No summary available.
ኀዳር 24 ቀን 2AAA ዓ.ም.
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ፍስሐ ወርቅነህ ሐጎስ ወልዱ ሒሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- ማኀበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ -ነ/ፈጅ ተስፋዬ ምንዳገኝ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ውባየሁ Aበበ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን ቀጥሎ የተመለከተውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር Aቤቱታ ላቀርብ የቻለው Aመልካች ሲከፍለኝ የነበረውን የጡረታ Aበል ልላ ባል ሳላገባ Aግብተሻል በሚል ምክንያት ያቋረጠ ስለሆነ Eንዲከፈለኝ ይወሰንልኝ በማለት በምስራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ክስ Aቅርበው ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን Aከራክሮ Aመልካች የጡረታ Aበል ክፍያውን ያቋረጠው ያለ Aግባብ ስለሆነ ላከፍል ይገባል በማለት ውሣኔ በመስጠቱና ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተውም የAማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በድምጽ ብልጫ ይግባኙን በመሰረዙ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት Aመልካች ቅሬታ በማቅረቡ ነው።
ይህ ችሎትም የቀረበውን የሰበር Aቤቱታ መርምሮ ክስ የቀረበበት ጉዳይ በፍ/ቤት ላታይ የሚችል ስለመሆኑ ለሰበር ቀርቦ ላጣራ Eንደሚገባው በማመኑ ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
የጡረታ Aበል ክፍያን በተመለከተ ይህ ችሎት በመዝገብ ለጉዳዩ Aግባብነት ያለውን የማኀበራዊ ዋስትና ባለሥልጣንን በAዲስ መልክ ለማቋቋም የወጣውን Aዋጅ ቁጥር 38/88 Aንቀጽ 5፣ 8 Eና 11ን በመተርጎም የማኀበራዊ ዋስትና ባለሥልጣን በሕጉ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት የማኀበራዊ ዋስትና መብት ጥቅምን በሚመለከት በሚሰጠው ውሣኔ 130 131 ላይ ይግባኝ የሚቀርበው ለማኀበራዊ ዋስትና ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ Eንደሆነ ጉባኤውም የሚሰጠው ውሣኔ የመጨረሻ መሆኑን በሕግ ተለይተው በAስተዳደራዊ ውሣኔ Eንዲቋጩ በተባሉ ጉዳዮች ላይ መደበኛ ፍ/ቤት የመዳኘት የሥረ ነገር ሥልጣን Eንደልለው በመዘርዘር የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል።
በመሆኑም በዚህ ጉዳይ ተጠሪ ተቋርጦብኛል የሚሉት የጡረታ Aበል ክፍያን በተመለከተ Aቤቱታውን ማቅረብ የሚገባቸው ለማኀበራዊ ዋስትና ባለሥልጣን ወይንም በAሁኑ Aጠራር ለማኀበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ መሆን ያለበት ሲሆን ኤጀንሲው በሚሰጠው ውሣኔ ቅሬታ ያለው ወገን Aቤቱታውን ለማኀበራዊ ዋስትና ይግባኝ ሰሚ ጉባዔ ከሚያቀርብ በስተቀር ከላይ Eንደተመለከተው በዚህ ጉዳይ ፍ/ቤቶች የሥረ ነገር ሥልጣን የልላቸው በመሆኑ የምስራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዳዩን ተመልክቶ ውሣኔ መስጠቱ የAማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይህንኑ ስህተት ሳያርም መቅረቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ
የምስራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 1257A በ22/9/98 የሰጠው ውሣኔና የAማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. A9916 በ16/2/99 ዓ.ም. በAብላጫ ድምጽ የሰጠው ትEዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
ይህን ጉዳይ በተመለከተ መደበኛ ፍ/ቤት ተቀብሎ ለማየት የሥረ ነገር ሥልጣን የለውም ተብሎ ተወስኗል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።
No topics extracted.