No summary available.
መጋቢት 18 ቀን 2AAA ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ መስፍን Eቁዮናስ ሒሩት መለሰ መድኀን ኪሮስ ዓላ መሐመድ Aመልካች፡- የIትዮጵያ ንግድ ባንክ - ነገረ ፈጅ ደረጀ - ቀረቡ።
ተጠሪ፡- 1ኛ/ ዶ/ር ሻውል ገብሬ - ጠበቃ ወንድሜነህ ዳኜ 2ኛ/ ወ/ሮ ሸዋርካብ ተሾመ - ቀረቡ።
መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ነበር። መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዳዩ ለዚህ ፍርድ ቤት የቀረበው Aመልካች የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመዝገብ ቁጥር A3926 ሰኔ 3A ቀን 1995 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔና የፍ/ከ/ፍ/ቤት በይግባኝ መዝገብ ቁጥር 2378A መስከረም 26 ቀን 1997 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ጥቅምት 8 ቀን 1997 ዓ.ም. በተፃፈ Aቤቱታ በማቅረቡ ነው።
የክርክሩ መነሻ ተጠሪዎች ለፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ከ1968 ዓ.ም. ጀምሮ በሕጋዊ ጋብቻ ተሣሥረው የሚኖሩ ባልና ሚስት መሆናቸውን ገልፀው በጋብቻ Eያሉ በወቅቱ በነበረው Aስተዳደራዊ ስያሜ በAዲስ Aበባ ከተማ ወረዳ 1A ቀበል 22 ቁጥሩ 715/2 የሆነ ቤት በጋራ ሰርተን Eኛ በቡልጋሪያ Aገር በነበርንበት ጊዜ Aቶ ገዛኸኝ በልሁ ይህንን ቤታችንን Eንዲያስተዳድርልን Eንዲሸጥልን ወክለነው ነበር። Aቶ ገዛኸኝ በልሁ Eኛ በሰጠነው የውክልና ማስረጃ ልላ የውክልና ማስረጃ በማዘጋጀት ከሰጠነው የውክልና ስልጣን ውጭ ቤታችንን መያዣ በማድረግ ከIትዮጵያ ንግድ ባንክ ብር 2AA,AAA /ሁለት መቶ ሺህ/ ተበድሯል። ስለዚህ Aንደኛ ተከሣሽ የሆነው የIትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁለተኛ ተከሣሽ ለሆነው Aቶ ገዛኸኝ በልሁ ብድር የሰጠውና የEኛን ቤት በመያዣነት የያዘው ተበዳሪው Aቶ ገዛኸኝ በልሁ ቤቱን በመያዣነት Aስይዞ ለመበደር የሚያስችለው የውክልና ሥልጣን ያለው መሆኑን ሣያረጋግጥ ነው።
ሁለተኛው ተከሣሽ Aቶ ገዛኸኝ በልሁ ከAንደኛው ተከሳሽ የEኛን ቤት በማስያዝ ብድር የተበደሩት የተጭበረበረ የውክልና ሰነድ Aቅርበው ነው። ስለዚህ በማናውቀውና ፈቃዳችንን ያልሰጠንበትን የተጭበረበረ የውክልና ሰነድ በመቀበል Aንደኛ ተከሣሽ ቤታችንን በመያዣነት መያዙ ሕጋዊ ባለመሆኑ የመያዣ ውሉ ፈርሶ በባንኩ የተያዙት የባለቤትነት ሰነዶች ተመላሽ Eንዲሆኑ ውሣኔ ይስጥልን በማለት ክስ Aቅርበዋል።
በሥር ፍርድ ቤት Aንደኛ ተከሣሽ የሆነው Aመልካች ነገረ ፈጅ ለተጠሪዎች ወኪል ለሆነው ለAቶ ገዛኸኝ በልሁ የከሳሾችን ቤት በመያዣነት በመያዝ ብር 2AA,AAA /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ ያበደርነው ከሣሾች ወኪላቸው ቤቱን Aስይዞ ብድር ለመበደር የሚያስችለው የውክልና ስልጣን የሰጡት መሆኑን በወኪላቸው በኩል ከቀረቡት ማስረጃዎች Aረጋግጠን ነው። ስለዚህ ከሳሾች ፈቃዳችንን ሳንሰጥ Aላግባብ ቤታችን በመያዣነት ተይዟል በማለት የሚያቀርቡት ክርክር ውድቅ ይደረግልን በማለት ተከራክሯል።
ጉዳዩን በመጀመሪያ ያየው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ Eንደዚሁም ተጠሪዎች ለማስረጃነት ይጠቅመናል ያሉትን የፖላስ የምርመራ መዝገብና የተጭበረበረ የውክልና ሰነድ በመጠቀም በወንጀል ጉዳይ ተጠርጣሪ የሆነውን የተጠሪዎቹን ወኪል የAቶ ገዛኸኝ በልሁን የምስክርነት ቃል ከሰማ በኋላ ተከሳሹ የIትዮጵያ ንግድ ባንክ የከሳሾችን ቤት ለማስያዝ ህጋዊ የውክልና ስልጣን ስለልለው ለAቶ ገዛኸኝ በልሁ የከሳሾችን ቤት በመያዣነት በመያዝ ብድር የሰጠው በAግባቡ Aይደለም ስለዚህ የመያዣ ውሉ ፈራሽ ነው የባለቤትነት ሰነዱን ይመልስ በማለት ወስኗል። Aመልካች ይህንን ውሣኔ ለማስቀየር ይግባኝ ለፍ/ከ/ፍ/ቤት ያቀረበ ቢሆንም ከፍተኛው ፍርድ ቤት የሥር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ Aጽንቶታል።
2 3 የAመልካች ነገረ ፈጅ ለዚህ ፍርድ ቤት ባቀረቡት የሰበር Aቤቱታ የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ከAዲስ Aበባ Aስተዳደር የውልና ማስረጃ ጽ/ቤት በኩል በቁጥር 1A76A/484 የካቲት 12 ቀን 1989 ዓ.ም የተመዘገበው Aቶ ገዛኸኝ በልሁ ያቀረቡት የውክልና ሰነድ ትክክለኛ የውክልና ሰነድ ስለመሆኑ የAዲስ Aበባ የውልና ማስረጃ ጽ/ቤት መጠየቅና ማረጋገጥ ነበረበት። ሰነዱን Aረጋጋጦ የመዘገበው የውልና ማስረጃ ጽ/ቤት ሣይጠይቅ የፖላስን የምርመራ መዝገብ የተጠሪዎችን ፓስፖርትና የተጠሪዎች ወኪል የሆኑትን የAቶ ገዛኸኝ በልሁን ምስክርነት በመቀበል ሕጋዊ ስልጣን ባለው Aካል ተረጋግጦ የተሰጠውን የውክልና ሰነድ በተጭበረበረ ተግባር የተገኘ ሀሰተኛ ሰነድ ነው በማለት የሰጠው ውሣኔ የሕግ ስህተት Aለበት።
በሁለተኛ ደረጃ ተጠሪዎች በቡልጋሪያ በሚገኘው የIተዮጵያ ኤምባሲ በኩል ለወኪላቸው Aቶ ገዛኸኝ በልሁ የሰጡት የውክልና ስልጣን ቤቱን Eንደወካዮቹ ሆኖ ለማከራየት ለመሸጥ ለመለወጥና በስሙ ለማዞር የሚያስችለው የውክልና ስልጣን ነው። ስለሆነም በዚህ የውክልና ማስረጃ መሰረት የተጠሪዎች ወኪል ቤቱን በመያዣነት Aስይዞ ብድር ለመውሰድ Eንደሚችል የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 3A49 ንUስ Aንቀጽ 2 ይደነግጋል።
No topics extracted.
ይህንን ግልጽ የሕግ ድንጋጌ ሣያገናዝቡ ቤቱን በመያዣነት ለማስያዝ የውክልና ስልጣን ከልለው ሰው ጋር ነው ውል የተዋዋላችሁት በማለት የመያዣ ውሉ Eንዲሰረዝ የሥር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት Aለበት በማለት Aመልክቷል።
ተጠሪዎች በበኩላቸው ቡልጋሪያ በሚገኘው የIትዮጵያ ኤምባሲ በኩል ለተወካያችን Aቶ ገዛኸኝ በልሁ የሰጠነው ውክልና ቤቱን በመያዣያነት ለማስያዝና ከባንክ ብድር ለመውሰድ የሚያስችለው የውክልና ስልጣን Aይደለም። ተወካያችን ለAመልካች ቤታችንን በመያዣነት ያስያዘው Eኛ Aገር ውስጥ በልለንበት ፈቃዳችንን ባልሰጠንበት ሁኔታ የሐሰት መታወቂያ በማዘጋጀት ልላ ሰው በAንደኛው ተጠሪ ስም Aቅርቦ በቁጥር 1A76A/484 የካቲት 12 ቀን 1989 ዓ.ም የAዲስ Aበባ ውልና ማስረጃ የሰጠው Eኛ የማናውቀውን Eና ያልፈረምንበትን በማጭበርበር ወንጀል የተገኘ ሰነድ ነው።
ስለዚህ በዚህ ሀሰተኛ የውክልና ሰነድ መሰረት ቤታችን በመያዣነት መያዙ ሕጋዊ ስላልሆነ፣ የመያዣ ውሉ ፈርሶ የቤቱን ባለቤትነት የሚያረጋግጡት ሰነዶች Eንዲመለሱልን የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት ተከራክረዋል። Aመልካች የሰበር Aቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልስ Aቅርቧል።
ከሥር የክርክሩ Aመጣጥና ግራ ቀኙ ለዚህ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን Eኛም መዝገቡን መርምረናል። መዝገቡን Eንደመረመርነው በAቶ ገዛኸኝ በልሁ Eና በተጠሪዎቹ መካከል የተወካይና የወካይ ግንኙነት Eንዳለ ተረድተናል። ተጠሪዎች ቡMጋሪያ በሚገኘው የIትዮጵያ ኤምባሲ በኩል ተወካያቸው Aቶ ገዛኸኝ በልሁ በAዲስ Aበባ ከተማ Aስተዳደር በፊት በነበረው ስያሜ ወረዳ 1A ቀበል 22 ቁጥሩ 715/2 የሆነውን ቤታቸውን Eንዲያስተዳድርላቸው Eንዲሸጥላቸው የወከሉት መሆኑን ለሥር ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስና ማስረጃ ያሣያል። ስለሆነም ተጠሪዎች ተወካያቸው Aቶ ገዛኸኝ በልሁ ቤታቸውን Eንዲያስተዳድሩ Eንዲሸጡ Eንዲለውጡና ለሦስትኛ ወገን ለማስተላለፍ Eንዲችሉ ቡልጋሪያ በሚገኘው የIትዮጵያ ኤምባሲ በኩል የውክልና ስልጣን የሰጡ መሆኑ Aከራካሪ Aይደለም። ይህም የውክልና ማስረጃ በመጀመሪያ ተጠሪዎች ለተወካያቸው የሰጡት የውክልና ማስረጃ ለመሆኑ ክርክር Aልተነሣም።
ተጠሪዎች Aናውቀውም ብለው የሚከራከሩት የተጠሪዎች ተወካይ የሆነው Aቶ ገዛኸኝ በልሁ የወካዮችን ቤት በመያዣነት በማስያዝ ገንዘብ ለመበደር Eንደሚችል የሚዘረዝረው በAዲስ Aበባ ውልና ማስረጃ ጽ/ቤት በኩል ተመዝግቦ የካቲት 12 ቀን 1989 ዓ.ም. Aንደኛው ተጠሪ ለተወካይ Aቶ ገዛኸኝ በልሁ ሰጥተውታል የተባለው የውክልና ማስረጃ ነው። ተጠሪዎች ይህ ሰነድ የተጭበረበረ ሰነድ በመሆኑ፣ ይህንን መነሻ በማድረግ የIትዮጵያ ንግድ ባንክ ቤታችንን በመያዣነት መያዙ ሕጋዊ ውጤት ላሰጠው Aይገባም በማለት የሚከራከሩ ሲሆን፣ Aመልካች በበኩሉ ይህ የውክልና ሰነድ የተጭበረበረ 4 5 ለመሆኑ ሰነዱን Aረጋግጦ የሰጠው የመንግሥት Aካል ያላረጋገጠውና በቂ ማስረጃ ያልቀረበበት ነው በማለት ይከራከራል። ስለዚህ ተከራካሪዎቹ የሀሣብ ልዩነት ያላቸው በዚህ በሁለተኛው የውክልና ሰነድ ትክክለኛነትና ሕጋዊነት ላይ ነው። ስለሆነም የተጠሪዎቹ ወኪል የሆነው Aቶ ገዛኸኝ በልሁ ሁለት የውክልና ማስረጃ Eንዳለውና ማስረጃዎቹንም የውክልና ስልጣኑን ለማስረዳት የተጠቀመባቸው መሆኑን ለመረዳት ይቻላል። የሥር ፍርድ ቤት የተጠሪዎቹ ተወካይ Aቶ ገዛኸኝ በልሁ የወካዮቹን ቤት በመያዣነት ለማስያዝ የሚያስችለው ሥልጣን Aለው ወይስ የለውም የሚለውን ጭብጥ ላይ Aተኩሮ የሁለቱን የውክልና ማስረጃዎች ይዘትና ሕጋዊ ውጤት Aልመረመረም።
በAንፃሩ የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት የክርክሩ መሰረታዊ ጭብጥ Aድርጎ የያዘው በAዲስ Aበባ ውልና ማስረጃ ጽ/ቤት በኩል የተሰጠው ሁለተኛ የውክልና ማስረጃ ትክክለኛ ማስረጃ ነው ወይስ በማጭበርበር ተግባር የተገኘ የሀሰት የውክልና ማስረጃ የሚለውን ነጥብ ነው።
Aቶ ገዛኸኝ በልሁ የተጠሪዎች ወኪል መሆኑ ግራ ቀኙ ያልተካካዱበትና የታመነ ፍሬ ጉዳይ ነው። Aከራካሪው ነጥብ የተወካይ የውክልና ስልጣን Eስከ ምን ድረስ ነው የሚለው ሲሆን የጉዳዩም ዋና ጭብጥ ወካይ የሆኑት ተጠሪዎች ተወካይ ለሆነው Aቶ ገዛኸኝ በልሁ ቤታቸውን በመያዣነት ለማስያዝ የሚያስችለው የውክልና ስልጣን ሰጥተውታል ወይስ Aልሰጡትም የሚለው ነው።
ይህንን ጭብጥ ለመወሰን በተጠሪዎቹ Eና በAቶ ገዛኸኝ በልሁ መካከል የወካይና የተወካይ ግንኙነት ያለ መሆኑንና ወካዮች ለተወካዩ የሰጡትን የውክልና ስልጣን ይዘትና ወሰን ያሣያሉ ተብለው የቀረቡ የሰነድ ማስረጃዎች ይዘት ተዓማኒነትና ክብደት በዝርዝር መመርመርና መመዘን ያስፈልጋል። ከዚህ Aንፃር ስንመለከተው ተጠሪዎች ቡልጋሪያ በሚገኘው በIትዮጵያ ኤምባሲ በኩል ለተወካዩ የተሰጡት የውክልና ማስረጃ በሁለቱም ማለትም በAመልካችም ሆነ በተጠሪዎች በኩል ክርክር ያልተነሣበት ተዓማኒነት ያለው ማስረጃ ነው። ይህ ማስረጃ በይዘቱ የተጠሪዎች ተወካይ የሆነው Aቶ ገዛኸኝ በልሁ የወካዮቹን ቤት Eንዲያስተዳድር፣ Eንዲሸጥ Eንዲለውጥና ለሦስተኛ ወገን ለማስተላለፍ የሚችል መሆኑን በግልጽ የያዘ መሆኑን Aመልካችና ተጠሪዎቹ ተማምነዋል። ተዓማኒነቱም ሆነ ይዘቱ ሁለቱም ተከራካሪ ወገኖች የተስማሙበት ተጠሪዎች ቡልጋሪያ በሚገኘው የIትዮጵያ ኤምባሲ በኩል Aረጋግጠው ለተወካያቸው Aቶ ገዛኸኝ በልሁ የሰጡት የውክልና ማስረጃ Aግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ስንመረምረው ሁለት መሰረታዊ ባሕሪያትና ውጤት ያለው ነው። የመጀመሪያው ተጠሪዎቹ ተወካዩ ቤታቸውን Eንዲያስተዳድር ጠቅላላ የውክልና ስልጣን የሰጡት መሆኑን የሚያስረዳ ሲሆን የውክልና ማስረጃው የተወካይ Aቶ ገዛኸኝ በልሁ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2204 ድንጋጌዎች የAስተዳደር ሥራ ተብለው የተዘረዘሩትን ተግባራት Eንዲያከናውን ስልጣን የሚሰጥ ነው። በዚህ መሰረት በውክልና ማስረጃው ውስጥ በዝርዝር ባይገለጹም “ቤታችንን Eንዲያስተዳድር” የሚለው ቃል፣ ተወካይ የወካዮቹን ቤት የመጠበቅ የማከራየት የቤት ኪራይ የመቀበል ደረሰኝ የመስጠትና ልሎች Aስተዳደራዊ ተግባራትን Eንዲያከናውን የውክልና ስልጣን የሰጡት መሆኑን የሚያመለክት ነው።
በሁለተኛ ደረጃ ይኸው የውክልና ማስረጃ የተጠሪዎች ተወካይ ቤቱን ለመሸጥ የመለወጥና ለሶስተኛ ወገን የማስተላለፍ ልዩ የውክልና ስልጣን ያለው መሆኑን የሚያስረዳ ነው። የውክልና ማስረጃው ለተወካዩ ልዩ የውክልና ስልጣን የሚሰጥ ከሆነ ሕጋዊ ውጤቱ በውክልና ማስረጃው ላይ ከተፃፉት ተግባራት በተጨማሪ፣ በውክልና ማስረጃው የተገለፁትን ጉዳዮችና Eንደ ጉዳዩ ¡wŃ“ Eንደ ልምድ Aሰራር በውክልና ማስረጃው የተገለጹትን ጉዳዮች ተከታታይና ተመሣሣይ የሆኑ Aስፈላጊ ተግባራትን የመፈፀም ስልጣንን የሚያካትት መሆኑ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2206 ንUስ Aንቀጽ 1 ይደነግጋል። ስለዚህ የተጠሪዎች ተወካይ ቤቱን Aስመልክቶ የተሰጠው ልዩ የውክልና ስልጣን፣ በውክልና ማስረጃው በግልጽ የተመለከቱትን ጉዳዮችና በውክልና ማስረጃው ባይገልፁም በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2206 ንUስ 6 7 Aንቀጽ 1 የሚሸፈኑ ጉዳዮችን የመፈፀም ችሎታ Eንደሚጨምር ለመረዳት ይቻላል።
በመሆኑም የተጠሪዎቹን ቤት የመሸጥ የመለወጥና ለሦስተኛ ወገን የማስተላለፍ ስልጣን በውክልና ማስረጃው ያለው የተጠሪዎች ተወካይ የተጠሪዎቹን ቤት በመያዣነት የማስያዝ ስልጣን Aለው ወይስ የለውም የሚለው ጥያቄ ከላይ ከተጠቀሰው የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2206 ንUስ Aንቀጽ 1 ድንጋጌ Aንፃር መመዘን ያለበት ሲሆን የንብረቱን ባለቤትነት ለሦስተኛ ወገን የማስተላለፍ ስልጣን ያለው ሰው ከዚህ መለስ የሆኑ ተግባራትን የመፈፀም ችሎታ Eንዳለውና በተለይም ንብረቱን በመያዣነት ለማስያዝ የሚያስችል ስልጣን Eና ችሎታ Eንዳለው “ለራሱ Eዳ ዋስትና Eንዲሆን Aንዱን የማይንቀሣቀሥ ንብረትን በEዳ መያዣነት Aድርጎ ለመስጠት የሚችለው የማይንቀሣቀሰውን ንብረት ለመሸጥ ችሎታ ያለው ሰው ነው” ከሚለው በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 3A49 ንUስ Aንቀጽ 2 ድንጋጌ ለመረዳት ይቻላል።
በመሆኑም ተጠሪዎች ለወኪላቸው Aቶ ገዛኸኝ በልሁ ቤቱን Eንዲሸጥ Eንዲለወጥና ለሶስተኛ ወገን Eንዲያስተላልፍ በቡልጋሪያ የIትዮጵያ Aምባሲ በኩል የሰጡት የውክልና ስልጣን ተወካያቸው ቤቱን በመያዣነት ለማስያዝ የሚያስችለው ስልጣንና ችሎታ የሚያጎናጽፈው መሆኑንን የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2206 ንUስ Aንቀጽ 1 Eና የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 3A49 ንUስ Aንቀጽ 2 ይደነግጋሉ። በመሆኑም ለAቶ ገዛኸኝ በልሁ ተጠሪዎች በመጀመሪያ የሰጡት የውክልና ስልጣን ቤቱን በSያዣነት ለማስያዝ የሚያስችል የውክልና ስልጣን ነው። ስለሆነም ተጠሪዎች ተወካያችን Aቶ ገዛኸኝ በልሁ ቤታችን Eንዲሸጥ Eንዲለወጥ Eንጂ በመያዣነት Eንዲያስይዝ የውክልና ስልጣን Aልሰጠነውም በማለት የሚያቀርቡት ክርክር የሕግ መሰረት Eና ድጋፍ የለውም።
ተጠሪዎች ለተወካያቸው የሰጡት የመጀመሪያው የውክልና ማስረጃ የተጠሪዎች ተወካይ ቤቱን በመያዣነት የማስያዝ ስልጣንና ችሎታ ያለው መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው። ይህም የተጠሪዎች ተወካይ በተሰጠው የውክልና ስልጣን መሰረት ቤቱን በመያዣያነት ያስያዘና ከAመልካች ገንዘብ የተበደረ ለመሆኑ ብቃት ያለው ማስረጃ ነው። ይህ ከሆነ የተጠሪዎች ተወካይ ቤቱን በመያዣነት የማስያዝና የመበደር ስልጣን ያለው መሆኑን ለማስረዳት ታስቦ ያቀረበው ሁለተኛው የውክልና ማስረጃ ተዓማኒነት የልለውና በሀሰት የተዘጋጀ ሰነድ ሆኖ ቢገኝ Eንኳን በክርክሩ ውጤት ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም።
ምክንያቱም የተጠሪዎች ተወካይ ሁለተኛው ሰነድ በAዲስ Aበባ ውልና ማስረጃ ጽ/ቤት በኩል ተረጋጋጦ ሣይሰጠው በፊት ተጠሪዎች በቡልጋሪያ በሚገኘው የIትዮጵያ ኤምባሲ በኩል፣ ለተወካያቸው የውክልና ስልጣን ከሰጡበት ቀን ጀምሮ የተጠሪዎቹ ተወካይ Aቶ ገዛኸኝ በልሁ ቤቱን በመያዣነት የማስያዝ ስልጣንና የሕግ ችሎታ ያለው በመሆኑ ነው። Aመልካች ከተጠሪዎቹ ተወካይ ጋር የመያዣ ውል የተዋዋለው ተጠሪዎቹ የተወካያቸውን ልዩ ውክልና ከመሻራቸው በፊት በመሆኑ በAመልካቾችና በተጠሪዎቹ ተወካይ መካከል የተፈፀመው የመያዣ ውል ሕጋዊ ውጤትና ተፈፃሚነት ያለው ነው።
ተጠሪዎች Aመልካች ከተወካያቸው ጋር የመያዣ ውል የተዋዋለው የAዲስ Aበባ ውልና ማስረጃ ጽ/ቤት በቁጥር 1A76A/484 የመዘገበውን ሀሰተኛ ማስረጃ Eና የውክልና ሰነድ መሰረት በማድረግ በመሆኑ የመያዣ ውሉ ፈራሽ Eንዲሆን የተከራከሩ ቢሆንም፣ ተጠሪዎች ከዚህ የውክልና ማስረጃ በፊት ለተወካያቸው በሰጡት የውክልና ማስረጃ መሰረት ተወካይ ቤቱን በመያዣነት የማስያዝ ስልጣን Aለው። ስለሆነም የተጠሪዎቹ ተወካይ ቤቱን በመያዣነት ለማስያዝ የሚያስችለው የውክልና ስልጣን Eና ችሎታ ባለው ጊዜ ከAመልካች ጋር የመያዣ ውሉን የተዋዋለ መሆኑ ከተረጋገጠ Aመልካቹ ውሉን ሲፈጽም Aንደኛውን ወይም ሁለተኛውን ሰነድ Aይቶ ከተጠሪዎች ወኪል ጋር ውል የተወዋለ መሆን Aለመሆኑ መሰረታዊ ጉዳይ Aይደለም። መሰረታዊው ነጥብ የተጠሪዎች ተወካይ ከAመልካች ጋር ውል ሲዋዋል ቤቱን የመሸጥ የመለወጥ ለሶስተኛ ወገን የማስተላለፍና በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2206 ንUስ Aንቀጽ 1 Eና በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 3A49 ንUስ Aንቀጽ 2 መሰረት ቤቱን 8 9 በመያዣነት ለማስያዝ የሚያስችለው ስልጣንና ችሎታ ባለው ጊዜ ውስጥ ውሉን የተዋዋሉ መሆኑ ወይም Aለመሆኑ ነው።
ከዚህ Aንፃር በAመልካችና በተጠሪዎቹ ተወካይ መካከል የተደረገው የመያዣ ውል ተጠሪዎች በቡልጋሪያ የIትዮጵያ ኤምባሲ በኩል Aረጋግጠው በላኩለት የውክልና ማስረጃ መሰረት የተጠሪዎች ተወካይ የወካዮቹን ቤት ለመሸጥ፣ ለመለወጥ ለሦስተኛ ወገን ለማስተላለፍ Eና በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2206 ንUስ Aንቀጽ 1 Eና በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 3049 ንUስ Aንቀጽ 2 መሰረት ቤቱን በመያዣነት ለማስያዝ የሚያስችለው ስልጣንና ችሎታ በነበረው ጊዜ ሆኖ Eያለ ይህንን መሰረታዊ ነጥብ ሣይመረምር Eና ሣይመዝን ሁለተኛ የውክልና ማስረጃ ተዓማኒነት ያለው ማስረጃ ነው ወይስ በሀሰትና በማጭበርበር የተገኘ የሚለውን ነጥብ ብቻ ነጥሎ በማየት የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በAመልካችና በተጠሪዎች ተወካይ መካከል የተደረገው የመያዣ ውል ሕጋዊ ውጤት የለውም በማለት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ Aግኝተነዋል። Eንደዚሁም የይግባኝ ክርክሩን በመስማት የሥር ፍርድ ቤትን ውሣኔ ያፀናው የፍ/ከ/ፍ/ቤት ከላይ የተጠቀሱትን የሕግ ድንጋጌዎች ያላገናዘበ Eና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያበለት ውሣኔ ነው በማለት ፍርድ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል፣ ይፃፍ።
የፍ/ከ/ፍ/ቤት በይግባኝ መዝገብ ቁጥር 2378A መስከረም 26 ቀን 1997 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል ይፃፍ።
Aመልካች ከተጠሪዎች ወኪል ከAቶ ገዛኸኝ በልሁ በAዲስ Aበባ ከተማ Aስተዳደር በፊት በነበረው ስያሜ በወረዳ 19 ቀበል 22 የሚገኘው ቁጥሩ 715/2 የሆነውን ቤት በመያዣነት በመያዝ ብር 2AA,AAA /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ ያበደረው ብድር በሕግ ፊት Aስገዳጅነት ያለው ውል ነው ብለናል። Aመልካቹ ይህንኑ Aውቆ በAዋጅ ቁጥር 9A/1997 በተሰጠው ስልጣንና ሀላፊነት መሰረት ተገቢውን ይፈጽም ዘንድ የፍርድ ግልባጭ ከመሸኛ ጋር ይሰጠው።
በዚህ ፍርድ ቤት የወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻቻሉ።
ይህ ፍርድ በAዳሪ ተሰርቶ መጋቢት 18 ቀን 2AAA ዓ.ም. በሙሉ ድምጽ ተሰጠ።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት።
ነ/ዓ 10 11 የሰበር መ.ቁ. 2A89A ሐምለ 10 ቀን 1999 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ Aሰግድ ጋሻው ሒሩት መለሰ Aብዱራሂም Aህመድ ታፈሰ ይርጋ Aመልካች፡- የIትዮጵያ ልማት ባንክ - ነ/ፈጅ Aክላሉ ተስፋዬ ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ዓለምነሽ ኃይል - ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥሎ የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር Aቤቱታ ላቀርብ የቻለው የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት Aመልካች ከሥር 2ኛ ተከሣሽ ጋር ያደረገው የብድር ውል የተጭበረበረ የውክልና ሰነድን መሰረት በማድረግ ስለሆነ Aመልካች የተጠሪን ቤት መያዣ በማድረግ የሰጠው ብድር ፈራሽ ነው በማለት የሰጠውን ውሣኔ በመቃወም ነው።
የጉዳዩ Aመጣጥም ባጭሩ ሲታይ የAሁን ተጠሪ የሆኑት በAሁን Aመልካችና በሥር 1ኛ Eና 2ኛ ተከሣሾች በሆኑት ላይ በOሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ 1ኛ ተከሣሽ የቡል ሆራ ወረዳ ፍትሕ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ሆኖ ሲሰራ ለ2ኛ ተከሣሽ የግል ቤቴን ለባንክ መያዣ ሰጥቶ ገንዘብ Eንዲበደር የሚል ውክልና Eኔ ሳላውቀው በተጭበረበረ ሁኔታ በመስጠት Eንዲሁም 2ኛ ተከሣሽም ይህንኑ Eኔ ያልሰጠሁትን ውክልና ለ3ኛ ተከሣሽ ለAሁን Aመልካች በማቅረብ ገንዘብ የተበደረ ስለሆነ የብድርና የመያዣ ውሉ ፈራሽ ነው ተብሎ ይወሰንለኝ በማለት ጠይቀዋል።
የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤትም ግራ ቀኙ Aከራክሮና የውክልና ሰነዱ ላይ ያረፈው ፊርማ የተጠሪ ስለመሆኑ በፍድራል ፖላስ የፎረንሲክ ምርመራ መምሪያ በኩል ተመርምሮ ውጤቱ Eንዲገለጽለት ትEዛዝ ሰጥቶ መምሪያው በትEዛዙ መሰረት ሰነዱን መርምሮ ፊርማው የተጠሪ Aለመሆኑን በመግለጽ ለፍ/ቤቱ ሙያዊ Aስተያየቱን ሰጥቷል።
ከዚህ በኋላም ፍ/ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ 1ኛ ተከሣሽ የሐሰት ማስረጃ በመስጠት 2ኛ ተከሣሽ ደግሞ የሐሰት ማመልከቻ በማቅረብ የከሣሽን (ተጠሪ) ቤት ለ3ኛ ተከሣሽ (ለAመልካች) በማስያዝ ገንዘብ መበደሩ የተረጋገጠ ከመሆኑም በላይ ተሰጥቷል በተባለው ውክልና ላይ ያረፈው ፊርማ የከሣሽ Aለመሆኑ የተረጋገጠ ስለሆነ ጥቅምት 16 ቀን 1998 ዓ.ም በካርታ ቁጥር 36/81 በተመዘገበው በ21A ካ/ሜትር ቦታ ላይ በተገነባው የከሣሽ ቤት የተደረገው የመያዣና የብድር ውል ፈራሽ ነው በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
ጉዳዩ በይግባኝ የቀረበለትም የOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት Aመልካችና ተጠሪን Aከራክሮ በAመልካችና በሥር 2ኛ ተከሣሽ መካከል የተደረገውን ውል ለማፍረስ የሚችል በቂና ሕጋዊ ምክንያት Aለ ወይ? የሚለውን ጭብጥ መሥርቶ መዝገቡን በመመርመር Aመልካች ከሥር 2ኛ ተከሣሽ ጋር ውሉን የተዋዋለው ተጠሪ ለሥር 2ኛ ተከሣሽ የሰጡትን ልዩ ውክልና መሰረት በማድረግ ነው፣ የውክልና ሥልጣኑ የተፈረመው ውል ለመዋዋል ሥልጣን ባለው Aካል ፊት ስለሆነና ይህ ሰነድ የጽ/ቤቱ ማህተምና የባለሥልጣን ፊርማ ያለው መሆኑን ብቻ Aመልካች ማረጋገጥ ከሚጠበቅበት በስተቀር ማስረጃውን ለመጠራጠርም ሆነ ስለማስረጃው ተጨማሪ ማጣራት ለማድረግ ግድታ የልለበት በመሆኑ በከፍተኛው ፍ/ቤት የብድሩ ውል ፈራሽ ነው ተብሎ የተሰጠው ውሣኔ ተቀባይነት የለውም በማለት ሽሯል።
ተጠሪም በዚህ ውሣኔ ቅሬታ Aድሮባቸው የይግባኝ ቅሬታቸውን ለፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት Aቅርበው ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን Aከራክሮ የካቲት 10 ቀን 1990 ዓ.ም ተሰጠ የተባለው የውክልና ማስረጃ በፖላስ የቴክኒክ ምርመራ ክፍል ተመርምሮ በውክልና ሰነዱ ላይ የይግባኝ ባይ ፊርማ ነው ተብሎ የሰፈረው የይግባኝ ባይ (የAሁን ተጠሪ) Aለመሆኑ የተረጋገጠ ከመሆኑም በላይ የውክልና ማስረጃው ይዘትም ሲታይ ስርዝ ድልዝ ያለበትና በግልጽ 12 13 ለመጠራጠር የሚያስችሉ ሁኔታዎች የሚስተወሉበት ሆኖ Eያለ Aመልካች ቤቱን በመያዣ በማድረግ ብድር ከመሰጠቱ በፊት ተገቢውን ማጣራት ሲገባው Aጠራጣሪ ሆኖ የሚታየውን የውክልና ማስረጃ በመቀበል የብድር ውል ወደ መፈረም የገባው ያለAግባብ ነው በማለት በሰፊው ተችቶ የOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤትን ውሣኔ በመሻር በAመልካችና በሥር 2ኛ ተከሣሽ መካከል የተደረገው የመያዣና የብድር ውል በሕግ Aግባብነት ስላልተቋቋመ ፈራሽ ነው በማለት ወስኗል።
የሰበር Aቤቱታውም የቀረበው ይህንኑ በመቃወም ሲሆን ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት የቀረበውን የሰበር Aቤቱታ መርምሮ የውክልና ውሉ ፊርማው የተጭበረበረ መሆኑ በፖላስ የቴክኒክ ምርመራ በመረጋገጡና ውል Aዋዋይም ተጠሪ Eኔ ፊት ቀርቦ Aልፈረመችም በማለቱ የመያዣና የብድር ውሉ በፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት Eንዲፈርስ መወሰኑ ለሰበር ችሎት ቀርቦ መጣራት የሚገባው ሆኖ በመገኘቱ ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙን Aከራክሯል።
በAጠቃላይ የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን ከAመልካች ጋር የተደረገው የብድርና የመያዣ ውል ፈራሽ ነው ተብሎ በፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ ከሕጉ Aኳያ Aግባብነቱ Eንደሚከተለው ተመርምሯል።
Aመልካች ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ቤት መያዣ በማድረግ የብድር ውል የተዋዋለው ተጠሪ ለሥር 2ኛ ተከሣሽ የሰጡትን ልዩ የውክልና ሥልጣን መሰረት በማድረግ ነው።
የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይህ የውክልና ሥልጣን በAግባቡ የተሰጠ Aይደለም ወደሚል ድምዳሜ መድረስ የቻለው በAንድ በኩል የውክልና ሰነዱ በፖላስ የቴክኒክ ምርመራ ተመርምሮ በሰነዱ ላይ ያረፈው ፊርማ የተጠሪ Aይደለም ተብሎ ስለተረጋገጠና በልላም በኩል ተጠሪ ወረዳው ፍትሕ ጉዳይ ጽ/ቤት ቀርቦ በውክልናው ሰነድ ላይ Eንዳልፈረመች ውክልናውን Aስፈርሟል በተባለው ሰራተኛም ጭምር የተረጋገጠ በመሆኑና የውክልና ሰነዱም ሲታይ ስርዝ ድልዝ ያለበትና በግልጽ ለመጠራጠር የሚያስችሉ ሁኔታዎች የሚስተውሉበት ስለሆነ ቤቱን መያዣ በማድረግ ብድር ከመሰጠቱ በፊት ተገቢውን ማጣራት ማድረግ ይጠበቅበት ነበር የሚል ትችት በማስፈር ነው።
በመሰረቱ በባለሥልጣን ፊት የተደረጉ ጽሁፎች በግልጽ ከሚደረጉ ጽሁፎች የሚለዩ ሲሆን በግል የሚደረጉ ጽሁፎች (non-authentic deeds) ተዋዋዮች በግል ችሎታቸው የሚያዘጋÍቸው ውልን የሚመለከቱ ሰነዶች ናቸው። በባለሥልጣን ፊት የሚደረጉት ደግሞ ለዚሁ ሥራ ተብሎ የተሰየመ ባለሥልጣን ሰነዱን የተመለከታቸውና ምስክርነቱንም የሰጠባቸው ናቸው።
ሰነዱ በባለሥልጣን ተረጋግጦ Eስከቀረበ ድረስ በሰነዱ መሰረት ግድታ የሚገባው ወገን ማረጋገጥ ያለበት ፊርማውንና ማኀተሙን በመመልከት ሰነዱ በባለሥልጣን ፊት መረጋገጡን ብቻ Eንጂ ከዚህ Aልፎ የሰነዱን ትክክለኛነት ላሆን Aይችልም።
Eዚህ ላይ ተጠሪ በሰነዱ ላይ ያረፈው ፊርማ በፖላስ የቴክኒክ ምርመራ ተመርምሮ የተጠሪ ፊርማ Eንዳልሆነ ቢረጋገጥም ከላይ Eንደተመለከተው Aመልካች ማጣራት የሚጠበቅበት ውሉ በባለሥልጣን ፊት መደረጉንና ባለሥልጣን ምስክርነቱን የሰጠበት ስለመሆኑ Eንጂ የፊርማውን ትክክለኛነት ማጣራት የሚጠበቅበት Aይሆንም። ይልቁንም በመርህ ደረጃ በባለሥልጣን ፊት በተረጋገጡ ሰነዶች ላይ ያሉትን ፊርማዎችና የሰነዶቹን ይዘት ማስተባበል Eንደማይችል ይሄውም ውሉን የሚያዋውሉት ሰዎች የሕዝብ Aደራ የተቀበሉና Aደራውን ወደ ጎን በማድረግ ሐሰተኛ ሰነድ ያዘጋጃሉ ተብሎ ስለማይገመት ነው።
ስለሆነም ሰነዱ ተመርምሮ ፊርማው የተጠሪ Aለመሆኑ ቢረጋገጥም ይህ ሁኔታ ሰነዱን ባፈራረመው ባለሥልጣንና ከዚሁ ባለሥልጣን ጋር ተገቢ ያልሆነ ድርጊት ፈጽሟል በሚባለው ግለሰብ ላይ የክስ ምክንያት ከሚሆን በስተቀር በባለሥልጣን የተረጋገጠውን የውክልና ሰነድ Aመልካች ከቶውንም ላጠራጠር ስለማይችል የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ በመሻር የመያዣና የብድር ውሉ ላፈርስ ይገባል በማለት የሰጠው ውሣኔ በAግባቡ ሆኖ Aልተገኘም።
14 15 ው ሣ ኔ የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በAመልካችና በሥር 2ኛው ተከሣሽ መካከል የተደረገው የብድርና የመያዣ ውል በተጭበረበረ ሰነድ ላይ ተመሥርቶ የተደረገ ስለሆነ ላፈርስ ይገባል በማለት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ ስለተገኘ ይህንኑ ውሣኔ በፍ.ብ.ሕ.ሥ.ሥ.ቁ. 348/1/ መሰረት በመሻር የOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ውሉ ላፈርስ Aይገባም በማለት የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት ተ.ወ
ጥቅምት 14 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ ተገኔ ጌታነህ መስፍን Eቁበዮናስ ተሻገር ገ/ስላሴ ብርሃኑ Aመነው Aመልካች፡- ላቀስዩማን Aስፋ በሻህውረድ ወኪል ጀነነው Aሰፋ ቀረቡ ተጠሪ፡- የሣህላተ ምህረትና ክርስቶስ ሳምራ ደብር Aስተዳደር Aልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል
ለዚህ Aቤቱታ መንስኤ የሆነው የAመልካች ወኪል ጀነነው Aሰፋ የተባለው በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ክስ መስርቶ ክሱ በመታየት ላይ Eያለ ፍ/ቤቱ Aቶ ጀነነው Aሰፋ ክሱን የመሰረተው “ከሳሽ ጀነነው Aሰፋ” ብሎ ፅፉል፣Eሱ ወኪል Eንጂ ከሳሽ ላሆን Aይችልም በማለት ክሱን ውድቅ በማድረጉና በከፍተኛው ፍ/ቤትም Aያስቀርብም በመባሉ ነው።
ለዚህ ፍ/ቤት የቀረበው Aቤቱታ መሰረተ ሃሳብም Aቶ ጀነነው Aሰፋ የAመልካች ወኪል በመሆኑ ክሱን የመሰረተውም Aመልካችን ወክሎ Eንጂ በራሱ ስላልሆነ ክሱ ውድቅ የተደረገው በማይገባ ነው በማለት ነው።
Aቤቱታው ለሰበር ችሎት ያስቀርባል ተብሎ ለተጠሪ መጥሪያ ተልኮለት ባለመቅረቡ ክርክሩ በልለበት ታይቷል።
የሥር ፍ/ቤት የAመልካቹ ወኪል “ከሳሽ ጀነነው Aሰፋ” በማለቱ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.33 መሰረት ክስ ማቅረብ Aይቻልም ብሐል። ፍ/ቤቱ ውሣኔ በሰጠበት በግንቦት 29 ቀን 1997 ዓ.ም በውሣኔው ላይ የመዘገበው “ከሳሽ ጀነነው Aሰፋ” ብሎ ነው። በነሐሴ 2 ቀን 1995 ዓ.ም በቀረበው የክስ ማመልከቻ ላይ ግን “ከሳሽ ጀነነው Aሰፋ ላቀስዩማን Aሰፋ በሻህውረድ ወኪል” ተብሎ ተፅፏል።
16 17 የውክልና ሥልጣን ያለው ሰው በዋናው ባለመብት ስም የክስ ወይም የAቤቱታ ማመልከቻ ማቅረብ Eንደሚችል የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 58 ይደነግጋል።
Aቶ ጀነነው Aሰፋ የላቀስዩማን Aሰፋ በሻህውረድ ወኪል መሆኑ በፍ/ቤቱም የተገለፀ በመሆኑ Aመልካቹን ወክሎ ክስ ማቅረብ ይችላል። ክስ የመሰረተውም በውክልናው መሰረት ለመሆኑ ለየካ ምድብ ፍትሃብሄር ችሎት የፃፈው የክስ ማመልከቻ ያረጋግጣል። በመሆኑም የሥር ፍ/ቤት የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 33/2/ በመጥቀስ በጉዳዩ ላይ መብት ስለልለው ላከስ Aይችልም ማለቱ ተገቢ ሆኖ Aላገኘነውም። ምክንያቱም ክስ የመሰረተው በውክልናው Eንጅ ባለመብት ነኝ በማለት ስላልሆነ ነው።
ፍ/ቤቱ ውሣኔ በሰጠበት Eለት “ከሳሽ ጀነነው Aሰፋ” ብሎ ይመዝገብ Aንጂ የክስ ማመልከቻው ከሳሹ (ወኪሉ) የላቀስዩማን Aሰፋ በሻህውረድ ወኪል መሆኑን ያሣያል። ወኪሉ ወኪል መሆኑን Eስካሣየና Eስከገለፀ ድረስ በማመልከቻው ላይ የራሱን ወይም የወካዩን ስም Aስቀድሞ መፃፉም ቢሆን ወኪልነቱን ለውጦ ባለመብት የሚያደርገው Aይሆንም። በክስ ማመልከቻው ላይ ባለመብት ናቸው ተብለው ዋነኛ የጉዳዩ ባለቤት ተደርገው በዝርዝሩ የተጠቀሱት የAሁን Aመልካች ላቀስዩማን Aስፋ በሻህውረድ ናቸው። ይህ Eየታወቀ ወኪሉ በከሳሽነት ዘንግ ሆኖ ክስ መስርቷል በሚል ክሱ ውድቅ መደረጉ ስህተት ነው።
ወኪሉ በክስ ማመልከቻው ላይ የራሱን ስም ከወካዩ Aስቀድሞ መፃፉን ፍ/ቤቱ ግልፅነት ይጎለዋል Eንኳን ብሎ ቢገነዘብ ይህንኑ Aስተካክሎ Eንዲያቀርብ ማድረግ ሲችል ክሱን ያለመቀበሉ ተገቢ ባልሆነ Aሰራር ሙግት Eንዲራዘምና ባለጉዳይ Eንዲጉላላ ማድረግ ነው። በመሆኑም የሚከተለው ተወስኗል።
ው ሣ ኔ
የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ክሱን የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 33 በመጥቀስ መዝጋቱም ሆነ ከፍተኛው ፍ/ቤትም ይግባኙን መሰረዙ ተገቢ ስላልሆነ ውሣኔዎቹን በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348/1/ መሰረት ሽረናል።
የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት Aቶ ጀነነው Aሰፋ የላቀስዩማን Aሰፋ በሻህውረድ ወኪል በመሆን የመሰረተውን ክስ ተቀብሎ ግራ ቀኙን በማከራከር ተገቢውን ውሣኔ Eንዲሰጥ ታዟል። ይፃፍ። መዝገቡ ተዘግቷል።