No summary available.
ሚያዝያ 9 ቀን 2AAA ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ መስፍን Eቁበዮናስ ሂሩት መለሰ መድሕን ኪሮስ ዓላ መሐመድ Aመልካች ፡- የIት/ንግድ ባንክ - ነ/ፈጅ ወንድምAገኝ ቶሎሣ ቀረበ ተጠሪ፡- Aቶ መሐመድ ባህሙድ - Aልቀረቡም **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዳይ የመዋዋል ችሎታን የተመለከተ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የAሁን ተጠሪ ለAቅመ Aዳም ላልደረሰው ልጄ ለወጣት Aህመድ መሐመድ ሞግዚትና Aሳዳሪ ሆኜ የተሾምኩ ሲሆን ንብረትነቱ የልጄ የሆነውንና ግምቱ ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ የሆነውን ቤት Eኔን ሞግዚቱን ሳያስፈቅዱ Aመልካች ባንክና Aቶ ሐሰን የተባሉት ግለሰብ ላደረጉት የብድር ውል መያዣ Eንዲሆን ልጁን የዋስትና ግድታ Aስገብተው ከማስፈረማቸውም በላይ በቤቱ ላይ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ ወጥቶ ገዢ ስላልተገኘ ባንኩ ቤቱን ተረክቦ በወር ብር 500 /Aምስት መቶ ብር/ Eያከራየው ይገኛል፤ ስለዚህ ባንኩ ያለAግባብ የያዘውን ቤትና የኪራዩን ሂሳብ Eንዲመልስ ይወሰንልኝ በማለት በOሮሚያ ክልል Aርሲ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ ነው።
የAሁን Aመልካች በሰጠው መልስ የቤቱ ባለቤት የሆነው Aህመድ መሐመድ ለAቅመ Aዳም የደረሰ ነው፣ ለAካለመጠን Aልደረሰም ቢባል Eንኳን ክሱ በይርጋ የታገደ ነው፣ Aህመድ መሐመድ Aሜሪካን Aገር Eየኖረ ባለበት ወቅት ተጠሪ የEሱ ሞግዚትና Aሳዳሪ ነኝ በማለት ያለAግባብ ያገኙትን ማስረጃ ተቃውመን ጉዳዩ በሂደት ላይ ይገኛል፣ ባንኩ ውሉን ያደረገው ችሎታ ካለው ሰው ጋር መሆኑ Eንዲረጋገጥ ፍ/ቤቱ ግለሰቡን በAካል Aስቀርቦ ይመልከትልን፣ ውሉ ቤቱ በሚገኝበት ዲክሲስ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የተመዘገበና የፀና ውል ነው፣ የቤቱ ግምት ብር 9,000 /ዘጠኝ ሺህ ብር/ ሲሆን በወር ከብር 15 /Aስራ Aምስት ብር/ በላይ የሚከራይ Aይደለም በማለት ተከራክሯል።
ፍ/ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ Aህመድ መሐመድ በሞግዚት ስር የሚገኝ የ16 ዓመት ልጅ መሆኑ በፍ/ቤት ስለተረጋገጠ ልጁ የመዋዋል ችሎታ ሳይኖረው ከባንኩ ጋር የተረገው ውል በህግ ፊት ዋጋ የለውም፣ Aመልካች የልጁ Eድሜ 2A ዓመት ነው በAካልም ቀርቦ ይታይ ከማለት ውጪ ይህንን የሚደግፍ ማስረጃ Aላቀረበም፣ ስለዚህ ውሉ ውድቅ ነው፣ Aመልካች ለተጠሪ ቤቱን ይመልስ Eንዲሁም ቤቱን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ መልሶ Eስከሚያስረክብበት ጊዜ ያለውን የቤቱን ኪራይ በወር ብር 100 /Aንድ መቶ ብር/ ሂሳብ ታስቦ ለተጠሪ ይክፈል በማለት ወስኗል። Aመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ቢያቀርብም ፍ/ቤቱ ቅሬታውን ባለመቀበል ውሣኔውን Aጽንቶታል።
የሰበር Aቤቱታው የቀረበው ይህንን ውሣኔ ለማስለወጥ ነው።
የAቤቱታው ይዘት በAጭሩ የመያዣ ውሉ የተፈረመው በ1988 ዓ.ም ስለሆነ ተጠሪ ያቀረቡት የውል ይፍረስልኝ ጥያቄ በይርጋ የታገደ ነው፣ በስር ፍ/ቤት ግለሰቡ በAካል ቀርቦ ይታይልን Eድሜውም ይመርመርልን በማለት ያቀረብነው መከራከሪያ የታለፈው ያለAግባብ ስለሆነ ይታረምልን የሚል ነው።
ይህ ችሎት የስር ፍ/ቤቶችን ውሣኔዎች Aግባብ ካለው ህግ ጋር Aገናዝቦ በመመርመር የበታች ፍ/ቤት የመያዣ ውሉ ይፈርሳል ብሎ የወሰነው በAግባቡ መሆን Aለመሆኑ ተጣርቶ መወሰን ያለበት ነጥብ ሆኖ ስላገኘው ጉዳዩ ለሰበር Eንዲቀርብ Aድርጓል። መዝገቡን Eንደመረመርነው ለዚህ ጉዳይ መነሻ የሆነው የመያዣ /የዋስትና/ ውል በAመልካችና በAቶ Aህመድ መሐመድ መካከል የተፈረመው ሚያዝያ 5 ቀን 1988 ዓ.ም መሆኑንና ተጠሪ ለ16 ዓመቱ ልጃቸው ለAህመድ መሐመድ ሞግዚትና Aስተዳዳሪ ሆነው የተሾሙት 102 103 በAዳማ ወረዳ ፍ/ቤት በመዝገብ ቁ. 04027 ሐምል 14 ቀን 1997 ዓ.ም መሆኑን ተገንዝበናል። በመሆኑም Aቶ Aህመድ መሐመድ በ1997 ዓ.ም 16 ዓመት ታዳጊ ከነበረ Aከራካሪውን ውል ከAመልካች ጋር ባደረገበት ወቅት /በ1988 ዓ.ም/ የሰባት /7/ ዓመት ህፃን ነበረ ማለት ነው። ይህ ከሆነ ደግሞ Aመልካች ባንክ ከAንድ የሰባት /7/ ዓመት ልጅ ጋር የዋስትና /የመያዣ/ ውል Aድርጓል ለማለት የማይቻል ነው። በመሆኑም ከላይ የተገለፀው Eውነታ ተገናዝቦ ሲታይ Aቶ Aህመድ መሐመድ ውሉን ከAመልካች ጋር ያደረገው ችሎታ ሳይኖረው ነው ለማለት የሚያስችል Aይደለም። ስለሆነም የስር ፍ/ቤት ልጄ ችሎታ ሳይኖረው የፈረመው ውል ፈራሽ ይሁንልኝ በማለት ተጠሪ ያቀረቡትን ጥያቄ ተቀብሎ ውሉ ፈራሽ ነው፣ Aመልካች ለተጠሪ ቤቱንና የኪራይ ገንዘቡን ይመልስ ሲል የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ
የOሮሚያ ክልል Aርሲ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመዝገብ ቁ. 07730 ግንቦት 18 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ Eና የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመዝገብ ቁ. 42931 ግንቦት 3A ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ተሽረዋል። ይፃፍ።
Aቶ Aህመድ መሐመድ ክርክር የተነሳበትን ውል ከAመልካች ጋር ያደረገው ችሎታ Eያለው ስለሆነ ውሉ Aይፈርስም፤ ቤቱንና የኪራይ ገንዘቡንም Aመልካች ለተጠሪ Eንዲመልስ Aይገደድም በማለት ተወስኗል።
ግራ ቀኙ ወጪና ኪሣራቸውን ይቻቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቷል ይመለስ።