No summary available.
ሚያዝያ 9 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ መስፍን Eቁበዮናስ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ መድሕን ኪሮስ Aመልካች፡- የIትዮጵያ ቴልኮሚኒኬሽ ኮርፖሬሽን ቀረበ ተጠሪ፡- Aቶ ሲሳይ ጥላሁን ቀረበ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል
በጉዳዩ ላይ ክርክር የተጀመረው በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ሲሆን የAሁኑ Aመልካች ሐምል 20 ቀን 1997 ዓ.ም በAዘጋጀው የክስ ማመልከቻ ተጠሪው ከAመልካች ጋር መጋቢት 20 ቀን 1997 ዓ.ም ባደረገው የቴልፎን ደንበኝነት ውልና ተጨማሪ ሲ.ዲ.ኤ.ም.ኤ ደብልዩ.ኤል.ኤል ውል መሰረት Eንዲጠቀምበት በተሰጠው 9 በሆነ ስልክ መስመር በግንቦት 1997 ዓ.ም ላገኘው Aገልግሎት መክፈል የሚገባውን ብር 85,032 (ሰማንያ Aምስት ሺ ሰላሳ ሁለት) የAገልግሎት ሒሳብ Aለመክፈሉን በዚህ ምክንያትም ድርጅቱ Aገልግሎቱን ማቋረጡን ገልጾ ተጠሪ ይህንን ሒሳብ Eንዲከፍል Eንዲወሰንበት ሲል ክስ Aቅርቧል።
ተጠሪውም ታህሳስ 3 ቀን 1998 ዓ.ም ጽፎ ባቀረበው መልስ በክሱ ቁጥሩ የተጠቀሰውን ስልክ በውል መረከቡን Aምኖ በክሱ የተጠቀሰው ክፍያ Eንዲከፍል ምንም Aይነት ጥሪም ሆነ ማስታወቂያ Eንዳልደረሰው ስልኩንም ከ18 ቀን ባልበለጠ ጊዜ Eንደተጠቀመበትና ክፍያው የተጋነነ መሆኑን በመጥቀስ ክሱ ውድቅ Eንዲደረግለት ተከራክሯል።
ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ከውላቸው ጋር በማገናዘብ መዝገቡን ከመረመረ በኋላ ከሳሽ ያቀረበው የውል ሰነድ Aንቀጽ 11 የሚከፈለው ገንዘብና የሚከፈልበት ጊዜ ተጠቅሶ ለተከራዩ Eንደሚቀርብ ስለሚደነግግ ከሣሽ ይህን ማስታወቂያ ወይም ጥሪ ሳያቀርብለት Eንዲከፍለው ክስ ማቅረቡ ተቀባይነት የለውም። በውሉ በስልኩ የተገለገለው ደንበኛ ማስታወቂያው በጊዜው ሳይደርሰው ቢቀር ደግሞ በመጠየቅያው ላይ በተመለከተው ጊዜ ውስጥ Eንዳይከፍል Eንደሚያግደው ተብሎ የተደነገገውም ለተከሳሹ መብት የሚሰጥ Eንጂ ተከሳሹ ማስታወቂያ ሳይደርሰው Eንዲከፍል ግድታ የሚጥልበት Aይደለም በማለት ክሱን ውድቅ Aድርጐታል።
የፍ/ከ/ፍ/ቤት የቀረበለትን ይግባኝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ/337 መሰረት በመሰረዝ መዝገቡን ዘግቶ መልሶታል።
Aመልካች የሰበር Aቤቱታውን ያቀረበው የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔና የፍ/ከ/ፍ/ቤት የሰጠውን ትEዛዝ በመቃወም ሲሆን ቅሬታውም ተጠሪው ከተሰጠው በራሪ ወረቀትና በ1997 ዓ.ም ነፃ የመረጃ ማEከል Aማካኝነት የተጠቀመበትን የAልግሎት ሒሳብ ስለሚያውቅ Eንደዚሁም የውሉ Aንቀጽ 11 ማስታወቂያ በማይሰጣቸው ሁኔታዎች ደንበኞች መክፈል የሚችሉባቸውን ሁኔታዎች በግልጽ ባስቀመጡበት ሁኔታ ማስጠንቀቂያ የመስጠት Aስፈላጊነት Eንደዋና ምክንያት ላቆጠር Aይችልም። ተጠሪው Aገልግሎት ማግኘቱን Aምኗል። ክርክሩ የተጠየቀው ሒሳብ የተጋነነ ነው የሚል ነው። የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ሒሳቡ የተጋነነ መሆን ያለመሆኑን ተጣርቶ ክፍያው Eንዲፈፀም መወሰን ሲገባው በውሉ Aንቀጽ 11 ደንበኛው ማስታወቂያ ባይደርሰውም ክፍያውን ከመፈፀም Aይድንም ተብሎ የተደነገገውን ያለAግባብ በመተርጐም ክሱን ውድቅ ማድረጉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መፈፀሙን ያሳያል። ፍ/ከ/ፍ/ቤትም የቀረበለትን ይግባኝ መሰረዙ በAግባቡ Aይደለም።
በመሆኑም የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ተሽሮ መጀመሪያ ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤት Eንደገና Aከራክሮ የቀረበውን ክስ ከማስረጃው ይዘትና ከሕግ Aኳያ መርምሮ በፍሬ ጉዳዩ ላይ ተገቢውን ውሳኔ Eንዲሰጥ ተብሎ Eንዲወሰንልን የሚል ነው።
Aቤቱታው ያስቀርባል ከተባለ በኋላ ተጠሪው ቀርበው መልስ ባለመስጠታቸው ክርክሩ በልሉበት Eንዲታይ ታዟል። በመቀጠልም ተጠሪው 98 99 የስልክ ክፍያውን Eንዲፈጽሙ ጥሪ ስላልተደረገላቸው ወይም ማስጠንቀቂያ ስላልተሰጣቸው ክፍያውን ላፈጽሙ Aይገባም ተብሎ በስር ፍ/ቤት የተሰጠው ውሳኔ በAግባቡ ነው ወይስ Aይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ መዝገቡን መርምረናል።
መዝገቡን Eንደመረመርነውም ተጠሪው ስልኩን ላገለገሉበት ከAመልካች ጋር ውል መስርተው ማስገባታቸውንና በዚሁ ስልክ መጠቀም መጀመራቸውን Aልካዱም። የስልክ Aገልግሎት ክፍያ Eንድከፍል ጥሪ Aልተደረልኝም ማስታወቂያም Aልደረሰኝም ማለታቸው ደግሞ ሒሳቡ ተመርምሮ ክፍያው ሲታወቅ Eከፍላለሁ የሚል ሐሳብ ያላቸው መሆኑን Eንጂ ማስታወቂያ ስላልደረሰኝ ክፍያውን Aልከፍልም፣ Eንድከፍልም ሕጉ Aያስገድደኝ ማለታቸው ያለመሆኑ ግልጽ ነው። የስልክ Aገልግሎት ክፍያ በየወሩ የሚከናወን Eንደመሆኑ መጠን ተጠሪው ክፍያውን በወቅቱ የመክፈል ግድታ Aለባቸው። በውላቸው Aንቀጽ 11 ስር የተደነገገውም ተጠሪው የክፍያ ማስታወቂያ ሣይደርሳቸውም የAገልግሎት ክፍያውን መክፈል Eንደማይጠበቅባቸው የሚያሳይ Eንጅ ተጠሪው ካልፈለጉ ላለመክፈል የሚችሉበት ምክንያት የሚሳጣቸው Aይደለም። በመሆኑም የስር ፍ/ቤት ክሱን ተቀብሎ ግራ ቀኙን በክፍያ መጠኑ Aከራክሮ ተገቢውን መወሰን ሲገባው ክሱ ተቀባይነት የለውም በማለት የሰጠው ውሳኔ የAመልካች የስልክ Aገልግሎት ከፍያን የመሰብሰብ መብት የሚከለክል በመሆኑ ውሳኔው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል። ከ/ፍ/ቤትም ይግባኙን መሰረዙ Aግባብ Aይደለም።
No topics extracted.
የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 56323 የካቲት 16 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔና ፍ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 46451 የካቲት 30 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ትEዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
ፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በፍሬ ጉዳዩ ላይ ግራ ቀኙን Aከራክሮና በAገልግሎት ክፍያ መጠኑ ላይ ያለው ክርክርም Aጣርቶ ተገቢውን ይወስን ዘንድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 341/1/ መሰረት ጉዳዩን መልሰናል። ይፃፍ።
ወጪና ኪሣራን በተመለከተ ግራ ቀኙ Eንዲቻቻሉ ብለናል።