No summary available.
መጋቢት 2 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ዓብዱልቃድር መሐመድ ሐጐስ ወልዱ ሒሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- ዘይነባ ሐሰን ተጠሪ፡- ፍሬው ተካልኝ መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥሎ የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር Aቤቱታ ላቀርብ የቻለው የOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችሎት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት Aመልካች ቅሬታ በማቅረባቸው ነው።
የAሁን Aመልካች በምEራብ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ከሣሽ በመሆን በተጠሪ ላይ የሚከተለውን ክስ Aቅርበዋል። ተከሣሽ ባደረሰብኝ ድብደባ ምክንያት ቀኝ ዓይኔ የጠፋ ሲሆን ተከሣሹም በወንጀል ተከሶ ተቀጥቷል።
በAይኔ ላይ የደረሰውን ጉዳት በሕክምና ለመከታተል ከሚረዳኝ Aንድ ሰው ጋር በመሆን ወደ Aዲስ Aበባ ለሕክምና ስንመላለስ ለትራንስፖርት ብር 2950.90 (ሁለት ሺ ዘጠኝ መቶ ሃምሣ ብር ከዘጠና ሣንቲም) ለሆስፒታልና ለመድኃኒት ክፍያ ብር 363.16 (ሶስት መቶ ስልሣ ሶስት ብር ከAሥራ ስድስት ሣንቲም)፣ ለሰው ሰራሽ ዓይን ማስተከያና ለመነጽር ብር 415.00 (Aራት መቶ Aሥራ Aምስት)፣ A.Aበባ ከተማ ለቆየንበት መቶ ሰላሳ Aምስት ቀናት ለምግብ፣ ለAልጋና ለታክሲ በቀን ብር ስልሳ ብር ሒሳብ በድምሩ ብር 8100 (ስምንት ሺ Aንድ መቶ) Eንዲሁም የሞራል ካሳ ብር 1000 ይከፈለኝ በማለት ጠይቃለች።
በተጨማሪም ዓይኔ ሲጠፋ 10ኛ ክፍል የደረስኩና Eድሜዬም 20 ዓመት የነበረ ሲሆን በጉዳቱ ምክንያት ትምህርቴን በማቋረጤ የመንግሥት ሰራተኛ የመሆን ፍላጐቴ Eውን K=ሆን ባለመቻሉ ዓይኔ ባይታወር ኖሮ በትንሹ በወር ብር መቶ ሃያ መቀጠር Eችል የነበረ ሲሆን በመንግሥት ሥራ ላይም Eስከ 55 ዓመት Eድሜ ብሰራ 35 ዓመት በሥራ ላይ Eቆይ የነበረ በመሆኑ ይህም ሲሰላ 120x12x35= ብር 40,000.00 (Aርባ ሺህ) ይሆናል። ስለሆነም በAጠቃላይ ብር 52,830.56 (Aምሳ ሁለት ሺህ ስምንት መቶ ሰላሳ ብር ከሃምሳ ስድስት ሳንቲም) ከወጪና ኪሳራ ጋር Eንዲከፍል ይወሰንልኝ በማለት ጠይቀዋል።
የከሳሽ ክስና ማስረጃም ለተከሳሽ ደርሶ በካሳ መጠኑ ላይ ብቻ ክርክሩን መሰረት በማድረግ የካሳ ክፍያው ጥያቄ በጣም የተጋነነ ከመሆኑም በላይ የማስረጃም ድጋፍ የልለው ስለሆነ በነጻ ልሰናበት ይገባል በማለት ተከራክሯል።
የግራ ቀኙ ክርክር በዚህ መልኩ የቀረበለትም የምEራብ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ክርክሩን ከቀረበው ማስረጃ ጋር Aገናዝቦ መርምሮ ከሳሽ በደረሰባት ድብደባ ምክንያት Aንድ ዓይኗን ያጣች ስለሆነና Aንድ ዓይን ያለው ሰው ሁለት ዓይን ካለው ሰው ጋር Eኩል የመሥራት ችሎታ Eንደማይኖረው ይታመናል ካለ በኋላ ጉዳቱ ሲደርስ ከሳሽ Aድሜዋ 27 ዓመት የነበረ ሲሆን ጉዳቱ ባይደርስባት ኖሮ በቀን ብር 4 ሂሳብ በወር ብር 120 በዓመት ብር 1440.00 Eንደምታገኝ መረዳት ይቻላል። ከሳሽ Eስከ 50 ዓመት ድረስ ትኖራለች ተብሎ ስለሚገመት በAጠቃላይ ብር 41,760.00 ገቢ ታገኝ ነበር።
ይሁንና በደረሰባት ጉዳት ምክንያት 40%(Aርባ በመቶ) የመስራት Aቅሟ የቀነሰ ስለሆነ ይህም ሲሰላ ብር 16,800.57(Aስራ ስድስት ሺህ ስምንት መቶ ብር ከሃምሳ ሰባት ሳንቲም) ስለሚሆን የሞራል ካሳ ብር 1000 (Aንድ ሺህ) ጨምሮ በድምሩ ብር 17,800.57 (Aስራ ሰባት ሺህ ስምንት መቶ ብር ከሃምሣ ሰባት ሣንቲም) ተከሳሽ ለከሳሸ Eንዲከፍል Eንደዚሁም ለመድኃኒት መግዣ ብር 363.05 ለመነጽር ብር 415.40 ለትራንስፖርት ብር 1060.30(Aንድ ሺ ስልሳ ከሰላሳ) በAዲስ Aበባ ቆይታ የAልጋ የምግብና የታክሲ ከሳሽንና ረዳቷን ጨምሮ ብር 1740.00(Aንድ ሺ ሰባት መቶ Aርባ) በAጠቃላይ ብር 21,378.92 (ሃያ Aንድ ሺህ ሶስት መቶ ሰባ ስምንት ብር ከዘጠና ሁለት ሳንቲም) ተከሳሽ ለከሳሽ ይክፈል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል። ተከሳሽ በዚህ ውሳኔ ቅሬታ Aድሮበት 106 107 የይግባኝ ቅሬታውን ለOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ያቀረበ ቢሆንም በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/377 መሰረት ፍ/ቤቱ ይግባኙን ሳይቀበለው ቀርቷል።
የሰበር Aቤቱታ የቀረበለትም የOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት በበኩሉ ግራ ቀኙን Aከራክሮ ተጠሪ የAሁን Aመልካች በAንድ ዓይኗ መጥፋት ምክንያት ሰርታ ገቢ ለማግኘት የሚከለክላት ባለመሆኑ የሥር ፍ/ቤቶች የወደፊት ጉዳት ካሳ ላከፈላት ይገባል በማለት የሰጡት ውሳኔ ከፍ/ብ/ሕ/ቁ/ 2090(1) Aኳያ ተገቢ Aይደለም በማለት በዚህ ረገድ የተወሰነውን የካሳ ክፍያ በመሻር ሕክምናውን ለመከታተል ተጠሪ ያወጣችው ወጭና የሞራል ካሳን በተመለከተ Eንዲከፈላት የተወሰነውን Aጽንቷል።
No topics extracted.
ይህ ሰበር ሰሚ ችሎትም የቀረበለትን የሰበር Aቤቱታ መርምሮ በAመልካች ላይ Aንድ ዓይን የመጥፋት የAካል ጉዳት የደረሰባት መሆኑ በተረጋገጠበት ሁኔታ ሰርታ ለመኖር የሚከለክላት ነገር የለም በሚል የOሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በበታች ፍ/ቤቶች ካሳ Eንዲከፈላት የተሰጠውን ውሳኔ የመሻሩ Aግባብነት ለሰበር ቀርቦ ላታይ Eንደሚገባው በማመኑ ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
በAጠቃላይ የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን ይህ ሰበር ችሎትም Aቤቱታውን Eንደሚከተለው መርምሯል።
ተጠሪ በAመልካች ላይ በፈጸመው ድብደባ ምክንያት የAመልካች የቀኝ ዓይን የጠፋ ስለመሆኑ በሥር ፍ/ቤት ክርክር ሲደረግ በማስረጃ ተረጋግጧል።
በAመልካች ላይ የደረሰው ጉዳት የAካል ጉዳት Eንደመሆኑ መጠን Aመልካች ማስረዳት የሚጠበቅባት ጉዳት የደረሰባት መሆኑን ጉዳቱን ባደረሰው የተጠሪ ድርጊትና በተገኘው ውጤት መካከል ቅርብና ቀጥተኛ የሆነ የምክንያትና የውጤት ግንኙነት /cause and effect relationship/ መኖሩን ብቻ ነው። ምክንያቱም በፍ/ብ/ሕ/ቁ/ 2067 መሰረት ኃላፊነቱ በጥፋት ላይ ያልተመሰረተ ጥብቅ /Strict/ ስለሆነ የጉዳት Aድራሹን የAEምሮ ሁኔታ /State of mind/ ማስረዳት Aይጠበቅባትም። የሥር ፍ/ቤቶችም በዚሁ ላይ ተመሥርተው የኃላፊነት ውሳኔ የሰጡ ከመሆኑም በላይ ኃላፊነቱ ግራ ቀኙን Aላከራከረም።
የዚህን ችሎት ምላሻ የሚሻው የጉዳዩ ጭብጥ ለደረሰው ጉዳት ተጠሪ ኃላፊ ነው ከተባለ ካሳ ለመክፈል ይገደዳልን? የሚለው በመሆኑ ይህንኑ ጭብጥ በመያዝ ከሕጉ Aኳያ Eንደሚከተለው መርምረናል።
በቅድሚያም ከጉዳዩ ጋር Aግባብነት ያላቸውን የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2090(1)፣ 2091 Eና 2092 ድንጋጌዎችን መረዳት Eንደሚያስፈልግ ችሎቱ ተገንዝቧል።
በዚህም መሰረት የተጠቀሱት ድንጋጌዎች ቀጥሎ የተመለከተው ይዘት Aላቸው።
2090 የኪሣራ Aከፋፈል (1) በመደቡ በጉዳቱ ምክንያት ተበዳዩ የሚካሰው ለጉዳቱ ተመዛዛኝ የሆነ ካሣ በመክፈል ነው።
2091 የኪሣራው ልክ ለደረሰው ጉዳት Aላፊ መሆኑ በሕግ የታወቀው ሰው የሚከፍለው የጉዳት ካሣ ኃላፊነቱን ያመጣው ጉዳይ በተበዳዩ ላይ ከደረሰው ጉዳት ጋር Eኩል ሆኖ መመዛዘን Aለበት።
2092 ለወደፊት ላደርስ ስለሚችል ጉዳት ለወደፊት ላደርስ ይችላል ተብሎ የሚገመተው ጉዳት የተረጋገጠ ሲሆን Aስኪፈፀም ሳይጠብቅ ካሳ ላከፈለው ይገባል።
የብዙ Aገራት ከውል ውጭ የሚደርስ ኃላፊነት ሕጎች ሁለት ግቦችን ማለትም ጉዳቱን የመካስ /Insurace goal/ Eና የጥፋት ባህሪን የመግራት /Deterrence goal/ ተብለው የሚታወቁትን መርሆች መሰረት በማድረግ የተቀረጹ ሲሆን የIትዮጵያ ከውል ውጭ የሚደርስ ኃላፊነት ሕግም ይህንኑ ዓላማ Aካቶ Eንደተቀረጸ በሕጉ ላይ ማብራሪያ የጻፉት ፕሮፍሰር ጆርጅ ቺቺኖቪት /The Ethiopian law of compensation for damages/ በሚለው ማብራሪያቸው ላይ Aንጸባርቀውታል።
ከላይ በተጠቀሱት የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2091 Eና 2092 መርሆች መሰረት ካሳና ጉዳት Eኩል መሆን Eንዳለበት ይህ ማለትም በመርህ ደረጃ ተጎጂው ከጉዳቱ Aትራፊ መሆን Eንደማይገባውና ከደረሰበትም ጉዳት በታች መካስ Eንደልለበት መገንዘብ ይቻላል። በተግባርና በተጨባጭ ሲታይ የጉዳት መጠኑ በፍርድ ቤቱ የሚወሰን ቢሆንም ጉዳዩ የሕግ ጥያቄ ብቻ ባለመሆኑ ውስብስብነት ያለው ከመሆኑም ልላ ሕጉ በተጨባጭ የደረሰ ጉዳት ብቻ ሳይሆን ወደፊት ላደርስ የሚችል ጉዳትም የተረጋገጠ ሲሆን Eንዲካስ ስለሚፈቅድ ወደፊት ስለሚሆን ነገር Eርግጠኛ መሆን ስለማይቻል በካሳ Aወሳሰን ረገድ ስልትን የማዛነፍ ውጤት ያስከትላል። ከዚሁ ጋር በተየያዘም በካሳ Aወሳሰን ረገድ ከንብረት ጉዳት ይልቅ Aተማመኑ የበለጠ ውስብስብ የሚሆነው የደረሰው ጉዳት የAካል ጉዳት በሚሆን ጊዜ ነው። በEርግጥ በጉዳቱ ምክንያት የተከፈለ ወጪ፣ ለመድኃኒት መግዣ Eንደዚሁም ለሰው ሰራሽ የAካል ምትክና ተጎጂው ወደ ሆስፒታል የተመላለሰበት ወጪ የጉዳት ካሳው Aካል ስለሆነና በቀላሉም በማስረጃ የሚረጋገጥ በመሆኑ በAወሳሰን ረገድ Aስቸጋሪ Aይሆንም። ነገር ግን ጉዳቱ የዘላቂነት ባህሪይ ሲኖረውና የተጎጂው የመሥራት Aቅም በሙሉ ወይንም በከፊል ሲጓደል በጉዳት ካሳው Aተማመን ረገድ Aስቸጋሪ ሁኔታ መፈጠሩ Aይቀርም።
ስለሆነም ካሳ ከደረሰው ጉዳት ጋር Aኩል ሆኖ መመዛዘን Aለበት ሲባል መታየት የሚገባው በAጠቃላይ በተጎጂው ላይ ጉዳት በመድረሱ ምክንያት Eንደሰው በAጠቃላይ የመሥራት ኃይል ቅነሳ /General utility/ Aንጻር Eንጂ ከጉዳቱ በፊት ሲሰራው የነበረውን ሥራ ላለመሥራት ጉዳቱ ያስከተለውን ልዩ ጫናና የቅነሳ መጠን /special utility/ ግምት ውስጥ በማስገባት Aይሆንም። ምክንያቱም በተጨባጩ ዓለም ሲታይ Eያንዳንዱ የሰውነት ክፍል ሥራ ለመሥራት ብቻ ሳይሆን በAጠቃላይ Eንደ ሰው ለመኖር የተለያየ ፋይዳና ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ ነው።
በEጃችን ወዳለው ጉዳይ ስንመለስ በAመልካች ላይ የደረሰው ጉዳት የAንድ ዓይን መጥፋት ሲሆን ይህም ጉዳት ዘላቂ ከፊል ስንኩልነት /Permanent partial disablement/ ተብሎ የሚመደብ ነው።
የOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችሎት ለAመልካች የወደፊት ጉዳት ካሳ ላከፈላት Aይገባም ያለው Aንድ ዓይኗን ያጣች ቢሆንም ወደፊት ሥራ ሰርታ ገቢ ከማግኘት ጉዳቱ Aይከለክላትም በማለት ነው።
ነገር ግን ጉዳት መድረሱ በተጨባጭ Eስከተረጋገጠ ድረስ ለተጎጂው ካሳ Aይከፈለውም ማለት ከላይ የተመለከተውንና ጉዳትን የመካስና የጥፋት ባህሪን የመግራት የሕጉን ዓላማንና ግብ የሚጻረር ነው። Aመልካች በደረሰባት የAንድ ዓይን መጥፋት ምክንያት ሙሉ ለሙሉ የመሥራት ችሎታዋን Aጥታለች ባይባልም ከላይ Eንደተመለከተው ካሳ ከደረሰው ጉዳት ጋር Eኩል ሆኖ መመዛዘን Aለበት ሲባል ከAጠቃላይ የመሥራት ኃይል ቅነሳ ጋር ተገናዝቦ Eንጂ ከልዩ የመሥራት ኃይል ቅነሳ ጋር ተገናዝቦ ባለመሆኑ Aመልካች Aንድ ዓይኗን ማጣቷ በወደፊት ሕይወቷ የገቢ መጠን መቀነስ ባያስከትልም Eንኳን በAጠቃላይ Eንደ ሰው ለመኖር በEያንዳንዱ የEለት ሕይወቷና Eንቅስቃሴ ላይ ጉዳት /Punitive damage/ መድረሱ ምክንያታዊ Eርግጠኛነት /Reasonable Certainty/ ያለው በመሆኑ ከAጠቀላይ የሕጉ ዓላማም ሆነ ከቁጥር 2091 Eና 2092 ድንጋጌዎች Aንጻር ካሳን መወሰን Aግባብነት ይኖረዋል።
በልላ በኩልም ጉዳት የደረሰበት ወገን የደረሰበትን ጉዳት ልክና ጉዳት Aድራሹ ካሳ በመክፈል ረገድ ያለበትን ግድታ ማስረዳት Eንዳለበት በፍ/ብ/ሕ/ቁ/2141 ላይ የተመለከተ ቢሆንም ተጎጂው ጉዳት የደረሰበት መሆኑን Aረጋግጦ ነገር ግን የካሳውን መጠን ለመገመት Aስቸጋሪ ሁኔታ በሚያጋጥም ጊዜ በቁጥር 2102 መሰረት ዳኞች የካሳውን መጠን በርትE ለመወሰን ሥልጣን የተሰጣቸው በመሆኑ ይህም ጉዳት የደረሰበት ሰው የካሳውን መጠን በማስረዳት ረገድ ያለበትን ሸክም በመጠኑም ቢሆን Eንደሚያቀልለት የሚያስገነዝብ ነው።
110 111 ሲጠቃለልም Aመልካች ጉዳት የደረሰባት ስለመሆኑ በማስረጃ የተረጋገጠ ከመሆኑም በላይ ጉዳቱም በወደፊት ሕይወቷ ላይ Aሉታዊ ተጽAኖ ማሳደሩ Eንደማይቀር ምክንያታዊ Eርግጠኛነት ያለው ስለመሆኑም የተረጋገጠ በመሆኑ ላወሰን የሚገባውም የካሳ መጠን በፍ/ብ/ሕ/ቁ/2102 መሰረት በርትE መወሰን የግድ የሚል በመሆኑ በዚሁ መሰረትም የምEራብ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የካሳውን መጠን በርትE መወሰኑ በይግባኝ የተመለከተውም የOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይህንኑ ውሳኔ ማጽናቱ Aግባብነት ያለው ሆኖ ሳለ የክልሉ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችሎት ይህንኑ ውሳኔ በመሻር ለAመልካች የወደፊት ካሳ ላከፈል Aይገባም በማለት የሰጠው ውሳኔ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል።
የOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችሎት በመ.ቁ. 04500 ጥር 9 ቀን 1997 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የምEራብ ወለጋ ዞን ከፍ/ቤት በመ.ቁ. 210/93 በሚያዝያ 16 ቀን 1995 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ Eንደዚሁም የOሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት በመ.ቁ.2444/95/1 በኀዳር 8 ቀን 1996 ዓ.ም የሰጠው ትEዛዝ በAግባቡ ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ጸንቷል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሳራ ይቻቻሉ
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል