No summary available.
ግንቦት 02 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ አሉ መሀመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ሲ/ር መዓዛ ዮሴፍ ቀረቡ ተጠሪ፡- ዶ/ር ዮሴፍ ደነቀው ጠበቃቸው አቶ ሙለቀን ሉበን ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
የአሁኑ የሰበር ተጠሪ ለሥር የፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት ያቀረቡት ክስ ፍሬ ቃለ ከተከሣሽ /ያሁኗ የሰበር አመልካች / ጋር ጏፊ ገብርኤል ከፍተኛ ክሉኒክ ኃ/የተ/የግል ማህበር አቋቁመን በድርጅቱ መመስረቻ ጽሁፍ ከተገለፀው ካፑታል በተጨማሪ የህክምና መሳሪያዎችን በመግዛት በሁለት ቦታዎች የክሉኒክ ሥራ እየሰራን ቆይተን ከጊዜ በኋላ ከተከሣሽ ጋር ተግባብተን መሥራት ያልቻልንና ተከሣሽ ከሣሽን ከማህበር በማግለል ድርጅቱን ይዘው ለብቻቸው እየተጠቀሙ ስለሆነ ማህበሩ በፍ/ቤት ውሣኔ ፈርሶ የንብረት አጣሪ ተሹሞ የሚገባኝ ድርሻ እንዱከፈለኝ አመለክታለሁ የሚል ነው።
የሥር ተከሣሽም የክስ መቃወሚያና በፍሬ ነገር ላይ በአማራጭ መልስ አቅርበዋል።
ያቀረቡት የክስ መቃወሚያም ከሣሽ ከማህበሩ ለመውጣት ባቀረቡት ተደጋጋሚ ጥያቄ መሰረት ጉዲዩ በሽማግላዎች ሲታይ ቆይቶ ሰኔ 24 ቀን 1998 ዓ/ም በተደረገው ስምምነት ከሣሽ በዓይነት ያዋጡትን ንብረትና ብር 6ዐ,ዐዐዐ /ስድሣ ሺህ ብር/ ወስደው ጉዲዩ በሽምግልና ያለቀ በመሆኑ ከማህበሩ ከወጡ በኋላ ክስ ለማቅረብ የሚያስችል መብትና ጥቅም ስለላላቸው ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ብለዋል።
ተከሣሽ በፍሬ ነገሩ ላይ በአማራጭ በሰጡት መልስ ከከሣሽ ጋር ማህበሩን አቋቁመናል የማህበሩም ካፑታል ማህበሩ ሲቋቋም ብር 4ዐ,ዐዐዐ/አርባ ሺህ ብር/ ሲሆን ከሣሽና ተከሣሽ እያንዲንዲችን ብር 20,000 ማምጣት የሚጠበቅብን ቢሆንም ከሣሽ ገንዘብ አልያዝኩም በማለታቸው ላላ ጊዜ ይከፍላለ በማለት በእምነት የከሣሽ ድርሻ ብር 2ዐ,ዐዐዐ እንደተከፈለ ተደርጏ በመመስረቻ ጽሁፍ ተሞልቷል። ሆኖም ገንዘቡን ሳይከፍለ ቀርተዋል። በከሣሽ ተደጋጋሚ ጥያቄ ምክንያት ሽማግላዎች ተመርጠው ጉዲዩን ሲያዩ ከቆዩ በኋላ በ24/10/98 ዓ/ም በተደረገው ስምምነት መሰረት 6ዐ,ዐዐዐ ብር እና በአይነት ንብረት ወስደው ከወጡ በኋላ ጉዲዩን በግልግል ለመጨረስ ተከሣሽ እንቢተኛ በመሆን ድርጅቱን በግላቸው እየተጠቀሙ ነው በማለት ያቀረቡት ክርክር ሐሰተኛ ነው።
በመተዲዲሪያ ደንባችን የአንደ ማህበርተኛ ከማህበሩ መውጣት ማህበሩን አያፈርሰውም በሚል የተስማማን ስለሆነና ከሣሽም ድርሻቸውን ወስደው ከማህበሩ የወጡ በመሆናቸው ማህበሩ ፈርሶ ሂሣብ አጣሪ ተሹሞና ሂሣቡ ተጣርቶ ድርሻዬ ይከፈለኝ ያለትም የሚቻል አይደለም በማህበሩም ምንም አይነት ድርሻ የላቸውም። ማህበሩ በከሣሽ ጥያቄ እንዱፈረስ ውሣኔ የሚሰጥ ከሆነ ደግሞ ከሣሽ ከማህበሩ እወጣለሁ ብለው የወሰደትን ብር 6ዐ,ዐዐዐ እና ላልች በዓይነት የወሰደአቸውን ንብረቶች እንዱመልሱና ለማህበሩ ጽ/ቤት ኪራይ ብር 114,000 እንዱሁም ከሣሽ የፈረሙበት የማህበሩ ዕዲ ብር 2ዐ7,536.85 በድምሩ ብር 321,536.85 ከግል ገንዘቤ እየከፈልኩ ስለምገኝ እንደማህበሩ ዕዲ እንዱቆጠር፣ የማህበሩ አባል ተከሣሽ ብቻ ስለሆንኩኝ በንግድ ህግ ቁጥር 511/1/ መሰረት የማህበሩ አባላት ቁጥር ከ2 በታች ስለሆነ ማህበሩ በፍ/ቤት ውሣኔ እንዱፈርስ እጠይቃለሁ ብለዋል።
የሥር የፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤትም አጣሪ በመሾም የማህበሩ ንብረት እንዱጣራ ካደረገ በኋላ የግራ ቀኙን ክርክር በመመርመር ከሣሽ ለማህበሩ ባዋጡት የገንዘብ መጠን ድርሻቸው ሲሰላ 36.63 ከመቶ ስለሚሆን በጠቅላላው 83,081.04 ብር ተከሣሽ ለከሣሽ እንዱከፍለና ማህበሩም በንግድ ህግ አንቀጽ 511/1/ መሰረት እንዱፈርስ ወስኗል።
ይህ የፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት ውሣኔ በአሁኗ የሰበር አመልካች ይግባኝ ጠያቂነት ለፋ/ከ/ፍ/ቤት ቀርቦ ክርክር ከተካሄደበት በኋላ ከፍተኛው ፍ/ቤትም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348/1/ መሰረት የሥር የመ/ደ/ፍ/ቤት ውሣኔን አጽንቷል።
በሥር ፍ/ቤቶች ውሣኔ ቅር የተሰኙት የሰበር አመልካችም ባቀረቡአቸው የቅሬታ ነጥቦች፡ጉዲዩ በሽምግልና ታይቶ ውሣኔ አግኝቷል በሚል በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 244/2/ረ/ መሰረት ያቀረብኩትን መቃወሚያ የሥር ፍ/ቤት ውድቅ ማድረጉ ያለአግባብ ነው፣ ማህበሩ ይፈርሣል ከተባለም ወደ ነበርንበት ልንመለስ ሲገባ ተጠሪው ብር 6ዐ,ዐዐዐ እና የህክምና መገልገያዎች እንዱሁም የጽ/ቤት ዕቃዎችን ከማህበሩ ወስደው ወጥተው ባለበት በተጨማሪ ብር 83,ዐ81.04 አመልካች ለተጠሪ እንዱከፍል መወሰኑ ያለአግባብና የሽምግልና ስምምነቱን ያላገናዘበ ነው፣ በማህበሩ መተዲደሪያ ደንብ አንቀጽ 17/2/ መሰረት አንድ ማህበርተኛ ከማህበሩ በመውጣቱ ምክንያት ማህበሩ እንደማይፈርስ ተገልጾ እያለ ከስምምነታችን ውጪ የተሰጠው ውሣኔ ተገቢነት የለውም፣ ማህበሩ ከፈረሰ ተጠሪውና አመልካች ለማህበሩ ዕዲ ብር 321,536.85 በጋራ ተጠያቂዎች መሆን ሲገባንና ተጠሪውም ዕዲውን ባላስተባበለበት የሥር ፍ/ቤቶች በምን ምክንያት ዕዲውን እንዲለፈ በውሣኔያቸው አልጠቀሱም ከዚህ ላላ ማህበሩ ሲፈርስ ትርፍና ኪሣራ ሳይለይ ለተጠሪው ብር 83,081.04 አመልካች እንዱከፍል ሲወሰን የአመልካች ድርሻ ምን እንደሆነ ሳይወሰን ታልፎል፣ ሂሣቡን ያጣሩት ሰዎች ቀደም ሲል ጉዲዩን በሽምግልና ከማየታቸው ውጪ በሂሣብ አጣሪነት እንዱሰሩ አመልካች ሳልፈቅድ ፍ/ቤቱ እንዱያጣሩ ያደረገ ሲሆን ምንም አይነት የሂሣብ ሞያ የላላቸው ናቸው በማለት የሥር ፍ/ቤቶች የፈፀሙት መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት በዚህ ችልት እንዱታረምላቸው ጠይቀዋል።
የሰበር ተጠሪ በበኩላቸው በሰጡት መልስ፡- አመልካች ለአጣሪዎች ያላቀረቡአቸውን ክርክሮች ሪፕርቱ ለሥር ፍ/ቤት ከቀረበለት በኋላ ያቀረቡ በመሆናቸው ተጠሪ አግባብነት ያላቸውን የማስተባበያ ማስረጃዎች በማቅረብ እንዲልከላከል ያደረገ ከመሆኑም ላላ አዱስ ክርክር በመሆኑ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 329 መሰረት ተቀባይነት የለውም፣ የሂሣብ አጣሪዎች የሂሣብ ዕውቀት የላቸውም በሚል የቀረበው ክርክርም ቢሆን ተቀባይነት አይኖረውም። ምክንያቱም አጣሪዎች የተለየ ሞያ ክህልት እንዱኖራቸው የሚያስገድድ ህግ የለም። አጣሪዎቹ የተሾሙትም አመልካች ተጠሪ በፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት ቀርበን ባመለከትነው መሰረት ነው። ጉዲዬ በሽምግልና የተጠናቀቀ ነው ላለትም ስምምነቱ የማህበሩን መፍረስ የሚመለከት ካለመሆኑም በላይ አንድ የማህበር አባል በሀገሪቱ ህግና በማህበሩ ደንብ መሰረት ማህበሩ እንዱፈርስና ከንብረቱ ድርሻው እንዱከፈለው የመጠየቅ መብቱን የሚያስቀር ወይም የሚያሣጣ አይደለም። ተጠሪው በማህበሩ ባለኝ 5ዐ% ድርሻ ታስቦ ሉከፈለኝ የሚገባውን ገንዘብ በህግ የመጠየቅ መብት ቢኖረኝም ለሰላም ሲባል አነስተኛ ቀመር ተቀብያለሁ።
የማህበሩ ካፑታል ብር 4ዐ,ዐዐዐ ሲሆን እኔም ድርሻዬን በሙለ ከፍያለሁ፣ የከፈልኩ ስለመሆኔም አጣሪው አረጋግጧል።
የማህበሩ ሀብት እና ዕዲ ተጣርቶ ቀደም ሲል ከተቀበልኩት የካሣ ክፍያ በተጨማሪ ብር 83,081.04 የሚገባኝ መሆኑን አጣሪዎች በማረጋገጣቸው ፍ/ቤቱም ተቀብል አጽድቆታል። ይህም ላሆን የቻለው ማህበሩ ያለበት ዕዲ ፣ ሀብት እና ሁለቱም የማህበሩ አባላት ከማህበሩ ካፑታል በተጨማሪ ገቢ ያደረግነው ገንዘብ ተመዛዝኖ ነው።
አጣሪዎች ሂሣቡንም የሰሩት እስከ 24/10/1998 ባለው ጊዜ ብቻ ሲሆን ከዚህ ከተጠቀሰው በኋላ የተገኘው ሀብትም ሆነ የመጣው ዕዲ በ24/10/98 አመልካችና ተጠሪ ባደረግነው ስምምነት መሰረት እንዱሰላ በፍ/ቤትም ሆነ በአጣሪዎች ዘንድ የተስማማን በመሆኑ በዚህ ነጥብ ላይ ተጠሪን የሚጠቅም ወይም በሀላፉነት የሚያስጠይቅ ነገር የለም ሲለ በሥር ፍ/ቤቶች ውሣኔ ላይ የተፈፀመ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት አለመኖሩን በመጥቀስ ተከራክረዋል።
የግራ ቀኙ ክርክር ከዚህ በላይ እንደተመለከተው የቀረበ ሲሆን እኛም የሚከተለውን ጭብጦች ይዘን ክርክሩን እንደሚከተለው መርምረናል።
የግራ ቀኙ ክርክር ከዚህ በፉት በሽምግልና ተጠናቅቋል ወይስ አልተጠናቀቀም?
አመልካች ለተጠሪ እንዱከፍለ የተወሰነባቸውን ገንዘብ ሉከፍለ ይገባል ወይስ አይገባም?
የመጀመሪያውን ጭብጥ በሚመለከተ፡- አመልካች የሚከራከሩት ጉዲዩ በሽምግልና ሲታይ ቆይቶ ሰኔ 24 ቀን 1998 ዓ/ም ስምምነት የተደረሰ በመሆኑና ተጠሪዉም በዚሁ ስምምነት መሰረት ብር 60,000 ፣ የህክምና መሣሪያዎች እና ላልች የጽ/ቤት ቁሳቁሶችን ወስደው ከማህበሩ የወጡ በመሆናቸው በተጠናቀቀ ጉዲይ ክስ ማቅረብ አይችለም በማለት ለክርክራቸውም የጠቀሱት የፍትሃብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁ 244/12/ረ/ ነው።
በእርግጥ የተጠቀሰው የፍብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 244/2/ረ/ ክስ የተነሣበት ነገር በሽምግልና ታይቶ በስምምነት የተፈፀመ ከሆነ ወይም ለዕርቅ የተቀጠረ ከሆነ ክሱን መቃወም እንደሚቻል የሚደነግግ ነው። ይህ ችልትም አመልካች እንደሚለት በእርግጥ የግራ ቀኙ ክርክር በሽምግልና ታይቶ በስምምነት ተፈጽሟል ወይስ አልተፈፀመም የሚለውን አከራካሪ ነጥብ ለመወሰን ሰኔ 24 ቀን 1998 በግራ ቀኙ ተከራካሪዎች የተፈረመ ቃለ ጉባኤና ብር 60,000 ለተጠሪ የተከፈለበትን ሰነድ ይዘት ተመልክቷል።
ቃለ ጉባኤውም አመልካችም ሆነ ተጠሪ ለማህበሩ የተለያዩ ወጪዎችን ማውጣታቸውን የሚገልጽ ሲሆን የሰበር አመልካች ግን ከተጠሪው የበለጠ ወጪ ማውጣታቸውን ይገልጻል። ከዚህ በተጨማሪ ቃለጉባኤ ድርጅቱ ከተቋቋመ በኋላ፣ በሥራ ሂደት ወይም በመጀመሪያ አካባቢ በድርጅቱ የተፈሩ ወይም የተገዙ ቋሚ ዕቃዎችን በሚመለከት እስከ 24/10/98 ድረስ ተከፍል ያልተጠናቀቀ ዕዲ እና የተከፈለው ተሰልቶ ለተጠሪ የሚገባ ክፍያ ያዋጡት መጠን በመቶኛ ተሰልቶ እንዱሰጣቸው ያልተከፈለ የተጠሪ ደመወዝ እንዱከፈላቸው በቅድመ ክፍያ የተከፈለው የቤት ኪራይ ገንዘብ ቅድመ ክፍያ የተፈፀመበት ወራት ተለይቶ የተጠሪ ድርሻ እንዱመለስላቸው እና ተጠሪው ድርሻቸውን በማስተላለፍ ከማህበሩ ስለሚወጡ ካሣ ብር 60,000 አመልካች እንዱከፍለ ማህበሩ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 24/10/1998 በማህበሩ ላይ ያለውን ዕዲ በተመለከተ ድርጅቱን በማስቀረት ይዘው የሚያዙት አመልካች በሚያቀርቡት እና በተጠሪው ምትክ በሚገባ ግለሰብ ይሸፈናል የሚለትንና ባጠቃላይ ከተራ ቁጥር 1-9 የተጠቀሱትን ነጥቦች ያካተተ ነው።
አመልካች ግን ለተጠሪው ብር 60,000 /ስልሳ ሺህ ብር/ የተከፈላቸው በመሆኑንና በአይነት የህክምና መሣሪያዎችን ወስደዋል በሚል ነው አጥብቀው እየተከራከሩ ያለት ብር 6ዐ,ዐዐዐ ለተጠሪ የተከፈለበት ሰነድም ቢሆን ላልች ክፍያዎች በቃለጉባኤው በተገለፀው መሰረት የሚከናወኑ መሆናቸውን በግልጽ ይናገራል። ይህ ሆኖ ሣለ አመልካች ቃለጉባኤው ተጠሪው ከማህበሩ የሚደርሣቸውን አጠቃላይ ድርሻ ያላስቀመጠና ገና ሂሣብ ተጣርቶ የሚፈፀም መሆኑን እየገለፀ ባለበት ብር 6ዐ,ዐዐዐ /ስልሳ ሺህ ብር/ እና የህክምና መሣሪያዎችን በአይነት ተጠሪው ወስደው በስምምነት ተጠናቅቋል ሲለ ያቀረቡት መቃወሚያ ከፍትሃብሄር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 244/2/ረ/ መንፈስ ውጪ በመሆኑ ያለአግባብ የቀረበውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የሥር ፍ/ቤቶች ውድቅ በማድረጋቸው የተፈፀመ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም።
2ኛን ጭብጥ በሚመለከት፡- አጣሪው ጥቅምት 21 ቀን 2001 ዓ/ም በተጻፈ ደብዲቤ ሸኚነት በ24/10/2000 ዓ/ም የተዘጋጀ ቃለጉባኤ /ሪፕርት / ለሥር የመ/ደ/ፍ/ቤት ያቀረበ ሲሆን ሪፕርቱም መሰረት ያደረገው ቀደም ሲል ፍ/ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ የማጣራቱ ሥራ ሰኔ 24 ቀን 1998 ዓ.ም የተደረገውን የሽምግልና ስምምነት መሰረት ያደረገ መሆን እንዲለበት በገለፀው መሰረት ነው ብሎል።
ይህ ችልትም እንደተረዲው በ24/10/98 ዓ/ም በተደረገው የሽምግልና ስምምነት መሰረት አጣሪው የማጣራቱን ሥራ አከናውኗል። የማጣራቱ ሥራም የግራ ቀኙ ተከራካሪዎች ያቀረቡአቸውን ማስረጃዎች ጭምር በመመዘን የተሰራ ስለመሆኑ ሪፕርቱ ያመለክታል።
ለድርጅቱ ሥራ በብድር የተገዙና ዕዲቸው ተከፍል ያልተጠናቀቁ ቋሚ ዕቃዎችን በሚመለከትም እስከ ሽምግልና ስምምነት ድረስ መከፈለ በማስረጃ የተረጋገጠ ተጠሪው ባዋጡት ድርሻ መጠን ተሰልቶ ገንዘብ እንዱሰጣቸው በብድር ተገዝቶ ክፍያው የተጠናቀቀው ፍቶ ሜትር የተባለው የህክምና መሣሪያ ክፍያው የተጠናቀቀው የሽምግልና ስምምነት ከተደረገበት ቀን በፉት መሆኑ በመረጋገጡ ለተጠሪው ባዋጡት መጠን ድርሻቸው እንዱሰጥ የተወሰነ ሲሆን ላልች ዕቃዎችን በሚመለከት የግራ ቀኙ ተከራካሪዎች በ1ዐ/6/99 ዓ.ም የተፈራረሙበት ደረሰኝ ከተጠሪው በኩል በመቅረቡ ተጠሪው ባዋጡት የገንዘብ መጠን ተሰልቶ ድርሻቸው እንዱከፈል ተወስኗል።
ያሁን አመልካችም እነዚህን በ1ዐ/6/99 ዓ/ም በተደረገው ውል የተዘረዘሩትን ንብረቶች እንዱያስቀሩ ተደርጓል።
የቤት ኪራይም ቢሆን የአጣሪው ሪፕርት እንደሚያመለክተው ኪራይ ከ23/4/98 እስከ 23/4/99 ድረስ ብር 39,000 የተከፈለ ሲሆን ተጠሪው ከሰኔ 24 ቀን 1998 ጀምረው ከድርጅቱ ስለተሰናበቱ ከሐምል 1998 - ታህሣሥ 99 ዓ.ም ያለው የ6 ወራት ታስቦ ባዋጡት መጠን ድርሻቸውን አመልካች እንዱከፈለ ሲደረግ ይህም ክሉኒክ ቁጥር 1 የተባለውን የሚመለከት ነው።
ቁጥር 2 የተባለውን ክሉኒክ በሚመለከት ደግሞ ከመስከረም 19 ቀን 1998 ዓ/ም እስከ መስከረም 19 ቀን 1999 ድረስ የ12 ወር ብር 24,ዐዐዐ የቤት ኪራይ የተከፈለ ሲሆን ከአመልካች ጋር የተገለገለበት እስከ 24/10/1998 ዓ/ም በመሆኑ ሐምልና ነሐሴ 1998 የ2 ወር በቅድሚያ የተከፈለ በወር በብር 2ዐዐዐ ሂሣብ ተጠሪው ባዋጡት የገንዘብ መጠን ተሰልቶ ድርሻቸውን አመልካች እንዱከፈለ መወሰኑን ሪፕርቱ ያመለክታል። ለዚሁ ለቁጥር 2 ክሉኒክ ተጨማሪ ግንባታ ቅድመ ክፍያ ብር 3ዐ,ዐዐዐ እንደተከፈለ ተቆጥሮ ከመስረከም 19 ቀን 1998 - ሰኔ 24 ቀን 1999 ድረስ ለ9 ወራት አመልካችና ተጠሪ በጋራ የተጠቀሙበት ስለሆነ የ51 ወራት በወር በብር 5ዐዐ ሂሣብ ተጠሪው ባዋጡት መጠን ድርሻቸውን እንዱያገኙ ተብሎል።
ደመወዝን በሚመለከት አጣሪው ከመቼ ጀምሮ መከፈል እንዲለበት በግልጽ የተቀመጠ ነገር የግራ ቀኙ አከራካሪዎች ባለማቅረባቸው የተነሣ አመልካች ድርጅቱ ሥራውን ከጀመረበት ቀን አንስቶ ከ2 ወር በኋላ መሆን አለበት ያለትን አጣሪው በመቀበልና ድርጅቱ ሥራ የጀመረው 17/4/1999 በመሆኑ ከየካቲት 18 ቀን 1997 – 24/10/98 ድረስ የ16 ወራት ደመወዝ ማናቸውም የመንግስት ግብር ተቀንሶና ቀደም ሲል ተጠሪው በብድር የወሰደት ብር 37,000 ተቀናሽ ተደርጏ የሚደርሣቸውን ድርሻ አመልካች እንዱከፍለ በሚል በሪፕርቱ ገልጿል።
እንግዱህ እነዚህ ከዚህ በላይ የተጠቀሱት ልዩ ልዩ ክፍያዎች ናቸው ተጠቃልለው ብር 83,ዐ81.04 ሳንቲም የሆኑት አጣሪው በዚህ ዓይነት በጥልቀት የቀረቡለትን ማስረጃዎች በመመርመር አግባብነት ያላቸውን በመቀበልና አግባብነት የላላቸውን በመጣል የተጠቀሰውን ገንዘብ የሰበር አመልካች እንዱከፍለ በሪፕርት የገለፀውና የሥር ፍ/ቤቶች በየደረጃው የቀረበላቸውን ጉዲይ በመመርመር ገንዘቡን አመልካች ለተጠሪ እንዱከፍል የወሰኑት።
አመልካች ብር 6ዐ,ዐዐዐ በ24/10/98 ዓ/ም በተደረገ ስምምነት መክፈላቸውን በመግለጽ ያቀረቡት የመከራከሪያ ሀሣብም ቢሆን ብር 6ዐ,ዐዐዐ / ስልሳ ሺህ / የተከፈለው ካሣ በሚል ስለሆነና በዚሁ ስምምነት ላልች ሂሣቦች ለወደፉት ተሰልቶ የሚቀርቡና ክፍያ የሚፈፀምባቸው መሆኑ የተገለፀ በመሆኑ በስላቱ መሰረት እንዱከፍለ የተጠየቁትን ገንዘብ መክፈል አይገባኝም ማለታቸው ተቀባይነት ያለው አይደለም።
በልላ በኩል የማህበሩን ዕዲ በሚመለከት ምንም ሳይባል ታልፎል ያለትም ቢሆን የግራ ቀኙ ተከራካሪዎች ሰኔ 24 ቀን 1998 ዓ/ም በተፈራረሙት ቃለ ጉባኤ ገጽ 6 በቁጥር ‛7 ድርጅቱ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ይህ ውል እስከ ተደረገበት እለት ድረስ በድርጅቱ ላይ ያለውን ዕዲ በተመለከተ ድርጅቱን በማስቀረት ይዘው የሚጓዙት አመልካች በሚያቀርቡትና በተጠሪው ‛ሼር“ ምትክ በሚገባው ግለሰብ የሚሸፈን ይሆናል“ ተብሎል። በዚህ መልክ ስምምነት ላይ የተደረሰ ከሆነ ደግሞ እንደገና አመልካች ተጠሪው ለማህበሩ ዕዲ ተጠያቂ ሉሆኑ ይገባል ያለት ከተፈረመው ስምምነት ጋር የሚጋጭ ይሆናል።
የማህበሩን መፍረስ በሚመለከት አመልካች ባቀረቡት ክርክር ተጠሪ ድርሻቸውን ይዘው ከማህበሩ የወጡ በመሆናቸው በተጠሪው ጥያቄ መነሻ ማህበሩ ሉፈርስ አይገባም ካለ በኋላ የማህበሩ አባላት ከሁለት በታች በመሆኑ እንዱፈርስ ጠይቀዋል የሥር ፍ/ቤትም ማህበሩ እንዱፈርስ የወሰነው ከዚህ በላይ በተጠቀሰው የክርክር ሃሣብ መነሻ ነው። አመልካችና ተጠሪ የመሰረቱት ማህበር ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሲሆን ማህበሩ ሉመሰረት የሚችለው ደግሞ በንግድ ህግ አንቀጽ 510/2/ እንደተጠቀሰው ማህበርተኛው ከሁለት ያላነሰና ከአምሣ ያልበለጠ ከሆነ ነው።
በዚህ በተጠቀሰው ማህበር ደግሞ አባላቱ አመልካችና ተጠሪ ብቻ ሲሆኑ ተጠሪው ከማህበሩ ከተሰናበቱ አመልካች ብቻ ይቀራለ። ይህ ከሆነ ደግሞ በህጉ ከተጠቀሰው አነስተኛ ቁጥር በታች በመሆኑ መፍረሱ የግድ ነው።
በመሆኑም የሂሣብ አጣሪ ያቀረበውን ሪፕርት መነሻ በማድረግ የሥር የመ/ደ/ፍ/ቤት ከውሣኔው በፉት ተጠሪ የተቀበለትን ብር 6ዐ,ዐዐዐ/ስድሳ ሺህ/ እና በሂሣብ አጣሪ ተሰልቶ የቀረበውን ብር 83,081.04 /ሰማንያ ሶስት ሺህ ሰማንያ አንድ ከዜሮ አራት ሳንቲም/ አመልካች ለተጠሪ እንዱከፍለና የንግድ ማህበሩም እንዱፈርስ የሰጠውን ውሣኔ ከፍተኛ ፍ/ቤትም ያፀናው በአግባቡ ስለሆነ በሥር ፍ/ቤቶች ውሣኔ ላይ የተፈፀመ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም።
ው ሣ ኔ
የሥር የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/ በቀን 01/7/2001 ዓ/ም በዋለው ችልት እንዱሁም የፋ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ በቀን 10/03/2003 በዋለው ችልት የሰጡት ፍርድች ፀንተዋል።
አመልካች ለተጠሪ ቀደም ሲል ከከፈለት ብር 6ዐ,ዐዐዐ/ስድሳ ሺህ/ በተጨማሪ ብር 83,081.04/ሰማንያ ሶስት ሺህ ሰማንያ አንድ ከዜሮ አራት ሳንቲም/ እንዱከፍለ የተወሰነባቸው በአግባቡ ነው ብለናል።
የዚህን ፍ/ቤት ወጪና ኪሣራ አመልካችና ተጠሪ የየራሣቸውን ይቻለ።
መዝገቡ የተዘጋ ስለሆነ ወደ መዝገብ ቤት ተመላሽ ይሁን።
No topics extracted.