No summary available.
ሚያዝያ 5 ቀን 2003ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አመልካች፡- አቶ ቴዎድሮሰ ተስፊዬ ጠበቃ ሰመረ አሰፊ ቀረቡ ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የደቡብ ክልል ወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና የሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ ህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልካች ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ የሚጣራ ነጥብ ያለው መሆኑ ተገልፆ ለሰበር ስለቀረበ ነው። የክርክሩ መነሻ በሰበር መዝገብ ከተዘረዘሩት ንብረቶች ውስጥ የሰላዲ ቁጥሩ 3-33129 ኢት፣ የሆነው የፍስሽ ጭነት ማመላለሻ መኪናን የሚመልከት ነው። አመልካች በሥር ፍርድ ቤት በተከሳሽነት ቀርቦ ንብረቱ የሆነውን ከላይ ቁጥሩ የተገለፀውን መኪና አንደኛ ተጠሪ እንዱሸጥ እንዱለወጥ እና እንዱያስተዲደር ውክልና የሰጠው መሆኑንና ውክልናውን ያሰረዘው መሆኑን ገልፆ ንብረቱን እንዱመልስልኝና በመኪናው ተሰርቶ የተገኘውን ገንዘብ እንዱከፍለኝ በማለት ክስ አቅርቧል። አንደኛ ተጠሪ አመልካች በሰጠው ውክልና ሥልጣን መሰረት መኪናውን ለሁለተኛ ተጠሪ በብር 1‚250‚000/አንድ ሚሉዬን ሁለት መቶ አምሳ ሺህ ብር/ የሸጠው መሆኑንና ገንዘቡንም የአመልካች ወኪል ለሆኑት አቶ ታፈሰ አርጌ ያስረከበ መሆኑን በመግለፅ ተከራክራል። አንደኛ ተጠሪ በሥር ጣልቃ ገብ ተከራካሪ ሆነው በመቅረብ የመኪናውን ብር 1‚500‚000 /አንድ ሚሉዬን አምስት መቶ ሺህ ብር/ ከፍለው የተረከቡና የሚጠበቅባቸው ቀሪ ገንዘብ ብር 50‚000 /ሀምሣ ሺህ ብር/ መሆኑን በመጥቀስ ተከራክረዋል። አቶ ታፈሰ አርጌ በሥር ፍርድ ቤት ጣልቃ ገብ ተከራካሪ ሆነው ቀርበው አመልካች ገንዘብ ለመቀበል የሚያስችል ውክልና ያላቸው መሆኑን ገልፀው የመኪናውን ዋጋ ከአንደኛ ተጠሪ በመቀበል የካቲት 26 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ መተማመኛ 1‚200‚000 /አንድ ሚሉዬን ሁለት መቶ ሺህ ብር/ ለአመልካች የሰጡት መሆኑን ገልፀው ተከራክረዋል። ላላኛው ጣልቃ ገብ ወ/ሮ ገነት ደምሴ መኪናው የጋራ ንብረት ሆኖ እያለ ወደ አመልካች መዛወሩን በመቃወም ጣልቃ ገብ ሆነው ተከራክረዋል።
የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች ለአንደኛ ተጠሪ የውክልና ሥልጣን ለመስጠት የውክልና ውለ ረቂቅ የተፃፈው ሀምላ 11 ቀን 1999ዓ.ም መሆኑን የውክልና ሥልጣን የሚሰጠው ሰነድ ለውልና ማስረጃ ቀርቦ የተረጋገጠው መስከረም 28 ቀን 2000ዓ.ም መሆኑን አንደኛ ተጠሪ ለሁለተኛ ተጠሪ የመኪና ሽያጭ ውል ያደረገው ነሐሴ 12 ቀን 1999ዓ.ም መሆኑን በውሣኔው ካስፈረ በኃላ አንደኛ ተጠሪ አመልካች ውክልናው ሥልጣን እንደሚሰጠው በቅን ልቦና በማሰብ የውክልና ሰነድ ረቂቅ ከተፃፈ ከሀምላ 11 ቀን 1999ዓ.ም በኃላና የውክልና ሰነድ በውልና ማስረጃ ቀርቦ ሣይመዘገብ በፉት ነሐሴ 11 ቀን 1999 ዓ.ም የፈፀመው የሽያጭ ውል በቅን ልቦና የተደረገ በመሆኑ የፀና ነው በማለት በድምፁ ብልጫ ውሣኔ ሰጥቷል። አመልካች የይግባኝ ውሣኔውን በመቃወም ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ያቀረበ ቢሆንም ይግባኙ ተሰርዞበታል። አመልካች ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የቀረበው የሰበር አቤቱታ ውድቅ ተደርጎበታል።
አመልካች አንደኛ ተጠሪ ለህፃን ልጁ ለሁለተኛ ተጠሪ መኪናውን የሸጠው እኔ የውክልና ሥልጣን ከመሰጠቴ በፉት ነው። ስለዚህ በመኪልነት ሥልጣን ይሰጠኛል በሚል በቅን ልቦና የፈፀመው ህጋዊ ተግባር ነው በማለት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ያመለከተ ሲሆን አንደኛ ተጠሪ መኪናውን ሸጨ ገንዘቡን ለአመልካች ወኪል ሰጥቻለሁ። አመልካች ገንዘቡን ተቀብሎል ስለዚህ ውለ እንዱፈርስ የሚያመለክትበት ህጋዊ ምክንያት የለም በማለት ተክራክሯል፡ ሁለተኛ ተጠሪ በበኩላቸው በ1982 ዓ.ም የተወለደና ህፃን እንዲልሆኑ በመግለፅ ንብረቱን በአግባቡ የገዛሁት በመሆኑ የሚፈርስበት ምክንያት የለም በማለት መልስ ሰጥተዋል።
አመልካች የመልስ መልስ አቅረበዋል። ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የተደረገው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው የበታች ፍርድ ቤቶች አንደኛ ተጠሪ ለክርክሩ መነሻ የሆነውን መኪና ሁለተኛ ተጠሪ የሸጠው የውክልና ስልጣን የተሰጠበት ረቂቅ ሰነድ ከተፃፈ በኃላ በቅን ልቦና በመሆኑ የሽያጭ ውለ የፀና ነው በማለት የሰጡት ውሣኔ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም; የሚለው ጭብጥ መመርመር ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ይህንን ጭብጥ ለመወሰን አንደኛ ተጠሪ የሰላዲ ቁጥሩ 3-3312927 የሆነውን መኪና የማስተዲደር የመሸጥና የመለወጥ ሥልጣኑን ያገኘበትን መንገድና መኪናውን የሸጠበትን ጊዜ እንደዚሁም አመልካች መኪናው ከተሸጠ በኃላ ፈጽሟቸዋል ለማለት አንደኛ ተጠሪ በሥር ፍርድ ቤት አንደኛ ጣልቃገብ የነበሩት አቶ ታፈሰ አርጌ ያነሱትን ክርክና ፍርድ ቤቶቹ የያዙትን ጭብጥና የሰጡትን ውሣኔ መመርመር አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል። የላላ ሰው እንደራሴ በመሆን ሥራዎችን የመፈፀም ሥልጣን የሚገኘው ከህግ ወይም ከውል እንደሆነ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2179 መሰረታዊ መርህ ሆኖ ተደንግጓል። አንደኛው ተጠሪ ከላይ ቁጥሩ የተገለፀውን የፈሳሽ ጭነት ማመላለሻ መኪና የማስተዲደር የመሸጥና የመለወጥ የውክልና ሥልጣን ያገኘው በህግ የተደነገገን ድንጋጌን መሰረት በማድረግ ሣይሆን አመልካች ወኪለ እንዱሆን ተስማምቶ በውልና ማስረጃ አስመዝግቦና አረጋግጦ በሰጠው የውል ሰነድ መሆኑን ግራቀኙ አልተካካደም። ግራቀኙ የሚከራከሩት አመልካች ለተጠሪ የሰጠው የውክልና ሰነድ ህጋዊ ውጤት የሚኖረው ረቂቁ ከተፃፈበት ከሀምላ 11 ቀን 1999 ዓ.ም ጀምሮ ነው; ወይስ የውክልና ሰነደ በአመልካች ከተፈረመበትና በውልና ማስረጃ ተመዝግቦና ተረጋግጦ ከተሰጠበት ከመስከረም 28 ቀን 2000 ዓ.ም ጀምሮ ነው; በሚለው ነጥብ ላይ ነው።
ስለ ውለ አፃፃፍ ህጉ አንድ አይነት ፍርም እንዱደርግ ያስገደደ እንደሆነ ውለን የሚፈፀምበት ሥልጣን በዚሁ አይነት ፍርም ለወኪል ሥልጣን መስጠት እንዲለበት በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2080 የሚደነግግ መሆኑንና ውክልና በግልፅ ወይም በዝምታ ላሰጥ የሚችል መሆኑን በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2200 ንዐስ አንቀፅ 1 የሚደነግግ መሆኑን በመመልከት አንደኛ ተጠሪን አመልካች ረቂቁ ከተፅፈበት ሀምላ 11 ቀን 1999 ዓ.ም ጀምሮ እንደወከለውና አንደኛ ተጠሪም መኪናውን በቅን ልቦና የአመልካች ወኪል ነኝ በሚል ውክልና ሰነድ በውልና ማስረጃ ከመረጋገጡ በፉት ነሐሴ 12 ቀን 1999 ዓ.ም አንደኛ ተጠሪ ከሁለተኛ ተጠሪ ጋር ያደረገው የመኪና ሽያጭ ውል በተሰጠው ውክልና መሰረት እደፈፀመው የሚቆጠር ነው በማለት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት እና የሰበር ችልት አፅንተውታል።
ሆኖም ይህ የበታች ፍርድ ቤቱች የሰጡት ውሣኔ ስለ ሰነድች ማረጋገጫና ምዝገባ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 334/1995 በአንቀፅ 3 ንዐስ አንቀፅ 1 እና በአንቀፅ 5 ንዐስ አንቀፅ 5 ንዐስ አንቀፅ 1/ለ/ የተደነገገውን ከግንዛቤ ውስጥ ያስገባ ሆኖ አላገኘነውም። በአዋጅ ቁጥር 334/1995 አንቀፅ 3 ንዐስ አንቀፅ 1 አዋጁ ይህንን አዋጅ ለማስፈፀም ሥልጣን በተሰጣቸው አካላት ላይ ተፈፃሚነት ያለው መሆኑ "የተፈፃሚነት ወሰን" በሚለው ርዕስ ሥር በግልፅ ደንግጓል። ፍርድ ቤት ማስረጃ የመመዘን የመመርመርና የመቀበል ህገ መንግስታዊ ሥልጣን ያላቸው አካላት በመሆናቸው ይህንን አዋጅ የመተግበር ግዳታ ያለባቸው መሆኑ የአዋጅ ቁጥር 334/95 አንቀፅ 3/1/ ድንጋጌ ይዘት መንፈስና ዓላማ ከህገ መንግስቱ አንቀፅ 50 ንዐስ አንቀፅ 7 ጋር በጣምራ በማየት ለመረዲት ይቻላል። በአዋጅ ቁጥር 334/95 አንቀፅ 5 በህግ መሰረት ካልተረጋገጡና ካልተመዘገቡ ህጋዊ ውጤት እንደማይኖራቸው ከተዘረዘሩት ሰነድች አንደኛው የውክልና ሥልጣን መስጫ ሰነድ እንደሆነ በአንቀፅ 5 ንዐስ አንቀፅ 1/ለ/ በግልፅ ተደንግጓል። ስለሆነም አመልካች የውክልና ሰነደን ፈርሞና በውልና ማስረጃ አስመዝግበ እና አረጋግጦ መስከረም 28 ቀን 2000ዓ.ም ለአንደኛ ተጠሪ የውክልና ሥልጣን ከመስጠቱ በፉት አንደኛ ተጠሪ የውክልና ሰነድ ረቂቅ የተጻፈው ሀምላ 11 ቀን 1999 ዓ.ም ነው በማለት የፈፀመው ተግባር በወኪልነት ሥልጣኑ እንደፈፀመው የማይቆጠርና ወካዩ/አመልካች/ በግልፅ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ ካላፀደቀው በስተቀር አመልካችን የማያስገድድ በመሆኑ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው የህግ ትርጉምና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚና ሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ረቂቅ ሰነደን መሰረት በማድረግ አንደኛ ተጠሪ ነሐሴ 12 ቀን 1999ዓ.ም የአመልካች መኪናን ለመሸጥ ያደረገው ስምምነት ህጋዊ ውጤት የሚኖው አመልካች የመኪና ሽያጭ ውለን በግልፅ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ ሲያፀድቀው መሆኑን ከፍታብሓር ህግ ቁጥር 2090/1/ ድንጋጌዎች ለመረዲት ይቻላል። በያዝነው ጉዲይ የሥር ፍርድ ቤት የአመልካች ወኪል የሆኑት አንደኛ ተጠሪ መኪናውን የሸጡትና ገንዘቡን የአመልካች ላላው ወኪል ለሆኑት አቶ ታፈሰ አርጌ የሰጡ መሆኑን በማንሣት ያቀረቡትን ክርክርና የአመልካች ወኪል የነበሩት አቶ ታፈሰ አርጌ መኪናው ተሸጦ ገንዘቡን ተቀብለው ለአመልካች የሰጡ መሆናቸውን በማመን ያቀረቡትን ክርክር በመመልክት የሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ ሰጥቷል። ሆኖም የሥር ፍርድ ቤት አንደኛ ተጠሪ የውክልና ሥልጣን ሣይኖራቸው የፈፀሙትን የመኪና ሽያጭ ውል አመልካች በግልፅ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ መኪናው መሸጡን የተቀበለው መሆኑን የሚያሣይ ተግባራትን በመፈፀም አፅድቆታል ወይም አላፀደቀውም; የሚለውን ጭብጥ በመመሥረት በግራ ቀኙ በኩል ያቀረቡትን ክርክርና ማስረጃ በመመዘን የሰጠው ውሣኔ የለም።
አመልካች የመኪናውን ሽያጭ በግልፅ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ አፅድቆታል ወይስ አላፀደቀውም; የሚለውን ነጥብ ለመወሰን በአንደኛ ተጠሪና በአመልካች መካከል የተደረገውን ክርክርና ማስረጃ መመርመሩና መመዘኑ ብቻውን በቂ አይደለም። አመልካች መኪናውን አንደኛው ተጠሪ እንደሸጠው የሚያውቅና ከመኪናው ዋጋ ውስጥ 1‚200‚000 /አንድ ሚሉዬን ሁለት መቶ ሺህ ብር/ ከአንደኛው ተጠሪ ተቀብዬ ወስጄ ለአመልክች የካቲት 26 ቀን 2000 ዓ.ም በተፈረመ መተማመኛ ሰጥቸዋለሁ በማለት በሥር ፍርድ ቤት አንደኛ ጣልቃ ገብ ተከራካሪ የሆኑት አቶ ታፈሰ አርጌ ያቀረቡትን ክርክርና ማስረጃ በማጣራት በመመርመርና በመመዘን ውሣኔ መሰጠት አስፈላጊ ነው።
ስለሆነም አመልካች የመኪናው የሽያጭ ዋጋ ከሆነው ገንዘብ ውስጥ ብር 1‚200‚000 /አንድ ሚሉዬን ሁለት መቶ ሺህ ብር/ የካቲት 26 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ መተማማኛ ተቀብሎል ወይስ አልተቀበለም; የሚለው ነጥብ አመልካች የመኪናውን መሸጥ የሚያውቅ የነበረና ዋጋውን ተቀብል ሲጠቀምበት የቆየ መሆኑን ወይም አለመሆኑን ለመወሰን አስፈላጊ ሆኖ እያለ የበታች ፍርድ ቤቶች የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 248 በሚደነግገው መሰርት በክርክሩ ተካፊይ የሆኑት ተከራካሪ ወገኖች ያቀረቡትን የመከላከያ መልስና የፅሐፍ ማስረጃ በመመርመር መያዝ የሚገባውን ጭብጥ ሁለ በመያዝ ጉዲዩን አጣርተው ያልወሰኑ በመሆኑ ውሣኔያቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የደቡብ ክልል የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና የሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
የደቡብ ክልል የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሥር አንደኛ ጣልቃ ገብ ተከራካሪ የነበሩት አቶ ታፈሰ አርጌን ወደ ክርክሩ እንዱገቡ በማድረግ አመልካች አንደኛ ተጠሪ ከሸጠው የመኪና ዋጋ ገንዘብ ውስጥ ብር 1‚200‚000 /አንድ ሚሉዬን ሁለት መቶ ሺህ ብር/ ከአቶ ታፈሰ አርጌ ተቀብል ወስዶል ወይስ አልወሰደም; አመልካች ገንዘቡን ተቀብል እንደወሰደ ቢረጋገጥ አመልካች አንደኛ ተጠሪ የውክልና ሥልጣን ሣይኖረው መኪናውን ነሀሴ 12 ቀን 1999 ዓ.ም ለሁለተኛ ተጠሪ ለመሸጥ የተስማማውን ውል እንዲፀደቀው ይቆጠራል; ወይስ አይቆጠርም; የሚለውን ጭብጥ በማጣራትና የግራቀኙን ክርክር በመስማትና ማስረጃ በመመዘን ውሣኔ እንዱሰጥበት ጉዲዩን በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 343/1/ መሰረት መልስን ልከንለታል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ ብለናል። መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.