No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 25AA5 ኀዳር 3 ቀን 2AAA ዓ.ም.
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ፍስሐ ወርቅነህ ሐጎስ ወልዱ ሒሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- መኮንን በላቸው ቀርበ።
ተጠሪ፡- ወ/ሮ Aለሚቱ Aደም ቀረበች።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለሰበር Aቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዳይ የጋብቻን በፍቺ መፍረስ ተከትሎ የተነሳውን የንብረት ክፍፍል ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ በተጀመረበት የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተከራካሪ ወገኖች በየበኩላቸው ያቀረቡት የንብረት ጥያቄ Eና በዚህ ረገድ ያነሱት የመከራከሪያ ነጥብ በዝርዝር ታይተዋል። ክርክር ከተደረገባቸው ንብረቶች መካከል ዋነኛው በወረዳ 19 ቀበል 55 ክልል ውስጥ ይገኛል የተባለው በቁጥር 318 የሚታወቀው መኖሪያ ቤት ነው። በተደረገው ክርክር ተጠሪ የዚህን ቤት ብቸኛ ባለቤት Eንደሆነች የገለጸች ስትሆን፣ Aመልካች ደግሞ ቤቱ ጋብቻው ጸንቶ በነበረበት ጊዜ የተሰራ /የተፈራ/ የጋራ ንብረት ነው በማለት ተከራክሮAል።
የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም ሆነ የዚህን ፍ/ቤት ውሣኔ በይግባኝ የሰማው የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ደግሞ ቤቱ ከጋብቻው በፊት ተጀምሮ የነበረ ነው የሚል ምክንያት በመስጠት የተጠሪ የግል ሃብት መሆን Aለበት።
Aመልካች ለቤቱ ያወጣው ገንዘብ ታስቦ ይመለስለት በማለት ወስነዋል። የሰበር Aቤቱታው የቀረበው በዚሁ ላይ ነው።
Eኛም Aመልካች ግንቦት 21 ቀን 1998 ዓ.ም. በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን ቅሬታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን Aስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል።
Aቤቱታው በሰበር ችሎት Eንዲታይ የተወሰነው Aመልካች ለቤቱ ስራ የበኩሉን AስተዋጽO ማድረጉ በዝርዝር ተገልጾ ሳለ የጋራ ባለሃብት ላሆን Aይችልም የመባሉን Aግባብነት ለመመርመር ነው። በዚሁ መሰረትም ይህን ነጥብ ከስር ጀምሮ ከተደረገው ክርክር፣ Aቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ Eና ከሕጉ ጋር Aገናዝበን መርምረናል።
መዝገቡን በAጠቃላይ መርምረን Eንደተገነዘብነው ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቤት ያረፈበት መሬት ጋብቻው ከመፈጸሙ በፊት ተጠሪ በማኀበር ከተመራች በኋላ የቤት ስራው መስከረም 29 ቀን 1979 ዓ.ም. መጀመሩን፣ ጋብቻው ታሕሣሥ 26 ቀን 79 ዓ.ም. በመፈጸሙን፣ ቤቱ ሥራው Aልቆ ለማኀበሩ Aባላት የተከፋፈለው በጥቅምት ወር 198A ዓ.ም. መሆኑን፣ ቤቱ ተስፋፍቶ የተሰራውና ቤትም የሆነው ጋብቻው ከተፈፀመ በኋላ Eንደሆነ፣ ለቤቱ ማሰሪያ ከባንክ በብድር ገንዘብ የወሰደችው ተጠሪ ብትሆንም፣ ከ1981 ዓ.ም. ጀምሮ ጋብቻው በፍቺ Eስከፈረሰበት 93 ዓ.ም. ድረስ በAመልካች በኩል ሲከፈል መቆየቱን የስር ፍ/ቤቶች በማስረጃ Aረጋግጠዋል። በልላ በኩል ደግሞ ፍ/ቤቶቹ በፍሬ ነገር ረገድ ይህን ቢያረጋግጡም የቤቱ ስራ የተጀመረው ከጋብቻው በፊት ማለትም መስከረም 29 ቀን 1979 ዓ.ም. /ሦስት ወር የማይመዝን ጊዜ/ ነው የሚል ምክንያት በመስጠት ብቻ የተጠሪ የግል ሃብት ነው የሚለው መደምደሚያ ላይ ደርሰዋል።
በበኩላችን Eንደምናየው Aከራካሪው ቤት በEርግጥም ቤት የሆነው Aመልካች Eና ተጠሪ ጋብቻቸውን ከፈጸሙ በኋላ Eንደሆነ የሥር ፍ/ቤቶች በቀረበላቸው ማስረጃ በሚገባ Aረጋግጠዋል። ከሁሉ በላይ ደግሞ ለቤቱ መሥሪያ በሚል ከባንክ በብድር የተወሰደውን ገንዘብ ሲከፈል የቆየው በAመልካች በኩል Eንደሆነ Eና ይህም የሆነው ጋብቻው ፀንቶ በነበረበት ወቅት ነው። የባልና ሚስት የጋራ ሃብት የሚባለው ባልና ሚስቱ ከግል ንብረታቸውና ከግል ወይም ከጋራ ንብረታቸው የሚያገኘውን ገቢዎች ሁሉ Eንደሚያጠቃልል በተሻሻለው የቤተሰብ ሕ/Aዋጅ ቁ. 213/92/ Aንቀጽ 62/1/ ተመልክቶAል።
Aንደኛው ተጋቢ ሃብቱ የግሉ ስለመሆኑ ካላስረዳም ንብረቱ በAንደኛው ተጋቢ 198 199 ስም ብቻ የተመዘገበም ቢሆን የባልና ሚስቱ የጋራ ሃብት ነው ተብሎ በሕግ Aንደሚገመት በዚሁ የቤተሰብ ሕግ Aንቀጽ 63/1/ ተደንግጎAል። ወደያዝነው ጉዳይ ስንመለስ Aከራካሪው ቤት ያረፈበት ቦታ /መሬት/ ከጋብቻው በፊት ተጠሪ በማኀበር የተመራችው ከመሆኑ Eና ጋብቻው ላፈጸም ጥቂት ጊዜ ሲቀረው ሥራው ከመጀመሩ በስተቀር በተጠሪ የግል ጥረት Eና ሃብት ብቻ የተገነባ ነው የሚባል Aይደለም። ከሁሉ በላይ ደግሞ ጋብቻው በተፈጸመበት ጊዜ ወይም ከዚያ በፊት ቤቱ የተጠሪ የግል ሃብት ነው ተብሎ በጋብቻ ውል ተለይቶ Aልተመለከተም። Eንደምንመለከተው Eንግዲህ ቤቱ በማንኛውም መለኪያ የተጠሪ የግል ሃብት ነው ለማለት የሚቻል Aይደለም። በመሆኑም በዚህ ረገድ የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ Aግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
No topics extracted.
በዚህ ጉዳይ የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 2141 ታሕሣሥ 7 ቀን 1997 ዓ.ም. የሰጠው Eና የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 36A1A ሚያዝያ 18 ቀን 1998 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348/1/ ተሻሽለዋል።
Aከራካሪው ቤት የAመልካች Eና የተጠሪ የጋራ ሃብት ነው። ሁለቱም Eኩል የመካፈል መብት Aላቸው ብለናል።
ወጪና ኪሣራ በተመለከተ ግራ ቀኝ ወገኖች የየራሳቸውን ይቻሉ።
በዚህ ሰበር ችሎት ውሣኔ መሰረት ይፈጸም ዘንድ ለስር ፍ/ቤቶች ይፃፍ። መዝገቡ ይመለስ።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት።
ነ/ዓ
ጥር 29 ቀን 2AAA ዓ.ም ዳኞች፡- Aብዱልቃድር መሐመድ ተገኔ ጌታነህ መስፍን Eቁበዮናስ Aብዱራሂም Aህመድ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- ወ/ሮ መሰረት ፍስሐ ቀርባለች።
ተጠሪ፡- Aቶ ቀልቤሣ Aበው ቀርቧል።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር Aቤቱታ ላቀርብ የቻለው Aመልካች ሰኔ 6 ቀን 1998 ዓ.ም. ጽፈው ባቀረቡት ማመልከቻ መነሻነት ነው።
የጉዳዩ የስር Aመጣጥ Aመልካች የስር ከሣሽ በመሆን በተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ ጋብቻ መሥርተው ሲኖሩ ከየካቲት 1 ቀን 1996 ዓ.ም. ጀምሮ ከተጠሪ ጋር የነበራቸው ጋብቻ በፍቺ መፍረሱንና የጋራ ንብረት ክፍፍል Eንዲደረግ ባመለከቱት መሰረት የንብረት ዝርዝር Aቅርበው ከዚህ ዝርዝር ውስጥ በጋራ የሰሩትን ቤት Eንዲካፈሉና ተጠሪ ቤቱን Aከራይተው ስለሚጠቀሙና ኪራዩም በወር ብር 350 (ሦስት መቶ ሃምሳ) ስለሆነ የ1A ዓመት ኪራይ ብር 36AAA (ሰላሳ ስድስት ሺ) Aመልካች ስላገኙ ቤቱ ተገምቶ የግምቱን ግማሽ በመክፈል ልጆቼን Eንዳሳድግበት በማለት ጠይቀዋል። ክሱ የቀረበለት የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም ተጠሪ ቤቱ የተሰራበትን ቦታ ከAመልካች ጋር በጋብቻ ከመተሣሰራቸው በፊት ያገኙት ስለሆነ Aመልካች የቦታው ይዞታ ተካፋይ የሚሆኑበት ምክንያት የለም። ሆኖም ቤቱ የተሰራው ግራ ቀኙ ጋብቻ ከመሰረቱ በኋላ ስለሆነ በባለሙያ ተገምቶ የቤቱን ግማሽ ተጠሪ ለAመልካች ይክፈሉ። የኪራይ ገቢን በተመለከተ Aመልካች በማስረጃ 200 201 Aስደግፈው ባለማቅረባቸው ተቀባይነት የለውም በማለት ወስኗል። ይህ ውሣኔ በፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ፀንቷል።
Aመልካች የሰበር Aቤቱታ ያቀረቡት በዚህ መነሻነት ሲሆን ይህ ፍርድ ቤት Aቤቱታውን መርምሮ መልስ ሰጪን ካስቀረበ በኋላ ግራ ቀኙ” Aከራክሯል። ክርክሩንም ከሕጉ ጋር በማገናዘብ መርምሯል። በዚህም መሰረት የስር ፍርድ ቤት ያለAመልካች ስምምነት የቤቱን ግምት Aጋማሽ ከተጠሪ ይቀበሉ በማለት መወሰኑ ባግባቡ መሆን Aለመሆኑን ይህ ፍርድ ቤት Eንደሚከተለው መርምሯል።
Aመልካች የቤቱን ግምት ግማሽ ተቀብለው Eንዲወጡ የተወሰነውን በተመለከተ የሥር ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ተጠሪ የቦታውን ይዞታ ያገኙት ከAመልካች ጋር በጋብቻ ከመተሳሰራቸው በፊት በመሆኑ በዚህ ይዞታ ላይ Aመልካች ተካፋይ የሚሆኑበት ምንም ምክንያት የለም የሚል መሆኑን ተረድተናል። ከፍርድ ቤቱ ውሣኔ ለመረዳት የተቻለው ቤትና ቦታውን ነጣጥሎ ማየቱን ሲሆን ፍርድ ቤቱ ይህን ለማድረግ ያስቻለውን ድንጋጌ Aልጠቀሰም።
በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1131 ላይ Eንደተመለከተው በAመልካችና በተጠሪ መካከል ቤቱን በተመለከተ የጋራ ባለሀብትነት መብት በፍርድ ቤቱ ውሣኔ የተመሰረተ ከመሆኑ Aኳያ Aመልካች በቤቱ ላይ ያገኙት የጋራ ባለሀብትነት መብት የመሬቱ ይዞታንም ስለሚያጠቃልል መብታቸው በይዞታውም ላይ የተዘረጋ ይሆናል። ምክንያቱም በዚህ ድንጋጌ መሰረት በቤት ላይ የተገኙ መብቶች Eንደ Aንድ ሙሉ ክፍል መሬቱንም Eንደሚያጠቃልሉና በተከታዩ Aንቀጽ 1132 ላይ Eንደተመለከተው ቤቱም የመሬቱ Aንድ Aቋም ሆኖ የሚቆጠር በመሆኑ ነው። በተጨማሪም ከላይ በተጠቀሰው የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1131 መሰረት የቤቱ የጋራ ባለሀብትነትና ቤቱ የቆመበት መሬት የተጠሪ የግል ባለይዞታነት በተመለከተ ግራ ቀኙ Aስቀድሞ ያደረጉት ውል ባለመኖሩ ይህ በልKበት ሁኔታ የሥር ፍርድ ቤቶች ተጠሪ ከጋብቻው በፊት የመሬቱ ባለይዞታ ነበር በማለት መወሰናቸው Aግባብ ካለመሆኑም በላይ መሰረታዊ የሕግ ስህተትም ነው።
በልላም በኩል የጋራ ሀብትን ለማከፋፈል Aመቺ በማይሆንበት ጊዜ ግራ ቀኙ ንብረቱን Aንዳቸው Eንዲያስቀሩ መስማማት Eንደሚቻል፣ ለመስማማት ያልተቻለ ቢሆን ግን ንብረቱ ተሸጦ ገንዘቡን Eንደሚከፋፈሉ፣ በንብረቱ Aሻሻጥ ካልተስማሙ ደግሞ ንብረቱ በAንደኛው ጠያቂነት በጨረታ Eንደሚሸጥ የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ Aንቀጽ 92 በግልጽ ደንግጓል። ከዚህ ውጪ ተከራካሪ ወገኖች በንብረቱ Aከፋፈል ካልተስማሙ በስተቀር ፍርድ ቤቶች በራሳቸው ተነሣሽነት ንብረቱን ለAንደኛው ተከራካሪ ወገን Eንዲሰጥ የማድረግ ሥልጣን Eንደልላቸው ከድንጋጌው ለመረዳት ተችሐል። ከዚህ Aኳያ የሥር ፍርድ ቤቶች ሁለቱም ተከራካሪ ወገኖች ቤቱ ለAንዳችን ብቻ ይገባል በማለት Eየተከራከሩ ባሉበት ሁኔታ ተጠሪ ቤቱን Eንዲያስቀር በማለት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ
የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 33271 የካቲት 1A ቀን 1997 ዓ.ም. Eንዲሁም የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 38782 መጋቢት 27 ቀን 1998 ዓ.ም. ቤቱ ለተጠሪ ይገባል በማለት የሰ×D†¨< ውd’@ዎች ተሽረዋል፤ ይፃፍ።
የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ግራ ቀኙ ቤቱን በዓይነት መካፈል የሚችሉ ከሆነ ”Ç=ካፈሉ፣ መካፈል የማይችሉ ከሆነ Aንዱ ለልላው ግምቱን ሰጥቶ ቤቱን Eንዲያስቀር፣ በዚህ ካልተሰማሙ ቤቱ በሐራጅ ተሸጦ ገንዘቡን Eንዲካፈሉ Áደ`ግ ዘንድ ታዟል፤ ይፃፍ።