No summary available.
ኀዳር 1A ቀን 2AAA ዓ.ም.
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ፍስሐ ወርቅነህ ሐጎስ ወልዱ ሒሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- ወ/ሮ Aስካለ ለማ - ቀረቡ።
ተጠሪ፡- ሣህለ ሚካኤል በዛብህ - ቀረቡ።
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዳይ ግራ ቀኙ ጋብቻ በፍቺ ከፈረሰ በኋላ በንብረት ክፍፍል ላይ ያደረጉት ክርክር ታይቶ በተሰጠው ውሣኔ ላይ የቀረበ Aቤቱታ ነው።
ተጠሪ ለፍ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረቡት Aቤቱታ በ82 ካ.ሜ. ላይ የተሰራ ቪላ ቤት ከጋብቻ በፊት የተሰራ የግላቸው መሆኑንና ልሎችን ንብረቶች ዘርዝረው በማቅረብ ለመካፈል ጠይቀዋል።
Aመልካች ደግሞ የግል ቤቴን ሸጬ ባገኘሁት ገንዘብ ቤቱን ከማኀበሩ ተረክበን Aፍርሰን Aሁን ያለውን ይዘት Eንዲኖረው Aድርገን ስለሰራነው የግሉ Aይደለም፤ Eዳው ከጋብቻ በኋላ ነው የተከፈለው Eንዲሁም ከልሎቹ ንብረቶቹ ውስጥ በውርስ ያገኘኋቸው የግል ንብረቶቼ ይገኙበታል በማለት ተከራክረዋል።
ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ ከጋብቻ በኋላ ተሰሩ የተባሉት ስራዎች ተገምተው ብር 82‚293 (ሰማኒያ ሁለት ሺ ሁለት መቶ ዘጠና ሶስት) ስለሆኑ የዚህን ዋጋ ግማሽ ተጠሪ ለAመልካች ከፍለው ቤቱን ያስቀሩ በማለትና በልሎቹም ንብረቶች የክፍፍል ውሣኔ ሰጥቷል።
ጉዳዩን በይግባኝ ያየው የፍ/ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የስር ውሣኔን Aጽንቶታል።
የAሁን የሰበር Aቤቱታ የቀረበውም በዚህ ውሣኔ ላይ ነው። ይህ ችሎትም ተጠሪ ግምት ከፍለው ቤቱን Eንዲያስቀሩ የመወሰኑን Aግባብነት ለመመርመር Aቤቱታው ለሰበር ችሎት ቀርቦ Eንዲታይ Aድርጓል። ግራ ቀኙም ክርክራቸውን በጽሁፍ Aቅርበዋል። ችሎቱም መዝገቡን Eንደሚከተለው መርምሯል።
ከመዝገቡ ሂደት Eንደተረዳነው ተጠሪ ግምት ከፍለው ቤቱን Eንዲያስቀሩ የተወሰነው ቤቱ ከጋብቻ በፊት የተገኘ የተጠሪ የግል ንብረት ነው በማለት ነው። በመሆኑም ክርክር የተነሳበት ቤት የተጋቢዎቹ የጋራ ንብረት ነው ወይስ የተጠሪ የግል ሃብት የሚለው ላታይ የሚገባው ነው።
ባልና ሚስት ጋብቻቸውን በሚፈጽሙበት ጊዜ በየግል የነበሯቸው ንብረቶች ወይም ከጋብቻ በኋላ በውርስ ወይም በስጦታ በየግላቸው ያገኗቸው ንብረቶች የግል ንብረቶቻቸው ሆነው Eንደሚቀሩ የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ ቁጥር 57 ያመለክታል። Aንድ ንብረት ከግል Eና ከጋራ ሃብት ተቀላቅሎ የተገኘ ከሆነ ግን ንብረቱ የጋራ ወይም የግል ተብሎ Eንደሚቆጠር የሕጉ ድንጋጌ በግልጽ Aያመለክትም። በመሆኑም ይህ ሁኔታ ባጋጠመ ጊዜ ድንጋጌውን ከAላማው Aኳያ መተርጎም Aስፈላጊ ይሆናል። ከጋብቻ በፊት ¾ነበረ ንብረት የጋራ Eንዳይሆን የተፈለገበት ምክንያት ጋብቻ ንብረት ለማግኘት በሚል ሃሣብ ብቻ Eንዳይቋቋምና Eንዳይፈርስ ለመከላከል ሲባል ነው። በልላ Aነጋገር ምንም ንብረት ያልነበረው ሰው ንብረት ያለውን ሰው በማግባት ጋብቻ ሲፈርስ ያላፈራውን ንብረት የሚካፈልበት ሁኔታ ማመቻቸት ለፍትሕ Eና ለሕላና ተቃራኒ ነው ተብሎ ስለሚታመን ነው። ነገር ግን ለAንድ ንብረት መገኘት ተጋቢዎቹ ያደረጉት AስተዋጽO ተመርምሮ Eንደነገሩ ሁኔታ የግል ወይም የጋራ ላባል ይገባል። ይህንንም ለመወሰን በንጽጽር ሲታይ Aብዛኛው መዋጮ የተደረገው Ÿግል ነው ወይስ ከጋራ የሚለውን ከግምት ማስገባቱ ተገቢ ይሆናል። ንብረቱ በAብዛኛው ከጋራ ሃብት መዋጮ የተገኘ ከሆነና የግል 208 209 ንብረቱ ትንሽ ከሆነ ንብረቱ የጋራ ሆኖ መቆጠሩ ፍትሐዊ ይሆናል። የንብረቱ የተወሰነ ክፍል ከጋብቻ በፊት ተገኝቶ Eንኳን ቢሆን Aነስተኛ የሆነው ድርሻ ከግል ሃብት ከንብረቱ ላይ በመቀላቀሉ ብቻ ንብረቱ የግል Eንዲሆን ማድረጉ ፍትሐዊ Aይሆንም።
ከዚህ ተነስተን ወደተያዘው ጉዳይ ስንመለስ በEርግጥ ቤቱ የተጀመረው ከጋብቻ በፊት ቢሆንም ቤቱ ተሰርቶ የተጠናቀቀው ከጋብቻ በኋላ Eና ለቤቱ መስሪያ የተወሰደው ብድርም ከጋብቻ በኋላ መከፈሉን መዝገቡ ያስረዳል። የስር ፍርድ ቤት ይህን ካረጋገጠ በኋላ ከጋብቻ በፊት የተሰራው ሥራ ምን ያሕል Eንደሆነ ሳያጣራ Eንዲሁም ከጋብቻ በኋላ የተሰራውንም ቢሆንም በገበያ ዋጋ ሳይሆን የመሃንዲስ ግምት ብቻ በማስቀረብ የዚህን ግምት ግማሽ ብቻ Aመልካች ለተጠሪ ከፍለው Eንዲያስቀሩ መወሰኑ Aግባብ ሆኖ Aላገኘነውም። ቤቱ ተጀምሮ ከማለቁ በፊት ጋብቻው Eንደተፈፀመና የተጠናቀቀውም ከጋብቻ በኋላ መሆኑን፣ ለቤቱ መስሪያ የተወሰደው ብድርም ቢሆን ከጋብቻ በኋላ መከፈሉ Aብዛኛው ወጪ ከጋራ ሃብት የወጣ መሆኑን ያመለክታል። በEርግጥ በንብረቱ ላይ የተቀላቀለውን የግል ሃብት በተቀላቀለው መጠን የግሉ የሆነው ተጋቢ ላወስድ ይገባል። ይህም በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ ቁጥር 86/1/ ስር ከተመለከተው ድንጋጌ ጋር የሚስማማ ነው። በመሆኑም ቤቱ የተጀመረው ከጋብቻ በፊት በመሆኑ ብቻ ቤቱ የተጠሪ የግል ሃብት ነው በማለት የስር ፍርድ ቤት የደረሰበት መደምደሚያ ስህተት ሆኖ Aግኝተነዋል።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ
የፍ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 913 በግንቦት 29 ቀን 1996 ዓ.ም ክርክር የተነሳበትን ቤት በተመለከተ የሰጠው የውሣኔ ክፍል ብቻ ተሽሯል።
የክርክር ምክንያት የሆነው ቤት የግራ ቀኙ የጋራ ሃብት ነው።
ከጋብቻ በፊት የተሰራው ሥራ ተገምቶ ግምቱ ለተጠሪ ይከፈል። ቤቱን ከተቻለ ግራ ቀኙ በዓይነት ይካፈሉ፣ ካልተቻለ Aንዱ ለAንዱ የቤቱን ¾ገበያ ዋጋ ግምት ከፍሎ ያስቀር፣ በዚህ የማይስማሙ ከሆነ ቤቱ ተገምቶ በሃራጅ ተሸጦ የሽያጩን ገንዘብ Eኩል ይካፈሉ።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት።
ነ/ዓ