No summary available.
ሐምል 15 ቀን 2003 ዓ/ም ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የንግድ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር - ነ/ፈጅ ዮናስ ከበደ ቀረበ ተጠሪ፡- ታይገር ልጂስቲክ እና የንብረት ጥበቃ ኃ.የተ.የግል ማህበር - የቀረበ የለም **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ በአመልካች መስሪያ ቤት በአዋጅ ቁጥር 67/89 እና ይህንኑ አዋጅ ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 376/96 መሰረት የሚሰጣቸው የንግድ ስራ ፈቃድ ጉዲዮች ውድቅ የሚደረጉበትን አግባብ የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን ከሳሽ የነበረው የአሁኑ ተጠሪ ነው። ክሱ የተመሰረተውም ባሁኑ አመልካችና ታይገር ሴኩሪቲ ኃ.የተ.የግል ማህበር በተባለ ድርጅት ላይ ነው። የአሁኑ ተጠሪ በአመልካች መስሪያ ቤት ላይ የመሰረተው የክስ ይዘት ባጭሩ፡- ድርጅቱ ታይገር ልጅስቲክና የንብረት ጥበቃ( Tiger Logistic and property Protection) በሚል የንግድ ስያሜ ከአመልካች መስሪያ ቤት የንግድ ስራ ፈቃድ ቁጥር ኢ.አይኤ(ኦኤል) 2047/08 በቀን 02/05/2000 ዓ/ም በሕጋዊ መንገድ ተሰጥቶት እየተንቀሳቀሰ ባለበት ሁኔታ በዚሁ ተመሳሳይ ስም ታይገር ሴኩሪቲ በሚል አላማ ላይ የተሰማራ ድርጅት ፈቃድ ወስድ በአዋሳ ከተማ ከ2000 ዓ/ም ጀምሮ ተገቢ ያልሆነ የንግድ ውድድር(Unfair trade Competition) በማድረግ በአዋጅ ቁጥር 67/89 አንቀጽ 14(4(ሀ)) ስር ከተመለከተው መንፈስ ውጪ የተጠሪን ድርጅቶችን ደንበኞች በማደናገር የድርጅቱን ገቢ እየቀነሰ እንደሚገኝ ፣ አመልካች መስሪያ ቤትም ሁኔታውን እንዱያርም ተጠይቆ ተገቢውን ምላሽ ያልሰጠና ተመሳሳይ የንግድ ስያሜ የተሰጠው የሥር ሁለተኛ ተከሳሽም ጉዲዩን በድርድር ሉፈታው የማይችል መሆኑንና በአመልካች መስሪያ ቤት ጉዲዩ እልባት እንዱያገኝ ፍላጎት ያለው መሆኑን ገልጾ ሁኔታው እንዱታረምና እንዱሰረዝ እንዱወሰን እንዱሁም ኪሳራው በቁርጥ እንዱወሰን ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው።
የአሁኑ አመልካች በተከሳሽነቱ ቀርቦ በሰጠው መልስም የንግድ ስራ ፈቃድ የተሰጠበትን አሰራር በአዋጅ ቁጥር 67/89 እንዱሁም ይህንኑ አዋጅ ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 376/96 የተከተለ መሆኑን ፣ ለተጠሪ ድርጅትና ለስር ሁለተኛ ተከሳሽ የተሰጠው የንግድ ስራ ፈቃድ ተመሳሳይ ላልሆኑ ስራዎች የተሰጠ መሆኑን ገልፆ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል። የስር ሁለተኛ ተከሳሽም ቀድሞ የንግድ ስራ ፈቃድ የወሰደው ራሱ መሆኑና ተጠሪ ከተሰጠው የንግድ ስራ ፈቃድ ውጪ እየሰራ የሚገኝ መሆኑን ዘርዝሮ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል። ክሱ የቀረበለት ፍርድ ቤትም የአመልካችን መከራከሪያ ነጥቦችን ሕጋዊ አይደለም በማለት ውድቅ አድርጎ የስር ሁለተኛ ተከሳሽ የንግድ ድርጅቱን ስያሜ እንዱቀይር ፣ የአሁኑ አመልካችም የስር ሁለተኛ ተከሳሽን የንግድ ድርጅት ስያሜ እንዱሰርዝ ፣ ሁለተኛ ተከሳሽም ታይገር የምትለዋን ስያሜ እንዲይጠቀም በማለት ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ፀንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም አመልካች መስሪያ ቤት በጉዲዩ ላይ ውሳኔ የመስጠት ስልጣኑ በአዋጅ ቁጥር 67/89 አንቀጽ 16(2) ስር የተደነገገ ሁኖ እያለ የበታች ፍርድ ቤቶች ከዚሁ ድንጋጌ ውጪ በሆነ መንገድ የንግድ ድርጅቱ ስያሜ እንዱሰረዝ መወሰናቸው ያላግባብ ነው በማለት መከራከሩን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም ለጉዲዩ መነሻ የሆነው የንግድ ስያሜ ተመሳሳይ ስለሆነ እና ያልተገባ የውድድር ስሜት እየፈጠረ ስለሆነ ይቀየር መባለ ከአዋጅ ቁጥር 67/89 አንቀጽ 16(2) ድንጋጌ አንጻር ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ተጠሪ በተደረገለት ጥሪ ቀርቦ አመልካች የስር ሁለተኛ ተከሳሽ የሆነው ድርጅት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ተቀብል በተቀመጠበት ሁኔታ የሰበር አቤቱታውን ማቅረቡ ተገቢ ያለመሆኑንና በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔም ምንም የሕግ ስህተት የላለበት መሆኑን በመዘርዘር መልሱን የሰጠ ሲሆን አመልካች ደግሞ በሕጉ አግባብ የተሰጠውን ስልጣን በመጠቀም ለፈፀመው ድርጊት የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን የሕግ ስህተት በሕግ አግባብ ማሳረም መብቱ መሆኑን ዘርዝሮና የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልሱን ሰጥቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
በመሰረቱ አመልካች በአዋጅ ቁጥር 67/89 አንቀጽ 20 መሰረት የንግድ ስራ ፈቃድ የመስጠት ስልጣን ያለው ሲሆን ይህንኑ ስልጣን ተግባራዊ ሲያደርግ የሚያስፈልጉትንና ሉከተላቸው የሚገባቸው ስርዓቶች በአዋጅ ቁጥር 67/89 እና ይህንኑ አዋጅ ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 376/96 ስር ተደንግገው እናገኛለን። አዋጅ ቁጥር 67/89 አንቀጽ 14 የንግድ ስም ለማስመዝገብ መሟላት ስላለባቸው ነገሮችና ለምዝገባ የቀረበው የንግድ ስም ቀደም ሲል ከተመዘገበበት የንግድ ስሞች ጋር አንድ አይነት ወይም ተመሳሳይና አሳሳች አለመሆኑን ወይም ለመልካም ጠባይ ወይም ሥነ ምግባር ተቃራኒ አለመሆኑን በአዋጁ አግባብ አለው በተባለው ባለስልጣን ከተረጋገጠ በሁዋላ የንግድ ስሙ የሚመዘገብ ስለመሆኑ በአመልካቹ ወጪ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ እንዱወጣ በማድረግ ሉመዘግብ የሚችልበትን አግባብ አዋጅ ቁጥር 67/89 አንቀጽ 14(4) ድንጋጌ ደንግጎ ያለው ጉዲይ ሲሆን ይህንኑ አዋጅ ለማሻሻል የወጣው አዋጅ ቁጥር 376/96 ደግሞ የንግድ ስም ከዲታ ቤዝ ተጣርቶ የጋዜጣ ማስታወቂያ ሳያስፈልገው እንደሚመዘገብ ያስገነዝባል። የአሁኑ አመልካች አጥብቆ የሚከራከረውም የአሁኑ ተጠሪ ታይገር ልጂስቲክስ እና ንብረት ጥበቃ ኃ.የተ.የግል ማህበር የሥራ መስክ በላቀ ደረጃ የልጂስቲክ ፣ የንብረት ጥበቃ ስልጠና እና የምክር አገልግልት የሆነው እና የውጪ ኢንቬስቴር 70% ድርሻ የያዘ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ ዋና ምዝገባ እና የኢንቨስትመንት ፈቃድ የተሰጠው መሆኑን ፣ የስር ሁለተኛ ተከሳሽ የተሰማራበት የንግድ ስራ መስክ በደቡብ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጥቃቅንና አነስተኛ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ የተሰጠው የንግድ ስራ ፈቃድ ለሀገር ውስጥ ባለሀብት በተፈቀደ ‛ የጥበቃ ሥልጠና “ እና ‛የጥበቃ አገልግልት“ በመሆኑ አመልካች ሁለቱን የንግድ ማህበራት የተሰማሩበት የንግድ ስራ ጠባይ ፈጽሞ አለመመሳሰለንና በአዋጅ ቁጥር 67/89 አንቀጽ 16(2) የንግድ ስም መዝገብ የመግባት ውጤት ተገቢውን ማጣራት ከአደረገ በሁዋላ ምዝገባውን መፈፀሙን ነው። እንግዱህ በሕጉ የተዘረጋው ስርዓት ከላይ የተመለከተው ከሆነ እና አመልካች ተግባሩን ሕጋዊ ነው የሚልባቸው ምክንያቶች እነዚህ ከሆኑ በሕግ ረገድ ሉነሳ የሚችለው ጥያቄ አመልካች በአዋጅ ቁጥር 67/89 አንቀጽ 16(2) ስር የተደነገገውን ድንጋጌ መሰረት በማድረግ ምዝገባውን መፈጸም አለመፈፀሙን ነው። የዚህ ድንጋጌ ይዘት ሲታይ በንግድ ሕጉ ቁጥር 137 እና 138 የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ አንድ የንግድ ስም ቀድሞ የተመዘገበ መሆኑ ብቻውን በንግድ ስራ ጠባዩ ፈፅሞ ለማይመሳሰል የንግድ ስራ እንዲይመዘገብ ሉከለክል አይችልም በማለት በአስገዲጅ ሁኔታ የተደነገገ መሆኑን ያስገነዝባል።
አመልካች እንደተገለፀው ተጠሪ የንግድ ስራ የወሰደበት ስራ እና የስር ሁለተኛ ተከሳሽ የንግድ ስራ የማይመሳሰለ መሆናቸውን በሕጉ መሰረት በተሰጠው ስልጣን ማጣራቱን ገልፆ የተከራከረ ሲሆን የበታች ፍርድ ቤቶች የአሁኑ ተጠሪ እና የስር ሁለተኛ ተከሳሽ የንግድ ድርጅት ስም ይመሳሰላል ወደሚለው ድምዲሜ ከመድረሳቸው ውጪ ስራው አይመሳሰልም በማለት በአመልካች በኩል የቀረበውን ክርክር ተቀባይነት የላለበት መሆኑን የሚያሳይ ሕጋዊ ምክንያት በውሳኔአቸው ላይ አልገለፁም። በመሆኑም አንድ የአስተዲደር አካል ድርጊት ውድቅ ላደረግ የሚገባው ከሕግ ውጪ መሰራቱ ተረጋግጦ እንጂ ያለሕጋዊ ምክንያት ላሆን አይገባም። ያለሕጋዊ ምክንያት ተግባሩን ተገቢ አይደለም ብል እንዱስተካከል በማለት መወሰን በሕግ የተሰጠውን ኃላፉነትና ተግባር ባግባቡ እንዲይተገበር የሚያደርግ ጭምር ነው። በልላ በኩል የስር ሁለተኛ ተከሳሽ በጉዲዩ ላይ ስርዓቱን ጠብቆ ይግባኝ ያለማቅረብ የአመልካችን አቤቱታ አቀራረብ ሕጋዊ አይደለም ለማለት የሚያስችል አይደለም። ምክንያቱም አመልካች በሕጉ ተለይቶ የተሰጠውን ሥልጣን ባግባቡ ማከናወኑን እና አንድ ወጥ አሰራር ያለ መሆኑን ማረጋገጥ የራሱ ኃላፉነት ነውና። በአጠቃላይ የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በአዋጅ ቁጥር 67/89 አንቀጽ 16(2) ስር የተመለከተውን መመዘኛ መሰረት ማድረግ ሲገባው የውል ስም የሆነውን ታይገር የሚለውን ቃል ብቻ በመመልከት የተጠሪ የንግድ ስያሜና የስር ሁለተኛ ተከሳሽ ስያሜ የሚመሳሰልና ያልተገባ ውድድር የሚፈጥር ነው በማለት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
No topics extracted.