No summary available.
የካቲት ዐ4 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም.
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ አብደልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አመልካች፡- ሀጂ መሐመድ አደም ተከሣሽ ፡- አቶ ፍፁም ግርማ
ጉዲዩ የሚተላለፍ ሰነድ ላይ የግል ግንኙነትን መሰረት በማድረግ የሚቀርብን መቃወሚያ ይመለከታል። ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው በፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት የቀረበው አቤቱታ ነው።
የአሁኑ ተጠሪ በመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ አመልካች ለተጠሪ ዐ57442ዐ የሆነ ብር 55,000 ሺህ የያዘ ቼክ የሰጡ ቢሆንም ለክፍያ ለባንክ ሲቀርብ በቂ ገንዘብ የለም ተብል ተመልሶላቸዋል። አመልካች ከዚህ ገንዘብ ውስጥ ብር 25‚ዐዐዐ ከፍለው ብር 3ዐ‚ዐዐዐ ይቀርባቸዋል።
በመሆኑም ይህንኑ ገንዘብ ከወለደ ጋር ይክፈለኝ ሲለ ጠይቀዋል። አመልካችም ቀርበው ቼኩ የተሰጠው በተጠሪና በአቶ ሙሣ መሐመድ መካከል ለነበረው አለመግባባት የሽምግልና ጉባኤ ባቀረበው ሃሣብ መሰረት ለሁለቱ ተከራካሪዎች መተማመኛ እንዱሆን በመሆኑ ክሱን ለመከላከል እንዱፈቀድላቸው ጠይቀዋል። ፍ/ቤቱም ቼክ ግልጽ የሆነ የክፍያ ትዕዛዝ ብቻ የሚይዝ በዚህ ትዕዛዝ እንደቀረበ ክፍያ የሚፈፀምበትና ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በአውጪው ላይ የክፍያ ሃላፉነት የሚፈጥር የገንዘብ ሰነድ እንጂ የዋስትና ሰነድ ስላልሆነ ለመከላከል ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት የለውም በማለት ገንዘቡን ከወለድ ጋር እንዱከፍለ ወስኖባቸዋል።
አመልካች ይህንን ውሣኔ በመቃወም ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረቡት የይግባኝ ቅሬታም ተቀባይነት ሣያገኝ ቀርቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ላይ ሲሆን ይህ ችልትም ክሱ በይርጋ ሉታገድ የሚገባው መሆን አለመሆኑን እንዱሁም አመልካች ክሱን ሉከላከለ የሚገባቸው መሆን አለመሆኑን ለመመርመር ይግባኙ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ያደረገ ሲሆን ግራ ቀኙ በነዚህ ነጥቦች ላይ ክርክራቸውን አሰምተዋል። ችልቱም መዝገቡን እንደሚከተለው መርምሯል።
ክሱ በይርጋ ይታገዲል ወይስ አይታገድም የሚለውን ነጥብ በተመለከተ አመልካች ቼኩን ለተጠሪ የሰጡት ጥር 3ዐ ቀን 1997 ዓ.ም. መሆኑን ከመዝገቡና ከግራ ቀኙ የቃል ክርክር ጭምር መረዲት ተችሎል። ቼክ የወጣበት ቀን ከግምት ሳይገባ በቼክ ላይ ከተፃፈው ቀን አንስቶ በሚከተለት 6 ወራት ውስጥ እንዱከፈል መቅረብ እንዲለበት በንግድ ሕግ ቁጥር 855 ሥር ተመልክቷል።
በዚሁ ሕግ ቁጥር 881/1/ ሥር ደግሞ በቼክ የሚገደደ ሰዎች ላይ አምጪው ክስ ማቅረብ የሚችለው ቼኩን ለማቅረብ የተወሰነው ጊዜ ካለፈ ጀምሮ እስከ ስድስት ወር ድረስ መሆኑ ተመልክቷል። በመሆኑም አምጪው ክስ ማቅረብ የሚችለው ቼክ ከተፃፈበት ቀን አንስቶ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ መሆኑን መረዲት ይቻላል። በተያዘው ጉዲይ ቼክ የተፃፈው ጥር 3ዐ/1997 መሆኑ በግራ ቀኙ ያልተካደ ሲሆን ክስ የቀረበው ደግሞ ታህሣሥ 1ዐ/1998 መሆኑን ከመዝገቡ መረዲት ይቻላል። በመሆኑም ቼኩ ተጽፍ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ክስ እስከቀረበበት ቀን 1 ዓመት አያልፍም። ቼኩ ተጽፍ ከተሰጠ ጀምሮ ለባንክ እንዱከፈል እስከቀረበበት ድረስ 6 ወር አልፎል እንዲይባል ደግሞ ቼኩ የተሰጠው ጥር 3ዐ/1997 መሆኑና ለክፍያ የቀረበው ሐምል 29/1997 መሆኑን ግራ ቀኙ ተማምነዋል። በመሆኑም ከጥር 3ዐ/1997 እስከ ሐምል 29/1997 ዓ.ም. 6 ወር ስለማያልፍ በንግድ ሕጉ ቁጥር 855 ሥር የተመለከተው የይርጋ ጊዜም ቢሆን ስለማያልፍ አመልካች ይርጋን አስመልክቶ ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት የለውም።
በመቀጠል አመልካች ክሱን ሉከላከለ ይገባል አይገባም የሚለውን ነጥብ እንመለከታል።
በመሰረቱ ቼክ የተወሰነ ገንዘብ ለመክፈል ሐተታ የላለበት ትዕዛዝ የያዘና ቼኩም እንደቀረበ የሚከፈል መሆኑ በን/ሕ/ቁ. 827/ሀ/ እና 854 ሥር ተመልክቷል። በመሆኑም ቼኩ የታዘዘለት ሰው /አምጪው/ ቼኩን ይዞ እንደቀረበ ቼኩ ሉከፈል ይገባዋል። አውጪውም ሆነ የጀርባ ፈራሚዎቹ ለቼኩ አከፊፈል ኃላፉዎች በመሆናቸው /የን/ሕ/ቁ. 640 እና 868 /ሐ/ ይመለከቷል/ ቼክ ባልተከፈለ ጊዜ ተጠያቂዎች ይሆናለ። ቼክ እንደ ገንዘብ ወደተለያዩ ሰዎች በቀላለ ሉተላለፍ የሚችል ባህሪ ስላለው የቼክ አከፊፈል ላይ ማንኛውም መቃወሚያ ላቀርብ አይችልም። ሕጉ ለይቶ ባስቀመጣቸው ጉዲዮች ካልሆነ የቼክ ክፍያ በማንኛውም ምክንያት ሉቆምና ሉታገድ አይችልም።
ነገር ግን የተወሰኑ ሁኔታዎች ባጋጠሙ ጊዜ አውጪው ወይም ፈራሚዎቹ ቼክ ሉከፈል የማይገባበትን መቃወሚያ ሉያነሱ ይችላለ። በመሆኑም አግባብነት ያላቸው የንግድ ሕግ ድንጋጌዎች በመቃወሚያነት እንዱቀርቡ የፈቀድዋቸውንና የከለከለዋቸውን ጉዲዮች ለመለየት የሕጉን ድንጋጌዎች እንዲለ መመልከቱ ጠቃሚ ነው። በዚህ ረገድ ለዚሁ ቀጥተኛ ተፈፃሚነት ያላቸው ድንጋጌዎች የንግድ ሕጉ አንቀጽ 717 እና 85ዐ ሲሆኑ የአንቀጽ 717 ይዘት የሚከተለው ነው።
717 መቃወሚያ
ዕዲ ከፊዩ ሰነደን በያዘው ሰው በሁለቱ የግል ግንኙነቶች ላይ በተመሰረቱት፣ በሰነደ አፃፃፍ ፍርምና እንዱሁም በሰነደ ላይ በተፃፈት ቃልች ካልሆነ ላላ መቃወሚያ ሉያቀርብበት አይችልም።
እንዱሁም ፊርማን በማስመሰል የተሰራ፣ ችልታ ወይም ሰነደ ሲወጣ የውክልና ሥልጣን ባለመኖሩ ወይም ክስ ለማቅረብ አስፈላጊ የሆኑት ሁኔታዎች ባለመሟላታቸው የተነሱትን መቃወሚያዎች ለማቅረብ ይችላል።
አምጪው ይህን ሰነድ ባገኘበት ጊዜ ዕዲ ከፊዩን ለመጉዲት እያወቀ ያደረገው ካልሆነ በቀር ከዚህ በፉት ሰነደን ይዘው ከነበሩት ሰዎች ጋራ በግል ግንኙቶች ላይ በተመሰረቱ ክርክሮች ዕዲ ከፊዩ ሰነደን የያዘውን ሰው ሉቃወመው አይችልም።
717 Defenses 1/ The debtor may only set up against the holder of the instrument defenses based on their personal relations. Defenses of form and those based on the text of the instrument.
2/ He may set up defenses based on falsification of signature, lack of capacity or power of representation at the time of issue of the instrument or on the absence of the necessary conditions for bringing the proceeding.
3/ The debtor may not set up against the holder of the instrument defenses based on his personal relations with previous holders unless the holder in acquiring the instrument has knowingly acted to the detriment of the holder.
ከዚህ ሕግ ድንጋጌ ይዘት ሕጉ ለሚተላለፈ ሰነድች የሚሰጠው ጥበቃ እንደተጠበቀ ሆኖ ተዘርዝረው በተገለፁ ሁኔታዎች በነዚህ ሰነድች የተከሰሰ ሰው አንዲንድ መቃወሚያዎችን በማቅረብ ከእዲው ራሱን ነፃ ማድረግ እንደሚፈቅድ መገንዘብ ይችላል። የግል ግንኙነት መቃወሚያ ሉሆኑ ከሚችለ ጉዲዮች አንደ ሲሆን ከዚሁ ድንጋጌ ንኡስ ቁጥር አንድና ሶስት መገንዘብ እንደሚቻለው ሕጉ የግለ ግንኙነት መቃወሚያ ሉሆኑ የሚችልበትንና የማይችልበትን ሁኔታ ለይቶ አስቀምጧል።
በዚሁ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ አንድ ላይ በዕዲ ከፊዩና ሰነደን በያዘው ሰው መካከል ያለው የግል ግንኙነት በመቃወሚያነት ላቀርብ የሚችል ሲሆን በዕዲ ከፊዩና /በተከሣሹ/ ቀድመው ሰነደን ይዘው በነበሩ ሰዎች መካከል ያለ የግል ግንኙነት ግን በመርህ ደረጃ መቃወሚያ ሆኖ ላቀርብ አይችልም።
በመሆኑም የግል ግንኙነት ምን ማለት ነው? የሚለው ጥያቄ እንደተጠበቀ ሆኖ የግል ግንኙነት እንደመቃወሚያ መቅረብ የሚችለው ይኸው የግል ግንኙነት በከሣሹና በተከሣሹ መካከል ያለ እንደሆነ ብቻ ነው። ከላይ እንደተጠቀሰው ቼክም ሆነ ላልች የሚተላለፈ የገንዘብ ሰነድች በንግድ ልውውጥ ሂደት የመተላለፍ ባሕርይ ያላቸው በመሆኑ ከከሣሹና ከተከሣሹ በተጨማሪ ላልች ሰዎች በሂደት በፊርማ አስተላልፈዋቸው ወይም ተቀብለዋቸው ላሆን እንደሚችል መገንዘብ ጠቃሚ ነው። በመሆኑም በዚህ ሂደት የሚኖረው የግል ግንኙነት አንድ ብቻ ሳይሆን በእያንዲንደ ቼኩን ፈርሞ ባስተላለፈና በተቀበለ ሰው መካከል በርካታ የግል ግንኙነቶች ሉኖሩ ይችላለ። ከነዚህ በርካታ የግል ግንኙነቶች /Personal relations/ መካከል ሕጉ በመቃወሚያነት እንዱቀርብ የሚፈቅደው በተከሣሹና ሰነደን ይዞ በመጣው ሰው መካከል ያለውን የግል ግንኙነት ብቻ ነው። ተከሣሹ ሰነደን ይዞ ከመጣው ሰው ሣይሆን ቀድመው ሰነደን ይዘው ከነበሩ ሰዎች ጋር የነበረውን የግል ግንኙነት እንደመቃወሚያ በማቅረብ ክፍያውን አልፈጽምም እንዱል ሕጉ አይፈቅድለትም። ይህ መሰረታዊ መርህ በንግድ ሕጉ አንቀጽ 717 /1 እና 3/ ላይ ብቻ ሳይሆን በንግድ ሕጉ አንቀጽ 752 እንዱሁም አንቀጽ 85ዐ የተካተተ ነው። ቼክን የሚመለከተው አንቀጽ 85ዐ በተለይ ‛አምጪው ቼኩን ሲያገኝ ያውም ባለዕዲውን ለመጉዲት ካላደረገ በቀር በቼኩ መሰረት የተከሰሱት ሰዎች ከአውጪው ጋራ ወይም በፉት አምጪ ከሆኑት ጋራ በግል ግንኙነታቸው ላይ በተመሰረቱት ልዩነቶች አምጪውን ሉቃወሙት አይችለም“ በማለት በቼክ የተከሰሰ ሰው መቃወሚያ ሉሆነው የሚችለው ከአምጪው /holder/ ወይም ቼኩን ከያዘው ሰው ጋር ያለው የግል ግንኙነት እንጂ ከቼኩ አውጪ /drawer/ ወይም ቼኩን ቀድመው ይዘው ከነበሩ ሰዎች /previous holders/ ጋር ያለውን የግል ግንኙነት እንዲልሆነ ይደነግጋል። የንግድ ሕግ አንቀጽ 85ዐ የእንግሉዝኛው ትርጉም ‛ Persons sued on a cheque cannot set up against the holder defenses founded on their personal relations with the drawer or with previous holder. unless the holder in acquiring the cheque has knowingly acted to the detriment of debtor“ በሚል ነው።
ሕጉ የግል ግንኙነት በመቃወሚያነት የሚቀርብበት ሁኔታ ላልች መቃወሚያዎች ከሚቀርቡበት ሁኔታ ልዩነት አበጅቷል። ይህን ልዩነት የንግድ ሕጉን አንቀጽ 717 ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች በመመልከት መገንዘብ የሚቻል ነው። ከዚህ ድንጋጌ መገንዘብ እንደሚቻለው ሕጉ በግል ግንኙነት ያስቀመጠው ዓይነት ገደብ በላልች መቃወሚያዎች ላይ አላስቀመጠም። አንቀጽ 717 በመቃወሚያነት የሚቀበላቸው ላልች ጉዲዮች /የሰነደ አፃፃፍ፣ በሰነደ የተፃፈ ቃልች ምክንያት የሚነሱ መቃወሚያዎች /717/1/ ወይም በማስመሰል የተሰራ ፊርማ፣ ችልታ ወይም ሥልጣን አለመኖር፣ ክስ ለማቅረብ አስፈላጊ ሁኔታዎች አለመሟላት /717/2// የግድ በአምጪውና በተከሰሰው ሰው መካከል ብቻ የሚነሱ መሆናቸውን የሚገልጽ ድንጋጌ የለውም ይልቁንም እነዚህ ጉዲዮች መኖራቸውን ባረጋገጠ በማንኛውም ተከሣሽ ሉነሱ የሚችለ ጉዲዮች ናቸው። በመሆኑም በ717 ከተገለጹት መቃወሚያዎች መካከል የግል ግንኙነት /Personal relation/ ከሣሹንና ተከሣሹን ብቻ የሚመለከት ሆኖ ሲገኝ ላልች መቃወሚዎች ግን ላልችን በሂደቱ ላይ የነበሩትን ሰዎች የሚመለከት እንኳን ቢሆን በቃወሚያነት ማንሳት ይቻላል። በልላ አነጋገር ላልቹ መቃወሚያዎች ቼኩን ተከትለው የሚሄደ ሲሆን፣ የግል ግንኙነት ግን በሁለቱ /ከሣሽና ተከሣሽ/ ብቻ ተወስኖ የሚቀር ነው። በመሆኑም በአንቀጽ 717 የሚታዩት መቃወሚያዎች ሁለት ገጽታ ያላቸው ናቸው።
በአንድ በኩል ማንኛውም በቼክ የተከሰሰ ሰው ሉያነሳቸው የሚችል፣ አምጪውም ቢሆን እነዚህ መቃወሚያዎች አንተን የሚመለከቱ አይደለም ሉል የማይችልባቸው በመሆናቸው ሰነደ እስካለ ድረስ እሱን ተከትለው የሚሄደ በላልች የሕግ ሥርዓቶችና በሕግ ጽንሰ ሃሣብ real defense በመባል የሚታወቁ ሲሆን በልላ በኩል ደግሞ ሰነደ ይመለከታቸዋል ከሚባለ ሰዎች መካከል የተወሰኑ ሰዎች ብቻ ካልሆኑ በቀር ላልቹ እንዱያነሱዋቸው የማይፈቀደ በሕግ ሳይንስና በላልች የሕግ ሥርዓቶች Personal defense /in personal defense/ በመባል የሚታወቁ መቃወሚያዎች ናቸው። መቃወሚያዎችን /defense/ ብቻ ሳይሆን መብቶችን Personal እና Real ወይም rights in personal እና rights in rem/ ብል መከፊፈል በሁለም የሕግ ሥርዓቶች ያለ በኛም የሕግ ሥርዓት በተለያዩ ሁኔታዎች የተካተተ ነው።
በመሆኑም በንግድ ሕጉ የተለያዩ አንቀጾች በተለይም በአንቀጽ 717፣ 752 እንደሁም 85ዐ የተገለፀውና የግል ግንኙነትን የሚመለከተው መቃወሚያ ላታይ የሚገባው ከዚህ አንፃር ነው። ቼክ ለአምጪው የሚከፈል የንግድ ልውውጥን ለማቀላጠፍ ተብል የተዘጋጀ ሰነድ መሆኑ እሙን ነው።
የአፈፃፀሙ ሂደት የንግድ ሂደትን እንዲያውክና እንዲያስተጓጉል መደረግ እንዲለበትም እሙን ነው።
በልላ በኩል ግን ቼክ የሚሰጠው በአመዛኙ በንግድ ልውውጥና በግብይት ሂደት በመሆኑ ይህን ታሳቢ በማድረግ ሕጉ ያስቀመጣቸውን መቃወሚያዎች በአግባቡ ማስተናገድ ተገቢ ነው።
በቼክ የተከሰሰ ሰው ከላልች በቼኩ ከተጠቀሙ ወይም ካስተላለፈ ሰዎች ጋር ያለውን የግል ግንኙነት ማንሣት ባይፈቀድለትም ከአምጪው ጋር ያለውን የግል ግንኙነት ግን ማንሳት ይፈቀድለታል። የግል ግንኙነት ምንድነው የሚለው ደግሞ ሉተረጎም የሚገባው ከላይ ከተመለከትነው፣ የንግድ ሕግን ዓላማ የሚያሳካና ከተለመደው አተረጓጎም አንፃር እንጂ ከዚህ ባፈነገጠ መንገድ ላሆን አይገባውም። በመሆኑም የግል ግንኙነት ማለት ከሚመለከታቸው ሁለት ሰዎች ውጪ በላልች ሰዎች ሉነሳ የማይችል ግንኙነትን ለማመልከት እንጂ ከንግድና ከግብይት ውጪ የሚከሰቱ ግላዊ ግንኙነቶች ለማመልከት የተቀመጠ ነው ተብል ሉተረጎም አይገባውም።
የግል ግንኙነት /Personal relation/ በተለምድ in personal በመባል የሚታወቀውን ከሕግ ወይም ከውል የሚመነጭ በሁለት ሰዎች መካከል የተፈጠረ ግንኙነት ማለት ነው።
የንግድ ሕጉ አንቀጽ 85ዐ በቼክ የተከሰሱ ሰዎች ቼኩን ካዘጋጀው /አምጪው/ ወይም ቼኩን ቀድመው ይዘው ከነበሩት ሰዎች /Personal holder/ ጋር የነበረውን የግል ግንኙነት ቼኩን ይዞ በመጣ ሰው /holder/ ላይ እንዲያነሳ ከሚከላከል በቀር ተከሣሹ ቼኩን ካመጣው ሰው ጋር ያለውን የግል ግንኙነት እንዲያነሳ የሚከለክል አይደለም። ይልቁንም ለሁለም ሰነድች ተፈፃሚነት ያለውና ከላይ የተመለከትነው አንቀጽ 717/1/ በሁለቱም መካከል ያለ የግል ግንኙነት መቃወሚያ ላሆን እንደሚችል በግልጽ ያስቀመጠው ነው። ይህ የሕግ ይዘት በቼክ የተከሰሰ ሰው በቼኩ ላይ የተገለፀውን ገንዘብ በሙለ ወይም በከፉል ላለመክፈል መብት የሚሰጠውን ከውል የመነጨ ግንኙነት እንደመከላከያ እንዱያቀርብ የሚፈቅድለት ነው። ቼክ አብዛኛውን ጊዜ የሚሰጠው ከውል ወይም ከሕግ የመነጨ ግዳታን ለመፈፀም /in consideration/ እንደመሆኑ ለግዳታው መነሻ የሆኑ ጉዲዮችን በማስመልከት መከላከያ እንዱሆኑ መፍቀድ ተገቢም ነው። ይህ አሰራር የሁለቱም ወገን ማስረጃን ለመመዘን ዕድል በመስጠት እውነት እንዱወጣ ከማገዙም ባሻገር የተለያዩ ክሶች እንዲያቀርቡ ስለሚያደርግ ወጪ ቆጣቢም ነው።
የሥር ፍርድ ቤት አመልካች ያቀረቡትን መቃወሚያ ውድቅ ያደረገው የንግድ ሕጉ አንቀጽ 827/84ዐ እንዱሁም 854 ቼክ እንደቀረበ ክፍያ የሚፈፀምበትና ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በአውጪው ላይ የክፍያ ኃላፉነት የሚፈጥር የገንዘብ ሰነድ እንጂ የዋስትና ሰነድ አለመሆኑን ይደነግጋል በማለት ነው። በመሰረቱ እነዚህ የተጠቀሱት የንግድ ሕጉ ድንጋጌዎች ቼክ በዋስትና ላሰጥ የማይችል መሆኑን አይደነግጉም። ቼኩ የሚሰጥበት ምክንያት በሰጪውና በተቀባዩ የሚወሰን እንጂ በሕጉ የተዘረዘረ አይደለም። ሕጉ ቼክ ላምጪው ወዱያው የሚከፈል መሆኑን መግለፁ ደግሞ መከላከያና መቃወሚያ የማይቀርብበት ሰነድ ነው ማለት አይደለም። የሕጉ ዓላማ ይህ ቢሆን በማያሻማ ሁኔታ በ717 በተዘዋዋሪ መንገድ ደግሞ በአንቀጽ 85ዐ መቃወሚያ የሚቀርብባቸውን ሁኔታዎች አይደነግግም ነበር።
በመሆኑም ፍርድ ቤቱ ተከሣሽ ያቀረቡትን መቃወሚያ አልቀበልም ያለው ከሕጉ ድንጋጌ ውጪ በመሆኑ ሉሻር የሚገባው ሆኖ አግኝተነዋል። ቼኩ በዋስትና የተሰጠ መሆኑን በመገለፁ የአሁን አመልካች ከከሳሽ ጋር የዋስትና ውል ግንኙነት ያላቸው መሆኑን የሚያመለክት ነው። ይህ ውል ደግሞ በመካከላቸው የግል ግንኙነት መኖሩን ስለሚያሳይ በመቃወሚያነት መቅረብ የሚችል ነው። የቀረበው መቃወሚያ የተጠየቀውን ገንዘብ ላለመክፈል በቂ ምክንያት መሆን አለመሆኑ የሚታወቀው ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን በአግባቡ ካከራከረ በኋላ ነው። በመሆኑም ክሱ የቀረበለት ፍርድ ቤት መቃወሚያውን ተቀብል ክርክሩን ሉያስተናግድ የሚገባ ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 62ዐ28 የካቲት 28/98 የሰጠው ውሣኔ እንዱሁም የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 454ዐ9 በ22/7/98 የሰጠው ትዕዛዝ በድምጽ ብልጫ ተሽሯል።
አመልካች መከላከያቸውን አቅርበው ፍ/ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ሰምቶ የመሰለውን እንዱወስን ጉዲዩ ለፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ተመልሷል።
ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ መዝገቡ ተዘግቷል። ለመዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.