No summary available.
የሰ/መ/ ታህሳስ 1 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ፍሰሐ ወርቅነህ ሐጐስ ወልዱ ሒሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- የኔዘርላንድ ልማት ድርጅት Aልቀረቡም ተጠሪ፡- ውበት Aድባሩ ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥሎ የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር Aቤቱታ ላቀርብ የቻለው የበታች ፍ/ቤቶች ተጠሪ ክስ ባቀረበበት ጉዳይ Aመልካች ኃላፊ ነው በማለት ካሣ Eንዲከፍል ውሣኔ በመስጠታቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት Aመልካች ቅሬታ በማቅረቡ ነው።
የጉዳዩ Aመጣጥም ባጭሩ ሲታይ ተጠሪ በሞግዚቱ Aማካይነት በሰሜን ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በAመልካችና በሥር 1ኛ ተከሣሽ ላይ ባቀረበው ክስ ንብረትነቱ የAመልካች የሆነውን መኪና 1ኛ ተከሣሽ ሲያሽከረክር ተሳፍሬ በመጓዝ ላይ ሳለሁ መኪናው በመገልበጡ ምክንያት የAካል ጉዳት የደረሰብኝ ስለሆነ የሞራል ካሣን ጨምሮ ብር 31ሺህ ተከሣሾች Eንዲከፍሉ ይወሰንልኝ በማለት ጠይቋል።
የሥር 2ኛ ተከሣሽ የAሁን Aመልካችም በሰጠው መልስ በኃላፊነትና በካሣ መጠኑ ላይ ክርክር ያቀረበ ሲሆን በኃላፊነት ረገድ ባቀረበው ክርክር ከሣሽ በመኪናው ተሳፍሮ ሲጓዝ መኪናው በመገልበጡ ምክንያት ጉዳቱ የደረሰ መሆኑን Aምኖ ነገር ግን ከሣሽ የተሳፈረው ገንዘብ ከፍሎ ሳይሆን በነፃ ለምኖ ስለሆነ ኃላፊነት የለብኝም ብሐል።
112 113 1ኛ ተከሣሽም የመኪናው ባለንብረት 2ኛ ተከሣሽ ስለሆነ በኃላፊነት ተጠያቂ ልሆን Aልችልም በማለት ተከራክሯል።
የግራ ቀኙ ክርክር በዚህ መልኩ የቀረበለትም የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ማስረጃ ከሰማ በኋላ 2ኛ ተከሣሽን በከሣሽ ላይ ጉዳቱ የደረሰው በነፃ ተሳፍሮ በመጓዝ ላይ Eንዳለ ነው ቢልም ያቀረባቸው ምስክሮች ይህንን ካለማስረዳታቸውም በላይ Aስረድተው የነበረ ቢሆን Eንኳን 2ኛ ተከሣሽ በኃላፊነት ተጠያቂ ላሆን የማይችለው በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2081(2) ላይ Eንደመለከተው መኪናው የተሰረቀበት መሆኑን ባስረዳ ጊዜ ብቻ ስለሆነ ሁለቱም ተከሣሾች ኃላፊ ናቸው በማለት በክስ የተጠየቀውን ገንዘብ ላከፍሉ ይገባል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው የAማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በበኩሉ ግራ ቀኙን Aከርክሮ ኃላፊነትን በተመለከተ ይግባኝ ባይ /የAሁን Aመልካች/ መ/ሰጭው በመኪናው ተሳፍሮ የተጓዘው ገንዘብ ሳይከፍል በነፃ ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2089(1)መሰረት ኃላፊነት የለብኝም የሚል ክርክር ቢያቀርብም የዚህ ድንጋጌ ተፈፃሚነት መ/ሰጭም የይግባኝ ባይን መኪና Eራሱ ይዞ በሚገለገልበት ጊዜ ጉዳት ደርሶ በሚገኝበት ጊዜ Eንጂ መኪናዋ በይ/ባይ ቁጥጥር ሥር Eያለች መ/ሰጪው ዋጋ ሳይከፍል ስለተጓዘ ብቻ ተፈፃሚነት Aይኖረውም በማለት በዚህ ረገድ የቀረበውን የይግባኝ ቅሬታ ውድቅ Aድርጎ የካሣ መጠኑንም በተመለከተ የከፍተኛው ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ የደረሰውን ጉዳት መሰረት ያደረገ ስለሆነ ይግባኙ ተቀባይነት የለውም ብሎ የሥር ፍ/ቤት ውሣኔን Aጽንቷል።
ይህ ሰበር ችሎትም የቀረበውን የሰበር Aቤቱታ መርምሮ ተጠሪ ጉዳት የደረሰበት በAመልካች መኪና በነፃ ሲጓዝ ከሆነ Aመልካች ለደረሰው ጉዳት ኃላፊ ነው ተብሎ መወሰኑ ከፍ/ብ/ሕ/ቁ 2089(1) Aኳያ Aቤቱታው ለሰበር ቀርቦ ላጣራ Eንደሚገባው በማመኑ ተጠሪን ጠርቷል። ሆኖም የግራ ቀኙን የቃል ክርክር ለመስማት በተቀጠረበት ቀን ተጠሪ ባለመቅረቡ የAመልካችን የቃል ክርክር ብቻ ችሎቱ Aዳምጧል።
ምላሽ ማግኘት የሚገባውም የጉዳዩ ጭብጥ ክስ በቀረበበት ጉዳይ Aመልካች ኃላፊ ነው መባሉ በAግባቡ ነው Aይደለም የሚለው በመሆኑ ይህንኑ ጭብጥ በመያዝ Aቤቱታው Eንደሚከተለው ተመርምሯል።
Aመልካች ተጠሪ ተሳፍሮበታል የተባለው መኪና ባለንብረት Eንደመሆኑ መጠን የሚኖርበት ኃላፊነት ጥብቅ /strict/ ስለሆነ ተጠሪ ማስረዳት የሚጠበቅበት Aመልካች የዚሁ ተሽከርካሪ ባለቤት መሆኑንና በዚሁ ንብረትም ሲጓዝ ጉዳቱ የደረሰ መሆኑን ብቻ ሲሆን በዚሁ መሰረትም ተጠሪ በማስረጃ Aረጋግጧል።
በልላ በኩልም ጥፋት ሳይኖር ለሚደርስ ኃላፊነት ሕጉ ሦስት መከላከያዎችን ያስቀመጠ ሲሆን Eነዚህም የተጎጂው ጥፋት፣ የውል ግንኙነት መኖርና ጥቅም የልለው ግንኙነት /disinterested parties/ መሆናቸውን ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2069፣ 2071፣ 2086፣ 2088፣ Eና 2089 ድንጋጌዎች መረዳት ይቻላል።
በዚህ Aንቀጽ በሰሜን ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ክርክር ሲደረግ Aመልካች ባቀረበው ክርክር ተጠሪ በመኪናው ላይ የተሳፈረው ገንዘብ ከፍሎ ሳይሆን በነፃ መሆኑን ገልጾ ይህንን ፍሬ ነገር ያስረዱልኛል ያላቸውን ሁለት ምስክሮች Aቅርቦ Aሰምቷል። Eነዚህ ሁለት ምስክሮች የሰጡት የተሟላ የምስክርነት ቃል ዋናው የፍ/ቤቱ መዝገብ ወይንም ምስክርነት ቃላቸው ተገልብጦ ባለመቅረቡ ምክንያት ዝርዝር ቃላቸውን መገንዘብ ባይቻልም ፍ/ቤቱ ከሰጠው ውሣኔ ላይ መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ ገንዘብ ከፍሎ በመጓዝ ላይ የነበረ Aለመሆኑን ነው። በመሆኑም ተጠሪ በይ/ባይ መኪና የተሳፈረው ጥቅም ሳይኖር መሆኑን ይህ ችሎት ለመገንዘብ ችሐል።
No topics extracted.
ግንኙነቱ ጥቅም የልለው በሆነ ጊዜ ደግሞ ጉዳት የደረሰበት ወገን ከውል ውጭ ኃላፊነት ድንጋጌዎችን ጠቅሶ ለመከርከርና ካሣ ለመጠየቅ Eንደማይችል በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2089 (1) ላይ ተመልክቷል። ባለሀብቱም ሆነ የንብረቱ ጠባቂ ኃላፊ ላሆኑ የሚችሉት ጥፋት ከፈፀሙ ብቻ Eንደሆነ በዚሁ Aንቀጽ በንUስ ቁጥር (2) ላይ ተመልክቷል። ከዚህም መገንዘብ የሚቻለው 114 115 ተጎጂው ከውል ውጭ ኃላፊነትን ድንጋጌ ጠቅሶ ካሣ መጠየቅ የሚችለው Aደጋው የደረሰው በባለቤቱ ወይም በጠባቂው ጥፋት መሆኑን ማስረዳት ከቻለ ሲሆን የባለቤቱ ወይም የጠባቂው ኃላፊነት የሚመሰረተው በቁጥር 2084(1) ወይንም 2082(1) ድንጋጌ ሳይሆን በጥፋት ላይ የተመሰረተ ኃላፊነትን በሚመለከት በቁጥር 2028 Eና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት ይሆናል ማለት ነው። ከዚህም Aኳያ ተጠሪ በሥር ፍ/ቤት ያቀረበው ማስረጃ ሲታይ Aመልካች የተሽከርካሪው ባለንብረት መሆኑን በዚህ ተሽከርካሪም ተሳፍሮ ሲጓዝ መንገድ ላይ መኪናው በመገልበጡ ምክንያት ጉዳት የደረሰበት መሆኑን ነው።
ይህ ማስረጃ በጥፋት ላይ ላልተመሰረተ ኃላፊነት በቂ ቢሆንም ጉዳቱ የደረሰው በንብረቱ ባለቤት ወይንም በጠባቂው ጥፋት መሆኑን ግን የሚያረጋግጥ Aይደለም።
ስለሆነም የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ክርክሩን ከፍ/ብ/ሕ/ቁ 2089(2) Aኳያ ሳይመለከት Aመልካች ኃላፊ ነው ማለቱ በAግባቡ ካለመሆኑም በላይ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤትም ጉዳዩን ከዚህ ድንጋጌ ጋር Aያይዞ መርምሮ በቁጥር 2089 (1) Aነጋገር መሰረት ባለሀብቱ ወይም ጠባቂው Aንድ ጥቅም ሳያገኝ በEንስሳው፣ በሕንፃው ወይም "በልላ ነገር" ይገለገል የነበረው ተብሎ ከተዘረዘረው "በልላ ነገር" የሚለው ቃል ተሽከርካሪን የሚያጠቃልል ስለመሆኑ Aከራካሪ Eንደሆነ በውሣኔው ላይ Aስፍሮ፣ ያጠቃልላል ቢባል Eንኳን ተጠሪ ጉዳት የደረሰበት የAመልካች መኪናን Eራሱ ይዞ በመገልገል ላይ ሳይሆን የመኪናዋ ሹፍር መኪናዋን ይዞ በመንቀሳቀስ ላይ Eያለ ስለሆነ ድንጋጌው ተፈፃሚነት የለውም በማለት ያሰፈረው ውሣኔ Aግባብነት የለውም። ይሁንና በቁጥር 2089 (1) ሥር ከተዘረዘረው ላይ "ልላ ነገር" የሚለው ቃል ልላ ሰው ላገለገልበት የሚችል ተሽከርካሪን ጨምሮ ልላ ማንኛውም ዓይነት ንብረት Eንደሚያጠቃልል መገንዘብ የሚቻል ከመሆኑም በላይ በሕጉ ላይ መገልገል የሚለው ቃል ተጠሪ የAመልካችን መኪና Eራሱ ይዞ Eያሽከረከረ በሚገኝበት ጊዜ ነው የተባለውንም በተመለከተ ያለጥፋት ኃላፊነት /strict liability/ ከAንድ ንብረት ባለቤትነት ከሕንፃ፣ ከEንስሳ፣ ከተሽከርካሪና ከልሎችም ዓይነት ንብረቶች ላመነጭ የሚችል Eንደመሆኑ መጠን በEነዚህ ንብረቶች ላይ መገልገል Eስከተቻለ ድረስ ከማንኛውም ሁኔታ ጥቅም ሳይኖር የተገለገለ ሰው ጉዳት ቢደርስበት ኃላፊነት Eንደሚኖር መገንዘብ ከሚቻል በስተቀር ተጎጂው Eራሱ ተሽከርካሪውን ማሽከርከር Aለበት የሚለው Aገላለጽ በጠባቡ የተተረጎመና በተለይም ከተሽከርካሪ ውጭ ባሉ የተለያዩ ንብረቶች ላይ ተፈፃሚነት ላኖረው ስለማይችል ፍ/ቤቱ ለሕጉ የሰጠው ትርጉም የተሳሳተ ሆኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ
የሰሜን ወሎ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 60/94 ግንቦት 21 ቀን 1995 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ የAማራ ክልል ጠ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 222/95 በግንቦት 29 ቀን 1997 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 348(1) መሰረት ተሽሯል።
Aመልካች በተጠሪ ላይ ጥፋት መፈፀሙ ያልተረጋገጠ ስለሆነ ኃላፊ Aይደለም ተብሎ ተወስኗል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደመዝገብ ቤት ተመልሷል።