No summary available.
ህዳር 24 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ፍስሐ ወርቅነህ ሐጐስ ወልዱ ሒሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- የኪራይ ቤቶች ኤጀንሲ - Aልቀረበም ተጠሪ፡- Aቶ ካሣ ግዛው መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥሎ የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር Aቤቱታ ላቀርብ የቻለው በተጠሪ በኩል ጥፋት መፈጸሙን Aመልካች ያላስረዳ ሰለሆነ በክስ የተጠየቀውን ገንዘብ ተጠሪ ላከፍል Aይገባም በማለት በበታች ፍ/ቤቶች በመወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት Aመልካች ቅሬታ በማቅረቡ ነው።
የጉዳዩ Aመጣጥም ሲታይ Aመልካች በፍድራል መ/ደ/ፍ/ቤት በተጠሪ ላይ ባቀረበው ክስ ተከሳሽ በድርጅታችን በመካኒክነት ተቀጥሮ በመሥራት ላይ Eንዳለ የዋጋ ግምታቸው ብር 1178.05 (Aንድ ሺህ Aንድ መቶ ሰባ ስምንት ብር ከAምስት ሣንቲም) የሆኑ የመኪና መለዋወጫዎችን በመኪና ላይ ለመግጠም ተረክቦ ያልገጠመ ከመሆኑም በላይ ጠፍቶብኛል በማለት ወደ ንብረት ክፍል ገቢ ሳያደርግ የቀረ ስለሆነ ተከሳሽ Eነዚህን የተከረባቸውን መለዋወጫ Eቃዎች መልሶ Eንዲያስረክብ ወይንም የዋጋ ግምታቸውን Eንዲከፍል ይወሰንልን በማለት ጠይቋል።
የከሳሽ ክስና ማስረጃም ለተከሳሽ ደርሶ በሰጠው መልስ የመኪና መለዋወጫ Eቃዎችን መረከቡን ሳይክድ የሥራ መደቡ የተበላሹ የከሳሽ መኪናዎችን መጠገን Eንደሆነና ጥገናውም የሚከናወነው በመደበኛ የሥራ 140 141 ሰዓት Eንደሆነ በሥራ መውጪያ ላይም Eንደማንኛውም ሰራተኛ ተፈትሾ Eንደሚወጣ ገልፆ ንብረቱ ላጠፋ የቻለው በጥበቃ ሰራተኞች ቸልተኝነት ስለሆነ ክሱ ከበቂ ኪሳራ ጋር ላሰረዝ ይገባል በማለት ተከራክሯል።
የግራ ቀኙ ክርክር በዚህ መልኩ የቀረበለትም የፍድራል መ/ደ/ፍ/ቤት ክርክሩን ከቀረበው ማስረጃ Aኳያ ተመልክቶ ተከሳሽ የተረከባቸውን የመለዋወጫ Eቃዎች Eስከ መቼ ድረስ ተሽከርካሪዎች ላይ መግጠም Eንዳለበት ወይም በምን ያህል ጊዜ ወደ ጥገና ክፍል መመለስ Eንዳለበት የተመለከተ ነገር ስለልለና ተከሳሽም የተረከባቸውን ንብረቶች ከሥራ ሰዓት ውጭ የመጠበቅ ኃላፊነት የልለበት ከመሆኑም ልላ ንብረቶቹን Eንዲያስረክብም ሆነ የዋጋ ግምታቸውን ለመክፈል Aይገደድም በማለት ክሱን ሳይቀበለው ቀርቷል።
ከሳሽ በዚህ ውሳኔ ቅሬታ Aድሮበት የይግባኝ ቅሬታውን ለፍድራል ከ/ፍ/ቤት ቢያቀርብም ፍ/ቤቱ በበኩሉ ግራ ቀኙን Aከራክሮ ይግባኙን ባለመቀበል የሥር ፍ/ቤትን ውሣኔ Aጽንቷል።
የሰበር Aቤቱታውም የቀረበው ይህንኑ በመቃወም ሲሆን ይህ ሰበር ችሎት Aቤቱታውን መርመሮ ተጠሪ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን መከረቡና በመኪናዎች ላይም Aለመገጠሙ ተረጋግጦ Eያለ በክስ የተጠየቀውን ገንዘብ ላከፍል Aይገባም ተብሎ መወሰኑ ለሰበር ቀርቦ መጣራት Eንዳለበት በማመኑ ተጠሪን ጠርቷል።
ሆኖም ተጠሪ በጋዜጣ ተጠርቶ ያልቀረበ ስለሆነ በAመልካች ክርክር ላይ በመመሥረት የሰበር Aቤቱታው Eንደሚከተለው ተመርምሯል።
ይህም ችሎት የሰበር Aቤቱታውን Eንደሚከተለው መርምሯል።
ላፈታ የሚገባው የጉዳዩ ጭብጥ ተጠሪ ከAመልካች የተረከባቸውን የመለዋወጫ Eቃዎች በዓይነት ለማስረከብ ወይንም የዋጋ ግምታቸውን ለመክፈል ይገደዳል ወይስ Aይገደድም የሚለው ሆኖ ተገኝቷል።
ተጠሪ ለክርክሩ ምክንያት የሆኑትን የመለዋወጫ Eቃዎች ከAመልካች ላይ መረከረቡን ሳይክድ ነገር ግን ላጠፉ የቻሉት በመ/ቤቱ የጥበቃ ሰራተኞች ጥፋት መሆኑን ገልፆ በኃላፊነት ላጠየቅ Eንደማይችል ተከራክሯል።
የፍድራል መ/ደ/ፍ/ቤት ተጠሪ በክስ የተጠየቀውን ገንዘብ ላከፍል Aይገባም ወደሚል ድምዳሜ ለመድረስ የቻለው የተረከባቸውን የተሽከርካሪ የመለዋወጫ Eቃዎች በምን ያህል ጊዜ ውስጥ ተሽከርካሪዎች ላይ መግጠም Eንዳለበት ወይም በምን ያህል ጊዜ ወደ ጥገና ክፍል መመለስ Eንዳለበት የተመለከተ ነገር ካለመኖሩም በላይ ተጠሪ የተረከባቸውን ንብረቶች ከሥራ ሰዓት ውጭ የመጠበቅ ግድታ ስለልለበትና ንብረቶቹ በሥራ ሰዓት የጠፉ ስለመሆኑም Aመልካች ያላስረዳ በመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2027፣ 2029 Eና 2031 መሰረት ተጠሪ ጥፋት የፈጸመ ስለመሆኑ በAመልካች ማስረጃ ስላልተረጋገጠ ኃላፊ Aይሆንም በማለት ነው።
ይሁንና ተጠሪ ከAመልካች ጋር በፈጠረው የሥራ ውል መነሻነት ለክሱ መነሻ የሆኑትን የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን ስለመረከቡ በAመልካች ማስረጃ የተረጋገጠ ከመሆኑም በላይ በተጠሪም Aልተካደም።
ተጠሪ Eነዚህን ለክርክሩ ምክንያት የሆኑትን የመኪና መለዋወጫዎች ከAመልካች ከተረከበ በኋላ በመኪና ላይ Eስከሚገጥምበት ጊዜ ድረስ በንብረቶቹ ላይ ለሚደርስ ማናቸውም ጉዳት፣ ብልሽት ወይንም መጥፋት በኃላፊነት ተጠያቂ ላሆን ስለሚችል ይህ ችግር Eንዳይከሰት ተጠሪ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ Eንደሚጠበቅበት ይታመናል። ተጠሪ ይህንን ጥንቃቄ ማድረግ ባያስፈልገው ኖሮ ቀድሞውንም ቢሆን Eቃዎችን ፈርሞ መረከብ ባላስፈለገው ነበር።
No topics extracted.
በልላ በኩልም ተጠሪ ፈርሞ የተከረባቸውን Eነዚህን የመኪና መለዋወጫ Eቃዎች Eንዳይጠፉ፣ Eንዳይሰረቁም ሆነ ልላ ጉዳት Eንዳይደርስባቸው ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ የሚጠበቅበት በሥራ ሰዓት Eንጂ ከሥራ ሰዓት ውጭ Eንዳልሆነም ይታመናል።
142 143 ሆኖም ንብረቶቹ በሥራ ሰዓት ሳይሆን ከሥራ ሰዓት ውጭ የጠፉ ስለመሆኑ የማስረዳቱ ሸክም የEራሱ የተጠሪ Eንጂ የAመልካች ላሆን የማይችል ሲሆን ተጠሪም በዚህ ረገድ ያቀረበው ማስረጃ የለም።
ተጠሪ ይህንን የማስረዳት ሸክሙን ካልተወጣ ንብረቱ በEራሱ ቁጥጥር ሥር Eያለ መጥፉቱን የሚያሳይና በተጠቀሰው የፍ/ብ/ሕ/ቁ/ 2027 መሰረት ቢያንስ በቸልተኝነት ጥፋት መፈጸሙን የሚያረጋግጥ ነው።
ስለሆነም የፍድራል መ/ደ/ፍ/ቤት ተጠሪ ንብረቶቹ ከሥራ ሰዓት ውጭ የጠፉ ስለመሆኑ ባላስረዳበት ሁኔታ የማስረዳት ሸክሙን ወደ Aመልካች በማዞር ንብረቶቹ በሥራ ሰዓት የጠፉ መሆኑን በማስረዳት ተጠሪ ጥፋት መፈጸሙን Aላረጋገጠም በማለት ክሱን ሳይቀበል መቅረቱ Eንደዚሁም ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይህንኑ ስህተት ሳያርም መቅረቱ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል።
የፍድራል መ/ደ/ፍ/ቤት በመ. ህዳር 1 ቀን 1997 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔና የፍድራል ከ/ፍ/ቤት በመ/ ጥቅምት 27 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/348(1) መሰረት ተሽሯል።
ተጠሪ ጥፋት መፈጸሙ የተረጋገጠ ስለሆነ በክስ የተጠየቀውን ብር 1178.05 (Aንድ ሺህ Aንድ መቶ ሰባ ስምንት ከዜሮ Aምስት ሣንቲም) ክስ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ተከፍሎ Eስካለቀ ድረስ ከሚታሰብ 9% (ዘጠኝ በመቶ) ወለድ ጋር ለAመልካች Eንዲከፍል ተወስኗል።
በዚህ ውሳኔ መሰረት Eንዲያስፈጽም ግልባጩ ለፍድራል መ/ደ/ፍ/ቤት ይተላለፍ።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሳራ ይቻቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።