No summary available.
ህዲር 27 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፣ ተሻገር ገብረስላሴ ብርሀኑ አመነው ፀጋዬ አስማማው ዓሉ መሐመድ ሱልጣን አባተማምአመልካች፡- ካፔቴን ዩናስ ህለፍ - አልቀረቡምተጠሪዎች፡- 1. አቶ እስጢፊኖስ ኪዲኔ - ቀረቡ 2. ወ/ሪት ሄለን ኪዲኔ 3. ወ/ሮ አዜብ ኪዲኔ አልቀረቡም 4. ወ/ሪት አስቴር ኪዲኔ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ስላመለከቱ ነው።
ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። ጉዲዩ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሁለት ጊዜ ቀርቦ ታይቶ ውሣኔ ተሰጥቶበታል።
በሥር ፍርድ ቤት ክርክሩ የተጀመረው አንደኛ ተጠሪ ጥር 21 ቀን 1995 ዓ.ም በተፃፈ የክስ ማመልከቻ የአባትና የእናታቸው የጋራ ሀብት የሆነውንና በውርስ የተላለፈላቸውን በቀድሞው አጠራር በወረዲ 21 ቀበላ 10 የሚገኘውና ቁጥሩ 383 የሆነውን ቤት የአሁን አመልካች /የሥር ተከሣሽ/ በመጀመሪያ ተከራይቶ ይኖርበት ነበር። ቤቱን እንዱለቅልኝ ብጠይቀው ገዠቸዋለሁ በማለት ለመልቀቅ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ቤቱን እንዱያስረክበኝና የቤቱን ኪራይ ክስ ካቀረብኩበት ቀን ጀምሮ እንዱከፍል ውሣኔ ይሰጥልኝ በማለት የክስ ማመልከቻ በማቅረቡ ነው። የሥር ተከሣሽ የአሁን አመልካች ሟች አቶ ኪዲኔ ተስፊሐዋሪያት ላልች ልጆች ስላሎቸው በክርክሩ እንዱገቡ ትዕዛዝ ይሰጥልኝ። ቤቱን የሟች ወኪል ከሆነችው የከሣሽ /የአንደኛ ተጠሪ/ እህት በውል የገዛሁት ስለሆነ ውለ እንዱፈርስ በፍርድ ሣይወሰንብኝ ቤቱን ይልቀቅልኝ በማለት ክስ ላቀርብብኝ አይገባም ውለ መመዝገብ የሚያስፈልገው ለሶሰተኛ ወገን እንጂ ለተዋዋይ ወገኖች አይደለም። አንደኛ ተጠሪ የእናቴ የጋራ ሀብት ነው የሚለውን በተመለከተ ውለ እንዱፈርስ መጠየቅ አይችልም የሚል ክርክርና ላልች የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎችን አቅርቧል። የሥር ፍርድ ቤት የግራቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከሰማ በኃላ አመልካች ከሟች ኪዲኔ ተስፊሀዋሪያት ወኪል ጋር መጋቢት 27 ቀን 1991 ያደረጉት የቤት ሽያጭ ውል በፍታብሐር ህግ ቁጥር 1923/1/ መሰረት ያልተፈፀመና እንደረቂቅ የሚታይ በመሆኑ ተከሣሽ የአሁን አመልካች ቤቱን ለአንደኛ ተጠሪ እንዱያስረክቡ በማለት ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበዋል።
ከዚህ በኋላ ሁለተኛ ሶስተኛና አራተኛ ተጠሪዎች የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአንደኛ ተጠሪንና የአመልካችን ክርክር ሰምቶ ጥር 4 ቀን 1997 ዓ.ም የሰጠውን ፍርድ በመቃወም የካቲት 15 ቀን 1997 ዓ.ም የተፃፈ የፍርድ መቃወሚያ ማመልከቻ አቅርበዋል። አንደኛ ሁለተኛና ሶስተኛ ተጠሪዎች ባቀረቡት የፍርድ መቃወሚያ የተጠሪዎች ወላጅ እናት ጥቅምት 1 ቀን 1990 ዓ.ም ወላጅ አባታቸው ሀምላ 1 ቀን 1991 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ መሆኑን ገልፀው በአባታቸው ስም ተመዝግቦ የሚገኘውን ቤት ከአባታቸው በተሰጠ የውክልና ሰነድ አራተኛ ተጠሪ መጋቢት 27 ቀን 1991 ዓ.ም በተፃፈ ውል ለአመልካች ሽጠውላቸዋል። ስለዚህ እኛ በክርክሩ ሳንሳተፍ የሽያጭ ውለ የእኛ መብት ያለበትን ቤት አንደኛ ተጠሪ እንዱረከብ የተሰጠው ውሣኔ እንዱሰርዝልን በማለት አመልክተዋል። ሁለተኛ ሶስተኛና አራተኛ ተጠሪዎች በፍርድ መቃወሚያ ማመልከቻ መነሻ የይርጋና የውል ፍርም ክርክሮች ያቀረቡ ሲሆን የሥር ፍ/ቤት የይርጋው ክርክር በሥር ተከሣሽ /አመልካች/ ያልተነሣ በመሆኑ በፍርድ መቃወም አመልካቾች በኩል መነሳቱ ተገቢ አይደለም በማለትና ላልቹን የመከራከሪያ ነጥቦችን ውድቅ በማድረግ በተጠሪዎች አባት ወኪል አራተኛ ተጠሪና በአመልካች መካከል የተደረገው የቤት ሽያጭ ውል የህጉን ፍርም የማያሟላ በመሆኑ ጥር 4 ቀን 1997 ዓ.ም የሰጠሁትን ውሣኔ የምሰርዝበት ወይም የምሽርበት ምክንያት የለም በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ሁለተኛ ሶስተኛና አራተኛ ተጠሪዎች ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅርበዋል።
የከፍተኛው ፍርድ ቤት አመልካች ያቀረበውን ይግባኝና ሁለተኛ ሶስተኛና አራተኛ ተጠሪዎች ያቀረቡትን ይግባኝ በመዝገብ በማጣመር በአንደኛ ተጠሪ በአመልካች እንደዚሁም በሁለተኛ ሶስተኛና አራተኛ ተጠሪዎችና በአንደኛ ተጠሪ መካከል የተደረገውን ክርክር መርምሮ ውሣኔ ሰጥቷል። የከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች ቤቱን የተጠሪዎች ወላጅ አባት ለአራተኛ ተጠሪ በሰጡት ውክልና መሰረት መጋቢት 21 ቀን 1991 ዓ.ም ሸጠው ሟች ሀምላ 1 ቀን 1991 ዓ.ም የሞቱ በመሆኑ የውለን ፍርም አንደኛ ተጠሪ በመከራከሪያነት ሉያነሣው አይችልም በማለት የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ ሽሮታል።
በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት አንደኛ ተጠሪ ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርቧል። ይግባኝ ሰሚ ችልት የመልስ ሰጭዎችን ማለትም የአመልካችን የሁለተኛ ተጠሪ የሶስተኛ ተጠሪና የአራተኛ ተጠሪን የቃል ክርክር ለማሰማት ለሀምላ 10 ቀን 2000 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቶ የአመልካች ጠበቃ በፅሐፍ መልስ ሰጥቷል። የሁለተኛ ሶስተኛና አራተኛ ተጠሪዎችን የቃል ክርክር መስማት ባለመቻለ ክርክሩን ለመስማት ለታህሣሥ 3 ቀን 2000 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል። በዚህ ቀን ይግባኝ ባዩ አንደኛ ተጠሪ ባለመቅረቡ አንደኛ ሁለተኛና ሶስተኛ ተጠሪዎች መዝገቡ እንዱዘጋላቸው በመጠየቃቸው ሁለተኛ ሶስተኛና አራተኛ ተጠሪዎችን አሰናብቷል ከዚህ በኃላ አመልካችና አንደኛ ተጠሪ ያቀረቡትን ክርክር መርምሮ ውለ በህጉ የተደነገገውን ፍርም አያሟላም በማለት የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ በመሻር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ በማፅናት ፍርድ ሰጥቷል።
አመልካች ሰኔ 23 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ውለ በህጉ የተመለከተውን ፍርም የማያሟላ በመሆኑ አመልካች ቤቱን ለአንደኛ ተጠሪ እንዱያስረክብ በማለት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ውሣኔ የህግ ስህተት አለበት በልላ በኩል የጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አንደኛ ተጠሪ በሁለተኛ ሶስተኛና አራተኛ ተጠሪዎች ላይ ያቀረበው ይግባኝ በሚሰማበት ቀነ ቀጠሮ ባለመቅረቡ የአንደኛ ተጠሪን ይግባኝ በመሰረዝ ሁለተኛ ሶስተኛና አራተኛ ተጠሪን አሰናብቷቸዋል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት ይግባኝ መዝገቦችን በማጣመር የወሰነ በመሆኑ ሁለተኛ ሶስተኛና አራተኛ ተጠሪዎች ባቀረቡት ይግባኝ መነሻ የሽያጭ ውለ የፀና ነው በማለት የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ እንዱፀና የቀረበና የአንደኛ ተጠሪ ይግባኝ ከተሰረዘ በኃላ እኔ ያቀረብኩትን መልስ መነሻ በማድረግ ውለ ፍርሙን አላሟላም ብል መወሰኑ እርስበርሱ የሚቃረን ነው።
ስለሆነም ይግባኝ ሰሚ ችልቱ የሰጠው ውሣኔ የህግ ሥርዓቱን ያልተከተለ በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል። አንደኛ ተጠሪ በበኩለ ጥቅምት 4 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ መልስ ይግባኝ ሰሚው ችልት ህግ በመተርጎም ረገድ የፈፀመው የህግ ስህተት የለም። ይግባኝ ሰሚው ችልት ይህ ሰበር ችልት የሰጠውን የህግ ትርጉም ተከትል ነው ውሣኔ የሰጠው ሁለተኛ ሶስተኛና አራተኛ ተጠሪዎችንም ያሰናበታቸው የእነርሱ በተከራካሪነት መቀጠል የሚያመጣው የፍርድ መዛባት የላለ በመሆኑ ነው። የአመልካች የሁለተኛ ሶስተኛና አራተኛ ተጠሪዎች ክርክር ተመሳሳይ በመሆኑ ይግባኝ ሰሚው ችልት በአመልካች ላይ የሰጠው ውሣኔ ሁለተኛ ሶስተኛና አራተኛ ተጠሪዎችን ክርክር የሚቋጭ ነው በማለት መልስ ሰጥቷል።
ሁለተኛ ሶስተኛና አራተኛ ተጠሪዎች በበኩላቸው ጥቅምት 4 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ መልስ ይግባኝ ሰሚው ችልት የአንደኛ ተጠሪን ይግባኝ በመሰረዝ እኛን አሰናብቶናል አንደኛ ተጠሪ ይህ ትዕዝዝ እንዱነሣ ወይም እንዱሰርዝ የሰበር አቤቱታ ያላቀረቡ በመሆኑ እኛን በተመለከተ የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ የመጨረሻ ውሣኔ መሆኑን በማረጋገጥ ውሣኔ እንዱሰጥልን በማለት መልስ ሰጥተዋል። አመልካች የመልስ መልስ በፅሐፍ አቅርበዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና ለሰበር በግራቀኙ የቀረበው የፅሐፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። መዝገቡን እንደመረመርነው ተጠሪዎች የሟች ወ/ሮ ለተስላሴ ኃይለና የሟች አቶ ኪዲኔ ተስፊሐዋሪያት ልጆችና የመጀመሪያ ደረጃ ወራሾች ናቸው። አንደኛ ተጠሪ ሟች አቶ ኪዲኔ ተስፊሐዋሪያት በወኪላቸው አራተኛ ተጠሪ በኩል ከአመልካች ጋር ያደረጉት የቤት ሽያጭ ውል እንዱፈርስና ቤቱን እንድረከብ በማለት ከፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ጀምሮ እስከ ሰበር ችልት ባቀረቡት ክርክር የሚከራከሩ ሲሆን ሁለተኛ ተጠሪ፣ ሶስተኛ ተጠሪና አራተኛ ተጠሪ በበኩላቸው ሟች አባታችን በወኪለ አራተኛ ተጠሪ በኩል የፈፀመው የቤት ሽያጭ ውል የሚፈርሰበት ምክንያት የለም፣ውለ አይፈርስም በማለት የከፍተኛው ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ እኛን በተመለከተ የመጨረሻና የፀና ነው በማለት የተከራከሩ መሆኑን ከሥር ጀምሮ እስከ ሰበር ችልት ካቀረቡት ክርክር ለመገንዘብ ችለናል። ከዚህ በተጨማሪ የከፍተኛው ፍርድ ቤት አመልካች በመዝገብ የቤት ሽያጭ ውለ ሉፈርስ አይገባውም በማለት ያቀረበውን የይግባኝ ቅሬታና ሁለተኛ ሶስተኛና አራተኛ ተጠሪዎሪች የሥር ፍርድ ቤት ውለ ረቂቅ ነው በማለት የሰጠውን ውሣኔ በመቃወም በመዝገብ ያቀረቡትን ይግባኝ በማጣመር በመዝገብ መርምሮ ውለ ሉፈርስ አይገባም አመልካችም ለአንደኛ ተጠሪ ቤቱን የማስረከብ ግዳታ የለበትም በማለት ውሣኔ መስጠቱን ይህንን ውሣኔ በመቃወም አንደኛ ተጠሪ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመልካችን አንደኛ መልስ ሰጭ ሁለተኛ ተጠሪን ሁለተኛ መልስ ሰጭ ሶስተኛ ተጠሪ ሶስተኛ መልስ ሰጭ አራተኛ ተጠሪን አራተኛ መልስ ሰጭ በማድረግ የይግባኝ ቅሬታ አቅርበው የነበረ መሆኑን ተገንዝበናል።
በይግባኝ በተደረገው ክርክር አንደኛ መልስ ሰጭ የነበሩት አመልካች የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ተገቢ ነው የይግባኝ ባዩ አንደኛ ተጠሪ የይግባኝ ቅሬታ የህግ መሰረት የለውም የሚል የፅሐፍ መልስ ሀምላ 10 ቀን 1999 ዓ.ም ለይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ያቀረቡ መሆኑንና ይግባኝ ሰሚው ችልት የሁለተኛ ሶስተኛና አራተኛ መልስ ሰጭ የነበሩትን ከተራ ቁ 2-4 ተጠሪዎች የቃል ክርክር ለመስማት ቀነ ቀጠሮ በያዘበት ታህሣሥ 3 ቀን 2000 ዓ.ም አንደኛ ተጠሪ /ይግባኝ ባዩ/ ባለመቅረቡ መዝገቡ እንዱዘጋላቸው በመጠየቃቸው ይግባኝ ሰሚ ችልቱ ሁለተኛ ሶስተኛና አራተኛ ተጠሪዎችን እንዲሰናበታቸው የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ መዝገብ ን በማስቀረብ ለማረጋገጥ ችለናል።
በዚህ መዝገብ ከፍሬ ጉዲይ፣ ከተከራካሪዎቹ መሰረታዊ ባህሪና በክርክር የያዙት አቋምና አንደኛ ተጠሪ ያቀረበው ይግባኝ በሚሰማበት ቀነ ቀጠሮ ባለመቅረቡ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሰጠው ትዕዛዝና በሰበር አመልካች አንደኛ ተጠሪና ከሁለተኛ እስከ አራተኛ ተራ ቁጥር ስማቸው የተጠቀሱ ተጠሪዎች ያቀረቡት ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሣኔ መሻሩ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ለጉዲዩ እልባት መስጠት አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።
አራተኛ ተጠሪ ወኪላቸው በመሆን የፈፀማቸውን ሽያጭ የፍርም ጉድለት ያለበት ስለሆነ ይፍረስልኝ የሚል ጥያቄ ሣያቀርቡ ቆይተው አቶ ኪዲኔ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ መሆኑን በአንደኛ ተጠሪ በአመልካችና በላልች ተጠሪዎች ካደረጉት ክርክርና ባቀረቧቸው ማስረጃዎች የተረጋገጠ መሆኑን ከሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ ለመገንዘብ ችለናል። አንድ ሰው ለላላ ሰው በሰጠው ፍፁም የውክልና ሥልጣን መሰረት የተከናወነውን ተግባር ለማፍረስና መከራከሪያ ሉያደርገው የሚችለው ወካዩ ራሱ እንደሆነ ከፍታብሓር ህግ ቁጥር 2189 ንዐስ አንቀጽ 1 እና ንዐስ አንቀጽ 2 ድንጋጌ የጣምራ ንባብ ለመገንዘብ ይቻላል። ሟች አቶ ኪዲኔ ወኪላቸው አራተኛ ተጠሪ በሰጡት የውክልና ሥልጣን መሰረት የፈፀማችው የቤት ሽያጭ ውል የህጉን ፍርም አያሟላም ብለው መከራከሪያ የማድረግ መብት በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2189/2/ የተሰጣቸው ቢሆንም በህይወት በነበሩበት ጊዜ ይህንን መብታቸውን አልተጠቀሙበትም አንድ ተወካይ ወካዩ ከሰጠው የሥልጣን ወሰን ሣያልፍ የሰራው ሥራ ላይ የሚታዩ የፍቃድ ጉድለቶችን እንደመከራከሪያ አድርጎ ለማንሣት የሚችለው ወካዩ ብቻ እንደሆነ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2189/2/ የተደነገገ በመሆኑ ወካዩ ይህንን መብት ሣይጠቀምበት ካለፈ ወራሾቹ የሟች ወኪል የውክልና ሥልጣን ወሰኑን ሣያልፍ የሰራውን ተግባር የሚቃወሙበት ህጋዊ መሰረት የለም። በመሆኑም የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት በዚህ መዝገብ አራተኛ ተጠሪ የሟች አቶ ኪዲኔ ወኪል በመሆን ከተሰጣት የውክልና ሥልጣን ወሰን ሣታልፍ የፈፀመችው የቤት ሽያጭ ውል አቶ ኪዲኔ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2189/2/ መሰረት መከራከሪያ ሣያደርጉ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ መሆኑን ሣያገናዝቡ አንደኛው ተጠሪ ያቀረበውን ክስ በመቀበል የቤት ሽያጭ ውለ እንዱፈርስና አመልካች ለአንደኛ ተጠሪ ቤቱን እንዱያስረክብ የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ለይግባኝ በፅሐፍ መልስ የሰጠውና አንደኛ መልስ ሰጭ የነበረው አመልካች በይግባኝ ይግባኝ ባይ የነበረው አንደኛ ተጠሪ ያቀረበውን ይግባኝ በመቃወም መልስ የሰጠ መሆኑን ለመገንዘብ ችለናል። ይግባኙ በሚሰማበት ቀን ይግባኝ ባይ ካልቀረበና መልስ ሰጭዎች ቀርበው በፅሐፍም ሆነ በቃል የሰጡት መልስ ይግባኝ ባይ ያቀረበውን ቅሬታ የሚደግፍ ካልሆነ ይግባኝ ሰሚው ችልት በፍታብሐር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 32/2/ እና በፍታብሐር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 73 በሚደነግገው መሰረት ይግባኙን ሙለ በሙለ በመሰረዝ ሁለንም መልስ ሰጭዎች ማሰናበት ይገባዋል። በያዝነው ጉዲይ ይግባኝ ሰሚው ችልት አመልካች አንደኛ መልስ ሰጭ በመሆን በፅሐፍ የሰጠው መልስ የአንደኛ ተጠሪን የይግባኝ ቅሬታ የሚነቅፍ ሆኖ እያለ የአንደኛው ተጠሪ በሁለተኛ ሶስተኛና አራተኛ ተጠሪዎች ላይ ያቀረበው የይግባኝ ክርክር እንዱቋረጥና ሁለተኛ ሶስተኛና አራተኛ ተጠሪዎች እንዱሰናበቱ ያደረገ ሲሆን በልላ በኩል የአመልካችን መልስ መነሻ በማድረግ የከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ መሻሩ ይግባኝ ሰሚው ችልት በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 32/2/ና የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 73 ድንጋጌዎች መሰረታዊ ይዘት መንፈስና ዓላማ ያልተከተለ ትዕዛዝና ውሣኔ የሰጠ መሆኑን ለመገንዘብ ችለናል። የዚህም ትዕዛዝና ውሣኔ ውጤት የከፍተኛው ፍርድ ቤት በአንድና ተመሳሳይ ጭብጥ የሰጠውን ውሣኔ ለአመልካች ባደረገው የይግባኝ ክርክር መነሻ የሚሽር ለሁለተኛ ሶስተኛ አራተኛ ተጠሪዎች የአንደኛ ተጠሪ ይግባኝ የተሰረዘና የከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሣኔ የሚያፀና እርሱ በርሱ የሚቃረን ውጤት የሚያስከትልና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ከላይ በዘረዘርናቸው የህግ ምክንያቶች የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት መጋቢት 25 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሣኔ ምክንያቱ ተለውጦ ፀንቷል።
አመልካች ለአንደኛ ተጠሪ ክርክር የተነሳበትን ቤት የማስረከብ ግዳታና ሃላፉነት የለበትም በማለት ወስነናል።
ወጪና ኪሣራ ግራቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.