No summary available.
ኀዳር A5 ቀን 2AAA ዓ.ም.
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ፍስሐ ወርቅነህ መስፍን Eቁበዮናስ ተሻገር ገ/ሥላሴ Aብዱራሂም Aህመድ Aመልካች፡- Aቶ ኃ/ማርያም ባዩ - ጠበቃ Aቶ ማርቆስ ወ/ሰንበት ቀረበ።
ተጠሪ፡- 1ኛ/ Aቶ ሳሙኤል ጎሳዬ 2ኛ/ ወ/ሪት ፀሐይ ጎሳዬ 3ኛ/ ወ/ት መንበረ ጎሳዬ ከ2ኛ Eስከ 5ኛ ያሉት ጠበቃ Aቶ ኃይሉ 4ኛ/ ወ/ት ወይንሸት ጎሳዬ Aግዘው Aልቀረቡም።
5ኛ/ መቅደስ ጎሳዬ 1ኛው ተጠሪ በዚህ የሰበር ክርክር Eንዲቀርብ በምትክ መጥሪያ ጥሪ ተደርጎለት በጥሪው መሰረት Aልቀረበም። በልላ ወገን Aመልካችነት በተመሣሣይ ጥሪው ተደርጎ Aለመቅረቡን በማረጋገጥ ጉዳዩ ይኸው ተጠሪ በልለበት ነገሩ Eንዲሰማ በሰበር መ/ቁ. 22556 ትEዛዝ የተሰጠበት ስለሆነ ይህም ጉዳይ Eርሱ በልለበት Eንዲሰማ ተደርጓል።
Eኛም ጉዳዩን ተመልክተን ፍርድ ሰጥተናል።
የሰበር Aቤቱታው የቀረበው የፍ/ከ/ፍ/ቤት በይግባኝ ተመልክቶ በመ/ ሐምል A3 ቀን 1998 ዓ.ም. በዋለው ችሎት በሰጠው ውሣኔ ቅር በመሰኘት መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው የሚልበትን ነጥብ በመደርደር Aመልካች ይኸው ውሣኔ Eንዲሻር በመጠየቁ ነው።
ጉዳዩም ባጭሩ Eንደሚከተለው ነው።
ከተራ ቁጥር 2 Eስከ 5 ድረስ የተዘረዘሩት ተጠሪዎች በሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ከሣሽ ሆነው በ1ኛ ተጠሪ ላይ ክስ Aቅርበዋል።
የክሱም ፍሬ ቃል ከሟች Aባታችን ከAቶ ጎሳዬ ሩጋቶ በወረዳ A5 ቀበል A6 የቤት ቁጥር 586 የተመዘገበውንና በውርስ የተላለፈልንን የጋራ ሀብታችንን Eንዲያስተዳድርልን Eና Eንዲሸጥ ውክልና ሰጥተነው የነበረ ቢሆንም ውክልናው ከተሻረ በኋላ መሻሩን Eያወቀ ስለሸጠው የተደረገው የሽያጭ ውል ይፍረስልን የሚል ነው።
ክስ የቀረበለት ፍ/ቤትም ጉዳዩን ተመልክቶ ጥር A3 ቀን 1994 ዓ.ም.
በዋለው ችሎት የሽያጭ ውል Eንዲፈርስ Aድርጎ ተዋዋዮቹ ወገኖች ሻጭና ገዢ ውሉ ከመደረጉ በፊት ወደነበሩበት ሁኔታ Eንዲመለሱ ወስኗል።
የAሁን Aመልካችም ይህ ውሣኔ በተሰጠበት ጉዳይ የክርክር ተካፋይ መሆን ይችል የነበረ መሆኑን በማሳየት ውሣኔው ተነስቶና የEርሱ ክርክር ተሰምቶ Eንደገና ዳኝነት ይሰጥበት ዘንድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 358 መሰረት Aቤቱታ Aቅርቧል። በዚህም Aቤቱታ ላይ፡-
ከሣሾች ካቀረቡት ክስ Eና ፍ/ቤቱ ከሰጠው ውሣኔ መረዳት Eንደሚቻለው ውሉ ተሰርዞ ይረከቡት የተባለው የንግድ ድርጅት Eና የንግድ ሥራው የሚከናወንበት ቤት የባለሃብትነትና የይዞታ ባለመብት በመሆን ይዘው የሚጠቀሙበት Aቤቱታ Aቅራቢ ወይም ተቃዋሚ በመሆናቸው የተሰጠው ውሣኔ መብቴን ይነካል።
Eንዲሁም ተዋዋይ ወገን ያልሆኑ 3ኛ ወገኖች ከተዋዋይ ወገኖች መካከል Aንዱን ብቻ በመክሰስ ተዋዋይ ወገኖች ያደረጉትን ውል ለማሰረዝ የሚያስችል የሕግ መሰረት የላቸውም።
የሥር ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ ለማስደገፍ የጠቀሳቸው የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 219A/2/ Eና 2193/1/ ይህንን ለማድረግ የሚያስችሉ ድንጋጌዎች Aይደለም።
በቁጥር 219A/1/ Eና /2/ የተደነገገው በመሰረቱ በቁጥር 2191 Eና በቁጥር 2193/1/ ከተደነገጉት ጋር ተገናዝቦ ሲታይ ከ3ኛ ወገን ጋር 20 21 የተደረገውን ውል ማፍረሱን ወካይ በግልጽ ወይም በዝምታ ለ3ኛ ወገን ባስታወቀው ጊዜ ውሉ Eንዲፈርስ Eንደሚቆጠር የውሉ መፍረስም ስለሚያስከትለው ውጤት በፍ/ብ/ሕ/ቁ 18A8-1818 የተደነገገው ተፈፃሚ Eንደሚሆን በቁጥር 2193/1/ ሥር የተመለከተው ከሚገልጽ በስተቀር ውሉ Eንዲፈርስ ወካዩ በፍ/ቤት ክስ በሚያቀርብበት ጊዜ ተዋዋዮችን የክስ ተከፋይ ሲያደርግ ወይም ከተዋዋዮቹ መካከል ተወካዩን ብቻ የክሱ ተከፋይ በማድረግ ከ3ኛ ወገን ጋር የተደረገውን ውል በማፍረስና በ3ኛ ወገን Eጅ የሚገኘውን ንብረት ለማስለቀቅ Eንደሚያስችል የሚደነግግ Aይደለም።
ተወካይ የተባለው ተከሣሹ Eና ተቃዋሚው የተዋዋሉበት ንብረት ከመጋቢት A9 ቀን 1988 ዓ.ም ጀምሮ ተመዝግቦ የሚገኘው በዚሁ በሻጩ ስም በመሆኑ፣
የውክልና ሰነዱም ከAባታቸው የውርስ ሀብት ውስጥ የሚደርሳቸውን ድርሻ Eንዲያስተዳድርላቸው፣ Eንዲሸጥና Eንዲለውጥላቸው የሚያሳይ Eንጂ ክርክር ያስነሳውን ንብረት በተለይ የሚጠቀስ ባለመሆኑ፣
No topics extracted.
ተቃዋሚው በተከሣሹ ስም ተመዝግቦ የሚገኘውን የንግድ ድርጅት ገዝተውና የንግድ ሥራው የሚከናወንበትን ቤት በስማቸው በማስመዝገብ ድርጅቱን ለልላ ለ3ኛ ወገን በሽያጭ Aስተላልፈውት የሚገኝ በመሆኑ፣
ከሳሾች የውክልና ሥልጣኑ ቀሪ ስለመሆኑ Aግባብ ባለው ማስረጃ ያላረጋገጡ በመሆኑ የሚሉትን በመጥቀስ Eንደዚሁም የሕግና የፍሬ ነገር ክርክሮች ታይተው Eንደገና ላወሰንልን ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
ተከሳሽም የተቃዋሚውን የመከራከሪያ ነጥብ Eንደሚቀበሉት ገልፀው የተሰጠው ውሣኔ Eንዲሻር ጠይቀዋል።
በከሣሾች በኩል የቀረበው ክርክር ደግሞ ሲታይ፡-
ስለሆነም ከሳሾች ውሉን በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 219A/2/ መሰረት በማፍረሳቸው ተቃዋሚው የሚኖረው መብት ውሉ Eንዳይፈርስ ወይም Eንዳይፀና በማለት መከራከር ሳይሆን በውሉ መፍረስ ምክንያት የደረሰ ጉዳት ካለ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2193፣ 2194 Eና 2195 በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሰረት ተገቢውን የዳኝነት ገንዘብ በመክፈል በተለየ ክስ ዳኝነት መጠየቅ ነው።
የንግድ ሥራው የሚንቀሳቀስበትን ቤት በስማቸው ማስመዝገባቸውን መነሻ በማድረግ የተከራከሩ ቢሆንም የንግድ ሥራ የሚንቀሳቀስበት ቤት የንግድ ድርጅቱ Aካል መሆኑ በንግድ ሕጉ የተደነገገ በመሆኑ ተቀባይነት ያለው Aይደለም።
የሽያጭ ውል የተደረገበት የንግድ ድርጅት በተከሳሽ ማለትም በተወካዩ ስም የተመዘገበ ነው የተባለውን Aስመልክቶ ለማስረዳት ያቀረቡት ማስረጃ በቤት ቁጥር 586/ሀ/ የተጠቀሰ መሆኑን የሚያስረዳ Eንጂ የAባታችን ንብረት የሆነውን ቁጥር 586 የሚጠቅስ Aይደለም። ይህም ንብረት በቁጥር 586/ሀ/ Eና/ለ/ ተብሎ ተከፍሎ Aይታወቅም።
ሿሚው ለEንደራሴው የሰጠውን ሥልጣን የሚሽርበት ሁኔታ የተለየ ሥርዓት Eንደሚከተል በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2183 የተመለከተ በመሆኑ የውክልና ሥልጣኑ ቀሪ ስለመሆኑ በተገቢው ማስረጃ Aልተረጋገጠም የሚለው መከራከሪያ ሕጋዊ መሰረት የለውም የሚል ነው።
22 23 በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 36A/2/ መሰረት ጉዳዩን የመረመረው ፍ/ቤትም በመ/ቁ. A1927 ሰኔ 12 ቀን 1995 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ተቃዋሚው ያቀረበው የዳኝነት ጥያቄ የንግድ መደብሩን Aስመልክቶ የተደረገ ውልን ለማሰረዝ ብቻ ሳይሆን የማይንቀሳቀስ ንብረት የሆነውን ቤት ጭምር ለማስለቀቅ ነው በማለት ክርክር ያቀረቡ ቢሆንም ፍ/ቤቱ Aስቀድሞ ውሣኔ የሰጠበት ጉዳይ የንግድ ድርጅትን የሚመለከት ነው። የንግድ ድርጅት ሲባል ደግሞ ድርጅቱ የሚገኝበትን ቤት የመከራየት መብትንም የሚያካትት በመሆኑ ክርክር በቤቱም ላይ ተደርጓል፤ ውሳኔም በቤቱ ላይ ተሰጥቷል ለማለት Aያስችልም።
በልላ በኩል ተዋዋይ ወገን ያልሆኑ ሦስተኛ ወገኖች ተዋዋይ ወገኖች ያደረጉትን ውል ለማሰረዝ ከተዋዋይ ወገኖች Aንዱን ብቻ ነጥለው ለመክሰስ የሚያስችላቸው የሕግ መሰረት የላቸውም በሚል የቀረበውን ጉዳይ በሚመለከት ወካዮች ከሳሾች Eንደራሴው ቀሪ በሆነው ሥልጣኑ የሰራውን ሥራ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2A9A/2/ መሰረት በተሰጣቸው መብት መሰረት መሻራቸውን ፍ/ቤቱ ከማረጋገጥ Aልፎ ውል Eንዲፈርስ ወይም Eንዲሰረዝ የሰጠው ውሣኔ የልለ መሆኑን ካለማገናዘብ የቀረበ ክርክር በመሆኑ ተቀባይነት ያለው Aይደለም በልላ Aገላለጽ የድርጅቱ ሽያጭ ውል የፈረሰው በፍ/ቤቱ በተሰጠው ውሣኔ ሳይሆን ከሳሾች በሕግ በተሰጣቸው ሥልጣን መሰረት ነው።
Eንደራሴው ቀሪ በሆነው ሥልጣኑ የሰራውን ሥራ ወካዩ የመሻር ሥልጣን ያለው ለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 219A/2/ የተደነገገ በመሆኑ ይህንን በማድረግ በቁጥር 2191 Eንደተደነገገው የ3ኛ ወገን ጥያቄ የማቅረቡ ጉዳይ Eንደቅድመ ሁኔታ የሚታይ Aይደለም። የ3ኛ ወገኑም ግድታ Aይደለም ስለሆነም በዚህ ረገድ የቀረበው ክርክርም ተቀባይነት ያለው ሆኖ Aልተገኘም።
Eንደዚሁም የሽያጭ ውሉ ከመፈፀሙ በፊት የወክልና ሥልጣኑ የተሻረ መሆኑን የመስቀለኛ ጥያቄ በተቃዋሚዎች Aማካኝነት በቀረበላቸው ምስክሮች በሚገባ የተረጋገጠ በመሆኑና ይህንንም ጉዳይ በምስክር ለማስረዳት የሚከለክል ሕግ ባለመኖሩ ማስረጃው ተቀባይነት የለውም በሚል ያቀረቡት ክርክር ዋጋ ያለው Aይደለም፤ የሚሉትን ምክያቶች በመንተራስ ተቃዋሚው በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2195 መሰረት ኪሣራ ከሚጠይቁ በቀር በዚህ መዝገብ የተሰጠውን ውሣኔ ለማሻር የሚያበቃ ምክንያት Aልተገኘም በማለት ከዚህ በፊት የሰጡትን ውሣኔ Aጽድቋል።
ይግባኙን የተመለከተው የፍድራል ከፍተኛው ፍ/ቤት በይግባኝ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ውሣኔውን Aጽንቷል።
የሰበር Aቤቱታው ፍሬ ቃል በሥር ፍ/ቤት በተሰጠው ውሣኔ ላይ ተፈጽሟል የተባለውን የሕግ ስህተት በዝርዝር የሚገልጽ ከመሆኑ በቀር በይዘቱ በሥር ፍ/ቤት ከተነሣው ክርክር የተለየ ባለመሆኑ በድጋሚ ማስፈሩ Aስፈላጊ ሆኖ Aልተገኘም። Eንዲሁም ለሰበር Aቤቱታው በተጠሪ በኩል የተሰጠው መልስ ከዚህ በፊት ከተደረገው ክርክርም የተለየ Aይደለም።
Eኛም ጉዳዩን Aግባብነት ካለው ሕግ ጋር Aገናዝበን ተመልክተናል።
በAንድ ውል ተዋዋይ ያልሆኑት ሦስተኛ ወገኖች Aንዱን ተዋዋይ ለብቻ ለይተው ለመክሰስ የሚያስችላቸው የሕግ መሰረት ሳይኖር በዚህ Aኳኋን የቀረበው ክስ ሥነ-ሥርዓታዊ Aልነበረም፣ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ላታረም ይገባል የሚለውን ነጥብ Eንደ Aንድ የሰበር ቅሬታ Aድርገው Aመልካች ማቅረባቸውን ተገንዝበናል። ይሁን Eንጂ Eንደተባለው የAሁን Aመልካች በዚህ በተነሣው ክርክር የሙግት ተካፋይ መሆን Eየተገባው ተከፋይ ሳይሆን ጉዳዩ Eንዲታይ መደረጉ በAንድ ሙግት የክርክር ተካፋይ መሆን የሚገባቸው ወገኖች Eነማን ናቸው? የሚለውን Aስመልክቶ ከሚደነግገው የሕግ ክፍል Aንፃር ሲታይ የክሱ Aቀራረብ የሕግ ግድፈት የተፈፀመበት መሆኑን ያሳያል። ይሁን Eንጂ ይህ መሆኑ Eንደታወቀ በክርክር Aመራር ረገድ የተፈፀመን ጉድለት ፍርድ ከተሰጠም በኋላ ቢሆን ፍርዱን በሰጠው ፍ/ቤት Eንደገና ከሚታይላቸው ሥርዓቶች ይህ Aንዱ መሆኑ ተረጋግጦ Aመልካች የክርክሩ ተሳታፊ ባልሆነበት ጉዳይ የተሰጠው ፍርድ መብቱን የሚነካ መሆኑን መነሻ በማድረግ ውሣኔው Eንዳልተሰጠ ተቆጥሮ Aመልካች ባለበት ክርክሩ 24 25 Eንዲቀጥል ተደርጓል። ከመሰማት መብትም ሆነ ከሚዛናዊ የዳኝነት Aካሄድ Aንፃር በAመልካች ላይ የተጓደለበት ሥርዓት ከላይ በተገለፀው ሁኔታ ተስተካክሎ Aመልካች Aለኝ የሚለውን የፍሬ ነገርም ሆነ የሕግ ክርክር የማቅረብ መብቱ የተጠበቀ በመሆኑ በሥር ፍ/ቤት የቀረበው የሰበር ቅሬታ ነጥብ ተቀባይነት ያለው ሆኖ Aላገኘነውም።
በልላ በኩል የሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የAመልካቾችን የመከራከር መብት ከጠበቀ በኋላ ከዚህ በፊት ሰጥቶት የነበረውን ውሣኔ ለማጽናት በዋነኛነት መሰረት Aድርጎ የያዘው ነጥብ ለተወካይ የተሰጠው የውክልና ሥልጣን ቀሪ ከሆነ በኋላ በወካዩ ስም ሕጋዊ ተግባር ፈጽሞ ከተገኘ Eና ወካዩም ይህንኑ ተግባር ካላፀደቀው ወይም ካልተቀበለው ተወካዩ የፈፀመው ውል ፈራሽ መሆኑን ሕጉ ይደነግጋል። Eነዚህ ፍሬ ነገሮች መኖራቸው ከተረጋገጠ ውልን የማፍረስ መብት ለወካዩ በሕግ የተሰጠው ሥልጣን በመሆኑ በዚህ Aኳኋን የተፈፀመው ውል ላፈርስ ይገባል ወይስ Aይገባም? የሚለውን Aስመልክቶ ፍ/ቤቶች ዳኝነት የመስጠት መብት የላቸውም የሚለውን ነው።
ይሁን Eንጂ ስለዚሁ ጉዳይ የተቀመጡትን ድንጋጌዎች Eርስ በርሳቸው Aስተሳስረን ከተመለከትናቸው ከዚህ መሰል ትርጉም የሚያደርሱ ሆነው Aይታዩም።
ይኸውም Eንደራሴው ቀሪ በሆነው ሥልጣን መሰረት በልላ ሰው ስም ወይም ወካይ በነበረው ሰው ስም በሰራ ጊዜ በስሙ የተሰራበት ስዉ Eንደፈቃድ በስሙ የተሰራውን ሥራ ለማጽደቅ፣ ለመቀበል ወይም ለመሻር መብት Aለው በማለት በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2191/2/ ከተደነገገ በኋላ በዚሁ በተሰጠው መብት ተጠቅሞ Aንዱን መንገድ Eንዲከተል ወይም Eንዲመርጥ ከEንደራሴው ጋር የተዋዋሉት ሦስተኛ ወገኖች ለማስገደድ Eንደሚችሉ Eና aôሚው ከሦስተኛ ወገኖች በቀረበለት ጥያቄ መሰረት ወዲያውኑ ካላስታወቃቸው Eንደራሴው የሰራውን ሥራ Eንዳልተቀበለው ሕጉ ግምት የወሰደ ለመሆኑ ተከታይ በሆነው ድንጋጌ ተመልክቷል።
Eንግዲህ aôሚው በግልጽም ይሁን በዝምታ Eንደራሴው ሥልጣኑ ቀሪ ከሆነ በኋላ የሰራውን ሥራ ያልተቀበለው መሆኑ ከተረጋገጠ የዚሁ ያለመቀበል ውጤት በቁጥር 2193 ተደንግጓል። የዚህን ድንጋጌ ይዘት ስንመለከት aôሚው ይህንኑ የEንደራሴውን ሥራ ካልተቀበለው ምን ጊዜም ይኸው ውል ፈራሽ ነው የሚል Aይደለም። ይልቁንም ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 18A8 Eስከ 1818 ድረስ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ተከትሎ የውሉ መፍረስ ወይም መሰረዝ ላወሰን የሚችል መሆኑን የሚያመለክት ነው። ይህም Eነዚህኑ Aግባብነት ያላቸውን ድንጋጌዎች በመከተል ውሉ ላፈርስ የማይችልበት Aጋጣሚ ያለ መሆኑን የሚያሳይና ነገር ግን ውሉ የሚፈርስ ሆኖ በተገኘ ጊዜ ውሉ በመፍረሱ ምክንያት በቅን ልቦና ከEንደራሴው ጋር በተዋዋሉት 3ኛ ወገኖች ላይ ለሚደርሰው ጉዳት ካሣ የሚጠየቅበት መንገድ የሚያመቻች ድንጋጌ ነው።
ይህ ሆኖ Eያለ የሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የaôሚው ፈቃድ ያልተሰጠበት መሆኑ በተረጋገጠ ጊዜ ሕጉ በEራሱ ውሉን ፈራሽ ያደርገዋል።
ፍ/ቤቱ ይህንኑ በሕግ የተሰጠውን ሥልጣን ከማወቅ Aልፎ ውሉ ላፈርስ ይገባል ወይስ Aይገባም? በሚለው ነጥብ ላይ ዳኝነት የመስጠት ሥልጣን የለውም በሚል የሰጠው ትርጉም መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ Aግኝተነዋል።
ከዚህ Aንፃር Aሁን የተያዘውን ጉዳይ ስንመለከት Aመልካች የንግድ ድርጅቱን ከ1ኛ ተጠሪ ከገዛ በኋላ መልሶ ለልላ ሦስተኛ ወገን በሽያጭ ያስተላለፈውና በEጁ የማይገኝ የመሆኑ ጉዳይ በተጠሪዎችም የተካደ ፍሬ ነገር Aይደለም። Eንደራሴው የውክልና ሥልጣኑ ቀሪ ከሆነ በኋላ የፈፀመው ተግባር ነው ከተባለና ይህንኑ ተግባር aôሚው Aልተቀበለውም ከተባለ የዚሁ የAለመቀበል ውጤት ከላይ Eንደተመለከተው ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 18A8-1818 የተመለከቱትን ድንጌዎች ተከትሎ የሚወሰን ይሆናል።
ከላይ ከተረጋገጠው ፍሬ ቃል Aንፃር Aግባብነት ያለው ድንጋጌ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1816 ነው። ይኸውም ግራ ቀኙ በጉዳዩ ላይ በተከራከሩበት ጊዜ 26 27 Aከራካሪውን ንብረት ልላ ሦስተኛ ወገን ከAመልካች ገዝቶ በEጅ Aድርጎት ይገኛል። በዚህም ድንጋጌ መሰረት በቅን ልቦና ለሆነ ሦስተኛ ወገን የተሰራው ሥራ ውጤት ጠቃሚ ከሆነ ይህ ይፍርስ Aይፈርስ የሚለው ውል Eንደረጋ Eንዲቀር ያደረጋል የሚል በመሆኑ የዚህ ክርክር Aድማስ በAመልካችና በተጠሪዎች ብቻ ተወስኖ የሚቀር ሳይሆን የሦስተኛ ወገኖችንም ጥቅም የሚጠብቅ ነው። ስለሆነም የዚህን 3ኛ ወገን መብት ለመጠበቅ Aስፈላጊ የሆኑት የቀና ልቦና Eና የተሰራው ሥራ ውጤት ጠቃሚነት መስፈርቶች የተሟሉ ሆነው Eስከተገኙ ድረስ የ3ኛውን ወገን መብት ከመጠበቅ Aንፃር ይህ Aከራካሪ የሆነው ውል የሚፈርስ ሆኖ Aልተገኘም።
በመሆኑም የተሸጠው ንብረት በሻጩ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ነው?
ወይስ Aይደለም? ሻጩ በEራሱ Aቋም የሰራው ሥራ ነው? ወይስ ቀሪ በሆነው በEንደራሴነቱ ሥልጣን? ወደሚሉት Aከራካሪ ነጥቦች ዘልቆ መመርመር ሳያስፈልግ ከላይ በተገለፀው የሕግ ትርጓሜ Aመልካች Eና 1ኛ ያደጉት ውል ላፈርስ የሚገባው ሆኖ Aልተገኘም።
ው ሣ ኔ
የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. A1927 ሰኔ 12 ቀን 1995 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ Eና የፍ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 23363 ሐምል A3 ቀን 1998 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
Aመልካች Aቶ ኃ/ማርያም ባዩ Eና 1ኛ ተጠሪ ሳሙኤል ጎሳዬ ጥር 24 ቀን 1993 ዓ.ም. በወረዳ A5 ቀበል A6 በቤት ቁጥር 586/ሀ/ በተመዘገበው ቤት ላይ ያደረጉት ውል ላፈርስ Aይገባም፤ የረጋ ነው ብለናል።