No summary available.
መ.ቁ. 2A89A ሐምለ 10 ቀን 1999 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ Aሰግድ ጋሻው ሒሩት መለሰ Aብዱራሂም Aህመድ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- የIትዮጵያ ልማት ባንክ - ነ/ፈጅ Aክላሉ ተስፋዬ ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ዓለምነሽ ኃይል - ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥሎ የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር Aቤቱታ ላቀርብ የቻለው የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት Aመልካች ከሥር 2ኛ ተከሣሽ ጋር ያደረገው የብድር ውል የተጭበረበረ የውክልና ሰነድን መሰረት በማድረግ ስለሆነ Aመልካች የተጠሪን ቤት መያዣ በማድረግ የሰጠው ብድር ፈራሽ ነው በማለት የሰጠውን ውሣኔ በመቃወም ነው።
የጉዳዩ Aመጣጥም ባጭሩ ሲታይ የAሁን ተጠሪ የሆኑት በAሁን Aመልካችና በሥር 1ኛ Eና 2ኛ ተከሣሾች በሆኑት ላይ በOሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ 1ኛ ተከሣሽ የቡል ሆራ ወረዳ ፍትሕ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ሆኖ ሲሰራ ለ2ኛ ተከሣሽ የግል ቤቴን ለባንክ መያዣ ሰጥቶ ገንዘብ Eንዲበደር የሚል ውክልና Eኔ ሳላውቀው በተጭበረበረ ሁኔታ በመስጠት Eንዲሁም 2ኛ ተከሣሽም ይህንኑ Eኔ ያልሰጠሁትን ውክልና ለ3ኛ ተከሣሽ ለAሁን Aመልካች በማቅረብ ገንዘብ የተበደረ ስለሆነ የብድርና የመያዣ ውሉ ፈራሽ ነው ተብሎ ይወሰንለኝ በማለት ጠይቀዋል።
የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤትም ግራ ቀኙ Aከራክሮና የውክልና ሰነዱ ላይ ያረፈው ፊርማ የተጠሪ ስለመሆኑ በፍድራል ፖላስ የፎረንሲክ ምርመራ መምሪያ በኩል ተመርምሮ ውጤቱ Eንዲገለጽለት ትEዛዝ ሰጥቶ መምሪያው በትEዛዙ መሰረት ሰነዱን መርምሮ ፊርማው የተጠሪ Aለመሆኑን በመግለጽ ለፍ/ቤቱ ሙያዊ Aስተያየቱን ሰጥቷል።
ከዚህ በኋላም ፍ/ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ 1ኛ ተከሣሽ የሐሰት ማስረጃ በመስጠት 2ኛ ተከሣሽ ደግሞ የሐሰት ማመልከቻ በማቅረብ የከሣሽን (ተጠሪ) ቤት ለ3ኛ ተከሣሽ (ለAመልካች) በማስያዝ ገንዘብ መበደሩ የተረጋገጠ ከመሆኑም በላይ ተሰጥቷል በተባለው ውክልና ላይ ያረፈው ፊርማ የከሣሽ Aለመሆኑ የተረጋገጠ ስለሆነ ጥቅምት 16 ቀን 1998 ዓ.ም በካርታ ቁጥር 36/81 በተመዘገበው በ21A ካ/ሜትር ቦታ ላይ በተገነባው የከሣሽ ቤት የተደረገው የመያዣና የብድር ውል ፈራሽ ነው በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
ጉዳዩ በይግባኝ የቀረበለትም የOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት Aመልካችና ተጠሪን Aከራክሮ በAመልካችና በሥር 2ኛ ተከሣሽ መካከል የተደረገውን ውል ለማፍረስ የሚችል በቂና ሕጋዊ ምክንያት Aለ ወይ? የሚለውን ጭብጥ መሥርቶ መዝገቡን በመመርመር Aመልካች ከሥር 2ኛ ተከሣሽ ጋር ውሉን የተዋዋለው ተጠሪ ለሥር 2ኛ ተከሣሽ የሰጡትን ልዩ ውክልና መሰረት በማድረግ ነው፣ የውክልና ሥልጣኑ የተፈረመው ውል ለመዋዋል ሥልጣን ባለው Aካል ፊት ስለሆነና ይህ ሰነድ የጽ/ቤቱ ማህተምና የባለሥልጣን ፊርማ ያለው መሆኑን ብቻ Aመልካች ማረጋገጥ ከሚጠበቅበት በስተቀር ማስረጃውን ለመጠራጠርም ሆነ ስለማስረጃው ተጨማሪ ማጣራት ለማድረግ ግድታ የልለበት በመሆኑ በከፍተኛው ፍ/ቤት የብድሩ ውል ፈራሽ ነው ተብሎ የተሰጠው ውሣኔ ተቀባይነት የለውም በማለት ሽሯል።
ተጠሪም በዚህ ውሣኔ ቅሬታ Aድሮባቸው የይግባኝ ቅሬታቸውን ለፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት Aቅርበው ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን Aከራክሮ የካቲት 10 ቀን 1990 ዓ.ም ተሰጠ የተባለው የውክልና ማስረጃ በፖላስ የቴክኒክ ምርመራ ክፍል ተመርምሮ በውክልና ሰነዱ ላይ የይግባኝ ባይ ፊርማ ነው ተብሎ የሰፈረው የይግባኝ ባይ (የAሁን ተጠሪ) Aለመሆኑ የተረጋገጠ ከመሆኑም በላይ የውክልና ማስረጃው ይዘትም ሲታይ ስርዝ ድልዝ ያለበትና በግልጽ 12 13 ለመጠራጠር የሚያስችሉ ሁኔታዎች የሚስተወሉበት ሆኖ Eያለ Aመልካች ቤቱን በመያዣ በማድረግ ብድር ከመሰጠቱ በፊት ተገቢውን ማጣራት ሲገባው Aጠራጣሪ ሆኖ የሚታየውን የውክልና ማስረጃ በመቀበል የብድር ውል ወደ መፈረም የገባው ያለAግባብ ነው በማለት በሰፊው ተችቶ የOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤትን ውሣኔ በመሻር በAመልካችና በሥር 2ኛ ተከሣሽ መካከል የተደረገው የመያዣና የብድር ውል በሕግ Aግባብነት ስላልተቋቋመ ፈራሽ ነው በማለት ወስኗል።
የሰበር Aቤቱታውም የቀረበው ይህንኑ በመቃወም ሲሆን ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት የቀረበውን የሰበር Aቤቱታ መርምሮ የውክልና ውሉ ፊርማው የተጭበረበረ መሆኑ በፖላስ የቴክኒክ ምርመራ በመረጋገጡና ውል Aዋዋይም ተጠሪ Eኔ ፊት ቀርቦ Aልፈረመችም በማለቱ የመያዣና የብድር ውሉ በፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት Eንዲፈርስ መወሰኑ ለሰበር ችሎት ቀርቦ መጣራት የሚገባው ሆኖ በመገኘቱ ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
በAጠቃላይ የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን ከAመልካች ጋር የተደረገው የብድርና የመያዣ ውል ፈራሽ ነው ተብሎ በፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ ከሕጉ Aኳያ Aግባብነቱ Eንደሚከተለው ተመርምሯል።
No topics extracted.
Aመልካች ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ቤት መያዣ በማድረግ የብድር ውል የተዋዋለው ተጠሪ ለሥር 2ኛ ተከሣሽ የሰጡትን ልዩ የውክልና ሥልጣን መሰረት በማድረግ ነው።
የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይህ የውክልና ሥልጣን በAግባቡ የተሰጠ Aይደለም ወደሚል ድምዳሜ መድረስ የቻለው በAንድ በኩል የውክልና ሰነዱ በፖላስ የቴክኒክ ምርመራ ተመርምሮ በሰነዱ ላይ ያረፈው ፊርማ የተጠሪ Aይደለም ተብሎ ስለተረጋገጠና በልላም በኩል ተጠሪ ወረዳው ፍትሕ ጉዳይ ጽ/ቤት ቀርቦ በውክልናው ሰነድ ላይ Eንዳልፈረመች ውክልናውን Aስፈርሟል በተባለው ሰራተኛም ጭምር የተረጋገጠ በመሆኑና የውክልና ሰነዱም ሲታይ ስርዝ ድልዝ ያለበትና በግልጽ ለመጠራጠር የሚያስችሉ ሁኔታዎች የሚስተውሉበት ስለሆነ ቤቱን መያዣ በማድረግ ብድር ከመሰጠቱ በፊት ተገቢውን ማጣራት ማድረግ ይጠበቅበት ነበር የሚል ትችት በማስፈር ነው።
በመሰረቱ በባለሥልጣን ፊት የተደረጉ ጽሁፎች በግልጽ ከሚደረጉ ጽሁፎች የሚለዩ ሲሆን በግል የሚደረጉ ጽሁፎች (non-authentic deeds) ተዋዋዮች በግል ችሎታቸው የሚያዘጋÍቸው ውልን የሚመለከቱ ሰነዶች ናቸው። በባለሥልጣን ፊት የሚደረጉት ደግሞ ለዚሁ ሥራ ተብሎ የተሰየመ ባለሥልጣን ሰነዱን የተመለከታቸውና ምስክርነቱንም የሰጠባቸው ናቸው።
ሰነዱ በባለሥልጣን ተረጋግጦ Eስከቀረበ ድረስ በሰነዱ መሰረት ግድታ የሚገባው ወገን ማረጋገጥ ያለበት ፊርማውንና ማኀተሙን በመመልከት ሰነዱ በባለሥልጣን ፊት መረጋገጡን ብቻ Eንጂ ከዚህ Aልፎ የሰነዱን ትክክለኛነት ላሆን Aይችልም።
Eዚህ ላይ ተጠሪ በሰነዱ ላይ ያረፈው ፊርማ በፖላስ የቴክኒክ ምርመራ ተመርምሮ የተጠሪ ፊርማ Eንዳልሆነ ቢረጋገጥም ከላይ Eንደተመለከተው Aመልካች ማጣራት የሚጠበቅበት ውሉ በባለሥልጣን ፊት መደረጉንና ባለሥልጣን ምስክርነቱን የሰጠበት ስለመሆኑ Eንጂ የፊርማውን ትክክለኛነት ማጣራት የሚጠበቅበት Aይሆንም። ይልቁንም በመርህ ደረጃ በባለሥልጣን ፊት በተረጋገጡ ሰነዶች ላይ ያሉትን ፊርማዎችና የሰነዶቹን ይዘት ማስተባበል Eንደማይችል ይሄውም ውሉን የሚያዋውሉት ሰዎች የሕዝብ Aደራ የተቀበሉና Aደራውን ወደ ጎን በማድረግ ሐሰተኛ ሰነድ ያዘጋጃሉ ተብሎ ስለማይገመት ነው።
ስለሆነም ሰነዱ ተመርምሮ ፊርማው የተጠሪ Aለመሆኑ ቢረጋገጥም ይህ ሁኔታ ሰነዱን ባፈራረመው ባለሥልጣንና ከዚሁ ባለሥልጣን ጋር ተገቢ ያልሆነ ድርጊት ፈጽሟል በሚባለው ግለሰብ ላይ የክስ ምክንያት ከሚሆን በስተቀር በባለሥልጣን የተረጋገጠውን የውክልና ሰነድ Aመልካች ከቶውንም ላጠራጠር ስለማይችል የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ በመሻር የመያዣና የብድር ውሉ ላፈርስ ይገባል በማለት የሰጠው ውሣኔ በAግባቡ ሆኖ Aልተገኘም።
14 15 ው ሣ ኔ የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በAመልካችና በሥር 2ኛው ተከሣሽ መካከል የተደረገው የብድርና የመያዣ ውል በተጭበረበረ ሰነድ ላይ ተመሥርቶ የተደረገ ስለሆነ ላፈርስ ይገባል በማለት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ ስለተገኘ ይህንኑ ውሣኔ በፍ.ብ.ሕ.ሥ.ሥ.ቁ. 348/1/ መሰረት በመሻር የOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ውሉ ላፈርስ Aይገባም በማለት የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት ተ.ወ