No summary available.
ጥቅምት 19 ቀን 2AAA ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ፍስሐ ወርቅነህ ሂሩት መለሰ ተሻገር ገ/ሥላሴ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- ግሎባል Iንሹራንስ /A.ማ/ ካሣዬ ተ/Aረጋይና ተፈራ ደምሴ ጠበቆች ቀረቡ ተጠሪ፡- ንብ ትራንስፖርት /A.ማ/ - Aልቀረበም መዝገቡን መርምረን ቀጥሎ የተመለከተውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር Aቤቱታ ላቀርብ የቻለው Aመልካች በመድን ውል መሰረት ለደንበኛው የከፈለው ካሣ Eንዲተካለት በፍ/ከ/ፍ/ቤት በተጠሪ ላይ ክስ መስርቶ ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን Aከራክሮ ጉዳት የደረሰው ከAቅም በላይ በሆነ ምክንያት ስለሆነ ተጠሪ ካሣ ለመክፈል ኃላፊነት የለበትም በማለት ውሣኔ የሰጠ ሲሆን የፍ/ጠ/ፍ/ቤትም ይሄው ውሣኔ ጉድለት የለበትም በማለቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት ተጠሪ ቅሬታ በማቅረቡ ነው።
የጉዳዩ Aመጣጥም ባጭሩ ሲታይ Aመልካች በተጠሪ ላይ በፍ/ከ/ፍ/ቤት ባቀረበው ክስ ደንበኛ የሆነው ፔትራም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኀበር በጅቡቲ በኩል ከውጭ ወደ Aዲስ Aበባ ለሚያስመጣው 9,6AA (ዘጠኝ ሺህ ስድስት መቶ) ካርቶን Eርሾ በጉዞ ላይ ለሚደርስበት ማንኛውም Aደጋ ከሣሽ የመድን ሽፋን የሰጠ ሲሆን የመድን ሽፋን ከተሰጠው 9,6AA (ዘጠኝ ሺህ ስድስት መቶ) ካርቶን Eርሾ ውስጥ 3,2AA (ሦስት ሺህ ሁለት መቶ) ካርቶን የAጓዡ የተከሣሽ በሆነ የጭነት መኪና ተጭኖ ከጅቡቲ ወደ A/Aበባ በመጓዝ ላይ Eንዳለ ከመኪናው በተነሣ Eሣት ጭነቱ በሙሉ ወድሟል። በIንሹራንስ ፖላሲው ላይ 9,6AA (ዘጠን ሺህ ስድስት መቶ) ካርቶን Eርሾ የመድን ዋስትና የተገባው ለብር 2,A66,A45.66 (ሁለት ሚላየን ስልሳ ስድስት ሺህ Aርባ Aምስት ከስልሳ ስድስት) ሲሆን ለወደመው 3,2AA (ሦስት ሺህ ሁለት መቶ) ካርቶን Eርሾ ብር 688,681.87 (ስድስት መቶ ሰማኒያ ስምንት ሺህ ስድስት መቶ ሰማኒያ Aንድ ከሰማኒያ ሰባት) ስለሚሆን በዚሁ መሰረት ከሣሽ በመድን ሰጭነቱ ይህንኑ ብር 688,681.87 ለደንበኛው ለፔትራም ኃ/የተ/የ/ማኀበር የከፈለ ሲሆን ተከሣሽ ይህንን ገንዘብ ለመክፈል ፈቃደኛ ስላልሆነ ገንዘቡን ከወለድ ወጭና ኪሣራ ጋር Eንዲከፍል ይወሰንልኝ በማለት ጠይቋል።
የAመልካች ክስና ማስረጃ ለተጠሪ ደርሶ በሰጠው መልስ ጉዳቱ መድረሱን ሣይክድ የተከሣሽ ንብረት የሆነው ከባድ የጭነት ተሽከርካሪ በጥቅምት 6 ቀን 1996 ዓ.ም የደረሰበት የEሣት ቃጠሎ Aደጋ ድንገተኛ ደራሽና ያልታሰበ የመኪናው ሾፍር ቃጠሎውን ለመከላከል ባደረገው ሙከራ ሰውነቱ Eንደተቃጠለና የተሽከርካሪውም ሞተር Aዲስ መሆኑን ከዚህ በፊት ምንም ዓይነት Aደጋ Eንዳላጋጠመው Aደጋው ፍፁም ላመልሱት የማይቻል በሹፍሩም ሆነ በAካባቢው ከነበሩ ሰዎች Aቅም በላይ የሆነ ከፍተኛ ኃይል /force majeure/ ስለሆነ ከንግድ ሕግ ቁጥር 591 Aኳያ ተከሣሽ ኃላፊነት ስለማይኖርበት ክሱ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል።
የግራ ቀኙ ክርክር በዚህ መልኩ የቀረበለትም የፍ/ከ/ፍ/ቤት ተከሣሽ ሲያጓጉዘው በነበረ Eቃ ላይ ጉዳት የደረሰው ከAቅም በላይ በሆነ ሁኔታ ነው ወይንስ Aይደለም ጉዳቱ የደረሰው ከAቅም በላይ በሆነ ሁኔታ Aይደለም የሚባል ከሆነ ተከሣሽ በከሣሽ የተጠየቀውን ገንዘብ የመክፈል ግድታ Aለበት ወይ? የሚሉትን ጭብጦች መሰርቶ ጉዳዩን መርምሯል።
በዚህም መሰረት የመጀመሪያውን ጭብጥ በተመለከተ በጅቡቲ የሚገኘው ኤክስፐርት በAደጋው ቦታ በመሄድ ሰለAደጋው Aደራረስ ባቀረበው ሪፖርት መኪናው ከነጭነቱ ሙሉ በሙሉ በEሣት መቃጠሉንመ፣ Eሣቱ ላነሣ የቻለው የኤክትሪክና የመካኒክ ሲስተሙ ድክመት ስለገጠመው በኤልክትሪክ መስመሩ ላይ ከፍተኛ ኃይል ያለው ኬብል ሥራውን ስላቋረጠና 88 89 ከብረት ጋር ስለተፋጨ የኤልክትሪክ ጭረት ተነስቶ ኃይለኛ ንፋስ በመኖሩ ተቀጣጣይ የሆኑት Aካሎች በEሣት ተያይዘው Eሣቱም ተስፋፍቶ ወደ ተሣቢው ስለደረሰ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሲሆን ልላው በማስረጃነት የቀረበውና Aሽከርካሪው ለፖላስ በሰጠው ቃል መኪናውን ከጅቡቲ ወደ A/Aበባ Eያሽከረከረ ሲጓዝ በመኪናው ጋቢና የEሣት ሽታ Eንደሸተተውና የተሣቢውን ጭነት ሲመለከት Eንደተቃጠለና በወቅቱም ኃይለኛ ንፋስ ስለነበር መኪናውን Aቁሞ ወርዶ Eሣቱን ለማጥፋት Eንደሞከረ በዚህ ጥረቱም Eጁን Eንደተቃጠለ የEሣቱን መንስኤ በተመለከተ በመኪናው ውስጥ የኮንታክት ችግር ያስነሣ Eንደሚመስለው ነገር ግን ሞተሩ Aዲስ መሆኑንና ከዚህ በፊት ምንም ዓይነት Aደጋ Eንዳላጋጠመው በመግለጽ ቃሉን Eንደሰጠ ያስገነዝባል።
የEቃ Aጓዥ በሚያጓጉዘው Eቃ ላይ ለሚደርስ ጥፋት ኃላፊ Eንደሆነ በንግድ ሕግ ቁጥር 59A ላይ የተደነገገ ቢሆንም በዚሁ ሕግ ቁጥር 591 ላይ ደግሞ በEቃው ላይ ጥፋት የደረሰው ከAቅም በላይ በሆነ ሁኔታ መሆኑን Aጓዡ ካስረዳ በኃላፊነት ተጠያቂ Eንደማይሆን ተመልክቷል።
No topics extracted.
ከላይ Eንደተገለፀው ተከሣሽ ባቀረበው ማስረጃ ለክሱ ምክንያት በሆነው ንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት Aጓዡ ላገምተውና ላያስቀረው በማይችል Aደጋ ምክንያት መሆኑን መገንዘብ የተቻለ ስለሆነ ተከሣሽ ለተከሰሰበት የንብረት ጉዳት ሙሉ በሙሉ ኃላፊነት የለበትም በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
ከሣሽም በዚሁ ውሣኔ ቅር በመሰኘት የይግባኝ ቅሬታውን ለፍ/ጠ/ፍ/ቤት ቢያቀርብም የፍ/ከ/ፍ/ቤት ውሣኔ ጉድለት የለበትም በማለት በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 337 መሰረት ይግባኙን ሰርዟል።
ከዚህ በኋላም ከሣሽ (የAሁን Aመልካች) የሰበር Aቤቱታ ለዚህ ሰበር ችሎት Aቅርቦ ይህ ሰበር ችሎት የቀረበውን የሰበር Aቤቱታ መርምሮ በEርሾው ላይ የደረሰው ቃጠሎ ከAቅም በላይ ምክንያት ስለመሆኑ ከሕጉ Aኳያ ተመርምሮ ላወሰን Eንደሚገባው በማመኑ ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
በAጠቃላይ የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን ይህ ችሎትም መዝገቡን መርምሯል።
ከላይ Eንደተመለከተውም Aመልካች ያቀረበው ክስ ተቀባይነት ሣያገኝ የቀረው ቃጠሎው የደረሰው ከAቅም በላይ በሆነ ምክንያት ነው በሚል ነው።
በመሆኑም Aደጋው የደረሰው ከAቅም በላይ በሆነ ሁኔታ ነው? ወይንስ Aይደለም? የሚለው ጭብጥ ተመርምሮ ምላሽ ማግኘት የሚገባው ነው።
Aንድ Aጓዥ በከፊል ወይም በሙሉ Eቃዎች ወይም የተመዘገቡ ጓዞች ሲጠፉ ወይም ጉዳት ሲያገኛቸው ወይም የማስረከቢያው ጊዜ ቢዘገይ በኃላፊነት Eንደሚጠየቅ የንግድ ሕግ ቁጥር 59A የሚያመለክት ሲሆን Aጓዡ ከዚህ ኃላፊነት የሚድነው ደግሞ ንብረቱ ላጠፋ፣ ጉዳት ላደርስበት ወይም ላዘገይ የቻለው ከAቅም በላይ በሆነ ምክንያት ወይም በEቃው ውስጣዊ ጉድለት ምክንያት ወይም በላኪና በተቀባዩ ጥፋት ምክንያት ሲሆን Eንደሆነ በዚሁ የንግድ ሕግ በቁጥር 591 ላይ ተመልክቷል።
የግራ ቀኙ ግንኙነትን የሚገዛው ይሄው የንግድ ሕጉ ስለሆነ ክርክሩ መታየትም ያለበት ከዚሁ የንግድ ሕጉ ድንጋጌዎች Aኳያ ነው። ይሁንና በንግድ ሕጉ ውስጥ "ከAቅም በላይ የሆነ ሁኔታ" ማለት ምን ማለት Eንደሆነ የተመለከተ ነገር ስለልለ ትርጉሙን ለማወቅ ከልዩ ሕጉ ወደ ጠቅላላ ሕጉ ማለትም ወደ ፍ/ብ/ሕጉ በተለይም ደግሞ ስለውሎች በጠቅላላው ስለሚመለከቱ ድንጋጌዎች ማምራት የግድ ይሆናል። በዚህ መሰረትም ከAቅም በላይ የሆነ ሁኔታ Aለ ለማለት የሚቻለው መቼ Eንደሆነ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.1792 ላይ የተመለከተ ሲሆን ይህም ድንጋጌ ከAቅም በላይ የሆነ ላመልሱት የማይቻል ኃይል ደርሷል የሚባለው ባለEዳው ባላሰበው ነገር ድንገት ደራሽ ሆኖበት ግድታውን Eንዳይፈጽም ፍፁም መሰናክል በሆነ Aይነት የሚያግደው ነገር ባጋጠመ ጊዜ Eንደሆነ ተደንግጓል። በዚሁ Aንቀጽ ንUስ ቁጥር 2 ላይ ደግሞ በAEምሮ ግምት ባለEዳው ቀደም ብሎ ላያስብበት የሚችል መሆኑ የታወቀ Aንድ ድንገተኛ ደራሽ ነገር ወይም ለውሉ Aፈፃፀም ከባድ የሆነ ወጭ በባለEዳው የሚደርስበት ቢሆን ከAቅም በላይ የሆነ ኃይል ነው ተብሎ Eንደማይገመት ተመልክቷል።
በመሆኑም በEነዚህ የሕጉ ድንጋጌዎች መሰረት ከAቅም በላይ የሆነ ሁኔታ ተከስቷል ላባል የሚችለው ባለEዳው በምንም መልኩ በቅድሚያ ላያስበው ወይም ላገምተው የማይችል ክስተት ሲፈጠር ነው። ነገር ግን ባለEዳው ሁኔታው ላፈጠር ወይም ላከሰት Eንደሚችል ቀድሞ ላገመት ወይም ላያስብና ጥንቃቄ ላያደረግበት የሚችል ከሆነ ሁኔታው ድንገተኛ ደራሽ ነገር ቢሆን Eንኳን ከAቅም በላይ የሆነ ነገር ተብሎ Eንደማይገመት መገንዘብ ይቻላል።
ወደተያዘው ጉዳይ ስንመለስም የሥር ፍ/ቤቶች ተጠሪውን ከኃላፊነት ነፃ ያደረጉት የክሱ ምክንያት የሆነው ንብረት በቃጠሎ ላወድም የቻለው ተሽከርካሪው የኤልክትሪክና የመካኒክ ሲስተሙ ድክመት ስለገጠመው በኤልክትሪክ መስመሩ ላይ ከፍተኛ ኃይል ያለው ኬብል ስራውን ስላቋረጠ ከብረት ጋር በመፋጨቱ ምክንያት በተነሣው Eሣት ስለሆነና ይህም Aጓዡ ላገምተውና ላያስቀረው የማይችል በመሆኑ ሁኔታው ከAቅም በላይ በሆነ ምክንያት የተፈጠረ ነው በማለት ነው። በጥቅሉ ሲታይ የሥር ፍ/ቤቶች ተጠሪ በኃላፊነት ተጠያቂ ላሆን Aይችልም ያሉት ከተሽከርካሪው የቴክኒክ ችግር ጋር በተያያዘ ነው።
ይሁንና የተሽከርካሪው ባለቤትና Aጓዥ የሆነው ተጠሪ ተሽከርካሪውን በሚገዛበት ጊዜ የቴክኒክ ደኀንነቱ Aስተማማኝ መሆኑን ለሥራ ከሚሰማራበት Aገርም ሆነ Aካባቢ የAየር ንብረት ጋር ተስማሚ መሆኑን Aጣርቶ ተሽከርካሪውን መግዛት Eንዳለበት የሚታመን ከመሆኑም በላይ በዚህ ረገድ Aስፈላጊውን ጥንቃቄ Aድርጎ ግዢውን ከፈፀመ በኋላም ቢሆን ለሥራ በተሰማራበት Aካባቢ ምንም ዓይነት የቴክኒክ ችግር Eንዳያጋጥመው ለጉዞ ከመሰማራቱ በፊትና በጉዞ በየጊዜው ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅበታል። ይህንን ሣያደርግ ቀርቶ ጉዳት ቢደርስ Eንደሕጉ Aገላለጽ ከAቅም በላይ የሆነ ሁኔታ ላባል Aይችልም። ስለሆነም ተጠሪ ከላይ Eንደተመለከተው በተሽከርካሪው ግዢ ወቅትም ሆነ ከግዢ በኋላ ተሽከርካሪው የቴክኒክ ችግር Eንዳይደርስበት Aስቀድሞ ላገምተውና ላከላከለው ሲገባ ይህንን የመከላከልና የጥንቃቄ Eርምጃ Aስቀድሞ ሣይወስድ በመቅረቱ በጉዞ ላይ ተሽከርካሪው በደረሰበት የቴክኒክ ብልሽት ምክንያት በተነሣው ቃጠሎ የመድን ሽፋን የተገባለት ንብረት መውደሙ የተረጋገጠ ስለሆነ ሁኔታው ከAቅም በላይ በሆነ ምክንያት ነው ላባል ስለማይችል የሥር ፍ/ቤቶች ለንብረቱ መቃጠል ምክንያት የሆነው Aደጋው ከAቅም በላይ የሆነ ሁኔታ ነው በማለት የሰጡት ትርጉም የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ 6. የፍ/ከ/ፍ/ቤት በመ.ቁ. 41594 በታህሳስ 26 ቀን 1998 ዓ.ም Eንደዚሁም የፍ/ጠ/ፍ/ቤት በመ.ቁ. 23649 በግንቦት 21 ቀን 1998 ዓ.ም ጉዳቱ የደረሰው ከAቅም በላይ በሆነ ሁኔታ ነው በማለት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ ስለተገኘ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል። ይፃፍ።
በተጠሪ መኪና ተጭኖ ሲጓጓዝ የነበረውና Aመልካች የመድን ሽፋን የሰጠው Eርሾ በቃጠሎ ጉዳት ላደርስበት የቻለው ከAቅም በላይ በሆነ ምክንያት Aይደለም ተብሎ ተወስኗል።
ቃጠሎው የደረሰው ከAቅም በላይ በሆነ ምክንያት Aይደለም ተብሎ የተወሰነ ስለሆነ የፍ/ከ/ፍ/ቤት የካሣ ክፍያ ጥያቄውን Aስመልክቶ የያዘውን ሁለተኛውን ጭብጥ በተመለከተ ከግራ ቀኙ ክርክርና ማስረጃ Aኳያ መርምሮ የበኩሉን ውሣኔ Eንዲሰጥበት ጉዳዩ ተመልሶለታል።
የዚህን ፍ/ቤት ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።