No summary available.
መጋቢት 9 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ዓብዱልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልዱ ሒሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- ወ/ሮ ካሣች ተካልኝ - ጠበቃ ጌታቸው ሞላ ተጠሪ፡-
Aቶ ኃ/ማርያም Aበበ - ቀረቡ።
ወ/ሮ ትEግሥት ዱሬሣ - ቀረቡ።
መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥሎ የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ ጉዳይ የተጀመረው በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ሲሆን የAሁን Aመልካች ከሳሽ ተጠሪዎች ደግሞ በተከሳሽነት ተከራክረዋል።
በዚህም መሰረት Aመልካች በተጠሪዎች ላይ ባቀረቡት ክስ 1ኛ ተጠሪ የAመልካችን ንብረት Eንዲያስተዳድር በAመልካች Aማካኝነት ጥቅምት 2 ቀን 1998 ዓ.ም. የውክልና ስልጣን ተሰጥቶት የነበረ ሲሆን ከዚያ በኋላም 1ኛ ተጠሪ Aመልካችን Aግባብቶ ቃለመሐላ ትፈጽሚያለሽ በማለት ወደ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት በመውሰድ Aመልካች Aንብቤ ምንነቱን ያልተረዳሁትን ሰነድ ሚያዝያ 19 ቀን 1998 ዓ.ም.
Eንድፈርም Aድርጎኛል። ከዚያም Aመልካች ያለAግባብ ለ1ኛ ተጠሪ ውክልና መስጠቴን ስገነዘብ በማግስቱ ሚያዝያ 2A ቀን 1998 ዓ.ም. ውክልናውን ሽሬያለሁ። ሆኖም ሰነዶቹ 1ኛ ተጠሪ Eጅ ስለነበሩ በAራዳ ክ/ከተማ የሚገኘውን የAመልካችን ጅምር ቤትና ኒሳን የቤት መኪና ለባለቤቱ ለ2ኛ ተጠሪ Eጅግ Aነስተኛ በሆነ ዋጋ ሸጧል።
ሰለሆነም 1ኛ ተጠሪ ከኑሮ Aጋሩ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ያደረገው የቤትና የመኪና ሽያጭ ውል ከEራሱ ጋር Eንደተደረገ ስለሚቆጠር በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2188 28 29 መሰረት ተቀባይነት የልለው በመሆኑ በሁለቱ ተጠሪዎች መካከል ሚያዝያ 19 ቀን 1998 ዓ.ም. የተደረገው የቤትና የመኪና ሽያጭ ውል ፈራሽ ነው ተብሎ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል።
የAመልካች ክስና ማስረጃም ለተጠሪዎች ደርሶ የየበኩላቸውን ክርክር Aቅርበዋል።
በዚህም መሰረት 1ኛ ተጠሪ በሰጡት መልስ 1ኛ ተጠሪ የAመልካችን ንብረቶች ለ2ኛ ተጠሪ ያስተላለፉት ከAመልካች በተሰጣቸው የውክልና ሥልጠና መሰረትና ከሥልጣናቸውም ወሰን ሳያልፉ በመሆኑ የሽያጭ ውሉ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2189/1/ መሰረት ከሣሽ Eራሳቸው Eንዳደረጉት ስለሚቆጠር በዚህ ክስ ውስጥ 1ኛ ተጠሪ የተካተትኩት ያለAግባብ ስለሆነ ከክሱ ልሰናበት ይገባል በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ Aቅርበዋል። ፍ/ቤቱም ይህንኑ መቃወሚያ መርምሮ የAመልካች የዳኝነት ጥያቄ ውል ይፍረስልኝ የሚል ሲሆን Eንዲፈርስ በተጠየቀው ውል ተዋዋይ ወገኖች ደግሞ Aመልካችና 2ኛ ተጠሪ ስለሆኑ 1ኛ ተጠሪ Aመልካችን በመወከል ውሉን ያደረጉ በመሆኑ ውሉ በማናቸውም ምክንያት የሚፈርስም ሆነ የሚቀጥል ቢሆን ውጤት የሚኖረው በAመልካችና በ2ኛ ተጠሪ መካከል ስለሆነ 1ኛ ተጠሪ በክሱ ውስጥ የተካተቱት ያለ Aግባብ ነው በማለት ከክሱ Aስወጥቷል።
2ኛ ተጠሪም በበኩላቸው ባቀረቡት ክርክር Aመልካች ለ1ኛ ተጠሪ የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት ለመሸጥ የሚያስችል ውክልና መስጠታቸውን በማረጋገጥ ለክርክሩ ምክንያት የሆኑትን ቤትና መኪና ከ1ኛ ተጠሪ መግዛታቸውን ውሉ በተደረገበት ሚያዝያ 19 ቀን 1998 በ1ኛ Eና በ2ኛ ተጠሪ መካከል የጋብቻ ግንኙነት Eንዳልነበረና ጋብቻው የተፈጸመው ከዚያ በኋላ መሆኑን ገልጸው የሽያጩ ውል ላፈርስ Aይገባም በማለት ተከራክረዋል።
የግራ ቀኙ ክርክር በዚህ መልኩ የቀረበለትም የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ጉዳዩን መርምሮ Aመልካች የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2188 ላይ የተመለከተውን በመጥቀስ 1ኛ ተጠሪ ከባለቤቱ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ያደረገው ውል ከEራሱ ጋር Eንዳደረገው ይቆጠራል በማለት ያነሱትን ክርክር በተመለከተ በሕጉ ላይ የተደነገገው ተወካዩ ከEራሱ ጋር ውሉን በሚያደርግ ጊዜ ሲሆን Aመልካች ይፍረስልኝ በማለት የሚጠይቁት ውል ግን 1ኛ ተጠሪ Aመልካችን ሻጭ Eራሱን ገዢ በማድረግ ሳይሆን 2ኛ ተጠሪን ገዢ በማድረግ ስለሆነ ከEራስ ጋር የተደረገ ውል የሚያስብል ሁኔታ የለም ካለ በኋላ 1ኛ Eና 2ኛ ተጠሪ በክብር መዝገብ ሹም ፊት ጋብቻ የፈጸሙት ሚያዝያ 3A ቀን 1998 ዓ.ም. ስለመሆኑ የክብር መዝገብ ኮፒ በማስረጃነት የቀረበ በመሆኑ ውሉ በተደረገበት በሚያዚያ 19 ቀን 1998 ዓ.ም. ሁለቱ ሰዎች ባልና ሚስት Aልነበሩም። ባልና ሚስት ነበሩ ቢባል Eንኳ የየራሳቸው ሰውነት /Personality/ በጋብቻው ምክንያት Eንደሚጠፋና Eንደ Aንድ ሰው Eንደሚቆጠሩ በሕግ ያልተመለከተ በመሆኑ 1ኛ ተጠሪ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ያደረጉት ውል ከገዛ Eራሳቸው ጋር Eንደተደረገ Aይቆጠርም በማለት በውሣኔው ላይ Aስፍሮ በመጨረሻም Aመልካች በወኪላቸው Aማካይነተ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ያደረጓቸው የቤትና የመኪና ሽያጭ ውሎች በAግባቡ በተሰጠ ሥልጣን የተደረጉ በመሆኑ ውሉ የሚፈርስበት ምክንያት የለም በማለት ክሱን ሳይቀበለው ቀርቷል።
No topics extracted.
Aመልካች በዚህ ውሣኔ ቅሬታ Aድሮባቸው የይግባኝ ቅሬታቸውን ለፍ/ከ/ፍ/ቤት ያቀረቡ ቢሆንም በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 337 መሰረት ፍ/ቤቱ ይግባኙን ሳይቀበለው ቀርቷል።
የሰበር Aቤቱታውም የቀረበው ይህንኑ በመቃወም ሲሆን ይህ ሰበር ችሎት Aቤቱታውን መርምሮ የቤትና የመኪና ሽያጭ ውሉ Aይፈርስም ተብሎ በበታች ፍ/ቤቶች መወሰኑ ተጠሪዎችን በመጥራት ላወሰን የሚገባው መሆኑን በማመኑ በዚሁ መሰረት ተጠሪዎችን በመጥራት ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
በAጠቃላይ የጉዳዩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ነው። የዚህን ሰበር ችሎት ምላሽ ማግኘት የሚገባውም የጉዳዩ ጭብጥ 1ኛ ተጠሪ Aመልካችን በመወከል ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ያደረጉት የቤትና የመኪና ሽያጭ ውል ላፈርስ ይገባልን? ወይንስ Aይገባም? የሚለው በመሆኑ ይህንኑ ጭብጥ በመያዝ Aቤቱታው Eንደሚከተለው ተመርምሯል።
Aመልካች ሚያዝያ 19 ቀን 1998 ዓ.ም. በተሰጠ የውክልና ሥልጣን በስማቸው ተመዝግቦ የሚገኝ የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት መሸጥንም ጨምሮ ለ1ኛ ተጠሪ የውክልና ስልጣን የሰጡ ስለመሆኑ በማስረጃ ተረጋግጧል።
Aወዛጋቢው ነጥብ ይህ የውክልና ስልጣን ከተሰጠ በኋላ 1ኛው ተጠሪ ለክርክሩ ምክንያት የሆኑትን ቤቶችና መኪና በሽያጭ ለ2ኛ ተጠሪ ማስተላለፋቸው ከውክልና ሕግ Aኳያ Aግባብነቱን በተመለከተ ነው። ይህንንም የክርክር ነጥብ የግራ ቀኙ ግንኙነት በተለይ ከሚገዛው የውክልና ሕግ ጋር በማገናዘብ ተመልክተናል።
1ኛ ተጠሪ ከላይ በተመለከተው ሚያዝያ 19 ቀን 1998 ዓ.ም.
የውክልና ሥልጣኑን ከAመልካች ከተቀበሉ በኋላ የዚያኑ Eለት ለክርክሩ ምክንያት የሆኑትን ቤትና መኪና በወካዩ በAመልካች ስም ለ2ኛ ተጠሪ በሽያጭ ያስተላለፉ ሲሆን Aመልካች ይህንን ሽያጭ የሚቃወሙት በ1ኛ Eና 2ኛ ተጠሪ መካከል የባልና ሚስት ግንኙነት ስላለ ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2188/1/ Aኳያ ከራስ ጋር Eንደተደረገ ስለሚቆጠር ፈራሽ ነው በማለት ነው።
የተጠቀሰውም የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2188/1/ ድንጋጌ Eንደራሴው ከEራሱ ጋር ውሉን ተዋውሎ በተገኘ ጊዜ ሿሚው ይሄው ውል Eንዲፈርስ መጠየቅ Eንደሚችል ይደነግጋል።
ነገር ግን 1ኛ Eና 2ኛ ተጠሪ የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በውሣኔው ላይ Eንደጠቀሰው የክብር መዝገብ ሹም ፊት በመቅረብ ጋብቻቸውን የፈጸሙት ሽያጩ ከተደረገ በኋላ ሚያዝያ 3A ቀን 1998 ዓ.ም. በመሆኑ በሕግ ዓይን የሽያጭ ውል በተደረገ ጊዜ በሁለቱ መካከል ጋብቻ Aለ ለማለት ስለማይቻል Aመልካች የጠቀሱት የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2188/1/ ለጉዳዩ Aግባብነት ያለው ሆኖ Aልተገኘም።
በልላ በኩልም Eንደራሴው የውክልና ሥልጣኑን በሚያከናውንበት ጊዜ ተቃዋሚ ጥቅሞችን የማስወገድ ግድታ Eንዳለበት /Duty to avoid conflict of interest/ ከEንደራሴውም ጋር ውሉን የፈጸመው 3ኛ ወገን የሚያውቅ ወይንም ማወቅ የሚገባው ሆኖ በተገኘ ጊዜ በሿሚው ጥያቄ መሰረት ውሉ ላፈርስ Eንደሚችል በፍ/ብ/ሕ/ብ/ቁ. 2187/1/ ላይ ተመልክቶ ይገኛል። ክርክሩም ከዚሁ ድንጋጌ Aኳያ ሲታይ የሽያጭ ውሉ በተደረገ ጊዜ ተጠሪዎች ባልና ሚስት Eንዳልነበሩ የተረጋገጠ ቢሆንም ሚያዝያ 19 ቀን 1998 ዓ.ም. ሽያጩ ተደርጎ ሚያዝያ 3A ቀን 1998 ዓ.ም. ከ1A ቀን በኋላ ጋብቻቸውን መፈጸማቸው ሲታይ ሽያጩ በተደረገ ጊዜ በሽያጭ የሚተላለፈው ንብረት በቅርብ Eርቀት የEራስ ንብረት ላሆን Eንደሚችል በማሰብ ውሉ የተደረገ መሆኑን Aጉልቶ የሚያሳይ ነው።
Eንደራሴ ደግሞ ምንጊዜም ቢሆን የሿሚውን ፍላጎትና ጥቅም ብቻ መሰረት Aድርጎ ግድታውን ሳይወጣ ከቀረና የEራሱን ፍላጎትና ጥቅም መሰረት ካደረገ የጥቅም ግጭት መኖሩ የማይቀር ይሆናል። 2ኛ ተጠሪም Eንደራሴው 1ኛ ተጠሪ በሚያደረገው የሽያጭ ውል የጥቅም ግጭት መኖሩን Eየተገነዘቡ ውሉን ማድረጋቸው የተረጋገጠ በመሆኑ በዚሁ ሁኔታ የተፈጸመው ውል ፈራሽ ነው Eንዲባል Aመልካች ያቀረቡት Aቤቱታ ከተጠቀሰው የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2187/1/ Aኳያ ተቀባይነት ያለው በመሆኑ የሥር ፍ/ቤቶች ውሉ ላፈርስ Aይችልም በማለት የሰጡት ውሣኔ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ
የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 69247 በሐምል 9 ቀን 1999 ዓ.ም. የሰጠው ፍርድ Eንዲሁም የፍ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 57884 በሐምል 19 ቀን 1999 ዓ.ም. የሰጠው ትEዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
1ኛ ተጠሪ Aመልካችን በመወከል በAራዳ ክ/ከተማ ቀበል A7/A8 በካርታ ተመዝግቦ የሚገኘውን ጅምር ቤትና የሰ/ቁ. 2-52117 ኒሳን የቤት መኪና ላይ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ያደረጉት የሽያጭ ውል የጥቅም ግጭት /Conflict of interest/ ያለበት መሆኑ የተረጋገጠ ስለሆነ ውሉ ላፈርስ ይገባል በማለት ተወስኗል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።