ ገንዘብ በመሉ ወይንም በከፊል Aመልካች Eጅ Eንደሚገኝ በማስረጃ ካልተረጋገጠ ጠቅላላ የመኪና ሽያጭ ገንዘቡ በጋብቻ ጊዜ ለጋራ የትዳር ጥቅም Eንደዋለ የባልና ሚስትን ሃብት ስለማጣራት በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ ከተደነገገው ከቁጥር 85-93 ካሉት ድንጋጌዎች Aንጻር የሕግ ግምት መውሰድ ይቻላል።
የዚህ የሕግ ግምት ተጠቃሚ የሆነ ወገንም ንብረቱ በጋብቻ ጊዜ የተሸጠ መሆኑን ካስረዳ በቂ ሲሆን ልላው ወገን ደግሞ ጋብቻው በፍቺ በፈረሰ ጊዜ ከንብረቱ የሽያጭ ገንዘብ በሙሉ ወይንም በከፊል የሚገኝ መሆኑን ካስረዳ የሽያጩ ገንዘብ በጋብቻ ጊዜ ለጋራ ጥቅም ውሐል የሚለውን የሕግ ግምት Eንዳፈረሰ ይቆጠራል።
Aመልካች ለክርክሩ መነሻ ምክንያት የሆነው መኪና በጋብቻ ጊዜ የተሸጠ መሆኑን በማስረዳት የሽያጩ ገንዘብ ለጋራ የትዳር ጥቅም Eንደዋለ ሕጉ በወሰደው ግምት ተጠቃሚ ሆነዋል። በልላ በኩልም ተጠሪ ጋብቻው በፈረሰ ጊዜ የመኪናው ሽያጭ ገንዘብ በሙሉ ወይንም በከፊል በAመልካች Eጅ Eንደሚገኝ ያላስረዱ በመሆኑ የሕግ ግምቱን ማፍረስ Aልቻሉም።
በፍድራል ከ/ፍ/ቤት ክርክር ሲደረግ ይ/ባይ ከመኪናው ሽያጭ ገንዘብ ላይ ብር 115,000 /Aንድ መቶ Aሥራ Aምስት ሺህ/ የሚያወጣ ወርቅ ለመ/ሰጭ ገዝቼ ወርቁም መ/ሰጭ Aክስት ቤት Eንዲቀመጥ የተደረገ ስለመሆኑ የሚያውቁልኝ ምስክሮች Eንዳሉ ጠቅሼ Eነዚህ ምስክሮች በፍድራል መ/ደ/ፍ/ቤት ላሰማልኝ ሲገባ Aልተሰሙልኝም የሚል ክርክር በማቅረባቸው ፍ/ቤቱ Eነዚህን ምስክሮች Aስቀርቦ ቢሰማም ወርቅ ተገዝቷል የሚለው የይግባኝ ባይ ክርክር ለትዳር ጥቅም ውሐል በሚለው የሕግ ግምት ውስጥ የሚጠቃለል ሆኖ ሳለ ማስረጃ መስማት ሳያስፈልገው በሕግ ግምቱ ላይ ተመስርቶ ውሣኔ መስጠት ሲገባው የይግባኝ ባይን የተሳሳተ የክርክር መስመር ተከትሎ ማስረጃ በመስማት ከመኪናው የሽያጭ ገንዘብ ላይ ይ/ባይ ለመ/ሰጭ ወርቅ ስለመግዛታቸው በማስረጃ Aልተረጋገጠም በማለት የመኪናውን ሽያጭ ገንዘብ ግማሹን ይግባኝ ባይ ለመ/ሰጭ Eንዲከፍሉ ውሣኔ መስጠቱ Eንደዚሁም የፍድራል መ/ደ/ፍ/ቤት ይህንኑ የሕግ ግምት ሳያገናዝብ ውሣኔ መስጠቱ በAግባቡ ሆኖ Aልተገኘም።
ው ሣ ኔ
የፍድራል መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. A6189 በሚያዝያ 28 ቀን 1995 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ Eንደዚሁም የፍድራል ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 2A828 በጥቅምት 30 ቀን 1999 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የሰ/ቁ. 3-38794 የሆነው መኪና Aመልካች የሸጡት በግራ ቀኙ መካከል የነበረው ጋብቻ ጸንቶ ባለበት ጊዜ ስለሆነና ገንዘቡም ለጋራ የትዳር ጥቅም Eንደዋለ ከላይ ከተጠቀሱት ድንጋጌዎች Aኳያ የሕግ ግምት ስለሚወሰድና ተጠሪም ይህንኑ የሕግ ግምት ያላፈረሱ ስለሆነ የሽያጩን ግማሽ ገንዘብ Aመልካች ለተጠሪ ላከፍሉ Aይገባም በማለት ተወስኗል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።