No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 2875A ኀዳር 24 ቀን 2AAA ዓ.ም.
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ፍስሐ ወርቅነህ ሐጎስ ወልዱ ሒሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- የIትዮጵያ ጉምሩክ ባለሥልጣን - ነ/ፈጅ ዝናቡ ታደሰ ተጠሪ፡- የIትዮጵያ ንግድ ባንክ - ነ/ፈጅ ዘውዱ ዓላ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር Aቤቱታ ላቀርብ የቻለው ተጠሪ በAመልካችና በሥር 1ኛ ተከሣሽ ላይ በክስ የጠየቀውን ገንዘብ ተከሳሾች ባልተነጣጠለ ኃላፊነት ላከፍሉ ይገባል በማለት የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ውሣኔ በመስጠቱና ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተውም የፍድራል ከ/ፍ/ቤት ይህንኑ ውሣኔ በማጽናቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት Aመልካች ቅሬታ በማቅረቡ ነው።
የጉዳዩ Aነሳስም ባጭሩ ሲታይ ተጠሪ በAመልካችና በሥር 1ኛ ተከሣሽ ላይ ባቀረበው ክስ 1ኛ ተከሣሽ ከባንክ ጋር ባደረጉት ስምምነት ኤል-ሲ ተከፍቶላቸው ከውጭ Eቃ Eንዲገባላቸው የተደረገ ሲሆን ነገር ግን ባንኩ ሳይጽፍላቸውና ሳይወከሉ በባንኩ ስም ወይም ትEዛዝ የመጣውን Eቃ በሕገ ወጥ መንገድ ከጉምሩክ ወስደዋል። በመሆኑም ክስ ለቀረበበት ገንዘብ ብር 395‚738.59 (ሶስት መቶ ዘጠና Aምስት ሺ ሰባት መቶ ሰላሣ Aምስት ብር ከሃምሣ ዘጠኝ) ተጠያቂ ናቸው። Eንዲሁም ሁለተኛ ተከሣሽ (የጉምሩክ ባለሥልጣን) በባንኩ ባለቤትነት የመጣውን Eቃ ባለመብት ላልሆነው Aንደኛ ተከሣሽ በAዋጅ ቁጥር 6A/89 Aንቀጽ 2A/1/ Eና በጉምሩክ ባለሥልጣን የወጣውን የEቃ Aወጣጥ ማንዋል በመጣስ በመልቀቁ ኃላፊነት ያለበት ስለሆነ ክስ የቀረበበትን ገንዘብ በAንድነትና በነጠላ Eንዲከፍሉ ይወሰንልኝ በማለት ጠይቋል።
የከሳሽ ክስና ማስረጃም ለተከሳሾች ደርሶ የየበኩላቸውን የመከላከያ መልስ ያቀረቡ ሲሆን 2ኛ ተከሣሽ የAሁን Aመልካች በሰጠው መልስ በAዋጅ ቁጥር 6A/89 Aንቀጽ 2A/1/ የተዘረዘሩትን ዶክመንቶች የማቅረብ ግድታ የተጣለበት Aስመጪ የተባለው ወገን ነው። Aስመጪው ጉምሩክ Eነዚህን ዶክመንቶች ሲጠይቀው የማቅረብ ግድታ Aለበት ማለትም ጉምሩክ Eነዚህን ዶክመንቶች የማየት ግድታ ተጥሎበታል። ወይም Eነዚህን ዶክመንቶች የሚሰጡት ወገኖች ካልፈቀዱ በስተቀር ባለንብረቶቹ Aይስተናገዱም ማለት Aይደለም ብሐል።
የIትዮጵያ ንግድ ባንክ የገባው Eቃ ባለቤት Eኔ ነኝ በማለት የከሰሰ ቢሆንም በቀረቡት ማስረጃዎች ዶክመንቶቹ በሙሉ የሚያስረዱት የEቃው ባለቤት 1ኛ ተከሣሽ መሆናቸውን ነው። በመሆኑም Aንደኛ ተከሣሽ Eቃው ወደ ጉምሩክ መጋዘን ሲገባ ባሉት ዶክመንቶች ቀረጥና ታክስ ከፍዬ ልስተናገድ ባሉበት ጊዜ የጉምሩክ ባለሥልጣን ይህንኑ መፍቀዱ ተገቢነት Aለው በማለትና ልሎችንም መከራከሪያዎች በማቅረብ ክሱ ላሰረዝ ይገባል በማለት ተከራክሯል።
የግራ ቀኙ ክርክር በዚህ መልኩ የቀረበለትም የፍድራል መ/ደ/ፍ/ቤት ጉዳዩን መርምሮ 2ኛ ተከሣሽ /Aመልካች/ በ1987 ዓ.ም. በወጣው የጉምሩክ ሥራና የቁጥጥር ማንዋል መመሪያ መሰረት Eቃዎችን ለማስረከብ የባንክ ፈቃድን የመጠየቅ ግድታ Aለበት። ነገር ግን ይህንኑ ግድታውን በመጣስ Eቃውን ለ1ኛ ተከሣሽ ያስረከበ ስለሆነ ብር 242‚121.45 /ሁለት መቶ Aርባ ሁለት ሺህ Aንድ መቶ ሃያ Aንድ ከAርባ Aምስት/ ከ1ኛ ተከሣሽ ጋር ባልተነጣጠለ ኃላፊነት ላከፍሉ ይገባል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
ጉዳዩ በይግባኝ የቀረበለትም የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 337 መሰረት ይግባኙን የሰበር Aቤቱታውም የቀረበው ይህንኑ በመቃወም ሲሆን ይህ የሰበር ችሎት Aቤቱታውን መርምሮ Aመልካች ለEዳው ከሥር 1ኛ ተከሣሽ ጋር በAንድነትና በነጠላ ኃላፊ ነው መባሉ ለሰበር ቀርቦ መጣራት የሚገባው መሆኑን በማመኑ ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
በAጠቃላይ የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን ምላሽ ማግኘት የሚገባውም የጉዳዩ ጭብጥ Aመልካች ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ከሥር 1ኛ ተከሣሽ ጋር ባልተነጣጠለ ኃላፊነት ለመክፈል ይገደዳል ወይ ? የሚለው በመሆኑ ይህንኑ ጭብጥ በመያዝ Aቤቱታው ከሕጉ ጋር ተገናዝቦ ተመርምሯል።
ተጠሪ በAመልካች ላይ ክስ የመሰረተው በባንኩ ባለቤትነት የመጣውን Eቃ ባለመብት ላልሆነው Aንደኛ ተከሣሽ በAዋጅ ቁጥር 6A/89 Aንቀጽ 2A(1) Eና በጉምሩክ ባለሥልጣን የወጣውን የEቃ Aወጣጥ ማንዋል በመጣስ Eቃውን የለቀቀ ስለሆነ ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ከ1ኛ ተከሣሽ ጋር ባልተነጣጠለ ኃላፊነት ላከፍል ይገባል በማለት ነው። Aመልካችም Eንዲለቀቁ የተደረጉት Eቃዎች ባለቤትነታቸው የ1ኛ ተከሣሽ Eንጂ የሣሽ Aይደለም በማለት ክሱን በመቃወም ተከራክሯል።
ይሁንና Aመልካች ለክሱ ምክንያት የሆኑትን ከውጭ Aገር Eንዲገቡ የተደረጉ Eቃዎችን ለ1ኛ ተከሣሽ ከማስረከቡ በፊት የባንክ ፈቃድን ጨምሮ የተለያዩ ሰነዶች ተሟልተው ሲቀርቡለት ብቻ መሆኑን የAመልካችን መ/ቤት ለማቋቋም በወጣው Aዋጅ ቁጥር 6A/89 Eና Aመልካች Eራሱ ባወጣው የAዋጁ Aፈፃፀም መመሪያ ላይ ተመልክቷል።
No topics extracted.
በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2A35 መሰረት Aንድ ሰው ተለይቶ የታወቀና ግልጽ የሆነ የሕግ ድንጋጌ ወይም የAስተዳደር ደንብ ከተላለፈ ጥፋት ፈጽሟል ላባል Eንደሚችል ተመልክቷል። በመሆኑም ተጠሪ በሰነድ Aማካይነት መያዣ ያደረገውን ንብረት Aመልካች በሕግና በመመሪያ የተጣለበትን ግድታ በመጣስ ለሥር 1ኛ ተከሣሽ በመልቀቁ በተጠቀሰው የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2A35 መሰረት በጥፋት ላይ የተመሰረተ ከውል ውጭ ኀላፊነት Eንዳለበት ይህ ሰበር ችሎት ለማረጋገጥ ችሐል።
በልላ በኩልም Aመልካችና የሥር 1ኛ ተከሣሽ ባልተነጣጠለ ኃላፊነት ለተጠሪ ኃላፊ ላሆኑ ይችላሉን? የሚለውን ነጥብ ሲታይ የAንድነትና የነጠላ ግድታ ከውል ወይንም በቀጥታ ከሕግ ላመነጭ የሚችል ሲሆን ግድታው ከውልም ሆነ ከሕግ ቢመነጭም ሁልጊዜም ቢሆን Eንደ Aንድ ግድታ የሚቆጠር ከመሆኑም በላይ የዚህ ዓይነት ግድታ በሚኖርበት ጊዜም ባለገንዘቡ በሁሉም ባለEዳዎች ላይ የሚኖረው መብት ከAንድ የክስ ምክንያት /Cause of action/ Eንደመነጨ በማድረግ ሕጉ ግምት የሚወስድ ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ሕ/ቁ.
1896 Eና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል።
ማንኛውም ከሣሽ የሆነ ወገንም ልላው ወገን Aንድ ግድታ Eንዲፈጽምለት ክስ ሲያቀርብ ተከሣሹን የሚጠይቀው በምን ዓይነት ግንኙነት Eንደሆነ ለይቶ ማመልከት ይኖርበታል።
በተያዘው ጉዳይ በተጠሪና በሥር 1ኛ ተከሣሽ መካከል ሰነድን መያዣ በማድረግ በተሰጠ ብድር በውል ላይ የተመሰረተ ግንኙነት የተፈጠረ ሲሆን ተጠሪም ይህንኑ በክሱ ለይቶ በመጥቀስ በውሉ ላይ ተመሥርቶ ላከፍለኝ ይገባል የሚለውን ጠይቋል በልላ በኩልም ተጠሪ ክሱን ሲያቀርብ 2ኛው ተከሣሽ የAሁን Aመልካች በሰነድ Aማካይነት መያዣ ያደረግሁትን ንብረት በሕግና በመመሪያ የተጣለበትን ግድታ በመጣስ ለ1ኛ ተከሣሽ ለቋል በማለት ስለሆነ ኃላፊነቱም ከውል ውጭ በጥፋት ላይ የተመሰረተ Eንደመሆኑ መጠን የሚኖርበትም ግድታ ከውል ውጭ በፈፀመው ጥፋት ምክንያት በተጠሪ ላይ ጉዳት የደረሰ ከሆነ ይህንኑ ጉዳት መካስ ስለሚሆን በዚሁ መሰረት ተጠሪ ከውል ውጭ ደርሶብኛል የሚለው ጉዳት ካለ ይህንኑ Aስልቶና ለይቶ በክስ መጠየቅ ሲገባው የሁለቱ ተከሣሾች ኃላፊነት ከውልና ከውል ውጭ ከተለያየ የክስ ምክንያት የመነጨ በሆነበት ሁኔታ ተጠሪ የውል ግንኙነት ካለው ከ1ኛው ተከሣሽ ከውሉ Aፈፃፀም ጋር በተያያዘ ላከፈለኝ ይገባል በማለት በክስ የሚጠይቀውን ገንዘብ ከውል ውጭ ኃላፊነት ያለበት 2ኛውም ተከሣሽ 138 139 /Aመልካች/ በAንድነትና በነጠላ ላከፈለኝ ይገባል በማለት መጠየቁ Aግባብነት ያለው ሆኖ Aልተገኘም።
ሲጠቃለልም ተጠሪ በAመልካች ላይ ያቀረበው ክስ ከውል ውጭ በለ ግንኙነት ሆኖ Aመልካችም በዚሁ መልሱ ኃላፊ መሆን Eንዳለበት የተረጋገጠ ቢሆንም Aመልካች በፈጸመው ጥፋት ምክንያት በተጠሪ ላይ ጉዳት ደርሶ ከሆነ ይህንኑ ጉዳት ተጠሪ Aስልቶና ለይቶ ካሣ Eንዲከፈለው መጠየቅ ሲገባው በዚህ መልኩ ክሱ ባልቀረበበት ሁኔታ ከተለያየ የክስ ምክንያት የመነጨውን የሁለቱን ተከሣሾች ኃላፊነት በመቀላቀል የውል ግድታ ካለበት ከ1ኛ ተከሣሽ ጋር Aመልካች በAንድነትና በነጠላ ካሣ ላፍለኝ ይገባል በማለት ተጠሪ ያቀረበውን ክስ የፍድራል መ/ደ/ፍ/ቤት ተቀብሎ በዚሁ መሰረት መወሰኑ ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተውም የፍድራል ከ/ፍ/ቤት ይህንኑ ማጽናቱ የሕግ ስህተት የተፈፀባቸው ሆነው ተገኝተዋል።
ው ሣ ኔ
348/1/ መሰረት ተሽሯል።
Aመልካች በፈፀመው ጥፋት ከውል ውጭ ኃላፊነት ያለበት መሆኑ የተረጋገጠ ቢሆንም በዚህ ምክንያት ተጠሪ ደርሶብኛል የሚለው ጉዳት ተለይቶ በክስ ያልተጠየቀ ስለሆነ ከሥር 1ኛ ተከሣሽ በAንድነትና በነጠላ በክስ የተጠየቀውን ገንዘብ ላከፍል Aይገባም ተብሎ ተወስኗል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።