No summary available.
ሰኔ 3ዐ ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ተክለ ካሣ ገብረየስ - ጠበቃ ስንታየሁ ባህሩ - ቀረበ ተጠሪ፡- ማርኮባርዚ - በላለበት መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
በመዝገቡ ለቀረበው የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዲይ ቼክን መሰረት ያደረገ ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ በተጀመረበት የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ከሣሽ የነበረው የአሁኑ አመልካች ሲሆን ፣ የአሁኑ ተጠሪ እና ማባ /maba/ ኋ/የተ/የግ/ማህበር የተባለ ድርጅት ደግሞ ተከሣሾች ነበሩ። ክሱ በሁለት ቼኮች የታዘዘውን ብር 219,000 አልተከፈለኝም እና ሁለቱም ተከሣሾች ገንዘቡን ይከፍለኝ ዘንድ ይወሰንልኝ የሚል ነው። የአሁኑ ተጠሪ የማህበሩ ስራ አስኪያጅ እንደሆነ የቼኩ አውጪ ማህበሩ መሆኑን ቼኮቹ ወደ ታዘዘው ባንክ ሲወሰደ የማህበሩ /2ኛ ተከሣሽ/ ሂሣብ የተዘጋ መሆኑን መገለጹም በክሱ ተመልክቶአል። ተከሣሾች በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት ባለመቅረባቸዉ ክርክሩ በላለበት ታይቶ መወሰኑንም የስር ፍ/ቤቶች ከሰጡት ውሣኔ ለመገንዘብ ችለናል። ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤት ጉዲዩን ካየ በኋላ የአሁኑ ተጠሪን ከክሱ በነጻ በማሰናበት 2ኛ ተከሣሽ ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ከእነወለደ እንዱከፍል ወስኖአል።
በልላ በኩል ደግሞ አመልካች የተጠሪን ከክሱ በነጻ መሰናበት በመቃወም ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርቦ የነበረ ሲሆን ፣ ፍ/ቤቱም ይግባኝ የተባለበት ውሣኔ ጉድለት የለበትም በማለት ይግባኙን ሰርዞአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
በበኩላችንም አመልካች ሐምል 2 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በጻፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ክርክሩን ሰምተናል።
ተጠሪ በተደረገለት ጥሪ መሰረት ባለመቅረቡ ክርክሩ የተሰማው በላለበት ነው። አቤቱታው በሰበር ችልቱ እንዱታይ የተደረገው ተጠሪ የኩባንያው /በስር 2ኛ ተከሣሽ/ ስራ አስኪያጅ ቢሆንም ፤
ፈርሞ ለሰጠው ቼክ በኃላፉነት አይጠየቅም የመባለን አግባብነት ከንግድ ህግ ቁ. 530 አንጻር ሉመረመር ይገባል በመባለ ነው።
በዚህ መሰረትም ከስር ጀምሮ የተደረገውን ክርክር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና ከህጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
አመልካች ክስ የመሰረተው በቼኩ አውጪ ኩባንያ ላይ ብቻ ሣይሆን ቼኩን ፈርሞ በሰጠው የኩባንያው ስራ አስኪያጅ /ተጠሪ/ ላይ ጭምር ነው። በሰበር አቤቱታ ማመልከቻው ላይም እንደገለጸው ስራ አስኪያጁን አጣምሮ የከሰሰው በስራ አስኪያጅነቱ ብቻ ሣይሆን የኩባንያው የባንክ ሂሣብ መዘጋቱን እና ለቼኮቹ ክፍያ የሚሆን ኩባንያው የሚያዝበት ገንዘብ እንደላለ እያወቀ ሆነ ብል ቼኮቹን ፈርሞ በመስጠት ጥፊት ፈጽሞአል በማለት ጭምር ነው። ክሱን በመጀመሪያ ደረጃ የሰማው የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በውሣኔው እንዲመለከተው ቼኮቹ ባንክ ቀርበው ሉከፈለ ያልቻለት የኩባንያው የባንክ ሂሣብ በመዘጋቱ ምክንያት ነው። ፍ/ቤቱ ይህን ለማለት የቻለው ባንኩ የሰጠው ማረጋገጫ በአስረጂነት ቀርቦለት ከዚሁ በማረጋገጡ እንደሆነም ከውሣኔው ለመገንዘብ ችለናል።
በልላ በኩል ደግሞ ፍ/ቤቱ ተጠሪ በስራ አስኪያጅነቱ ለፈረመው ቼክ ሃላፉ አይሆንም እሚል መደምደሚያ ላይ መድረሱን ተመልክተናል።
እንደምናየው የቼኮቹ ባለቤት /አውጪ/ የሆነው ኩባንያ የባንክ ሂሣብ ስለመዘጋቱ ባቀረበው ማስረጃ ተረጋግጦአል። ኩባንያው ራሱን የቻለ ህጋዊ ሰውነት ያለው አካል ቢሆንም ስራውን የሚያንቀሣቅሰው በስራ አስኪያጅ እንደሆነ ግልጽ ነው። አመልካች ቼኮቹ በስራ አስኪያጁ ተፈርመው በተሰጡበት ጊዜ ሁለ ኩባንያው የሚያዝበት ገንዘብ በባንክ ሂሣቡ እንዲልነበረ አስረድቻለሁ በማለት የተከራከረ ሲሆን ፣ ተከሣሾቹ በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት ቀርበው አልተከላከለም። ከዚህም መገንዘብ የሚቻለው ተጠሪ የኩባንያው ሂሣብ መዘጋቱን እያወቀ ነው ቼኮቹን ፈርሞ የሰጠው የሚለው የአመልካች ክርክር እውነት አይደለም ወደሚለው መደምደሚያ የሚደረስበት ምክንያት እንደላለ ነው የተረጋገጠው ይህ ከሆነ ደግሞ ተጠሪ ጥፊተኛ ወይም ስህተት ፈጽሞአል ማለት ነው።
የኩባንያ ስራ አስኪያጅ በንግድ ህጉ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ወይም የማህበሩን /ኩባንያውን/ የመተዲደሪያ ደንብ በመጣስም ቢሆን በስራ አስኪያጅነታቸው በሰሩዋቸው ጥፊቶችም ፣ ስህተቶችም ቢሆን በማህበሩ እና በሶስተኛ ወገኖች ፉት በየራሣቸው ወይም በአንድነት ሣይከፊፈል እንደነገሩ ሁኔታ ሀላፉዎች እንደሚሆኑ በንግድ ህግ ቁጥር 530 ተደንግጓአል። በያዝነው ጉዲይ የኩባንያ /ማህበር/ ስራ አስኪያጅ የሆነው ተጠሪ ኩባንያውን ለመምራት ስልጣን ያለው /የነበረው/ ሰው እንደሆነ በመረጋገጡ እና ጥፊትም በመፈጸሙ ለፈረማቸው ቼኮች በሃላፉነት የማይጠየቅበት የህግ ምክንያት የለም። ይልቁንም በተጠቀሰው የንግድ ህጉ ድንጋጌ እንደተመለከተው እሱም በግለ ሃላፉ ነው የሚሆነው። የስር ፍ/ቤቶች በፍሬ ነገር ረገድ ያረጋገጡትን እውነታ ከህጉ ጋር አገናዝበው ባለማየታቸው ተጠሪን ነጻ በማድረግ የደረሱበት መደምደሚያ የተሣሣተ ላሆን ችልአል። ከዚህ የተነሣም አቤቱታ የቀረበበት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት ችለናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ. 16058 ታህሣስ 27 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ እና የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት በመ.ቁ. 89973 ሚያዝያ 5 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሻሽሎል።
ተጠሪም ክስ የቀረበበትን ገንዘብ የመክፈል ሃላፉነት አለበት በመሆኑም ተጠሪ እና ማባ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት እንዱከፈል የወሰነውን ገንዘብ በአንድነት እና በነጠላ ይክፈለ በማለት ወስነናል።
No topics extracted.