No summary available.
የካቲት 22 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ስላሴ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ኢትዮ ሴራሚክ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር - አልቀረቡም ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች አንደኛ ተጠሪ በሰጠው ውሣኔ ቅር በመሰኘት ያቀረቡትን ይግባኝ በማየት የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት የሰበር አቤቱታ በማቅረባቸው ነው።
የክርክሩ መነሻ አንደኛ ተጠሪ ሁለተኛ ተጠሪ ያቀረበውን የንግድ ምልክት ምዝገባ ጥያቄ በመቀበል ሁለተኛ ተጠሪ በአራት ማዕዘን ውስጥ ዙሪያውን በአስር ኮከቦች የተከበበ “ ETHIO CEMENT “ የሚለው የንግድ ምልክት ለመመዝገብ የሰጠው ውሣኔ ነው።፡ ሁለተኛው ተጠሪ ዓለም አቀፍ ምድብ ያለው የሲሚንቶ ምርት ግልጋልቱ በአራት ማዕዘን ውስጥ ዙሪያውን በአስር ኮከቦች የተከበበና መካከለ “ ETHIO CEMENT “ የሚል ፅሐፍ ያለበት የንግድ ምልክት በአንደኛው ተጠሪ እንዱመዘገብለት ቁጥሩ 1912 በሆነ ማመልከቻ ጠይቋል። አንደኛ ተጠሪ የንግድ ምልክቱን ከመመዝገቡ በፉት መቃወሚያ የሚያቀርብ ወገን ካለ መቃወሚያውን እንዱያቀርብ መጋቢት 15 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በወጣው አዱስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያ አውጥቷል። አመልካች "ኢትዮ ሲሚንቶ" በሚለው የንግድ ሥም የኢንቨስትመንት ፈቃድ በማውጣት የሲሚንቶ ፊብሪካ ለማቋቋም ጥረት እያደረገ መሆኑን በመግለፅ ሁለተኛ ተጠሪ እንዱመዘገብለት ያቀረበው የንግድ ምልክት ከአመልካች የንግድ ስም ጋር አንድ አይነት በመሆኑና ሁለቱም ድርጅቶች የሲሚንቶ ምርት ለተገልጋዩ የሚያቀርቡ በመሆናቸው ተጠቃሚውን የሚያደናግር በመሆኑ የንግድ ምልክቱ ሉመዘገብ አይገባውም የሚል መቃወሚያ አቅርቧል። አንደኛ ተጠሪ ኢትዮ ሲሚንቶ /ETHIO CEMENT/ የሚለው ሀረግ የአመልካች የንግድ ስም መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ያቀረበለት መሆኑን ገልፆ ሆኖም አመልካች ይህንን ሀረግ በንግድ ምልክትነት ስላላስመዘገበ፣ የሁለተኛ ተጠሪ የንግድ ምልክት ETHIO CEMENT የሚለው ሀረግ ብቻ ሣይሆን ዙሪያውን ያለት ኮከቦች አካል ሆኖ ያቀረበ በመሆኑና አመልካች “ ETHIO CEMENT “ የሚለውን ሀረግ ከላላ ሉመዘገብ ከሚችል ምልክት ጋር ማስመዝገብና መጠቀም ስለሚችል የአመልካች መቃወሚያ የህግ መሰረት የለውም በማለት፣ ሁለተኛ ተጠሪ እንዱመዘገብለት የጠየቀውን የግንድ ምልክት በመመዝገብ ዕውቅናና ጥበቃ ሰጥቷል።
አንደኛ ተጠሪ በተሰጠው ውሣኔ ቅር በመሰኘት አመልካች ይግባኝ ለፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበዋል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሣኔው የይግባኝ ቅሬታ የቀረበበት አንደኛ ተጠሪና ሁለተኛ ተጠሪ ያቀረቡትን መልስና የአመልካችን የመልስ መልስ ከሰማ በኋላ አንደኛ ተጠሪ ውሣኔ ሲሰጥ ያቀረባቸውን ምክንያቶች በመቀበል አንደኛ ተጠሪ በአራት ማዕዘን ውስጥ በአስር ኮከቦች የተከበበ “ ETHIO CEMENT “ የሚል ፅሐፍ ያለበት የንግድ ምልክት የሁለተኛ ተጠሪ ንብረትና የንግድ ምልክት መሆኑን በማረጋገጥ መመዝገቡ የአመልካችን መብትና ጥቅም ስለማይነካ የንግድ ምልክቱ አይሰረዝም በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
አመልካች ሰኔ 1ዐ ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ለሁለተኛ ተጠሪ በንግድ ምልክትነት የተመዘገበው “ ETHIO CEMENT “ የሚለው ሀረግ የአመልካች የንግድ ስምና መጠሪያ ሆኖ አግባብነት ባላቸው አካላት ተመዝግቧል። አንደኛ ተጠሪ የሁለተኛው ተጠሪን የንግድ ምልክት ሲመዘግብ አመልካች በንግድ ስሙ አምርቶ ፅፍ ለገበያ የሚያቀርበውን የሲሚንቶ ምርት ሁለተኛ ተጠሪ የንግድ ምልክት አድርጎ ለተገልጋዩ በሚያቀርበው የሲሚንቶ ምርት ላይ በንግድ ምልክትነት እንዱጠቀምበት ፈቃድ ሰጥቷል። ይህ ተጠቃሚውን ህብረተሰብ የሚያሣስትና የሚያደናግር ሲሆን የአንደኛ ተጠሪ ውሣኔ የንግድ አሰራር አዋጅ 329/95 እና የንግድ ምልክት ጥበቃና አሰራር አዋጅ 5ዐ1/1998 መሰረታዊ ግብና ዓላማ በሚያሣካ መንገድ ተጣጥመው ሥራ ላይ እንዱውለ የሚያደርግ አይደለም። ስለሆነም እኔ በንግድ ስምና መጠሪያነት የምገለገልበትን “ ETHIO CEMENT “ ሁለተኛ ተጠሪ የንግድ ምልክት አድርጎ እንዱጠቀም አንደኛ ተጠሪ የሰጠው ዕውቅና የአዋጅ ቁጥር 329/1995 ድንጋጌዎች እና የአዋጅ ቁጥር 501/1998 አንቀፅ 5 እና ላልች ድንጋጌዎች የሚጥስና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል።
አንደኛ ተጠሪ የንግድ ስም በአንድ ድርጅት መጠሪያነት የሚያገለግል ሲሆን ዓላማው አንደኛውን የንግድ ድርጅት ከላላው የንግድ ድርጅት ለመለየት ነው። የንግድ ስም የሚመዘገበው በንግድ ሚኒስትር ወይም በክልል ንግድ ቢሮዎች ነው። የንግድ ምልክት የአንድን ሰው ምርት ወይም አገልግልት ከላላው ሰው ለመለየት የሚያገለግል ነው። የንግድ ምልክት ጥበቃ የሚያደርገውና የሚመዘገበው በአዋጅ ቁጥር 501/1998 ሲሆን ይህንን ተግባር አንደኛ ተጠሪ እንዱያከናውን በአዋጅ ቁጥር 320/1995 ስልጣን ተሰጥቶታል። የንግድ ድርጅቶች የንግድ ስያሜያቸውን በንግድ ምልክትነት በማስመዝገብ ወይም በመጠቀም ባለቤት መሆን እንደሚቻል አዋጅ ቁጥር 501/98 በአንቀፅ 5/1/ እና በአንቀፅ 7/2/ በግልፅ የተደነገገ ቢሆንም አመልካች የንግድ ስማቸውን በንግድ ምልክትነት አላስመዘገቡም። አንደኛ ተጠሪ ጥበቃ የሰጠውና የመዘገበው ለኮከቦቹ እንጅ “ ETHIO CEMENT “ ለሚለው ሀረግ አይደለም። ስለዚህ የሰበር አቤቱታው የህግ መሰረት የላለው በመሆኑ ውድቅ ሆኖ እንድሰናበት በማለት ታህሣሥ 13 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም. በፅሐፍ መልስ ሰጥቷል።
ሁለተኛው ተጠሪ በበኩለ የንግድ ስምና የንግድ ምልክት የተለያዩ ናቸው። አመልካች ሲሚንቶ አምርቶ መሸጥ ስላልጀመረ በሚያመርተው ሲሚንቶ ላይ የሚያስቀምጠው የንግድ ምልክት ምን እንደሆነ ገና አልታወቀም። እኔ የአመልካችን የንግድ ስያሜ በንግድ ምልክትነት አልተጠቀምኩም። አመልካች ምርት ማከፊፈል አልጀመረም ስለዚህ የአመልካችን የሰበር አቤቱታ በመሰረዝ እንዱያሰናብተን በማለት ጥር 3ዐ ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም. የተፃፈ መልስ ሰጥቷል። ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር ግራ ቀኙ ያቀረቡት የፅሐፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው አንደኛ ተጠሪና ይግባኝ ሰሚው የከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ተጠሪ እንዱመዘገብለት ያቀረበው "የንግድ ምልክት" አመልካች የንግድ ስሙን በንግድ ምልክትነት ስላላስመዘገበ ወይም የንግድ ስሙ የሚያመርተውን የሲሚንቶ ምርት ለተጠቃሚው ማቅረብ ያልጀመረ በመሆኑ መቃወሚያ ሉያቀርቡበት አይችልም በማለት የሰጡት ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ጭብጥ መመርመር ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ከላይ የተያዘውን ጭብጥ ለመወሰን አመልካችና ተጠሪ ለማምረትና ለመስጠት የሚፈልጉትን አገልግልት አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች በተለይም ከንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 67/1989 በአዋጅ ቁጥር 328/1995 እንደተሻሻለ አግባብነት ያላቸውን የንግድ ህግ ድንጋጌዎች የንግድ አሰራር አዋጅ ቁጥር 329/1995 ከአንደኛው ተጠሪ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 32ዐ/1995 እና ከአዋጅ ቁጥር 5ዐ1/1998 ድንጋጌዎች ማገናዘብና ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የተከተለውን የህግ አተረጓጎም ተገቢነት መመርመር አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።
አመልካች በአዋጅ ቁጥር 67/1989 በአዋጅ ቁጥር 329/1995 እንደተሻሻለው በአንቀፅ 16 ንዐስ አንቀፅ 1 በሚደነግገው መሰረትና የንግድ ህግ አንቀፅ 135 ንዐስ አንቀፅ 1 እና ንዐስ አንቀፅ 2 በሚደነግጉት መሰረት "ኢትዮ ሲሚንቶ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር" በሚል የንግድ ስም ተመዝግቦ የሲሚንቶ ማምረቻ ፊብሪካ በማቋቋምና ሲሚንቶ በማምረት ለአገር ውስጥ ገበያና በተሻሻለው የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁ. 328/1995 አንቀፅ 32 መሰረት ምርቱን ወደ ወጭ አገር ለመላክ የሚችል የንግድ ድርጅት ስለመሆኑ አመልካች ለአንደኛ ተጠሪ ካቀረባቸው ማስረጃዎችና በይግባኝ እና በሰበር ካቀረበው ክርክር ለመገንዘብ ችለናል። አመልካች ይህንን ተግባሩን ሲያከናውን በንግድ ህጉና በንግድ ሥራ አዋጅ 329/1995 መሰረት ተገቢው ጥበቃ የሚሰጠው ሲሆን በንግድ ሥራ አዋጅ ቁ. 329/1995 እና በላልች ህጎች የተደነገጉትን ግዳታና ሀላፉነቶች በአግባቡ መወጣት ይጠበቅበታል። ይህም በመሆኑ አመልካች ፊብሪካውን በመገንባት ያመረተውን ሲሚንቶ ለአገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ሲያቀርብ በንግድ ሥራ አዋጅ ቁጥር 329/95 አንቀፅ 21 በተደነገገው መሰረት ስለ አመረተው ምርት መግለጫ የመለጥፍ ግዳታ አለበት። በምርቱ ላይ የሚለጥፈው መግለጫ በአዋጅ ቁጥር 329/95 አንቀፅ 21 ንዐስ አንቀፅ 2 የተደነገገውን መያዝ እንደሚገባውና በተለይም አመልካች የሲሚንቶ ምርቱን አሽጎ ለገበያ ሲያቀርብ በአዋጅ ቁጥር 329/95 አንቀፅ 21 ንዐስ አንቀፅ /3/ በሚደነግገው መሰረት የዕቃውን የተጣራ ክብደት፣ የፊብሪካው ወይም የአሻጊው ስምና አድራሻና ዕቃው አገልግልት መስጠት የሚያበቃበትን ቀን እና ዕቃው የተመረተበትን ቀን በምርቱ ላይ የመፃፍ ግዳታና ሀላፉነት እንዲለበት ከላይ ከተጠቀሰው የህግ ድንጋጌ ለመገንዘብ ይቻላል። ከዚህም የምንረዲው አመልካች የፊብሪካውን ግንባታ አጠናቅቆ የሲማንቶ ምርት በማምረት ለገበያ ሲያሰራጭ ሲሚንቶውን ያመረተው ‛ኢትዮ ሲሚንቶ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር‛ መሆኑን በመግለፅ የመለጠፍ ህጋዊ ግዳታና ኃላፉነት ያለበት መሆኑ በአዋጅ ቁጥር 329/95 አንቀፅ 21 ንዐስ አንቀፅ 3/ለ/ በግልፅ የተደነገገ መሆኑ ነው። አመልካች ከዚህ በፉት የሲሚንቶ ምርት በንግድ ስሙ በመጠቀም ያላሰራጨ ቢሆንም ምርት ሲጀምር የንግድ ስሙንና አድራሻውን አሽጎ በሚያቀርበው የሲሚንቶ ምርት ላይ የመግለፅ /የመፃፍ/ ህጋዊ ግዳታና ኃላፉነት አለበት።
በልላ በኩል ሁለተኛው ተጠሪ የሚሰራው ሥራ የሲሚንቶ ምርት ስርጭት ጋር የተገናኘ መሆኑ ሁለተኛው ተጠሪ ለአንደኛ ተጠሪ ባቀረበው አቤቱታ የተገለፀ ሲሆን፣ ሁለተኛው ተጠሪ በአራት ማዕዘን ውስጥ ሆኖ በአስር ኮከቦች የተከበበና /ETHIO CEMENT/ የሚለው ሀረግ ያለበት የንግድ ምልክት አንደኛ ተጠሪ ብቸኛ ባለሀብትና ተጠቃሚ መሆኑን በማረጋገጥ እንዱመዘግብለት፣ ጥያቄ አቅርቧል። ይህ የሁለተኛው ተጠሪ የንግድ ምልክት በአራት ማዕዘን ምስል ውስጥ በአስር ኮከቦች መካከል የሚፃፍ ቢሆንም በአዋጅ ቁጥር 329/95 አንቀፅ 21 ንዐስ አንቀፅ 3/ለ/ መሰረት አመልካች በሚያመርተውና አሽጎ በሚሸጠው የሲሚንቶ ምርት ላይ መግለፅ ህጋዊ ግዳታው ከሆነው የአመልካች የንግድ ስም / ኢትዮ ሲሚንቶ/ በእንግሉዝኛው “ ETHIO CEMENT “ PRIVATE LIMITED ጋር አንድና ተመሣሣይ ነው። ተጠሪ በንግድ ምልክትነት በሚያመርተውና በሚያሰራጨው የሲሚንቶ ምርት ላይ እንዱለጥፍ በአንደኛ ተጠሪ የተመዘገበለት የንግድ ምልክት አመልካች በህግ ተገድድ በምርቱ ላይ መግለፅ ከሚገባው የንግድ ስያሜ ጋር የሚመሳሰል ተመሣሣይ “ ETHIO CEMENT “ የሚል ሀረግ ያለው ነው።
የንግድ ሥራ አዋጅ መሰረታዊ ዓላማ ለነፃ ገበያ ውድድር እንቅፊት የሆኑ ድርጊቶችና ተገቢ ያልሆኑ የንግድ ሥራዎች እንዲይፈፀሙ በመከላከልና በማስወገድ ተገቢ የንግድ ውድድር እንዱሰፍን ማድረግ እንደሆነ በአዋጅ ቁጥር 329/95 አንቀፅ 3 ንዐስ አንቀፅ 1 ተደንግጓል። በዚህ አዋጅ መሰረት ተገቢ ያልሆነ የንግድ ውድድር ማለት በንግድ ሥራ ኦዱት ውስጥ በተለያዩ መንገድች ተወዲዲሪን ለማጥፊት ያለመ ማንኛውም ድርጊት ወይም ተግባር ሁለ ተገቢ ያልሆነ የንግድ ውድድር እንደሆነ እንደሚቆጠር በአዋጅ ቁጥር 329/95 አንቀፅ 10 ንዐስ አንቀፅ 1 በመርህ ደረጃ የተደነገገ ሲሆን፣ በልላው የንግድ ድርጅት ወይም በንግድ ድርጅቱ ተግባሮች በተለይም ድርጅቱ ከሚያቀርበው ምርት ወይም አገልግልት ጋር በተገናኘ ሁኔታ ማደናገርን ያስከተለ ወይም ሉያስከትል የሚችል ማናቸውም ድርጊትና የአንድ ድርጅት ወይም የድርጅቱን ተግባሮች በተለይም ድርጅቱ ከሚያቀርበው ምርት ወይም አገልግልት ጋር በተገናኘ ሁኔታ የሕዝብ ግንዛቤን ያዛባ ወይም ሉያዛባ የሚችል ማናቸውም ድርጊት ተገቢ ያልሆኑ የንግድ ውድድሮች እንደሆኑ በአዋጅ አንቀፅ 1ዐ ንዐስ አንቀፅ 2/ሀ/ እና /ሐ/ በግልፅ ተደንግጓል።
በተመሣሣይ ሁኔታ የንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ አዋጅ መሰረታዊ ግብ ዕቃ በማምረት እና በማከፊፈል ወይም አገልግልት በመስጠት የንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሰዎችን መልካም ስም እና ዝና መጠበቅና በተመሣሣይ ዕቃዎችና አገልግልቶች መካከል መሣከርን ማስወገድ መሆኑ በአዋጅ ቁጥር 501/1998 መግቢያ በመጀመሪያው ፒራግራፍ በግልፅ ተመልክቷል። ከዚህ በተጨማሪ አንደኛ ተጠሪ የፕተንትና የንግድ ምልክት የምዝገባ ወረቀት ማመልከቻዎችን ተቀብል ውሣኔ ከመስጠቱ በፉት የንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ አዋጅን መሰረታዊ ግብና ዝርዝር ድንጋጌዎች እንደዚሁም ላልች አግባብነት ያላቸውን የህግ ድንጋጌዎች መመርመር ወይም እንዱመረመር የማድረግ ግዳታና ኃላፉነት ያለበት መሆኑ በአዋጅ ቁጥር 320/95 አንቀፅ 6 ንዐስ አንቀፅ 1 በግልፅ ተደንግጓል።
ስለሆነም አንደኛ ተጠሪ “ ETHIO CEMENT “ የሚል ሀረግ ያለበትን የንግድ ምልክት እንዱመዘግብለት ሁለተኛ ተጠሪ ሲጠይቀው ‛ኢትዮ ሲሚንቶ“ በእንግሉዝኛው “ ETHIO CEMENT “ በሚል የንግድ ስም የሚጠራው አመልካች በሚያመርተውና አሽጎ በሚሸጠው ሲሚንቶ ላይ ይህንን የንግድ ስሙን የመፃፍና የመግለፅ ግዳታና ኃላፉነት በአዋጅ ቁጥር 329 በአንቀፅ 21 ንዐስ አንቀፅ 3/ለ/ የተጣለበት መሆኑንና ለተጠቃሚው ህብረተሰብ በአንድ በኩል በአራት ማዕዘን ምስል ውስጥ ሆኖ በአስር ኮከቦች መካከል የተፃፈ “ ETHIO CEMENT “ የሚል ሀረግ ያለው የንግድ ምልክት ያለበት ሲሚንቶ በሁለተኛው ተጠሪ የሚቀርብ መሆኑና በልላ በኩል “ ETHIO CEMENT “ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የሚለው የአመልካች የንግድ ስም የተፃፈበት የሲሚንቶ ምርት ላቀርብለት የሚችል መሆኑን የማገናዘብ ሀላፉነት አለበት።
እነዚህ ሁለት ምርቶች ለተጠቃሚው በሚቀርቡበት ጊዜ የንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ አዋጅ የወጣበትን መሰረታዊ ዓላማ በሚፃረር መንገድ በሁለተኛው ተጠሪና የአመልካች ምርት መካከል መሣከርን የሚፈጥርና በአዋጅ ቁጥር 329/95 አንቀፅ 10 ንዐስ አንቀፅ 2/ሀ/ እና /ሐ/ ክልከላ የተደረገበት ተገቢ ያልሆነ የንግድ ውድድር ምክንያትና መንስኤ የሚሆኑ በመሆኑ አንደኛ ተጠሪ በአዋጅ ቁጥር 320/95 አንቀፅ 6 ንዐስ አንቀፅ 1 የተደነገገውን አግባብነት ያላቸውን ህጎች ሣይመረምር የአመልካችን የንግድ ስም በውስጡ የሚያካትተውን የሁለተኛ ተጠሪ የንግድ ምልክት ተቀብል መመዝገቡ ህግ አውጭው በአዋጅ ቁጥር 329/95 እና በአዋጅ ቁጥር 501/98 በንግድ ሥራ ለተሰማራው ሰውም ሆነ ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ለመስጠት ያሰበውን ህጋዊ ጥበቃና ዋስትና በተሟላ ሁኔታ ተፈፃሚ ለማድረግ የማያስችል የህግ አረዲድና አተገባበር ሆኖ አግኝተነዋል።
ስለሆነም አንደኛ ተጠሪና ሁለተኛው ተጠሪ የአመልካች የንግድ ስም የተካተተበትን የንግድ ምልክት በመመዝገብ የሰጠው ዕውቅና ከላይ በዝርዝር ይዘታቸው፣ መሰረታዊ ዓላማና ግባቸው የዘረዘርናቸውን ተያያዥነት ያላቸው የህግ ማዕቀፍችና ድንጋጌዎች ያላገናዘበና መሰረት ያላደረገ፣ እንደዚሁም በአዋጅ ቁጥር 320/95 አንቀፅ 6 ንዐስ አንቀፅ 1 መሰረት አግባብነት ያላቸውን ላልች የህግ ማዕቀፍችና ድንጋጌዎች ሣይመረምርና ሣያገናዝብ የሰጠው ውሣኔ በመሆኑ በይግባኝ ሉታረም የሚገባው ሆኖ እያለ በይግባኝ ሰሚው ከፍተኛ ፍ/ቤት መፅናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
አንደኛ ተጠሪና በከፍተኛው ፍርድ ቤት ሁለተኛ ተጠሪ ያቀረበውና የአመልካችን የንግድ ስም የሚያካትተውን የንግድ ምልክት እንዱመዘገብ የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
ሁለተኛ ተጠሪ የአመልካችን የንግድ ስም “ ETHIO CEMENT “ የሚለውን ሀረግ ከንግድ ምልክቱ በማውጣትና በልላ በመተካት የንግድ ምልክቱን ሰርቶ ካላቀረበ በስተቀር የንግድ ምልክቱ ሉመዘገብና ህጋዊ ጥበቃ ሉሰጠው አይገባም በማለት ወስነናል።
በዚህ ፍርድ ቤት የወጣውን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.