No summary available.
ግንቦት 19 ቀን 2003 ዓ/ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታህ ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረቶች ጽ/ቤት -ነ/ፈጅ አጥናፈ ደምሴ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ጥበበ አየለ - ጠበቃ ታገል ጌታሁን ቀረቡ።
**
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ በአመልካች መስሪያ ቤት በአዋጅ ቁጥር 501/98 መሰረት በሚሰጡት ውሰኔዎች ቅሬታ ያለበት ወገን አቤቱታውን ሉያቀርብ የሚገባበትን ፍርድ ቤት የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን ከሳሽ የነበሩት ተጠሪ ናቸው። የአሁኑ ተጠሪ በአመልካች መስሪያ ቤት ላይ የመሰረቱት የክስ ይዘት ባጭሩ፡- RISING የሚለውን የንግድ ምልክት እንዱመዘግብልኝ አመልክቼ ማመልከቻዬን ያላግባብ ያልተቀበለኝ ስለሆነ የንግድ ምልክቱን እንዱመዘግብልኝ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ አመልካች በተከሣሽነቱ ቀርቦ በሰጠው መልስም ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ ሥልጣኑ ማየት እንደማይችል ገልፆ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል።፡ ክሱ የቀረበለት ፍርድ ቤትም የአመልካችን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ነጥብን ውድቅ አድርጓል በፍሬ ጉዲዩ ላይም ተጠሪ የንግድ ምልክቱ እንዱመዘገብላቸው ሲል ወስኗል። የስር ፍርድ ቤት የአመልካችን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ውድቅ ያደረገው አመልካች መስሪያ ቤት በፍርድ ቤት ሉከሰስ እንደሚችል አዋጅ ቁጥር 501/98 ይደነግጋል በሚል ምክንያት ነው ። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ፀንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም የአመልካች መስሪያ ቤት በጉዲዩ ላይ ውሳኔ የመስጠት ስልጣኑ በአዋጅ ቁጥር 501/98 አንቀጽ 17 ስር የተደነገገ ሆኖ በውሳኔው ላይ ቅሬታ ያለው ወገን ደግሞ ይግባኙን ማቅረብ ያለበት ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስለመሆኑ የአዋጅ ቁጥር 501/98 አንቀጽ 49 ድንጋጌ በአዋጅ ቁጥር 25/1988 ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከተሰጠው የይግባኝ ስልጣን ድንጋጌዎች ጋር አጣምሮ በማንበብ መረዲት የሚቻልና በጉዲዩ ላይ በስራ ላይ የነበሩትና ላልች ተዛማጅ ሕጎችም ሆነ ያለው አሰራር አየመልካች መስሪያ ቤት የሚሰጠው ውሳኔ በይግባኝ ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይቀርብ የነበረ አሁንም እየቀረበ ያለ መሆኑን በግልጽ የሚያሳዩ ሁነው እያለ ጉዲዩን የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመጀመሪያ ደረጃ ስልጣኑ ቀጥታ ክስ መመልከቱ ተገቢነት የለውም በማለት መከራከሩን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በስር ፍርድ ቤት የቀረበውን የንግድ ምልክት ምዝገባ ጥያቄ ተቀብል የተጠሪን የንግድ ምልክት እንዱመዘግብ የተሰጠው ውሳኔ እንዱሁም የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉዲዩን በቀጥታ ክስ አስተናግድ ፍርድ የሰጠበትን አግባብ ከአዋጅ ቁጥር 320/1995 ፣ 501/98 እና 25/1988 አንፃር ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልት እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው የጽሁፍ መልሳቸውን ሰጥተዋል። ተጠሪ በጽሁፍ መልሳቸው በተመሳሳይ ጉዲይ በመ/ በሰበር ችልት የአመልካች የሰበር ቅሬታ ለሰበር ችልቱ አያስቀርብም ተብል መዘጋቱን ፣በአዋጅ ቁጥር 501/98 አንቀጽ 17/2/ ስር ይግባኝ የሚለው ቃል መቀመጡ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕጉ የተቀመጠውን የይግባኝ ቃል ትርጉም በመያዝ ሳይሆን ቅሬታ በሚል ቃል መንፈስ ነው የሚለትንና ላልች ነጥቦችን በማንሳትና በዋቢነትም አግባብነት አላቸው ያሎቸውን ሕጎችና ድንጋጌዎችን በመጥቀስ በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ የሕግ ስህተት የለም በማለት ተከራከረዋል። አመልካች በበኩለ የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልሱን አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። አንደመረመረውም የችልቱን ምላሽ የሚያሰፈልገው አቢይ ነጥብ የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉዲዩን የማየት የሥረ ነገር ስልጣን አለው?
ወይስ የለውም የሚለው ሆኖ አኝቶታል።
በመሰረቱ አመልካች በአዋጅ ቁጥር 320/1995 አንቀጽ 6/1/ መሰረት የንግድ ምልክት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማመልከቻዎችን በመቀበል አግባብ ባለው የአእምሯዊ ንብረት ሕግ መሰረት ምርመራ በማካሄድ ውሳኔ የመስጠትና በንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 501/98 አንቀጽ 36 መሰረት በተመዘገበ የንግድ ምልክት ላይ የሚነሱ ክርክሮችን በማየት ፈራሽ የማድረግ ስልጣን የተሰጠው መሆኑን የተጠቀሱት ድንጋጌዎች በግልፅ ያስገነዝባለ። የአዋጅ ቁጥር 501/98 አንቀጽ 17/1/ ድንጋጌ ሲታይም የአመልካች መስሪያ ቤት ስለንግድ ምልክቱ ምዝገባ በሰጠው የመጨረሻ ውሳኔ ላይ ቅሬታ ያለው ማንኛውም ሰው ቅሬታውን ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት ማቅረብ እንደሚችል አስቀምጧል። የአዋጁ አንቀጽ 49 ሲታይ ደግሞ ስልጣን ያለው ፍርድ ቤትን ያሳያል።
በዚህ ድንጋጌ መሰረት በአዋጁና አዋጁን ለማስፈጸም በአዋጁ አንቀጽ 47 መሰረት በሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚወጣው ደንብ የተመለከቱ ጉዲዩችን በሚመለከት የሚነሱ ክርክሮችንና ተዛማጅ ጉዲዮችን የማየት ስልጣን የሚኖራቸው የፋዳራል ፍርድ ቤቶች ናቸው በሚል የሚደነግግ ነው።
እንግዱህ በሕጉ ረገድ ያለው የውሳኔ አሰጣጥና የይግባኝ አቀራረብ ሥርዓት ከላይ የተጠቀሰው ሲሆን ሕጉ አመልካች መስሪያ ቤት በሚሰጠው የመጨረሻ ውሳኔ ላይ ቅሬታ ያለው ወገን ስልጣን ላለው ፍርድ ቤት ይግባኝ የማቅረብ መብት (The right to Appeal) እንዲለው በግልፅ ከማስቀመጡ ውጪ ይግባኙ በፋዳራለ ፍርድ ቤቶች በየትኛው እርከን ለሚገኝ ፍርድ ቤት እንደሚቀርብ ግልጽና አሻሚነት በላለው አነጋገር አያስቀምጥም። እንዱህ በሆነ ጊዜ ሕጉን መተርጎም ተገቢ ይሆናል።
የአዋጅ ቁጥር 501/98 አንቀጽ 17/1/ ድንጋጌ ርእሱ ሲታይ አማርኛው ‛ይግባኝ የማቅረብ መብት“ በሚል የተቀመጠ ሲሆን የእንግሉዝኛው ቅጂ ደግሞ ‛The right to Appeal“ በሚል የተቀመጠ ነው። እንግዱህ ሕጉ በይዘቱና በቅርጹ ይህን የሚመስል ከሆነ ይግባኝ የሚለው የሕጉ አገላለፅ ለየትኛው ፍርድ ቤት ነው ጉዲዩ መቅረብ ያለበት የሚለውን ጥያቄ ይፈታ ዘንድ የይግባኝ ትርጉሙንና የአቀራረብ ሥርዓቱን በአጠቃላይ ማየቱን፣ የአመልካች መስሪያ ቤትን ለማቋቋም የወጣውን ሕግና ለመስሪያ ቤቱ ስልጣን የሚሰጡ ላልች ተዛማጅነት ያላቸው ሕጎች የሚያስቀምጡትን የይግባኝ አቀራረብ ሥርዓት መመልከቱና ግንዛቤ መውሰደ ተገቢ ይሆናል።
ታዋቂው የ‛ Black’s Law Dictionary“ ይግባኝ የሚለውን ቃል ሲተረጎም A proceeding undertaken to have a decision reconsidered by bringing it to a higher authority, especially, the submission of a lower court’s or agency’s decision to a higher court for review and possible reversal. በሚል ያስቀምጣል። ከዚሁ መገንዘብ የሚቻለው ይግባኝ በበታች አካል የተሰጠ አንድ ፍርድን ወይም ውሳኔን በመቃወም ለበላይ ፍርድ ቤት አቤቱታ በማቅረብ የስር ፍርደ /ውሳኔ/ እንደገና የሚታይበትን ወይም እንዱጣራ የሚደረግበትን ወይም ሉለወጥ የሚችልበትን ሥርዓት የሚያመላክት መሆኑን ነው። በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ/ 320/1/ የተመለከተው ድንጋጌ ሲታይም በፍትሒብሓር ወይም በላልች ሕጎች ውስጥ በልላ ሁኔታ እንዱፈጸም የሚያዝ ድንጋጌ ከላላ በቀር ከሳሽ ወይም ተከሳሽ በፍትሐ ብሓር ፍርድ ቤት በተወሰነበት የመጨረሻ ፍርድ ላይ ይግባኝ ለማለት የሚችለ መሆኑን ይደነግጋል። በዚህ ድንጋጌ መሰረት የይግባኝ ትርጉም በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተከራካሪ የነበረና በተሰጠው ፍርድ ቅር የተሰኘ ወገን ይህንኑ ቅሬታውን ለበላይ ወይም ለይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት አቅርቦ የበታች ፍርድ ቤት የሰጠውን ፍርድ እንዱሻሻል ፣ እንዱለውጥ ወይም በጠቅላላው ውድቅ እንዱሆንና ዲኝነቱ ለእሱ እንዱሰጠው ለመጠየቅ የሚያስችል ሥርዓት ነው። በፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 ደግሞ የይግባኝ ስልጣን ያላቸው ፍርድ ቤቶች ተመልክተዋል። በልላ በኩል አዋጅ ቁጥር 501/98 አንቀጽ 17/1/ ድንጋጌ ስለንግድ ምልክት ምዝገባ ፅ/ቤቱ በሰጠው የመጨረሻ ውሳኔ ላይ ቅሬታ ያለው ማንኛውም ሰው ቅሬታውን ስልጣን ላለው ፍርድ ቤት ማቅረብ ይችላል ብል ሲያስቀምጥ ‛የመጨረሻ ውሣኔ“ የሚለው ሐረግ አቀራረፁና ይዘቱ የሚያሳየው በጉዲዩ ላይ ይግባኝ የሚቀርብበት መሆኑን እንጂ ቀጥታ ክስ የሚቀርብበት አለመሆኑን መገንዘብ የሚቻል መሆኑን ነው። እንዱሁም አመልካች የተቋቋመው አእምሯዊ ንብረትን የሚገዙ ብሓራዊ ሕጎችን የሚያስፈፅም ወይም ተፈፃሚነታቸውን የሚከታተል እንዱሁም አስፈላጊውን አቅም በመገንባት ቀልጣፊና ውጤታማ አገልግልት የሚሰጥ መንግስታዊ አካል ማቋቋሙ በማስፈለጉ መሆኑን አዋጅ ቁጥር 320/95 በመግቢያው ያስቀመጠው ጉዲይ ሲሆን የዚሁ አዋጅ አንቀፅ 2 ደግሞ ‛አእምሮአዊ ንብረት“ እና ‛ፒተንት“ የሚለትን ቃላት ትርጉም አስቀምጧል። በዚህም መሰረት አእምሯዊ ንብረት ማለት የሰው ልጅ አእምሮ ውጤት በሆኑ የፈጠራ ሥራዎች ላይ ያለ ሕጋዊ መብት ሲሆን ፕተንትን፣ የንግድ ምልክትን፣ የምስክር ወረቀትንና ኮፑ ራይትን እንደሚጨምር በአዋጁ አንቀፅ 2/1/ ድንጋጌ የተቀመጠ ሲሆን ፕተንት ማለት ደግሞ የፈጠራ ስራን ለማስጠበቅ የሚሰጥ መብት ሲሆን በፈጠራ በአነስተኛ ፈጠራና በኢንደስትሪያዊ ንድፍ በአዋጅ ቁጥር 123/87 መሰረት በፈጠራ በአነስተኛ ፈጠራና በኢንዲስትሪያዊ ንድፍ የሚሰጠውን የአስገቢ ፕተንት የግልጋልት ሞዳል ምስክር ወረቀትና የኢንደስትራያዊ ንድፍ የምዝገባ የምስክር ወረቀትን እንደሚጨምር በአንቀጽ 2/2/ ስር በግልፅ ሰፍሮ እናገኛለን። ይህ መስሪያ ቤት ከሚያስፈጽማቸው ሕጎች መካከል አንደ አዋጅ ቁጥር 41ዐ/1996 ሲሆን በዚህ አዋጅ አንቀጽ 2/9/ እና 15/ ድንጋጌዎች ሲታዩም በአዋጁ በሚገዙ ጉዲዮች ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችን የመመልከት ስልጣን የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስልጣን ስለመሆኑ በግልፅ ያሳያለ።፡ በልላ በኩል የፈጠራ፣ የአነስተኛ ፈጠራና የኢንደስትሪያል ንድፍ አዋጅ ቁጥር 123/1987 ስር የይግባኝ ስልጣኑ የማዕከላዊ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስልጣን ስለመሆኑ አንቀፅ 2/1፣ እና 54 ድንጋጌዎች በአንድ ላይ ሲነበቡ የሚያሳዩት ጉዲይ መሆኑን መገንዘብ የሚቻል ሆኖ አግኝተናል።
እነዚህ ሕጎች በአመልካች መስሪያ ቤት ይፈጸማለ ተብለው ከተጠቀሱት ሕጎች መካከል ሲሆኑ አመልካች መስሪያ ቤት በሚሰጠው ውሳኔ ይግባኙ የሚቀርበው በግልፅ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መሆኑን ያሳያለ። ከላይ እንደተገለጸው አመልካች መስሪያ ቤትን ያቋቋመው አዋጅ ቁጥር 32ዐ/1995 መስሪያ ቤቱን ለማቋቋም ያስፈለገበትን ሲገልፅ አእምሯዊ ንብረትን የሚገዙ ብሓራዊ ሕጎችን የሚያስፈፅም ወይም ተፈፃሚነታቸውን የሚከታተል አካል ማቋቋም በማስፈለጉ መሆኑን በግልፅ ያስፈረ ሲሆን ይህ ምክንያት አመልካች መስሪያ ቤት ተመሳሳይ የአእምሯዊ ንብረት ጉዲዮችን ለማስተናገድ ስልጣን የተሰጠው አካል ከመሆኑ ተዲምሮ ሲታይ ጽ/ቤቱ የሚሰጣቸው ውሳኔዎች በተለያዩ ፍርድ ቤቶች ይታያለ፣ ወይም በተወሰኑት ይግባኝ በተወሰኑት ደግሞ ቀጥታ ክስ ይቀርብባቸዋል ብል መደምደም የአመልካች መስሪያ ቤትን ሥልጣንና ተግባር ውጤት ያለው ማድረግ ያስችላል ተብል የማይታሰብ መሆኑን አመልካች መስሪያ ቤት የሚያስፈጽማቸው ሕጎች አውደ ንባብ (contextual interpretation) የሚያስገነዝበን ጉዲይ ነው። በመሆኑ አመልካች መስሪያ ቤት በሕጉ በተሰጠው ስልጣን መሰረት በሚሰጣቸው ውሳኔዎች ቅሬታ ያለው ወገን በሕግ የተሰጠው መብት ይግባኝ ማቅረብ እንጂ ቀጥታ ክስ መመስረት አይደለም። በሕጉ የተዘረጋው ሥርዓት ይግባኝ ከሆነ በፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 እና አግባብነት ባላቸው የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎች መሰረት በጉዲዩ ላይ የይግባኝ ሥልጣን ያለው ፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው። የተጠሪ ጠበቃ በሰ/መ/ በቀረበው ተመሳሳይ ጉዲይ በሰበር ችልቱ አጣሪ ችልት በበታች ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የለበትም ተብል መወሰኑን ገልፀው ይህ ጉዲይም በተመሳሳይ መልኩ ሉስተናገድ እንደሚገባው ያቀረቡትን ክርክር ስንመለከተውም ሦስቱ ዳኞች የሚሰጡት የሰበር ትዕዛዝ /ውሳኔ/ አስገዲጅነት የላለው መሆኑን አዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀፅ 2/1/ ድንጋጌ በግልፅ የሚያሳይ በመሆኑ ይህ ችልት የሚቀበለው አይሆንም።
በመሆኑም በሰ/መ/ የተሰጠው ትዕዛዝ ይህን ጉዲይ በተመሳሳይ መንገድ ለመወሰን የሚያስገድድ ባለመሆኑ በዚህ ረገድ የቀረበውን የተጠሪ ጠበቃ ክርክርን አልፈነዋል።
ሲጠቃለልም የአዋጅ ቁጥር 5ዐ1/98 አንቀፅ 6፣17፣36፣እና 49 ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ ከይግባኝ ትርጉምና አመልካች መስሪያ ቤት ከተቋቋመበት አላማና አመልካች መስሪያ ቤት የሚያስፈፅማቸው ከአዋጅ ቁጥር 5ዐ1/98 ውጪ ያለት ላልች ተዛማጅነት ያላቸው ሕጎች ከዘረጉት የይግባኝ አቀራረብ ሥርዓት አንጻር ሲታይ በንግድ ምልክት ምዝገባ ጉዲይ ላይ አመልካች መስሪያ ቤት በሚሰጠው ውሳኔ ቅሬታ ያለው ወገን ያለው መብት በይግባኝ ሥርዓት የማስከበር እንጂ በቀጥታ ክስ የሚስተናገድ አለመሆኑን ፣ ይግባኙ መቅረብ ያለበት ደግሞ ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መሆኑን የሚያስረዲ ሆኖ አግኝተነዋል። በመሆኑም የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉዲዩን በቀጥታ ክስ ለማየት አይችልም ተብል በአመልካች በኩል የቀረበውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አዋጅ ቁጥር 5ዐ1/98 አመልካች መስሪያ ቤት ሉከሰስ እንደሚችል ይደነግጋል በሚል በደፈናው ውድቅ ማድረጉና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ይህንኑ ሳያርም ማለፈ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተናል። በዚህም መሰረት ተከታዩን ወሰነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ በ13/4/2002 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በዐ3/1ዐ/2002 ዓ/ም የጸናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ/348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የንግድ ምልክት ምዝገባ አቤቱታ ላይ አመልካች በሚሰጠው የመጨረሻ ውሳኔ ቅሬታ ያለው ወገን ያለው መብት ይግባኙን ለፋዳራል ከፍተኛ ማቅረብ እንጂ ቀጥታ ክስ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ማቅረብ አይደለም ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.