No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 23A21 ሐምል 12 ቀን 1999 ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ Aሰግድ ጋሻው ተሻገር ገ/ሥላሴ Aብድራሂም Aህመድ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- ወ/ሮ Aበባወርቅ ጌታነህ - ጠበቃ Aቻምየለህ ተፈሪ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ዋጋዬ ኃይል - Aልቀረቡም።
መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥሎ የተመለከተው ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር Aቤቱታ ላቀርብ የቻለው Aመልካች የሟች Aቶ Aማረ ይልማ ሚስት ናቸው ተብሎ በፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ በፍድራል ጠ/ፍ/ቤት ተሽሮ ሚስት Aይደሉም ተብሎ በመወሰኑ ነው።
ጉዳዩ የተጀመረው በፍድራል መ/ደ/ፍ/ቤት ሲሆን የAሁን Aመልካች የሆኑት ባቀረቡት Aቤቱታ የሟች Aቶ Aማረ ይልማ ሚስትነቴ ይረጋገጥልኝ በማለት Aመልክተው ፍ/ቤቱም የAመልካችን ምስክሮች ሰምቶ በሰኔ 24 ቀን 1995 ዓ.ም. በዋለው ችሎት Aመልካች የሟች Aቶ Aማረ ይልማ ሚስት ናቸው በማለት ውሣኔ የሰጠ ሲሆን ከዚህ በኋላም የAሁን ተጠሪ ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም በሞግዚት Aድራጊያቸው በወጣት ወንድወሰን Aማረ ስም Aቤቱታ Aቅርበዋል።
የAቤቱታውም ይዘት በAመልካች ወ/ሮ Aበባወርቅ ጌታነህና በሟች Aቶ Aማረ ይልማ የነበረው ጋብቻ የቤተዘመድ ጉባኤ በሰጠው ውሣኔ Eና ፍ/ቤቱም በሐምል 23 ቀን 1976 ዓ.ም በሰጠው ትEዛዝ መፍረሱ የተረጋገጠ ስለሆነና Aመልካቿም ከዚህ ጊዜ በኋላ ከሟች ጋር በትዳር ያልኖሩ መሆናቸው ሟች ነዋሪ ከሆኑበት ቀበል ለባንክ በተፃፈ ደብዳቤ የተገለጸ በመሆኑ Aመልካች ሚስት ሳይሆኑ ሚስት ናቸው ተብሎ የተሰጠው ውሣኔ ሞግዚት የሆንኩለትን የወጣት ወንድወሰን Aማረን መብት የሚነካ በመሆኑ ፍ/ቤቱ የሰጠው ውሣኔ ይሰረዝልኝ የሚል ነው።
የተጠሪ መቃወሚያም ለAመልካች ደርሶ በሰጡት መልስ ከሟች ጋር የነበራቸው ጋብቻ በፍቺ ፈርሶ Eንደነበር ሳይክዱ ከፍቺው በኋላ ንብረት ሳይከፋፈሉ ትዳራቸውን ቀጥለው Eንደነበር ከፍቺው በኋላ በደንቡ መሰረት ጋብቻ Aልተፈጸመም ቢባል Eንኳ ጋብቻ መኖሩን በሁኔታ ማስረዳት Eንደሚቻል የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ የሚፈቅድ በመሆኑ ከፍቺ በኋላም Eንደ ባልና ሚስት መኖራቸውን በምስክሮች ማስረዳት ስለሚቻል ከፍቺ በኋላ ጋብቻ Aልተፈጸመም በማለት በተቃዋሚ የቀረበውን መቃወሚያ ውድቅ በማድረግ ፍ/ቤቱ ውሣኔውን Eንዲያፀናው በማለት ተከራክረዋል።
የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም በግራ ቀኙ በኩል የተቆጠሩትን ምስክሮችን ከሰማ በኋላ በAመልካችና በሟች መካከል የትዳር ሁኔታ ስለመኖሩ በAመልካች ምስክሮች Eንዳልተረጋገጠ በውሣኔው ላይ Aስፍሮ ይልቁንም በAመልካች ልጅ በAቶ ዮናስ Aማረ ጥያቄ Aመልካችና ሟች Aቶ Aማረ ይልማ በነዋሪነት ከተመዘገቡበት ቀበል በሶስት ምስክሮች ተረጋግጦ ለIትዮጵያ ንግድ ባንክ የተፃፈው ደብዳቤ ሟች ከAመልካች ጋር የነበራቸው ትዳር በፍቺ ከፈረሰ በኋላ Eስከ Eለተሞታቸው ትዳር Eንዳልነበራቸው የሚያስገነዝብ ስለሆነ ጋብቻ ስለመፈጸሙ የትዳር ሁኔታ መኖርን በማስረዳት ፍ/ቤቱ የሕግ ግምት ላወስድ Eንደሚችል በቤተሰብ ሕግ ቁጥር 97/1/ ላይ የተደነገገ ሲሆን ይህ ግምት በበቂ ማስረጃ ላፈርስ Eንደሚችል በዚሁ Aንቀጽ 97/2/ ላይ ስለተመለከተና በAመልካችና በሟች መካከል የትዳር ሁኔታ ስለመኖሩ Aስቀድሞ የተሰጠው ውሣኔ በበቂ ማስረጃ የተስተባበለ ስለሆነ ቀደም ሲል Aመልካች የሟች ሚስት ናቸው ተብሎ የተሰጠው ውሣኔ ተሰርዟል በማለት ፍርድ ሰጥቷል።
ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተውም የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ግራ ቀኙን Aከራክሮ ይግባኝ ባይና /Aመልካች/ ሟች Aማረ ይልማ በ1966 ዓ.ም.
ተጋብተው በ1976 ዓ.ም. ጋብቻው ከፈረሰ በኋላ ለAራት ወራት ተለያይተው ኖረው መልስ ሰጪ ታርቀው Eንደነበርና ጋብቻው ፈርሶ ከነበረ በኋላም 180 181 የንብረት ክፍፍል ተደርጎ Eንዳልነበረ በAመልካች ምስክሮች ተረጋግጧል በማለት በውሣኔው ላይ Aስፍሮ Aመልካችና ሟች መታረቃቸው ከተረጋገጠ የሚኖረውን ውጤት በተመለከተ የተፋቱ ባልና ሚስት ግንኙነታቸውን ለማደስ ቢፈልጉ Eንደገና መጋባት Aለባቸው ወይንስ በEርቅ ስምምነት ወደነበሩበት ይመለሳሉ የሚለውን የቤተሰብ ሕጉ ምላሽ Eንደማይሰጥና ነገር ግን በሃገራችን ባሕል መሰረት የተፋቱ ባልና ሚስት ከፍቺ በኋላ ሲታረቁ ድጋሚ ጋብቻ ሲፈጽሙ Eንደማይስተዋሉና የEርቅ ስምምነቱ በEራሱ Eንደ ባልና ሚስት ለመኖር ሃሣብ ያላቸው መሆኑን የሚያስገነዝብ ሲሆን በተመሳሳይም Aመልካችና ሟች በፍቺ ከተለያዩ በኋላ መታረቃቸውን Eንደ ባልና ሚስት ሆነው በጋብቻ የመኖር ውጤት ያለው መሆኑን የሚያስገነዝብ ከመሆኑም በላይ ከፍቺውም በኋላ ንብረት ያልተከፋፈሉ ስለሆነና የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ጋብቻ የለም በማለት የሰጠው ውሣኔ በAግባቡ Aይደለም በማለት ሽሯል።
በዚሁ ውሣኔ ቅር የተሰኙትም የAሁን ተጠሪ የይግባኝ ቅሬታቸውን ለፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት Aቅርበው ፍ/ቤቱም በበኩሉ ግራ ቀኙን Aከራክሮ Aመልካች ከሟች ጋር የነበራቸው ጋብቻ በፍቺ ከፈረሰ በኋላ የሟች ሚስት ነበርኩ የሚሉት Aዲስ ጋብቻ ከሟች ጋር ፈጽመው ወይንም ጋብቻው ስለመፈጸሙ የትዳር ሁኔታ መኖሩን Aስረዳለሁ በማለት ሳይሆን ጋብቻው ከፈረሰ በኋላ ታርቀን Aብረን ኖረናል በማለት ስለሆነ መታረቅም ሆነ Aብሮ መኖር ጋብቻን Eንደመፈጸም Aያስቆጥርም የሚል ትችት Aስፍሮ የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሣኔ በመሻር Aመልካች የሟች ሚስት Aይደሉም በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
No topics extracted.
የሰበር Aቤቱታም ለዚህ ሰበር ችሎት ላቀርብ የቻለው ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ሲሆን ችሎቱ የቀረበውን Aቤቱታ መርምሮ ጋብቻው የፈረሰው በፍቺ ወይንስ በሞት የሚለው ነጥብ ለሰበር ችሎት ቀርቦ መጣራት Eንደሚገባው በማጤኑ ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙን Aከራክሯል። ተጠሪም በበኩላቸው የፍድራል ጠ/ፍ/ቤት ውሣኔ የሚነቀፍ Aለመሆኑን በመዘርዘር Aቤቱታው ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
በAጠቃላይ የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን ምላሽ ማግኘት የሚገባው የሕግ ነጥብ በAመልካችና በሟች Aቶ Aማረ ይልማ መካከል የነበረው ጋብቻ በ1976 ዓ.ም. በፍቺ ከፈረሰ በኋላ ሟች Eስከሞቱበት 1995 ዓ.ም. ድረስ በመካከላቸው በድጋሚ ጋብቻ ተፈጥሯል ወይንስ Aልተፈጠረም የሚለው በመሆኑ ይህንኑ የሕግ ጭብጥ በመያዝ Aቤቱታው Eንደሚከተለው ተመርምሯል።
Aመልካችና ሟች Aቶ Aማረ ይልማ በ1966 ዓ.ም. ተጋብተው በ1976 ዓ.ም. ጋብቻ በፍቺ የፈረሰ መሆኑን ግራ ቀኙ Aልተካካዱበትም። በመካከላቸው የነበረው ጋብቻ በ1976 ዓ.ም. በፍቺ ከፈረሰ በኋላ ብዙም ሳይቆዩ ከAራት ወራት በኋላ ተመልሰው ታርቀው Aብረው መኖር Eንደጀመሩ በፍድራል መ/ደ/ፍ/ቤት ክርክር ሲደረግ በAመልካች ምስክሮች ተረጋግጧል።
በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ Aንቀጽ 94 መሰረት ጋብቻ መኖሩን ማስረዳት የሚቻለው በጋብቻ የምስክር ወረቀት መሆኑ የተመለከተ ሲሆን የምስክር ወረቀቱ በልለ ጊዜ የትዳር ሁኔታ መኖርን በማስረዳት ጋብቻ Eንዳለ ማረጋገጥ Eንደሚቻል በዚሁ የቤተሰብ ሕግ Aንቀጽ 96 Eና 97 ላይ ተመልክቷል።
በልላ በኩልም የተፋቱ ባልና ሚስት በሚታረቁበት ጊዜ በድጋሚ ጋብቻ መፈጸም የሚገባቸው ስለመሆኑ በቤተሰብ ሕጉ ላይ Aልተመለከተም።
በEርግጥ ጋብቻ በፍቺ ከፈረሰ በኋላ በድጋሚ መጋባት Aዲስ ጋብቻ ከመመሥረት የተለየ ስለማይሆን ድጋሚ ጋብቻ መመሥረትን በተመለከተ በሕግ መደንገግ Aስፈላጊ ላሆን Aይችልም የሚል ክርክር ላያስነሳ Eንደሚችል ቢታመንም በተያዘው ጉዳይ Aመልካችና ሟች ከ1A ዓመት የጋብቻ ጊዜ በኋላ በ1976 ዓ.ም. ተፋተው ብዙም ሳይቆይ ከAራት ወራት በኋላ ሟች Eስከሞቱበት 1995 ዓ.ም. ድረስ Aብረው Eንደኖሩ በAመልካች ምስክሮች የተነገረው ሲታይ Eራሳቸውን Eንደ ባልና ሚስት Eንደሚቆጥሩና ኀብረተሰቡም ባልና ሚስት ናቸው በማለት የተቀበላቸው መሆኑን የሚያሳይና ይህም 182 183 በቤተሰብ ሕግ Aንቀጽ 96 መሰረት በመካከላቸው የትዳር ሁኔታ መኖሩን የሚያስገነዝብ ሆኖ ተገኝቷል።
በመካከላቸው የትዳር ሁኔታ መኖሩ ከተረጋገጠ ደግሞ ጋብቻ መፈጸሙን በAንቀጽ 97/1/ መሰረት የሕግ ግምት /Legal presumption/ መውሰድ የሚቻል ሲሆን ይህንን የሕግ ግምት ማፍረስ የሚቻለው በAንቀጽ 97/2/ መሰረት ይህንን በሚክደው ወገን Aስተማማኝ ማስረጃ በሚቀርብ ጊዜ ነው።
በዚህ ረገድ በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ክርክር ሲደረግ Aመልካችና ሟች Aቶ Aማረ ይልማ ሲኖሩበት ከነበረው የቀበል Aስተዳደር ለIትዮጵያ ንግድ ባንክ በተፃፈ ደብዳቤ ጋብቻው በፍቺ ከፈረሰ በኋላ ሟች ትዳር ያልነበራቸው መሆኑ የተገለጸ ቢሆንም ይህ ማስረጃ ሕጉ Eንደሚጠይቀው የሕግ ግምቱን ለማፍረስ Aስተማማኝ ማስረጃ ሆኖ Aልተገኘም።
ው ሣ ኔ
32637 በሐምል 28 ቀን 1997 የሰጠው ውሣኔ ጸንቷል።
በAመልካች ወ/ሮ Aበባወርቅ ጌታነህና በሟች Aቶ Aማረ ይልማ መካከል የትዳር ሁኔታ መኖሩ ስለተረጋገጠ Aመልካች የሟች ሚስት ናቸው ተብሎ ተወስኗል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቷል።