No summary available.
የሰ/መ/ ጥቅምት 12 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ ተገኔ ጌታነህ ተሻገር ገ/ሥላሴ መስፍን Eቁበዮናስ ብርሃኑ Aመነው Aመልካች፡- ወ/ሮ ዘለቃሽ መንግሥቱ ቀረቡ።
ተጠሪ፡- 1A Aለቃ ታደሰ ወርቁ ቀረበ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፈርደናል።
ለዚህ ፍርድ ቤት ለቀረበው Aቤቱታ መነሻ የሆነው Aመልካች ለፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በግንቦት 24 ቀን 1996 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ ለተጠሪው በጥር 1989 ዓ.ም. ያደረግሁት የስጦታ ውል በማታለል የተደረገና ተጠሪውም ላጦረኝ ሲገባ ስለማይጦረኝ ውሉ ይፍረስልኝ በማለት ያቀረበችው ክስ ተቀባይነት በማጣቱና ይግባኝ Aቅርባም ይግባኙ በመሰረዙ ነው።
የሥር ፍ/ቤት ክሱን ውድቅ ያደረገው በጉድለት ምክንያት ውል Eንዲሰረዝ የሚቀርብ ጥያቄ በሁለት ዓመት ይርጋ ቀሪ ይሆናል፤ በማለትና ተጠሪ Aመልካችን የመጦር ግድታ በውሉ Aልተሰጠውም በማለት ነው።
Eኛም የስጦታ ውሉ ላፈርስ የሚገባው መሆን ያለመሆኑን Aይፈርስም ከተባለስ ተጠሪው ስጦታ ሰጪዋን Aመልካችን ላጦር ይገባል ወይንስ Aይገባም የሚሉትን ነጥቦች መርምረናል።
የመጀመሪያውን ነጥብ በተመለተ Aመልካች ለተጠሪው የስጦታ ውል ያደረገችው ጥር 27 ቀን 1989 ዓ.ም ሲሆን ይህ የስጦታ ውል Eንዲፈርስ ክስ የመሰረተችው ደግሞ በግንቦት 24 ቀን 1996 ዓ.ም ነው። የፍ/ሕ/ቁ 2441/1/ ሥጦታ Eንዲቀነስ ወይም Eንዲሻር የሚቀርብ ጥያቄ ሥጦታው ከተደረገበት ቀን Aንስቶ Eስከ ሁለት ዓመት ካልቀረበ በቀር ዋጋ የልለው Eንደሆነ 54 55 ደንግጓል። Aመልካች የስጦታ ውሉ Eንዲፈርስ ክስ የመሰረተችው የስጦታ ውሉ ከተደረገ ከ7 ዓመታት በኋላ ነው።
በመሆኑም የስጦታ ውሉ Eንዲፈርስ የቀረበውን ክስ የሥር ፍ/ቤቶች ያለመቀበላቸው የሚነቀፍ Aይደለም።
በልላ በኩል ግን ስጦታ ተቀባይ በስጦታ ውሉ ላይ በግልጽ ያልተመለከተ Eንኳን ቢሆን ሰጪው በድኀነት ላይ ከወደቀ ቀለብ የመስጠት ግድታ Eንዳለበት በፍ/ሕ/ቁጥር 2458/1/ ላይ ተደንግጓል። የሥር ፍ/ቤት ጥያቄውን ከዚህ ሕግ Aኳያ መመርመር ሲገባው ተጠሪው Aመልካችን ለመጦር የውል ግድታ የላቸውም ማለቱ ከሕጉ የሚፃረር ሆኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ
የስጦታ ውሉ Aይፈርስም በማለት በሥር ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
ተጠሪ ለAመልካች ቀለብ የመስጠት የውል ግድታ የለበትም በሚል የተሰጠው የውሣኔ ክፍል ግን ተሽሯል። Aመልካች በድኀነት ላይ ወድቃ የምትገኝ ከሆነ ተጠሪ ቀለብ የመክፈል ግድታ በሕጉ የተጣለበት በመሆኑ ይህንኑ በማስረጃ Aጣርቶ ተገቢውን Eንዲወስን የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 343/1/ መሰረት ታዟል። ይፃፍ።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት።
ነ/ዓ
ግንቦት 21 ቀን 2AAA ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ መድህን ኪሮስ Aላ መሐመድ ሱልጣን Aባተማም Aመልካች፡- ወ/ሮ ፀሐይነሽ ይሕደጎ ተጠሪዎች፡-
ጉዳዩ የቀረበው Aመልካች የትግራይ ክልል፤ ማEከላዊ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር A54A9 ሚያዚያ 17 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔና የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የመዝገብ ግንቦት 7 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ትEዛዝ Eንደዚሁም የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 2A118 ሐምል 11 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ Ãh`M” በማለት የሰበር Aቤቱታ በማቅረባቸው ነው። ፍሬ ጉዳዩም ተጠሪዎች በከፍተኛው ፍርድ ቤት በከሣሽነት ቀርበው ተከሣሽዋ የAሁን Aመልካች የAባታችን የAስር Aለቃ በርሄ ምሩፅ የጋራ ንብረት የሆነ ቤት የያዘች ስለሆነና Eኛ ደግሞ የAባታችን ወራሽ ስለሆን Eንድታካፍለን ውሣኔ ይሰጥልን በማለት ክስ Aቅርበዋል። Aመልካች በበኩሐ ተጠሪዎች ያቀረቡት ክስ ተገቢ Aይደለም። ምክንያቱም ሟች ቤቱን ለEኔና ለሁለት ልጆቹ 56 57 የካቲት 5 ቀን 1989 በውልና ማስረጃ በተመዘገበ የቁም ኑዛዜ ሰጥቶናል የሚልና ልላውን ቤት በተመለከተ Eኔ ነኝ የሰራሁት የሚል መከራከሪያ Aቅርባለች። ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ማስረጃና ክርክር ከመረመረ በኋላ፣ በውልና ማስረጃ የፀደቀው የቁም ኑዛዜ ስጦታ ሰነድ በዳኛ ፊት ወይም በAዋዋይ Aካል የተደረገ Aይደለም፣ ስጦታው በግልጽ ኑዛዜ በሚደረግበት ፎርም መፈፀም ያለበት በመሆኑና በሰነዱ ላይ የፈረሙት ሶስት ምስክሮች ስለሆኑ በፍታብሕር ሕግ ቁጥር 881 የተደነገገውን Aያሟላም። ስለዚህ ሕጋዊ ውጤት ስለልለው ተከሣሽ የተከሣሾችን የውርስ ድርሻ ያካፍሉ በማለት ወስኗል።
No topics extracted.
Aመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት Aቅርበው፤ የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ የሚነቀፍበት የሕግ ወይም የፍሬ ጉዳይ ስህተት ስለልለ ይግባኙ ፍሬ የለውም በማለት ሰርዞታል።
Aመልካች ይኸ ትEዛዝና የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት Aለበት በማለት ጉዳዩን ለትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት Aቅርባ ሰበር ሰሚው ችሎት የግራ ቀኙን የሕግ ክርክር ከሰማ በኋላ ሟች ያደረገው ሰነድ የቁም ኑዛዜ ስጦታ የሚል ርEስ ያለው ሲሆን ድርሻዩን ለሁለቱ ልጆች ሰጥቻለው ካለ በኋላ በፍታብሕር ሕግ ቁጥር 937 መሰረት ስጦታው Eንዲፀድቅላቸው የሚል በመሆኑ ሰነዱ ኑዛዜ ነው።
ሆኖም ኑዛዜው ልሎቹን ልጆች ከውርስ የሚነቅል በመሆኑና የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 937 መሰረት ሟችን በዚህ Aይነት መንገድ ተወላጆቹን ከውርስ መንቀል ስለማይችል፣ የሟችን ድርሻ ልሎች ልጆችም Eኩል የመካፈል መብት Aላቸው በማለት በልዩነት የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት ወስኗል። ከተሰየሙት Aምስት ዳኞች ወስጥ ሁለቱ ስጦታ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2443 ግልጽ ኑዛዜ በሚደረግበት Aሰራር መሆን Eንዳለበት ስለሚደነግግ ክርክር የተነሣበት ሰነድ በፍታብሕር ሕግ ቁጥር 882 መሰረት የተፈፀመ በመሆኑ ሕጋዊ የስጦታ ሰነድ ስለሆነ ስጦታ ከተደረገላቸው ልጆች ውጭ ያሉት የሟች ልጆች ለመጠየቅ Aይችሉም በማለት በልዩነት ሀሣባቸውን Aስቀምጠዋል።
Aመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ባቀረባቸው የሰበር Aቤቱታ በየደረጃው ያሉ ፍርድ ቤቶች የተለያዩ መሰረታዊ የሕግ ስህተቶችን ሰርተዋል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት በውልና ማስረጃ የተረጋገጠውንና ሶስት ምስክሮች የፈረሙበትን ሰነድ ኑዛዜው በAራት ምስክሮች ያልተፈረመ ስለሆነ ሕጋዊ ውጤት የለውም በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ሲሆን፤ የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ኑዛዜው፣ ልሎቹ ልጆችን ከውርስ የሚነቅል በመሆኑ ሕጋዊ ውጤት የለውም የሚል ውሣኔ ሰጥቷል። ስጦታ ሰጭው ገና በቁም ሣሉ ያደረጉት የቁም ስጦታ ሆኖ Eያለ የሥር ፍርድ ቤት ኑዛዜ ነው ማለታቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት Aመልክተዋል። ተጠሪዎች በበኩላቸው ሰነዱ "የኑዛዜ የቁም ስጦታ" የሚል በመሆኑ ሟች ያደረገው ኑዛዜ Eንጅ የቁም ስጦታ ውል Aይደለም። ከዚህ በተጨማሪ ኑዛዜው በሕግ የተቀመጡ ፎርማላቲዎችን ስለማያሟላ ውጤት የለውም መባሉ ተገቢ ነው በማለት ተከራክሯል። Aመልካች የመልስ መልስ Aቅርበዋል።
ከሥር የክርክሩ Aመጣጥና በሰበር Aመልካችና ተጠሪዎች ያቀረቡት የሕግ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን፣ Eኛም የግራ ቀኙን የመከራከሪያ ነጥቦችና በየደረጃው ያሉ ፍርድ ቤቶች የሰጡትን ውሣኔ መርመረናል። ጉዳዩን Eንደመረመርነውም
58 59 የሚለው ነጥብ በዝርዝር ማየትና መወሰን Aስፈላጊ ሆኖ Aግኝተነዋል።
የመጀመሪያው ነጥብ በተመለከተ፣ ሟች በሕይወት Eያሉ ከሚመለከተው የውልና ማስረጃ ጽ/ቤት በመቅረብ " የቁም ኑዛዜ ስጦታ" የሚል ሰነድ የካቲት 6 ቀን 1989 ዓ.ም Aድርገዋል። ይኸ ሟች የተውት ሰነድ መሰረታዊ ባህሪ፣ Aመልካችና ተጠሪ ለሚያደርጉት ክርክር መነሻ ነው። ስለሆነም ሟች ባደረጉት "የቁም ኑዛዜ ስጦታ" ላይ ተፈፃሚነት ያለው የሕግ ክፍል መለየት፤
የመጀመሪያውና ቀዳሚው ጉዳይ ነው። ከዚህ Aንፃር ስለ ስጦታ ውል በፍትታብሕር ሕግ ውስጥ የተደነገጉትን ድንጋጌዎች ስንመለከት የIትዮጵያ ሕግ "የስጦታ ውል" ወይም "ስጦታ" በማለት Eውቅና የሚሰጠው፣ ስጦታ ሰጭው ከመሞቱ በፊት የሕግ ውጤት Eንዲኖራቸው Aስቦ የሰጣቸው ስጦታዎችን ነው። የብዙ Aገሮች ሕግጋት ለሁለት ዓይነት ስጦታዎች Eውቅና Eና ውጤት ይሰጣሉ።
Eነርሱም ማለት ሟች በሕይወት Eያለ ተፈፃሚ ለሚሆን ስጦታ /Donation enter vivos/ Eና ሟች ከሞተ በኋላ ተፈፃሚ የሚሆን ስጦታ" Donation Martis causa በማለት ይሰይሟቸዋል።
የIትዮጵያ ሕግ ስጦታ ነው በማለት Eውቅና Eና ጥበቃ ለሚሰጠው ለመጀመሪያው Aይነት ስጦታ ማለትም ሟች ከመሞቱ በፊት ተፈፃሚ Eንዲሆን Eና ሕጋዊ ውጤት Eንዲኖረው Aስቦ ለሚሰጠው ስጦታ ነው። ሟች ከሞተ በኋላ ተፈፃሚ Eንዲሆን Aስቦ የሚያደርገው ስጦታ፣ የIትዮጵያ ሕግ ስጦታ ነው ብሎ Eውቅና Eና ጥበቃ Eንደማይሰጠውና Eንደዚህ Aይነት ስጦታ የውርስ ሕግ የኑዛዜ ድንጋጌዎች ተፈፃሚነት Eንዳላቸው "ሰጭው ሲሞት ይፈፀማሉ ተብለው በተወሰኑት ስጦታዎች ላይ ስለ ኑዛዜ የተደነገጉት ድንጋጌዎች ተፈፃሚዎች ይሆናሉ" በማለት የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2428 በግልጽ ይደነግጋል። ከዚህ Aንፃር ስንመለከተው የሟች " የቁም ኑዛዜ ስጦታ" ያደረጉት ስጦታው በሕይወት Eያሉ ተፈፃሚ Eንደሆን Aስበው ነው ወይስ ከሞቱ በኋላ ተፈፃሚነት Eንዲኖረው የሚለውን ነጥብ ስንመለከት በመጀመሪያ ሟች በግልጽ "የቁም ኑዛዜ ስጦታ" የሚል ርEስ የተጠቀሙ መሆኑና "ኑዛዜ" የሚለው ቃል ስጦታው ሟች ከሞተ በኋላ ተፈፃሚ የሚሆን Eንደሆነ ስለሚያመለክት፤
በሁለተኛ ደረጃ ሟች በቁም ኑዛዜ ስጦታ ያደረጉበት ቤት የባልና የሚስት የጋራ ንብረት በመሆኑና ጋብቻው በፍች ወይም በሞት ምክንያት ካልተቋረጠ በስተቀር ጋብቻው ፀንቶ ባለበት ጊዜ ባል ወይም ሚስት ከጋራ ንብረቷ Aንዱን ክፍል ለይቶ መስጠት ስለማይችልና በሶስተኛ ደረጃ ሟች ባደረጉት የቁም ኑዛዜ ስጦታ ጽሑፍና የጠቀሱት የሕግ ድንጋጌ፣ ማለትም የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 967 ሟች ከሞተ በኋላ ኑዛዜው ስለሚከፈትበት ቦታ የሚደነግግ በመሆኑ ሟች ያደረገው " የቁም ኑዛዜ ስጦታ" ሟች ከሞተ በኋላ፤ ተፈፃሚ Eንዲሆን Aስቦ ያደረገው በመሆኑ፤ በጉዳዩ ተጠቃሽ የሚሆኑትና ተፈፃሚነት ያላቸው ስለኑዛዜ የተደነገጉት ድንጋጌዎች ናቸው።
ሁለተኛውን ነጥብ በተመለከተ በማይንቀሣቀስ ንብረት ለመስጠት የሚደረግ የስጦታ ውል በግልጽ በሚደረግ ኑዛዜ Aስራር Aይነት ካልተደረገ ፈራሽ Eንደሚሆን የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2443 ይደነግጋል። ሟች ውል ለማዋዋል ስልጣን ባለው የውልና ማስረጃ ክፍል ሶስት፤ ምስክሮች ባሉበት "የቁም ኑዛዜ ስጦታ" Aድርጓል። ይኸም በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 882 የተደነገገውን ፎርም የሚያሟላ በመሆኑ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ሰነዱ የሕጉን ፎርም Aያሟላም በማለት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው። ስለሆነም ሟች ያደረጉት "የቁም ኑዛዜ ስጦታ" በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2443 Eና በፍታብሕር ሕግ ቁጥር 882 የተደነገጉትን የሕግ ፎርማላቲዎች የሚያሟላ ነው።
60 61 ሶስተኛውን ነጥብ በተመለከተ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ሟች ያደረገው የቁም ኑዛዜ ስጦታ የልሎችን ወራሾች ከውርስ መንቀል ውጤት Eንዳለው በመግለጽ ውድቅ Aድርጎታል። ሟች ከAንድ በላይ የሆኑ ልጆች ወይም ልሎች ወራሾች ቢኖሩትና ከነዚያ መካከል ለAንደኛው የኑዛዜ ስጦታ ቢያደርግ፣ የልሎቹን ወራሾች ከሟች ውርስ መነቀል Aያስከትልም። ይህንንም የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 913 የኑዛዜው ቃል የተናዛዡን ተቃራኒ ሀሣብ የሚገልጽ ካልሆነ በቀር ከውርስ ሀብት Aንድ ድርሻ ወይም Aንድ ንብረትን ሟቹ ለወራሾቹ መስጠቱ ተራ የሆነ የክፍያ ደንብ Eንጅ Eንደ ኑዛዜ ስጦታ ነው ተብሎ Aይቆጠርም በማለት ይደነግጋል። በያዝነው ጉዳይም የሟችን ልዩ ሀሣብ የቀረበው ሰነድ የማያሣይ በመሆኑ በዚህ ድንጋጌ መሰረት ሟች የውርስ ንብረት ሲደለደል ቤቱ "የቁም ኑዛዜ ስጦታ" ላደረጉላቸው ልጆች Eንዲደርሣቸው ያላቸውን ፍላጎት ከሚገልጽ በስተቀር ከሁለቱ ልጆች የተለየ የኑዛዜ ስጦታ መስጠቱን የሚያመለከት Aይደለም። ስለሆነም ቤቱን ሙሉ በሙሉ "የቁም ኑዛዜ ስጦታ" ላደረጉላቸው ልጆች ለማስተላለፍ የሚችል ሰነድ Aይደለም።
ከዚሁ ጋር መታየት ያለበት፤ ሟች ያደረጉት የቁም ስጦታ Aይደለም Eንጅ ቢሆንም Eንኳን ተጠሪዎች የውርሱን ንብረት የመካፈል መብታቸው Eንደማይገደብ ስለ ውርስ ንብረት ክፍያ በተለይም የጋራ ወራሾች ስለሚመልሷቸው ንብረቶች የተደነገጉትን ድንጋጌዎች በማገናዘብ ለመረዳት ይቻላል። ስለሆነም በውጤት ደረጃ Aመልካች የሟች ድርሻ ለተጠሪዎችና ለልሎች ወራሶቹ የማካፈል ግድታ Aለበት በማለት የትግራይ ክልል በየደረጃው ያሉ ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ የሚቀየር Aይደለም። ነገር ግን በሕግ Aተረጓጎም ወቅት የተለያዩ ስህተቶችን የፈፀሙ ሆነው Aግኝተነዋል። ስለሆነም በውሣኔው ተጠቃሽ ያደረጓቸውን የሕግ ድንጋጌዎች ከላይ በተገለፀው መንገድ በማስተካከል በውጤት ደረጃ ግን የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት Eና ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡትን ውሣኔ Aጽንተናል።
ው ሣ ኔ
ሟች ያደረጉት " የቁም ኑዛዜ ስጦታ" ተራ የክፍያ ደንብ Eንጅ የተጠሪዎች የውርሱን ንብረት የመካፈል መብት የማይገድብ በመሆኑ Aመልካች ለተጠሪዎች የውርሱን ንብረት የማካፈል ግድታ Aለበት ብለናል።
ለውሣኔያቸው መሰረት ያደረጓቸው የሕግ ድንጋጌዎች ትርጉምና ተፈፃሚት ተሻሽሎ ውሣኔያቸው በውጤት ደረጃ የፀና መሆኑን Eንዲያውቁት ይፃፍ።
ይህ ውሣኔ በፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ግንቦት 21 ቀን 2AAA ዓ.ም በሙሉ ድምጽ ተሰጠ።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት ተ.ወ ¨<KA‹ wÉ`
ኀዳር 24 ቀን 2AAA ዓ.ም.
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ፍስሐ ወርቅነህ ሐጎስ ወልዱ ሒሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- ወ/ሮ ማና ኃ/ሚካኤል - ጠበቃ ገ/EግዚAብሕር ተስፋዬ ተጠሪ፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥሎ የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር Aቤቱታ ላቀርብ የቻለው 1ኛ ተጠሪ በትግራይ ክልል ምEራባዊ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ባልና ሚስት የሆኑት 2ኛ ተጠሪና Aመልካች ብር 53‚398 (ሃምሳ ሦስት ሺህ ሦስት መቶ ዘጠና ስምንት) ተበድረውኝ ለብድሩ Aከፋፈል ቼክ የሰጡኝ ቢሆንም ገንዘቡ ያልተከፈለኝ ስለሆነ ይህንኑ ገንዘብ ከወለድ ወጭና ኪሣራ ጋር Eንዲከፍሉ ይወሰንልኝ የሚል ክስ Aቅርበው ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን Aከራክሮ ለክሱ ምክንያት የሆነውን ገንዘብ በብድር ከከሳሽ የወሰዱት 2ኛ ተጠሪ Aቶ ገ/Iየሱስ ገ/ፃዲቅ ብቻ ከመሆናቸውም በላይ ብድሩም ለትዳር ጥቅም ስለመዋሉ ያልተረጋገጠ ስለሆነ 2ኛ ተጠሪ ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ለከሳሽ Eንዲከፍሉ 1ኛ ተጠሪን በተመለከተ ገንዘቡን ላከፍሉ Aይገባም በማለት ውሣኔ ሰጥቶ ከሳሽ በዚሁ ውሣኔ ቅሬታ Aድሮባቸው የይግባኝ ቅሬታ ለክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት Aቅርበው ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤትም በበኩሉ ግራ ቀኙን Aከራክሮ የሥር ተከሳሾች ባልና ሚስት በመሆን ሕይወታቸውን በንግድ ሥራ የሚመሩ Aንደመሆኑ መጠን በንግድ ሕ/ቁ. 19 መሰረት Aንደኛው ተጋቢ የሚገባው Eዳ ልላውንም ተጋቢ የሚያስገድድ በመሆኑ የከፍተኛው ፍ/ቤት በዚሁ መሰረት ሚስትንም የEዳው ተጠያቂ ማድረግ ሲገባው ተጠያቂነት 6564 የለባትም በማለት ውሣኔ መስጠቱ ከሕጉ ጋር ያልተገናዘበ ነው በማለት ይህንኑ ውሣኔ ሽሮ ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ሁለቱም ተከሳሾች Eንዲከፍሉ በማለት የበኩሉን ውሣኔ ሰጥቷል። በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘትም የAሁን Aመልካች የሰበር Aቤቱታ ለክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት Aቅርበው ክሱ በቼክ ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ሰበር ችሎቱ ጉዳዩን መርምሮ ለመወሰን ሥልጣን የለውም በማለት ትEዛዝ በመስጠቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት Aመልካች ቅሬታ በማቅረባቸው ነው።
ይህ ሰበር ችሎትም በAመልካች በኩል የቀረበውን Aቤቱታ መርምሮ Aመልካች፣ ቼክ ሳትሰጥ በቼክ ተከሳ በቼኩ ላይ የተመለከተውን Eዳ በንግድ ሕግ ቁጥር 19 መሰረት የንግድ Eዳ ወይም Aግባብ ባለው የቤተሰብ ሕግ Aመልካችን የሚመለከት Eዳ መሆኑ በማስረጃ ሳይጣራ በAመልካች ላይ መፈረዱ ለሰበር ቀርቦ መጣራት Eንዳለበት በማመኑ ተጠሪዎችን በመጥራት ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
ምላሽ ማግኘት የሚገባውም የክርክሩ ጭብጥ 1ኛ ተጠሪ ክስ ያቀረቡበትን ገንዘብ Aመልካች ለመክፈል ይገደዳሉ የሚለው በመሆኑ ይህንኑ ጭብጥ በመያዝ የሰበር Aቤቱታው ከሕጉ ጋር ተገናዝቦ ተመርምሯል።
በቅድሚያም 1ኛ ተጠሪ በትግራይ ክልል ከፍተኛ ፍ/ቤት ክሱን ያቀረቡት በቼክ ላይ ተመስርተው ወይንስ በብድር የሚለውን ነጥብ ማየት ለጉዳዩ Aወሳሰን ጠቃሚ በመሆኑ ይህንኑ ተመልክተናል።
1ኛ ተጠሪ በክስ ማመልከቻቸው ላይ ገንዘቡ በምን ምክንያት ለከሳሾች Eንደተሰጠ ዘርዝረው ያቀረቡ Eንደመሆናቸው መጠን ክሱ በቼክ ላይ ተመስርቶ Eንዳልቀረበና ቼኩን Eንደተራ ማስረጃ በመቁጠር ክሱን Eንደመሰረቱ ለመገንዘብ ተችሐል። በተከሳሾች በኩል የሥር 2ኛ ተከሳሽ የAሁን 2ኛ ተጠሪ ገንዘቡን ከከሳሽ በብድር መውሰዳቸውን ያመኑ ሲሆን 1ኛ ተከሳሽ የAሁን Aመልካች ግን ብድሩን ክደዋል።
የብድሩ Eዳ በሥር 1ኛ ተከሣሽ በAሁኑ Aመልካች ከተካደ ደግሞ የብድሩን መኖር በተመለከተ Aግባብነት ያለውን ማስረጃ በማቅረብ የማስረዳት ሸክሙ የሚወድቀው በከሳሽ ላይ ይሆናል ማለት ነው። ነገር ግን በዚህ ረገድ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2472 ላይ Eንደተለከተው የሥር ከሳሽ የAሁን 1ኛ ተጠሪ Aግባብነት ያለውን ማስረጃ Aቅርበው ብድሩን በካዱት Aመልካች ላይ የብድሩን መኖር Aላስረዱም። ይህንንም መሰረት Aድርጎ የክልሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት Aመልካች ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ለመክፈል Aይገደዱም በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
በልላ በኩልም ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት Aመልካች Eዳው ይመለከታቸዋል በማለት ውሣኔ የሰጠው ከላይ Eንደተመለከተው Aመልካችና 2ኛ ተጠሪ ነጋድዎች ስለሆኑ ከ1ኛው ተጋቢ የሚጠየቅ የንግድ Eዳ በን/ሕ/ቁ.19 መሰረት ልላውንም ተጋቢ ስለሚመለከተው ኃላፊ ናቸው በማለት ነው። ነገር ግን ክሱ የቀረበው ከላይ Eንደተመለከተው በቼክ ላይ ተመስርቶ ሳይሆን በብድር ላይ ተመስርቶ ከመሆኑም በላይ ብድር መኖሩም በማስረጃ የተረጋገጠው በ1ኛው ተጋቢ ላይ ብቻ ነው። በAንድኛው ተጋቢ ብቻ በብድር መወሰዱ የተረጋገጠው ገንዘብ ከንግድ ሥራ ጋር በተያያዘ የተወሰደ ብድር ነው ለማለት የማይቻል ከመሆኑም በላይ ብድሩ ለጋራ ጥቅም መዋሉ ቢረጋገጥ Eንኳን የEዳው Aከፋፈል ወደ ጋራ ንብረት ወይንም ወደ ልላው ተጋቢ የግል ንብረት የሚሄደው በፍርድ Aፈጻጸም ጊዜ Eንጂ የብድር ውል ባልተዋዋለው ወገን ላይ ክስ ላመሰረትም ሆነ ፍርድ ላሰጥ Aይችልም።
ስለሆነም የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት Aመልካች ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ላከፍሉ ይገባል በማለት የሰጠው ውሣኔ ከንግድ ሕጉ ጋር የተጣጣመ ባለመሆኑ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል።
Aመልካች በዚሁ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ውሣኔ ቅሬታ Aድሮባቸው የሰበር Aቤቱታ ለክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችሎት ሲያቀርቡ ክሱ የቀረበው ከላይ Eንደተመለከተው በቼክ ላይ ተመስርቶ ሳይሆን በብድር ላይ ተመስርቶ ቼኩ በተራ ማስረጃነት የቀረበ በመሆኑ ጉዳዩን በሰበር ለማየት የሚችል ሆኖ ሳለ በቼክ ላይ ተመስርቶ የቀረበ ክስ በመሆኑ በሰበር ለማየት ስልጣን የለኝም በማለት Aቤቱታውን ሳይቀበል መቅረቱ በAግባቡ ሆኖ Aልተገኘም። ይሁንና 66 67 የክልሉም ሆነ የፍድራሉ ሰበር ችሎት የተቋቋሙበት ዓላማ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተትን ማረም በመሆኑ ጉዳዩን ወደ ክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት መመለስ ሳያስፈልግ ቀጥሎ የተመለከተው ተወስኗል።
ው ሣ ኔ
የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 19141 በሐምል 21 ቀን 1997 ዓ.ም. Eንደዚሁም የክልሉ ሰበር ችሎት በመ/ በ ጥቅምት 3A ቀን 1998 ዓ.ም. የሰጠው ትEዛዝ መሰረተዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የትግራይ ክልል ምEራባዊ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በግንቦት 23 ቀን 1997 ዓ.ም. ይህን ጉዳይ Aስመልክቶ Aመልካች ክስ በቀረበበት ጉዳይ ኃላፊ ላሆኑ Aይችሉም በማለት የሰጠው ውሣኔ ከሕጉ ጋር የተገናዘበ ሆኖ ስለተገኘ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ጸንቷል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።