No summary available.
የሰበር ፋይል ጥቅምት 5 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ መስፍን EቁበÄናስ ተሻገር ገ/ሥላሴ Aብዱራሂም Aህመድ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- Aቶ ማሞ ጐበና Aልቀረቡም ከተባለ በኋላ ቀረቡ ተጠሪ፡- Aቶ ወርቅነህ ተክለማርያም Aልቀረቡም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ ጉዳይ ለሰበር ላቀርብ የቻለው የሰበር Aመልካች (የሥር ከሣሽ) ግንቦት 28 ቀን 1998 ዓ.ም ፅፈው ባቀረቡት የሰበር ማመልከቻ መነሻነት ነው።
የጉዳዩ የሥር Aመጣጥ Aመልካች ለፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በAሁኑ የሰበር ተጠሪና (የሥር 2ኛ ተከሣሽ) በሥር 1ኛ ተከሣሽ (ጉዳያቸው በልሉበት የታየው) ላይ ያቀረቡት ክስ ከሥር 1ኛ ተከሣሽ ለነበሩት በጥቅምት 14 ቀን 1988 ዓ.ም በተፃፈ የሽያጭ ውል ላንድሮቨር መኪና በብር 14,000 (Aሥራ Aራት ሺህ) ሸጠው ከዚህ ውeØ ብር 10,000 (Aስር ሺህ) ተቀብለው ቀሪውን ብር 4,000 (Aራት ሺህ) በጊዜ ባለመክፈላቸው ብር 5000 (Aምስት ሺህ) Aድርገው ለመክፈል ተጨማሪ ውል ማድረጋቸውንና ያሁኑ ተጠሪም ባልተነጣጠለ ሃላፊነት ዋስ በመሆናቸው ዋናውን ገንዘብ ከነወለዱ ከወጪና ኪሣራ ጋር Eንዲከፍሉ የሚል ሲሆን ፍርድ ቤቱም ክስና ክርክሩን ከመረመረ በኋላ የሥር 1ኛ ተከሣሽ በቀረበው ክስ መሰረት Eንዲከፍሉ፣ያሁኑ ተጠሪ ግን ተራ ዋስ በመሆናቸው በርሣቸው ላይ የቀረበው ክስ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.1939 መሰረት ተቀባይነት የለውም በማለት ወስኗል፣ ውሳኔው በፍ/ከ/ፍ/ቤትም በይግባኝ ፀንቷል።
38 39 የሰበር ማመልከቻው የቀረበው የተጠሪን ዋስትና Aስመልክቶ በተሰጠው ውሣኔ ላይ ሲሆን ይህ የሰበር ሰሚ ችሎት ማመልከቻውን ከመረመረ በኋላ በተጠሪ ላይ ያልተወሰነው በAግባቡ መሆን Aለመሆኑን ለማጣራት ሲባል ተጠሪን Aስቀርቦ ለማከራከር ያዘዘ ቢሆንም ተጠሪ ለመቅረብ ፈቃደኛ ሆነው ባለመገኘታቸው ጉዳዩን በልሉበት Eንዲታይ Aዟል።
በዚህም መሰረት ፍርድ ቤቱ የሰበር ማመልከቻውን ከሥር ፍርድ ቤቶች ውሣኔና ከሕጉ ጋር በማገናዘብ መርም[ል።
ከፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ውሣኔ ላይ ለመረዳት Eንደተቻለው ተጠሪ ተራ ዋስ መሆናቸውንና በውሉም ስምምነት ላይ የሥር 1ኛ ተከሣሽ ገንዘቡን ሳይከፍሉ u=k\ ተጠሪ ሃላፊ ሆነው ገንዘቡን Eንደሚከፍሉ መገለፁን Aስፍሮ በተጠሪ ላይ የቀረበውን ክስ ግን በፍ/ብ/ሕ/ቁ.1939 መሰረት ውድቅ በማድረግ ተጠሪን በነፃ Aሰናብቷል። ይህ ፍርድ ቤት የፍ/ብ/ሕ/ቁ.1939 Eንደተመለከተው የድንጋጌው ንUስ ቁጥር /1/ ተራ ዋስ በÑvው ዋስትና መሰረት ለመክፈል የሚገደደው ዋናው ባለEዳ ግድታውን ለመወጣት የማይችል መሆኑ ሲረጋገጥ ብቻ Eንደሆነ ለመረዳት ችሐል። በልላም Aነጋገር ዋናው ባለEዳ ግድታውን ለመወጣት በቂ Aቅም (ችሎታ) ያለው Eስከሆነ ድረስ ገንዘብ ጠያቂው ዋናውን ባለEዳ ትቶ ዋሱ ገንዘቡን Aንዲከፍለው ለመጠየቅ Aይችልም። ምክንያቱም የተራ ዋስትና ዋናው መሰረት በቅድሚያ ዋናው ባለEዳ ከገባው ውል Aኳያ ግድታውን Eንዲወጣ በመቀጠልም ዋናው ባለEዳ ግድታውን ለመወጣት ካልቻለ (Aቅም ከልለው) ተራው ዋስ ገንዘቡን Eንዲከፍል ለመስቻል ታስቦ በሕጉ Eንዲካተት የተደረገ በመሆኑ ነው። በተያዘውም ጉዳይ Aመልካች ከሥር ጀምሮ ያቀረበው ክስ መስተናገድ የነበረበት ከዚህ ድንጋጌ መንፈስ Aኳያ በዚህ ቅደም ተከተል መሰረት በመጀመሪያ ደረጃ ለEዳው Aከፋፈል ዋናው ባለEዳ ላይ ሃላፊነትን በማስቀመጥና ዋናው ባለEዳ ለመክፈል Aቅም የልለው መሆኑ ከተረጋገጠ ተራው ዋስ (ተጠሪ) Eዳውን Eንዲሸከም በሚያስችል መልኩ መወሰን ሲኖርበት ተጠሪ Eስከናካቴው ክሱ ካስከተለው ኪሣራና ወጪ ጋር በነፃ Eንዲሰናበት መደረጉ ተገቢ ሆኖ Aልተገኘም።
Aንዲያውም በፍ/ብ/ሕ/ቁ.1931 ላይ Eንደተመለከተው ዋስ የሆነ ሰው በዋናው ባለEዳ ላይ ክስ ለማቅረብ ገንዘብ ጠያቂው ለመወሰኑ ማስጠንቀቂያ ሲደርሰው ክሱ ለሚያስከትላቸው ወጪዎችም ጭምር ሃላፊ Eንደሚሆን ተደንግጓል። በተጨማሪም በፍ/ብሕ/ቁ.1939 Eዳው መከፈል ባለበት ጊዜ ውስጥ ዋሱ ገንዘብ ለባለEዳው መክፈል Eንደሚችል ተገልፆAል። በመሆኑም በተጠቀሱት ድንጋጌዎች ዋሱ ባንድ በኩል Eዳውን በመክፈል ራሱን ነፃ Eንዲያደርግና በልላም በኩል ገንዘብ ጠያቄው ክስ መሥርቶ ከዋናው ገንዘብ በላይ ክሱ ለሚያስከትላቸው ወጪዎች Eንዳይዳረግ ከወዲሁ የጥንቃቄ Eርምጃዎችን Eንዲወሰድ ለማድረግ Eንዲያስችሉት መደንገጋቸው ሲታይ ተጠሪ ተራ ዋስ በመሆኑ ብቻ ስለEዳው Aከፍፈል ከላይ Eንደተመለከተው የቅደም ተከተል ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ከገባው የዋስትና ግድታ ሙሉ በሙሉ ከሃላፊነት ነፃ የሚሆንበት Aንዳችም የሕግ መሰረት Eንደልለ ፍርድ ቤቱ ተገንዘቧል።
በመሆኑም የስር ፍ/ቤቶች የፍ/ብ/ሕ/ቁ.1939 ተራ ዋስን (ተጠሪን) ሃላፊ Aያደርግም በማለት ድንጋጌውን በተሳሳተ Aኳኋን በመተርጐም የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል።
No topics extracted.
የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ.43622 ግንቦት 19 ቀን 1997 ዓ.ም ፣Eንዲሁም የፍ/ከ/ፍ/ መጋቢት 1 ቀን 1998 ዓ.ም ተጠሪን በተመለከተ የሰጡት ውሣኔ ተሽ[ል።
ተጠሪ ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ከነወለዱ ኪሣራና ወጪ ጋር የሥር 1ኛ ተከሣሽ ለመክፈል ካልቻሉ ላከፍሉ ይገባል ብለናል፣መዝገቡ ተዘግቷል።