No summary available.
መጋቢት 22 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ስላሴ በላቸው አንሺሶ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ነ/ፈጅ ናሆም ሸዋንግዛው ቀረቡ ተጠሪ፡- 1- የቻይና ዋንቦ ኢንጂሪንግ ኮርፕሬሽን ጠበቃ ደቺ ፈለቀ ቀረቡ 2- ታብትራ ኃ/የተ/የግል ማህበር ጠበቃ መኮንን ሽፈራው ቀረቡ የሰ/መ/ የሆነ መዝገብ ከዚህ መዝገብ ጋር ተጣምሮ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የመድን ውልን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ 1ኛ ተጠሪ በሰ/መ/ በአመልካች በ2ኛ ተጠሪና በአቶ ዮናስ ተስፊዬ ላይ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመሰረተው ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡- በአሁኑ አመልካች የመድን ዋስትና የተሰጠው የ1ኛ ተጠሪ ኤላክትሪክ ትራንስፍርመር ንብረትነቱ የአቶ ዮናስ ተስፊዬ በሆነ ተሽከርካሪ በአሁኑ 2ኛ ተጠሪ አስጫኝነት ከጅቡቲ ወደብ ተጭኖ ወደ ደብረ ብርሃን ሲሄድ መኪናው የመገልበጥ አደጋ ደርሶበት በትራንስፍርመሩ ላይ ከባድ ጉዲት መደረሱን ገልፆ የአሁኑ አመልካች በመድን ውለ መሰረት የአሁኑ ሁለተኛ ተጠሪ ደግሞ ወኪል ሁኖ በማስጫኑ የስር ሶስተኛ ተከሣሽ የነበሩት ግለሰብ /አቶ ዮናስ ተስፊዬ/ ደግሞ አጓዥ በመሆኑ ኃላፉነት እንደአለባቸው ጠቅሶ ለደረሰው ጉዲት ብር 2,223,293.80 /ሁለት ሚሉዮን ሁለት መቶ ሃያ ሶስት ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና ሶስት ብር ከሰማኒያ ሳንቲም/ በአንድነትና በነጠላ እንዱከፍለ ይወሰንለት ዘንድ ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው። የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በስር ከሣሽ በኩል ለቀረበበት ክስ በሰጠው መከላከያ መልስ ፡- ከከሣሹ ጋር የመሰረተው የመድን ዋስትና ውል የባህር መድን ዋስትና ውል በመሆኑ ጉዲዩ የሚገዛው በባሕር ሕጉ እንጂ በንግድ ሕጉ አለመሆኑን በትራንስፍርመሩ ላይ ጉዲት የደረሰው ተሽከርካሪው መጫን ከሚችለው አቅም በላይ በመጫኑ ይህም የተደረገው በከሣሹ ወኪል በሆነው ታብትራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በመሆኑና ወኪል ያደረገው ወካዩ እንዲደረገው ስለሚቆጠር እንዱሁም በመድን ውለ ላይ በግልፅ መድን ሰጭውን ከኃላፉነት ነፃ የሚያደርገው እንደሆነ ገልጾ ኃላፉነት የለብኝም በንግድ ሕጉ መሰረትም የእምቢታ ማስታወቂያ በሰባት ቀናት ውስጥ ለመድን ሰጪው ያለመገለፁ የመዲረግ መብቱን ያሳጣው በመሆኑም መድን ሰጪው ኃላፉነት የላለበት መሆኑን እንዱያሳይ እንዱሁም የኃላፉነት መጠኑም ቢሆን የተጋነነ እና በተገቢው ማስረጃ ያልተደገፈ መጠኑን ጠቀሶ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክሯል። በስር ፍርድ ቤት ሁለተኛ ተከሣሽ የነበረው ታብትራ ኃላ.የተ.የግል ማህበር በበኩለ ከተከሣሾች ጋር ተጣምሮ መከሰስ የላለበት መሆኑን በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት አንስቶ የተከራከረ ሲሆን በኃላፉነት ረገድ ደግሞ በተሰጠው የውክልና ስልጣን መሰረት በውለና በሕጉ አግባብ ግዳታውን የተወጣ መሆኑን ገልጾ ክሱ ውደቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል። የስር ሶስተኛ ተከሣሽ የነበሩት ግለሰብ /አቶ ዮናስ ተስፊዬ / በበኩላቸው ከአንድ አጓዥ በሚጠበቅ መልኩ ትራንስፍርመሩን ጭነው ለስር ከሣሽ ያስረከቡ መሆኑንና በጊዜውም በሕጉ አግባብ መሰረት የእቢታ ማስታወቂያ /Protest/ ሳይፃፍላቸው ከስምንት ወራት በሁዋላ ጉዲቱ ደርሷል በማለት ጥያቄ መቅረቡ ሕጋዊ አለመሆኑን ገልፀው ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክረዋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከመረመረ በሁዋላ ለጉዲዩ አግባብነት ያለው የባሕር ሕጉ መሆኑን ጠቅሶ የኢትዮጵያ መድን ድርጅትንና አቶ ዮናስ ተስፊዬን ከኃላፉነት ነጻ ሲያደረጋቸው ታቭታራ ኃ/የተ/የግል ማህበርን ለጉዲዩ ኃላፉ በማድረግ በከሣሽ የተጠየቀውን ገንዘብ ያህል እንዱከፍል ወስኗል። በዚህ ውሣኔ የስር ከሣሽ የኢትዮጵያ መድን ድርጅትና አቶ ዮናስ ተስፊዬ ከኃላፉነት ነፃ መባላቸው ያለአግባብ ነው በማለት ታብትራ ኃ/የተ/የግል ማህበር ደግሞ ኃላፉነት የለብኝም በማለት በየፉናቸው ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ መዛግብቱ ተጣምረው ታይተዋል። ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን መርምሮም ለጉዲዩ አግባብነት ያለው ሕግ የንግድ ሕጉ ሁኖ የስር ፍርድ ቤት የኢትዮጵያ መድን ድርጅትን ከኃላፉነት ነፃ መደረጉ ያላግባብ ነው ታብትራ ኃ/የተ/የግል ማህበር ከመድን ሰጪና ከአቶ ዮናስ ተስፊዬ ጋር ተጣምሮ መከሰሱም ያላግባብ ነው በማለት የስር ፍርድ ቤትን ውሣኔ ሽሮ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ለክሱ መሰረት የሆነውን ገንዘብ ለከሣሽ /ቻይና ወንቦ ኢንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን /እንዱከፍል መድን ሰጪው ገንዘቡን ለከሣሽ ከፍል የስር ሁለተኛ እና ሶስተኛ ተከሣሾችን የመክሰስ መብቱ የተጠበቀ መሆኑ ተገልጾ ተወስኗል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚህ ውሣኔ ላይ ሲሆን የሰበር አቤቱታ የቀረበው በሁለት መዛግብት ነው። በሰ/መ/ አመልካች የሆነው የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ሲሆን የሰበር ተጠሪ የሆኑት የስር ከሣሽና የስር ሁለተኛ ተከሣሸ ናቸው። በሰ/መ/ አመልካች የሆነው የስር ከሣሽ ሲሆን የሰበር ተጠሪ የሆነው ደግሞ የስር ሁለተኛ ተከሣሽ የነበረው ታቭትራ ኃ/የተ/የግል ማህበር ነው።
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ነገረ ፈጅ መስከረም 11 ቀን 2ዐዐ2 ዓ/ም በጻፊት ስምንት ገፅ የሰበር አቤቱታ በፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ውሣኔ ላይ የተፈፀመ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አለ የሚለባቸውን ምክንያቶችን ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ ፡- ለጉዲዩ አግባብነት ያለው የባህር ሕግ ሁኖ እያለ ከውለ መሰረታዊ ይዘት ውጪ የንግድ ሕጉ ተፈፃሚነት አለው መባለ ያላግባብ ከመሆኑም በተጨማሪ መድን ድርጅቱ የስር ሁለተኛና ሶስተኛ ተከሣሾችን በመክሰስ የመዲረግ መብቱን ሉያስከብር ይችላል ተብል መወሰኑ ከስነ ሥርዓት ውጪ ከመሆኑም በላይ በውጤት ደረጃ የመድን ድርጅቱን መብት ሉያስጠብቅ የሚችልበት ከሕግም ሆነ ከውል የመነጨ ምክንያት የላለ መሆኑን ጠቅሰው ውሣኔው ሉታረም የሚገባው ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። በዚህ ረገድ የቀረበው የኢትዮጵያ መድን ድርጅት የሰበር አቤቱታ ተመርምሮም ለጉዲዩ ተፈፃሚነት ያለው የባህር ሕጉ ሳይሆን የንግድ ሕጉ ነው ተብል መወሰኑ ባግባቡ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለውን ነጥብ ለመመረር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ተጠሪ የሆኑት የስር ከሣሽና የስር ሁለተኛ ተከሣሽ ቀርበው የፅሐፍ መልሳቸውን ሰጥተዋል። የስር ከሣሽ የሆነው ድርጅት ያቀረበው የሰበር አቤቱታ መስረከረም 18 ቀን 2ዐዐ2 የተፃፈ ሁኖ መሰረታዊ ይዘቱ የስር ሁለተኛ ተከሣሽ የነበረው ድርጅት /ታቭትራ ኃ/የተ/የግል ማህበር / ከስር ተከሣሾች ጋር ተጣምሮ መከሰስ የለበትም ተብል የተሰጠው ውሣኔ ያለግባብ ነው የሚል ሲሆን ይኸው አቤቱታ ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ የሚገባው ነው ተብል በመታዘዙም ግራ ቀኙ የጽሐፍና የቃል ክርክር እንዱያደርጉ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች እንዱሁም ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ከሰጠው የሕግ ትርጉም ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
በመድን ሰጪ በኩል ለጉዲዩ አግባብነት አለው ተብል የተጠቀሰው ሕግ የባህር ሕጉ ነው። መድን ገቢ የሆነው የቻይና ዋንቦ ኢንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን ደግሞ በንግድ ሕጉ ጉዲዩ ሉገዛ የሚችል ነው በማለት ምክንያቶችን ጠቅሷል። ይህ ችልትም ግራ ቀኙ ያደረጉትን የመድን ውል እንደተመለከተው የባህር ጉዞ ፕሉስ የሚባል መሆኑን ከሰነደ የተገነዘበ ሲሆን በኢንሹራንስ ውል ላይ በተራ ቁጥር 1.4 እስከ 7 ከተዘረዘሩት የአደጋ መንስኤዎች በስተቀር የጉዞው ሽፊኑ እቃው ከሚመጣበት የቻይና ሀገር እስከ እቃው የሚደርስበት የኢትዮጵያ ግዛት ደብረ ብርሃን ድረስ ለሚደርስ ማንኛውም ጉዲት ስለመሆኑ በውለ አንቀጽ 1 በግልጽ ተደንግጓል። በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠው ጉዲይ ደግሞ እቃው በሰላዲ ቁጥር 3-26454 ኢት ተሳቢ ቁጥር 3-02979 ኢት የጭነት መኪና ከጅቡቲ ወደብ ተጭኖ በመሬት ሲጓጓዝ በአፊር ብሓራዊ ክልል ኤሉዲር ከተማ መኪናው ተገልብጦ የመድን ዋስትና በተገባለት እቃ ላይ ጉዲት መድረሱ ሲሆን የመድን ውለ በአንቀጽ 19 ስር ኢንሹራንሱ የሚገዛው በኢትዮጵያ ሕግና ልማድ ስለመሆኑ ይደነግጋል። የኢትዮጵያ መድን ድርጅት የመድን ውለ ይዘት ከላይ በተመለከተው መልኩ ስለመሆኑ ግልፅ ማስተባበያ ክርክር ሳያቀርብ የውለን ርዕስና የባህር ኢንሹራንስ መሰረታዊ ባህሪያትን እንዱሁም የዓለም አቀፍ ልምድን መሰረት አድርጎ ክርክር አቅርቧል። በእርግጥ የባህር ኢንሹራንስ መሰረታዊ ባህርይ ሲታይ ኢንሹራንሱ የሚገባው በባህር ላይ ለሚደርስ አደጋ ላይ። የባህር ሕጉ አንቀፅ 292/1/ ሲታይም ግባቸው ሕጋዊ ለሆነው የገንዘብ ግምት ዋጋ ላላቸውና ሉደርስ የሚችል የባህር አደጋ ለሚያስፈራቸው ነገሮች ሁለ ኢንሹራንስ ላደረግላቸው እንደሚችል የተደነገገ ሲሆን የዚሁ አንቀፅ ንዐስ ቁጥር ሁለት ድንጋጌ ደግሞ በባህር አደጋ በደረሰበት ጉዲት ምክንያት ካልሆነ በቀር ማንም ሰው በኢንሹራንስ የሚገኘውን ጥቅም ለመጠየቅ አይችልም በማለት ይገልፃል። የባህር ሕጉ ስለኢንሹራንስ ውል የተደነገጉትን ድንጋጌዎች የሚያስቀምጠው አንቀጽ ሰባት ምዕራፍ አንድ በቁጥር 288 ስር ዋናው ዓላማ በባህር የሚደርሰውን አደጋ ወይም ከዚሁ ጋር ተጨማሪ የሆኑትን አደጋዎችም ለማረጋገጥ ቢሆን እንኳ ማንኛውም የኢንሹራንስ ውል በዚሁ ክፍል በተደነገጉት ውሣኔዎች ይመራል በማለት ደንግጓል።
ከእነዚህ ድንጋጌዎች ይዘት መገንዘብ የሚቻለው የባህር ሕጉ ተፈፃሚነት የሚኖረው በባህር አደጋ ሲደርስ ስለመሆኑ ነው። የባህር አደጋ የሚባለው ደግሞ በባህር ላይ ዘረፊ እና የመሳሰለ ሁነው የባህር ክልል ውስጥ የሚደርሱ አደጋዎች ናቸው። የባህር ሕጉ ከመግቢያው ጀምሮ ሲታይ የባህርን ጉዲይ የሚመለከቱ ጉዲዮችን የሚገዛ መሆኑን ያስገነዝባል። በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱት የባህር ሕጉ ድንጋጌዎችና የሕጉ መግቢያ ይዘትና መንፈስ ሲታይ የባህር ሕግ የተፈፃሚነት አድማሱ የባህርን ጉዲይ ለሚመለከቱ ጉዲዮች ነው። ለክርክሩ አግባብነት ያላቸው የባህር ሕጉ ድንጋጌዎች ይዘታቸውና መንፈሳቸው ከላይ የተመለከተው ሲሆን የንግድ ሕጉ አንቀጽ 655 ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ ሲታይም ለጉዲዩ ጭብጥ አወሳሰን ምላሽ የሚሰጥ ሁኖ ይገኛል። ይህ ድንጋጌ ስለኢንሹራንስ የተመለከቱት የንግድ ሕጉ ድንጋጌዎች የተፈፃሚነት ወሰንን የሚያሳይ ሲሆን በንዐስ ቁጥር አንድ በንግድ ሕጉ ስለኢንሹራንስ የሚደነግገው አንቀጽ ሶስት ተፈፃሚ የሚሆነው በመሬት ፣ በወንዝና በአየር ለሚደርሱ አደጋዎች መሆኑን ሲጠቅስ የድንጋጌው ንዐስ ቁጥር ሁለት ደግሞ በንግድ ሕጉ ስለኢንሹራንስ የተመለከተው አንቀጽ በባሕር ሕግ የሚተዲደረውን የባህር ኢንሹራንስን የማይመለከት ስለመሆኑ አስገዲጅነት ባለው መልኩ ይደነግጋል። ከዚህ ድንጋጌ መገንዘብ የሚቻለው የውለ አርዕት የባህር ኢንሹራንስ ነው ተብል በተዋዋይ ወገኖች መገለጹ ውለ በባህር ሕጉ እንዱገዛ ፍላጎት ስላላቸው በዚሁ መልኩ ውለ መገዛት ያለበት ሳይሆን የውለ ይዘትና አደጋው የደረሰበት ቦታ በራሱ ውለ የሚገዛበትን የሕግ አግባብ ለመለየት የሚያስችል መሆኑን ነው። በመሆኑም የተዋዋይ ወገኖች ፍላጎት ከውለ አጠቃላይ ይዘት ታይቶ ውላቸው የሚገዛበት ሕግ መለየቱ የውል አተረጓጎም ደንቦች የግድ የሚለት ጉዲይ ነው። በተያዘው ጉዲይም የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ለቻይና ዋንቦ ኮርፕሬሽን የሰጠው የመድን ውል በአርስት ደረጃ የባህር ጉዞ ፕሉሲ /Marine insurance / በሚል የተጠቀሰ ቢሆንም የውለ አንቀጽ 1 እና 19 ይዘት ሲታይ ግን በውለ በግልፅ ከተገለለት አደጋዎች ውጪ በመሬት ላይ ለሚደርሱ ላልች አደጋዎች ሁለ መድኑ የተገባ በመሆኑ በባህር ሕጉ ቁጥር 288 ፣ 292 እና በመግቢያው ላይ እንዱሁም በን/ሕ/ቁጥር 655 ድንጋጌ መንፈስ እና ይዘት ሲታይ ለጉዲዩ ተፈፃሚነት ያለው ሕግ የኢትዮጵያ ንግድ ሕግ ሁኖ ስለአገኘነው በዚህ ረገድ የቀረበው የኢትዮጽያ መድን ድርጅት ክርክር ተቀባይነት የላለው በመሆኑ የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዚህ ረገድ የሰጠው የሕግ ትርጉም መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት አልተቻለም።
እንግዱህ የቻይና ዋንቦ ኮርፕሬሽን ከታብተራ ኃ/የተ/የግል ማህበር ጋር ያደረገው ስምምነት ሲታይ የትራንዚት አገልግልትና የትራንስፕርት ስምምነት የሚል ስለመሆኑ የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በውሣኔው ላይ ያረጋገጠው ጉዲይ ነው። እንዱህ ከሆነ ግንኙነቱ የሚገዛውም በደንብ ቁጥር 37/1990 ነው። በዚህ ደንብ አንቀጽ 2/1/ ስር እቃ አስተላላፉ በአገር ውስጥ ወይም በአለም አቀፍ ደረጃ እቃ ተቀባይነት ወይም እቃ ላኪነት በመወከል የጉምሩክ የወደብ ወይም ላልች ስርዓቶች አስፈፅሞ ገቢ ወይም የወጪ እቃዎችን ወደብ እንዱገቡ ወይም እንዱወጡ የሚያደርግ ሲሆን እቃን የማጓጓዝና የማስረከብን ስራም እንደሚጨምር ተቀምጧል። የዚህ ድንጋጌ ጠቅላላ ይዘት ሲታይም እቃ አስተላላፉው ስራውን የሚያከናውነው እቃ ላኪዎችን ወይም ተቀባዮችን በመወከል ስልጣን መሆኑን የሚያስገነዝብ ቢሆንም በደንቡ አንቀጽ 3/6/ እና 7 ድንጋጌዎች ስር ያለት ሁኔታዎች ሲታዩ ደግሞ የእቃ መጓጓዝ ተግባሩ እንዳት ሉከናወን እንደሚገባ ያመላክታለ። በደንቡ አንቀጽ 3/6/ ድንጋጌ ስር እቃ አስተላላፉ የራሱን የትራንስፕርት አገልግልት ካለው የእቃ ማጓጓዙን ተግባር የሚያከናውነው እንደ አጓጓዥ ሁኖ እንጂ በውልክና አለመሆኑን በግልፅ ያሳያል። በልላ በኩል ግን የራሱ ትራንስፕርት ከላለው ወይም ባለእቃው የራሱን ማጓጓዣ ካላቀረበ እቃ አስተላላፉው ማጓጓዣ ተከራይቶ እቃውን እንደሚያጓጉዝ በደንቡ አንቀጽ 3 ንዐስ ቁጥር ሰባት ድንጋጌ ስር ተመልክቷል።
ይህ ድንጋጌ በአንቀጹ ንኡስ ቁጥር ስድስት እንደተመለከተው የማጓጓዝ ስራውን እንደ አጓጓዥ ሆኖ እንደሚሰራ አያስቀምጥም። ከፍ ሲል እንደተመለከተው እቃ አስተላላፉ ስራውን ሁለ የሚያከናውነው በውክልና ነው። በያዝነው ጉዲይ ታብትራ ኃ/የተ/የግል ማህበር የማጓጓዝ ተግባሩን ያስፈጸመው በአቶ ዮናስ ተስፊዬ ስለመሆኑ በበታች ፍርድ ቤቶች የተረጋገጠ ፍሬ ጉዲይ ሲሆን ታብትራ ኃ/የተ/የግል ማህበር የማጓጓዝ ተግባሩን ያከናወነው በውክልና ተግባሩ እንጂ ራሱ በሰራው የማጓጓዝ ስራ አይደለም። እንዱህ ከሆነ ታብትራ ኃላፉነቱ የሚኖረው በደንብ ቁጥር 37/1990 አንቀጽ 12 ስር በተመለከተው ሁኔታ ነው። በዚሁ ድንጋጌ ንዐስ አንቀጽ ሁለት ስር እቃ አስተላለፉ ወይም የመርከብ ወኪል ተግባሩን ባለማከናወኑ ጥፊት ቢፈጽም በተለይም እቃው ቢጠፊበት ቢጎድልበት ወይም እቃውን በወቅቱ ባያስረክብ ተጠያቂ የሚሆን መሆኑ የተቀመጠ ሲሆን የዚሁ ድንጋጌ የእንግሉዝኛው ቅጂም፡ ‛ the Frieght forwarder shall be liable for defaults in the performance of his duties, in particular he shall be liable for loss of or shortage of or damage to the goods or delay in delivery of the goods.“ የሚል ነው። የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የኢትዮጵያ መድን ድርጅትን ለጉዲቱ በመድን ውለ መሰረት ኃላፉ በማድረግ ካሳውን ለቻይና ዋንቦ ኮርፕሬሽን ከፍል ታብትራን ኃ.የተ.ግል ማህበር ወይም አቶ ዮናስ ተስፊዬን በን/ሕ/ቁጥር 683/3/ መሰረት እንዱጠይቅ መብቱን የጠበቀለት መሆኑን ውሣኔው ይገልፃል። ይሁን እንጂ በቻይና ዋንቦ ኮርፕሬሽንና በታብትራ ኃ.የተ.የግል ማህበር መካከል ያለው የእቃ ማጓጓዝ ተግባር የሚፈጸመው በውክልና ግንኙነት /እቃ አስተላላፉነት ነወ።/ በዚህ መልኩ ለሚፈፀም ተግባር እቃ አስተላላፉ የሚጠየቀው ደግሞ በደንቡ አንቀጽ 12/2/ ስር በተመለከተው ሁኔታ ነው።
በዚህ ድንጋጌ መሰረት እቃ አስተላላፉ ተግባሩን በጥንቃቄ ማከናወን እንደአለበት የተቀመጠ ሲሆን የጥንቃቄው መለኪያ ሲታይም እቃ አስተላላፉው በገባው ውል ግዳታ መሰረት እቃውን በማጓጓዝ ለባለንብረቱ የማስረከብ ኃላፉነትን የሚሸፍን መሆኑ በድንጋጌው ከሰፈሩት አመላካች ነጥቦች የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። አንድ እቃ አስተላላፉ እቃዎችን አጓጉዞ ለባለንብረቱ ካላስረከበ በሕጉ አግባብ ኃላፉነቱን የሚያስቀሩ ሁኔታዎችን እስካላስረዲ ድረስ ጥፊት እንደፈፀመ የሚቆጠር መሆኑን የተጠቀሰው ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ ያሳያል። በን/ሕ/ቁጥር 683/3/ ስር ወደ ተመለከተው ድንጋጌ ስንመለስ ደግሞ፡- ላላ ተቃራኒ የውል ቃል ቢኖርም በክፊት ያደረጉት ካልሆነ በቀር ኢንሹራንስ ሰጪው በኢንሹራንስ ገቢው ወደ ታች የሚቆጠሩ ተወላጆች ወደ ላይ የሚቆጠሩ ወላጆች ወኪልች ፣ ሰራተኞች ወይም ከእርሱ ጋር ዘወትር አብረው በሚኖሩት ሰዎች ላይ ኢንሹራንስ ሰጪው በምትክነት ክስ ለማቅረብ እንደማይችል ተቀምጧል። የድጋጌው የእንግሉዝኛ ቅጂም ‛Notwithstanding any provision to the contrary, the insurer may not claim against the ascendants, descendants, agents or employees of the insured person nor against persons living with him, unless such persons have acted maliciously..“ በማለት ይደነግጋል።
የዚህ ድንጋጌ አቀራራጽና ይዘት ሲታይ ኢንሹራንስ ሰጪ ክስ ሉያቀርብባቸው የማይቻላቸው ወገኖች ከኢንሹራንስ ገቢው ጋር የጠበቀ ግንኙነት ያላቸውና ለራሳቸው ጥቅም ሳይሆን ለኢንሹራንስ ገቢው ጥቅም በሚሰሩ ወገኖች ላይ መሆኑን የሚስገነዝብ ነው። ስለሆነም እነዚህ ወገኖች ከወካዩ ጋር ካላቸው የጠበቀ ግንኙነትና ስራቸውን የሚያከናውኑት ደግሞ ለወካዩ ጥቅም እስከሆነ ድረስ በደንብ ቁጥር 37/90 ስለእቃ አስተላለፉ ከተሰጠው ትርጉም ጋር እኩል ተደርገው ሉወሰደ የሚገባ አይደለም። ምክንያቱም የእቃ አስተላላፉነት ተግባር የሚከናወነው በውክልና ስልጣን መሰረት ቢሆንም እቃ አስተላላፉው ለእራሱ ጥቅም የሚሰራ ነውና። በመሆኑም እቃ አስተላላፉነት በን/ሕ/ቁጥር 683/3/ ስር ‛ወኪልች“ በሚል ከተዘረዘሩት ወገኖች ስር ሉካተት የሚችል አይደለም። በን/ሕቁጥር 683/3/ ስር የተመለከቱት ወገኖች የሚፈፅሙት ተግባር የመድን ሰጪውን በምትክነት እንዱገባና ሃላፉነቱን እንዱወስደ የሚያደርገው ተግባሩ በክፊት የተደረገ/Have acted maliciously/ መሆኑ ከተረጋገጠ ይህም የጥፊቱ አፈፃፀም መለኪያው በደንብ ቁጥር 37/1990 አንቀጽ 12 ስር ከተመለከተው የወኪልች ተግባር ጥፊት ጋር ሲነጻጸር የጠበቀ መሆኑን የድንጋጌው አቀራረፀ ያሳያል። ይኸውም አንድ ድርጊት በክፊት የተፈጸመ ነው የሚባለው ምንም ሕጋዊ ምክንያት ሳይኖር በአንድ ሰው መብት እና ጥቅም ላይ ጉዲት ለማድረስ ሆነ ተብል ሲፈፀም መሆኑ ታዋቂው የሄኔሪ ብላክስ የሕግ መዝገብ ቃላት ‛Malicious Act is an intentional, wrongful act performed against another without legal justification .“ በማለት ከሰጠው ትርጉም የምንገነዘበው ሲሆን ከደንብ ቁጥር 37/90 አንቀጽ 12 ጋር ተያይዞ የሚነሳው ጥፊት ደግሞ ከውል አፈጻጸም ጋር ተያይዞ ግዳታ ሳይፈጸም ሲቀር የሚነሳና ኃላፉነት የሚያስከትል፣ ሕጉም ምክንያቶችን አመልካችነት ባለው ሁኔታ የጠቀሰ በመሆኑ ጥፊቱ የሚፈፀመው ሰፊ ባለ አጋጣሚዎች መሆኑን የሚያሳይ ነው። ከላይ የተጠቀሰው መዝገበ ቃላት ጥፊትን ሲተረጎም ‛Default is the omission or failure to perform a legal or contractual duty.“ በማለት ያስቀመጠው ሲሆን ይህም ትርጉም ጥፊቱ ከውል አፈጻጸም ጋር ተያይዞ መታየት ያለበት ነው በማለት የገለፅነውን አባባል የሚያጠናክር ነው በመሆኑም የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በን/ሕ/ቁጥር 683/3/ መሰረት ታብትራ ኃ/የተ/የግል ማህበርን ለመጠየቅ ይችላል ብል ሲወሰን መሰረት ያደረገው ሕግ ለጉዲዩ አግባብነት የላለው ሲሆን ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ላይ የእቃ አስተላላፉ በክፊት ለፈጸመው ተግባር ካልሆነ በስተቀር የሚጠየቅበት አግባብ የለውም በማለት የን/ሕ/ቁጥር 683/3/ ‛ን“ መሰረት በማድረግ የሰጠው ትርጉምም ለጉዲዩ አግባብነት የላለውን ሕግ መሰረት በማድረግ የተሰጠ ሁኖ ስለአገኘነው በአዋጅ ቁጥር 454/1997 አንቀጽ 2/2/ መሰረት መለወጥ ያለበት ነው።
ላላው የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ካሣውን ከፍል ታብትራ ኃ/የተ/የግ ማህበርን እንዱጠይቅ ውሣኔ የተሰጠበትን የክርክር ሂደት አግባብነቱን መመልከቱ ተገቢ ነው። ከላይ እንደተገለፀው በእነዚህ ወገኖች መካከል የሚነሳው ክርክር የሚገዛው በአዋጅ ቁጥር 37/90 ሲሆን የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ለቻይና ዋንቦ ኮርፕሬሽን በሰጠው የመድን ውል መሰረት በእቃ አስተላላፉው ላይ የሚያቀርበው ክርክር እቃው አቅም በላለው መጓጓዣ ላይ በመጫኑ ጉዲቱ መድረሱን የሚያሳይ ሲሆን ታብትራ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ደግሞ በክሱ ውስጥ ተሳታፉ የሚሆንበት ወይም በጣምራ የሚከሰስበት አግባብ የላለ መሆኑን ጠቅሶ በመከራከሩ ይህንኑ የእቃ አስተላላፉ ክርክር የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት እንዲለ ተቀብል በስር ፍርድ ቤት የክሱ አመሰራረትም ሆነ የክርክሩ አመራር ስነ ሥርዓቱን የተከተለ አይደለም በማለት ወስኗል። ታብትራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ባቀረበው መልስም የመከራከር መብቱ መጣበቡን ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ተገንዝቦ የሰጠው ውሣኔ ተገቢ መሆኑንና በጭብጥ አመሰራረትም ሆነ ለጉዲዩ ተፈፃሚነት ካለው ድንጋጌ አንጻር አንድ ተከሣሽ ላላ ተከሣሽ ለሰጠው መከራከሪያ መልሱን የሚሰጥበት አግባብ በኢትዮጵያ የሙግት አመራር ሥርዓት ውስጥ የላለ መሆኑን ዘርዝሮ ተከራክሯል። እኛም እንደተመለከትነው የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በቻይና ዋንቦ ኮርፕሬሽን ላይ የሚያነሳው ክርክር የመድን ውለንና የንግድ ሕጉን መሰረት ያደረገ ቢሆንም ቻይና ዋንቦ ከእቃ አስተላላፉው ጋር የሚያቀርበውን ክርክር ደግሞ መድን ድርጅቱ በውለ በሚያገኘው የመዲረግ መብት በእቃ አስተላላፉው ላይ ከማቅረብ የሚከለክለው ሕግ የለም። የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትም መድን ድርጅቱ እቃ አስተላላፉውንና አጓዡን የመጠየቅ መብቱ የተጠበቀለት ነው ያለው በእነዚህ ወገኖች የቻይና ዋንቦ ኮርፕሬሽን ሉያነሳ የሚችለውን ክርክር ሁኖ እነዚህ ወገኖች ደግሞ ለመድን ድርጅቱ ጥያቄ ኃላፉነት የላለባቸው መሆኑን የሚያሳይ ክርክር ሉያቀርቡ የሚችለት በቻይና ዋንቦ ላይ ወይም ታብትራ ከአቶ ዮናስ ተስፊዬ ላይ ፣ ወይም ዮናስ ተስፊዬ ደግሞ በታብትራ ላይ ሉያነሱ የሚችለትን ክርክር ነው። ለጉዲዩ አወሳሰን ደግሞ ከመድን ውለ ጀምሮ ሁለም ወገኖች በመካከላቸው ያደረጉት ስምምነት አግባብነት የሚኖረው ይሆናል። የመዲረግ መብት አጠቃላይ ፅንሰ ሀሣብ ሲታይም የመጨረሻ ኃላፉነት ያለውን ወገን በመለየት ካሣውን የከፈለው ወገን ገንዘቡ እንዱተካለት ማድረግ ነው ። ፍርድ ቤቶች በመድን ውለ መሰረት ኃላፉነት ያለው ወገን ኃላፉ የማሆንበትን ምክንያት ገልፆ የሚከራከር ከሆነ ይህንኑ እንዱያስረዲ እድል መስጠት አለባቸው። እንዱሁም በክርክሩ ውስጥ የሚገባ ወገን ካለና ኃላፉነቱ የማን እንደሆነ እንዱለይ ከሣሽ ጥያቄ ከአቀረበም ይህንኑ በተገቢው መንገድ በመመራት ተገቢውን ውሣኔ መስጠት ይገባቸዋል። የፍ/ብ/ሥ/ሥሕ/ቁጥር 36/5/ ፣ 39 ፣ 40 ፣ እና 43 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስም ይህንኑ የሚያሳይ ነው። ግልፅ የሆነ ክርክር ቀርቦ ባለበት ሁኔታ እነዚህ ድንጋጌዎች በአግባቡ ሳይተገበሩ የሚሰጠው ውሣኔ በክርክር አመራር ስርዓት ተቀባይነት አለው ልባል የሚችል አይደለም። ከላይ እንደተመለከተው የኢትዮጵያ መድን ድርጅት የመድን ውለ መኖሩን ሳይክድ ኃለፉነት የላለበት መሆኑን ጠቅሶ የሚከራከረው መድን የተገባለት እቃ ላይ ጉዲት የደረሰው አቅም በላለው መኪና ላይ በመጫኑ ምክንያት ነው የሚል ክርክር ሲሆን ይኸው ተግባር እቃ አስተላላፉውን በደንብ ቁጥር 37/1990 አንቀፅ 12/2/ መሰረት ሉያስጠይቅ የሚችል መሆን ያለመሆኑ ፣እቃ አስተላላፉው አጓዡ /አቶ ዮናስ/ ኃላፉነት ያለው መሆን ያለመሆኑን ሉያስረዲ የሚችል መሆን ያለመሆኑ አጓዥ የተባለት አቶ ዮናስ ተስፊዬ ለጉዲቱ የማይጠየቁበት የህግም ሆነ የፍሬ ነገር ክርክር ያለ መሆን ያለመሆኑ እና ላልች አግባብነት ያላቸው ጭብጦች መለየት ያለባቸው የኢትየጵያ መድን ድርጅት ካሣውን ለቻይና ዋንቦ ኮርፕሬሽን ከከፈለ በኋላ ሳይሆን አሁን በቀረበው ክርክር መሆኑን የክርክሩ ይዘት ያስገነዝባል። የታብትራ ኃ/የተየግል ማህበር ጠበቃ አንድ ተከሣሽ ላቀረበው ክርክር ላላው ተከሣሽ መልስ እንዱሰጥበት የሚያስችል የክርክር ስርዓት በኢትዮጵያ የሙግት አመራር ሥርዓት የለም፣ የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔም ይህንኑ ያገናዘበ ነው በማለት ለሰበር ችልት በሰጡት መልስ ላይ ተከራክረዋል። ይሁን እንጂ በኢትዮጵያ የፍትሒ ብሓር ክርክር ላይ በክርክር አመራር እና እውነትን በማውጣት ረገድ የፍርድ ቤት ሚና ሲታይ እጅጉን ከፍተኛ መሆኑን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቀጥር 39 ፣ 40 ፣ 91 ፣ 136 ፣ 241 ፣ 246 ፣ 247 ፣ 248 ፣ 256 ፣ 265 ፣266፣ 272 እና ላልች በርካታ በዋቢነት የሚጠቀሱ ድንጋጌዎች ያለ በመሆኑ አንድ ተከሣሽ በሚያቀርበው ክርክር ላይ ላላው ተከሣሽ መልስ /ክርክር / እንዱያቀርብበት ማድረግ ሥርዓቱ የሚደግፈው አይደለም ልባል የሚችል አይሆንም። ዋናውና ቁልፈ ነገር የተከራከሪ ወገኖች የመከራከር መብት መጠበቅ ነው። በመሆኑም በዚህ ረገድ የታብትራ ጠበቃ ያቀረቡትን ክርክር የምንቀበለው ሁኖ አልተገኘም። ስለሆነም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የስር ፍርድ ቤት የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ባቀረበው ክርክር ታብትራ ኃ/የተ/የግል ማህበርም ሆነ አቶ ዮናስ ተስፊዬ ክርክር እንዱያቀርቡ አድርጎ ሙግቱን አለመመራቱን በማረም ጉዲዩን እንደገና እንዱመለከተው ማድረግ ሲገባው መድን ድርጅቱን ከወዱሁ ለጉዲቱ ኃላፉ በማድረግ ላላ ክስ አቅርቦ መብቱን ሉያስከብር ይችላል በማለት የሰጠው ውሣኔ የመድን ድርጅቱ የመድን ውለንም ሆነ በደንብ ቁጥር 37/1990 እንዱሁም አግባብነት ባላቸው ላልች ሕጎች መሰረት የሚያቀርበውን ክርክር ከወዱሁ ዋጋ ሉያሳጣ የሚችልበት ሁኔታ መኖሩን ከክርክሩ ይዘት ተገዝበናል። በዚህም ምክንያት ኃላፉነቱን በተመለከተ የተሰጠው ውሣኔ የክርክር አመራር ስርዓቱ በአግባቡ ሳይከናወን የተሰጠ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የፈፀመበት ሁኖ አግኝተናል።
ጉዲዩ ሲጠቃለልም ከላይ በተመለከቱት ክርክር ምክንያቶች መሰረት በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሣኔ ተሽሮ ክርክሩ እንደገና መመራት ያለበት ሁኖ ስለተገኘ ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ 1- በፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ ሰኔ 25 ቀን 2ዐዐ1 ዓ/ም የተሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
2- የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔም ተገቢነት የለውም ብለናል።
3- ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ላይ በደንብ ቁጥር 37/1990 መሰረት በራሱ ማጓጓዣ እቃ የማያስተላላፍ ሰው ለመድን ሰጪ ሉጠይቅ የሚችለው በን/ሕ/ቁጥር 683/3/ መሰረት የክፊት ተግባር የፈፀመ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው በማለት የሰጠው የህግ ትርጉም በአዋጅ ቁጥር 454/1997 አንቀጽ 2/2/ መሰረት ተለውጦ እንደዚህ አይነት ግንኙነት ሉገዛ የሚገባው በደንብ ቁጥር 37/1990 አንቀጽ 12/2/ በተመለከተው ሁኔታ ነው ብለናል።
4- የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩን እንደገና ተመልክቶ የስር 2ኛ እና 3ኛ ተከሣሾች/ታብትራ ኃ/የተ/የግል ማህበር እና አቶ ዮናስ ተስፊዬ /በኢትዮጵያ መድን ድርጅት በቀረበው ክርክር ተገቢ ነው የሚለትን ክርክር እንዱያቀርቡ አድርጎ እንዱሁም እነዚህ ተከሣሾች እርስ በራሳቸው የሚያቀርቡት ክርክር ካለም በመቀበል እና ማስረጃ ካላቸውም ከሰማ በሁዋላ ጉዲዩን ከደንብ ቁ
No topics extracted.