No summary available.
ሰኔ 14 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ - አ.ማ ጠበቃ ማረን ወንዳ ቀረቡ ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ መድን ድርጅት - ነ/ፈጅ ተመስገን ማሞ ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ባህር ላይ በሚደረግ የእቃ ጉዞ ለሚደርሰው ጉዲት ኃላፉነት ያለበትን ወገን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች ላይ በመሰረተው ክስ መነሻ ነው። ተጠሪ በአመልካች ላይ መጋቢት 25 ቀን 1999 ዓ/ም የመሰረተው ክስ ይዘት ፤ ንብረትነቱ የደንበኛው የቻይና የኤላክትሪክ ዋየርና ኬቬል አስመጪና ላኪ ድርጅት የሆነው ኤላክትሪክ ኃይል ማስተላለፉያ ከቻይና ሻንጋይ ወደብ በጅቡቲ ይርጋለም ዱላ ሀገረ ማርያም ፔሮጀክት ድረስ ተጓጉዞ እስኪመጣ ድረስ ለሚያጋጥም አደጋ በፕሉሲ ቁጥር ኤስ ኤን141 ኤም አር ኦኤ/10776102 የባህር ላይ ጉዞ የመድን ሽፊን መስጠቱን ፣ አመልካች እቃውን ከቻይና ሻንጋይ ወደብ አጓጉዞ ጅቡቲ ለማድስ ግዳታ መግባቱን ፣ አመልካች እቃውን ለተጠሪ ደንበኛ ከማስረከቡ በፉት ጅቡቲ ወደብ ላይ በሚራገፍበት ወቅት የመድን ሽፊን የተሰጠው የኤላክትሪክ ኃይል ማስለተላለፉያ ጥፊት በሆነ ቸልተኝነት ክሬኑ ተበጥሶ ከባህር ውስጥ መውደቁንና ፣ አመልካች እቃውን አደጋ እንደደረሰ ወዱያውኑ ከባህር እንዱወጣ ማድረግ ሲገባው ከባድ በሆነ ቸልተኝነት በባህር ውስጥ ሳይወጣ ለስድስት ሰዓታት በባህር ውስጥ መቆየቱን ፣ በዚህም ምክንያት ከፍተኛ ጉዲት የደረሰበት መሆኑ በባለሙያዎች መረጋገጡን ፣ ተጠሪም ባለበት የመድን ግዳታ መሰረት ለተጎዲው እቃ እና ጥገናውን ለማከናወን አስፈላጊ ከሆኑ ወጪዎች ጋር በድምሩ ብር 253,827.04 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሶስት ሺህ ስምንት መቶ ሃያ ሰባት ብር ከዜሮ አራት ብር) ወጪ አድርጎ ደንበኛውን መካሱን ፣ አመልካች ይህንኑ ገንዘብ እንዱከፍል ቢጠየቅም ኃላፉነትን በማመን ከብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በላይ እንደማይከፍል ማሳወቁን ገልፆ አመልካች ኃላፉነት አለበት ተብል ለክሱ መሰረት የሆነውን ገንዘብና ላልች ወጪዎችን እንዱተካ እንዱወሰንለት ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው።
አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስም የተጠሪ ክስ በሁለት አመት ይርጋ የታገደ መሆኑን በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ያቀረበ ሲሆን በፍሬ ነገር ረገድ ደግሞ አመልካች በውለ መሰረት ጅቡቲ ወደብ እቃውን በማድረስ የማጓጓዝ ግዳታውን የተወጣና ኃላፉነት የላለበት መሆኑን ፣ እቃውን ለማራገፍ ጥቅም ላይ የሚውለውን ክሬን የአመልካች በማስመሰል አመልካችን ኃላፉነት አለበት በማለት ተጠሪ ማቅረቡ አግባብነት የላለው መሆኑን ፣ የክሬኑን ብቃት የማረጋገጥ ኃላፉነት የባለሃብቱ እንጂ የአመልካች አለመሆኑን ፣ አመልካች የላላ ሰው ንብረት ባደረሰው ጉዲት ሉጠይቅ እንደማይችልና ሉጠየቁ የሚገባቸው የጅቡቲ ወደብ አስተዲደርና/ወይም ትራንዚት አገልግልት አ.ማ እና ወይም ፓይድ(PAID) የተባለው ጫኝና አራጋፉ ድርጅት መሆኑን ፣ አመልካች ሉከሰስ አይገባውም እንጂ ኃላፉነት አለበት ቢባል እንኳን ተጠሪ የጠየቀውን ተመዛዛኝ ያልሆነ(non-equivalent) ኪሳራ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም ፣ የቀረበው ገንዘብ መጠንና ማስረጃዎቹ ሕጋዊነት የጎደላቸውና ተቀባይነት የላላቸው ሲሆን ተጠሪ ስራዎችን አጫርቶና አወዲድሮ በአነስተኛ ዋጋ አለማሰራቱ ተገቢ አለመሆኑን ፣ አመልካች ብር 500 ለመክፈል የፃፈው ደብዲቤ ግዳታውን እንዲመነ እንዲማያስቆጥረው መሆኑን ዘርዝሮ ክሱ ወድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ አመልካችን ለክሱ ሃላፉ በማድረግ ለክሱ መሰረት የሆነውን ገንዘብ ብር 253,827.04 ክሱ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ ከሚታሰብ 9% (ዘጠኝ ከመቶ) ወለድ እና ለክሱ ከወጡ የተለያዩ ወጪዎች ጋር እንዱከፍል ሲል ወስኗል።
በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ሙለ በሙለ ፀንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ባጭሩ፡- ክሱ በሁለት አመት ይርጋ የታገደ ከመሆኑም በላይ አመልካች እቃውን ከቻይና ሻይንጋይ ወደብ በማጓጓዝ ጅበቲ ወደብ ማድረሱ ተረጋግጦ እያለና ይህም በውለ ያለውን ግዳታውን መውጣቱን የሚያሳይ ሁኖ እያለ በክሬን ችግር ደረሰ ለተባለው አደጋ ኃላፉ ተብል ውሳኔ መሰጠቱ በባህር ሕግ ቁጥር 138፣196፣197 ስር የተመለከተውን ያላገናዘበ በመሆኑ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም አመልካች ለክሱ ኃላፉነት አለበት ተብል መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪም ጥሪ ተደርጎለት ቀርቦ በፅሐፍ በሰጠው መልስ አመልካች እቃውን ለማስረከብ በውለ ግዳታ ገብቶ እንደውለ ያልፈፀመ መሆኑና በባህር ሕጉ ቁጥር 138፣196 እና 197 ድንጋጌዎች መሰረት ኃላፉቱን ያልተወጣና ኃላፉነቱንም በጽሐፍ ያመነ በመሆኑ ለክሱ ኃላፉ ተብል መወሰኑ የሚነቀፍበት አግባብ የለም በማለት ተከራክሯል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና አመልካችና ተጠሪ በጽሐፍ ያቀረቡት ክርክር በአጭሩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች የተጠሪ ደንበኛ ንብረት የሆነውን የኤላክትሪክ ኃይል ማስተላለፉያ ከቻይና ሻንጋይ ወደብ ጅቡቲ አጓጉዞ ለማድረስ ውል መግባቱንና ጅቡቲ ወደብ ማድረሱን ፣ እንዱሁም ይኸው እቃ ከመርከቡ በመውረድ ላይ እያለ ክሬኑ ተበጥሶ ውሃ ውስጥ ወድቆ የቆየና ጉዲትም የደረሰበት መሆኑን ያልካደው ጉዲይ መሆኑን ነው። አመልካች ከተጠሪ ደንበኛ የማጓጓዣ ሰነድ( Bill of lading) መረከቡም በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠ ጉዲይ መሆኑን ተገንዝበናል። ተጠሪ አመልካች ላይ ክስ ሉመሰርት የቻለው ባለበት የመድን ውል ለደንበኛው በንብረቱ ላይ ለደረሰው ጉዲት ካሳ ከከፈለ በኋላ ገንዘቡ እንዱተካለት ነው። አመልካች አጥብቆ የሚከራከረው ኃላፉነት የለብኝም በማለት ሲሆን ለዚህ በቅድሚያ የሚያቀርበው ክርክር የይርጋ ጊዜ ነው። ይሁን እንጂ በዚህ ረገድ አመልካች ያነሳው ክርክር አመልካቹ ታህሳስ 07 ቀን 1998 ዓ/ም ከፃፈው ደብዲቤ ይዘትና በይርጋው ጊዜ አቆጣጠር ላይ ሉያስከትለው ከሚችለው ውጤት አንፃር ላታይ የሚገባው ነው። በዚህም መሰረት አመልካች ታህሳስ 07 ቀን 1998 ዓ/ም የጻፈው ደብዲቤ ኃላፉነት ያለበት መሆኑን በማመን የኃላፉነት መጠኑ ግን ከብር 500.00(አምስት መቶ ብር ) በላይ ላሆን እንደማይችልና ይህንኑ የገንዘብ መጠን ተጠሪ ከአመልካች የፊይናንስ መመሪያ እንዱወስድ የገለፀ መሆኑን እንዱሚያሳይ ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያላቸው የበታች ፍርድ ቤቶች ያረጋገጡት ጉዲይ ነው። እንዱህ ከሆነ አመልካች እዲውን ማመኑ ተጠሪ ከደንበኛው ካለው ግንኙነት ፣ እንዱሁም አመልካች ከተጠሪ ደንበኛ ካለው ግንኙነት አንፃር በሕጉ የተመለከተው የይርጋ ጊዜ ያልተቋረጠ መሆኑን የባህር ሕግ ቁጥር 203 ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1851 ጋር አዲምሮ በማንበብ የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። በመሆኑን አመልካች ይርጋን መሰረት በማድረግ የሚያቀርብ የኃላፉነት ክርክር ታህሳስ 07 ቀን 1998 ዓ/ም ከፃፈው ደብዲቤ ይዘት አኳያ ሲታይ ተቀባይነት ያለው አይደለም።
ላላው አመልካች አጥብቆ የሚከራከረው የኤላክትሪክ ማስተላለፉያውን ከቻይና ሻንጋይ ወደብ ጅቡቲ አጓጉዞ ለማድረስ ውል የገባና በውለ መሰረትም ጅቡቲ ወደብ ያደረሰ በመሆኑ እቃው ከመርከብ በክሬን ሲወርድ ለደረሰበት የመውድቅ አደጋ ኃላፉነት የለብኝም በሚል ሲሆን ይህንም በምክንያት የሚያስደግፈው ክሬኑ የራሱ ንብረት ያለመሆኑን በመጥቀስ ነው።
በመሰረቱ በባህር ላይ እቃ አመላለሽ ያለበትን ኃላፉነት በተመለከተ የባህር ሕጉ በቁጥር 196 ስር ያስቀመጠ ሲሆን በዚህ ድንጋጌ መሰረት እቃ አመላላሽ ሁለት ዋና ዋና ግዳታዎች አለት።
የዚሁ አንቀጽ ንዐስ ቁጥር አንድ ድንጋጌ አንድን መርከብ በሙለ በመከራየት(ቻርተር ፒርቲ) እቃን የሚያጓጉዝ ባለመርከብ ስላለበት ግዳታ የባህር ሕጉን ቁጥር 138 በማጣቀስ የሚደነግግ ሲሆን የአንቀፁ ንዐስ ቁጥር ሁለት ድንጋጌ ደግሞ በመርከቡ ላይ የተጫኑትን እቃዎች በጥንቃቄና በሚገባ ለመጫን ፣ ለአጠባበቃቸው በሚገባ አቀማመጥ እንዱደረደሩ፣ ስለጉዞዋቸው ፣ ስለ ጥበቃቸው ፣ ስለ መልካም አያያዛቸውና ስለ ማራገፈ መልካም አፈፃፀም ግዳታ ያለበት መሆኑን በአስገዲጅ ሁኔታ ይደነግጋል። በመሆኑም አጓዡ በሕጉ የተጣለበትን እነዚህን ግዳታዎች ካልተወጣ ሃላፉነት ያለበት መሆኑን የድንጋጌው ይዘትና መንፈስ ያስረዲል። በጭነት ማስታወቂያ ደረሰኝ ውስጥ አመላላሹ አላፉነት የለበትም ተብል የተደረገው ውል የማይፀና ስለመሆኑም የባህር ሕግ ቁጥር 205 በግልፅ ይደነግጋል። የአመላላሹ መከላከያ ሉሆኑ የሚችለ ሕጋዊ ምክንያቶች በባህር ሕጉ ቁጥር 197 ስር የተመለከቱት ምክንያቶች ናቸው። ከላይ የተመለከቱት የባህር ሕግ ድንጋጌዎች የአመላላሽን አላፉነት ሉያስከትለና ቀሪ ሉያደርጉ የሚችለ ሕጋዊ ምክንያቶች የሚደነግጉ ሲሆን አላፉነትን በተመለከተ ቀሪ ከሚያደርጉ ምክንያቶች አንደ አመላላሽ እቃውን በአግባቡ ማስረከቡን መረጋገጡ ስለመሆኑም ያስገነዝባለ። የእቃው እርክክብ ተፈጽሟል የሚባለው ደግሞ መቼና በምን ሁኔታ ሲፈጸም እንደሆነም ድንጋጌዎቹ በተለይ ከባህር ሕጉ ቁጥር 180(3) ጋር ተዲምረው ሲነበቡ ያሳያለ። በዚህም መሰረት በጭነት ማስታወቂያ ደረሰኝ የተረጋገጠ የማመላለሻ ውልን የሚመለከቱ ልዩ ድንጋጌዎች የሚጸኑት በተለይ በመርከብ ላይ በተጫኑት የንግድ እቃዎች የጭነት ማስታወቂያ ደረሰኝ ወይም ይህን በመሰለ ላላ አይነት ሰነድ በተረጋገጡ የጭነት ማመላለሻ ውልች ብቻ መሆኑ ፣ የመርከብ መከራየት ውል ሰነድ ባለው ጉዲይ ላይ ተፈጻሚ እንደማይሆን ፣ ነገር ግን መርከቡ የተከራየው በኪራይ ሰነድ(በቻርተር ፒርቲ) የሆነ እንደሆነ የሚሰጠው የጭነት የማስታወቂያ ደረሰኝ ወይም ይህን የመሳሰለው ላላ ሰነድ በአመላላሹና በሰነድ አምጪው መካከል ያለው ግንኙነት ከሚመራበት ጊዜ አንስቶ በዚሁ በሚሰጠው የጭነት ማስታወቂያ ደረሰኝ ላይ ድንጋጌዎቹ ተፈጻሚ እንደሚሆኑ ፣ የሚፀኑትም እቃዎቹ ከመርከብ ላይ ከተጫኑበት አንስቶ እስከሚራገፈበት ጊዜ ብቻ ስለመሆኑ የተጠቀሰው ድንጋጌ ያሳያል። የዚህ አንቀፅ ንዐስ ቁጥር ሶስት በተለይ ሲታይም "…..ከመርከቡ ላይ ከተጫኑበት አንስቶ እስከሚራገፈበት ጊዜ ብቻ ነው።" በሚል በኃይል ቃል ማስቀመጡ አመላላሹ በማራገፍ ሂደት ለሚከሰቱ ጉዲቶቹም ኃላፉነት ያለበት መሆኑን በግልጽ የሚሳይ ነው። ከሁለም በላይ በአመልካችና በተጠሪ ደንበኛ መካከል የተደረገው የማጓጓዣ ውል አንቀፅ 4(1(i) እቃዎቹን ማጓጓዝ ፣ መጫን ፣ ማራገፍ ፣ ማከማቸትና መጋዝን ማስቀመጥ ስራዎች ለላልች ወገኖች በውል አሳልፍ የመስጠት መብት እንዲለው በክርክሩ ሂደት የተረጋገጠ መሆኑ እነዚህ ግዳታዎች የአመልካች ጭምር መሆናቸውን የሚያሳይ ሲሆን ይኸው ውል በአንቀጽ 5(ሀ(i)) ላይም የአጓጓዡን ሃላፉነት ሲዘረዝር እቃዎቹ በባህር ላይ በሚጓጓዙበት ወቅት የአጓጓዡ ኃላፉነት የማራገፈ ስራ እስከተፈፀመ ድረስ እንደሚዘልቅ በግልፅ መደንገጉን ተጠሪ አጥብቆ የሚከራከርበት ነጥብ ሲሆን በአመልካች በኩል የማስተባበያ ክርክር ካለመቅረቡ አንፃር ሲታይ የአመልካች ኃላፉት እቃውን በጥንቃቄ የማራገፍ ግዳታን ሁለ የሚያጠቃልል መሆኑን የሚያስገነዝብ ሁኖ አግኝተናል። በአጠቃላይ አመልካች አጓጓዥነቱንና እቃው ከመርከብ ወደ ውሃ በመውደቅ ጉዲት የደረሰበት መሆኑን ሳይክድ ኃላፉነት የለብኝም በማለት ያቀረበው ክርክር በበቂ ማስረጃና ሕግ ያልተደገፈ መሆኑን በማረጋገጥ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ የሰጠው መሆኑን የተገነዘበን በመሆኑ በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ አልተገኘም። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
No topics extracted.