No summary available.
መጋቢት 19 ቀን 2003 ዓ/ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጎስ ወልደ ዲኜ መላኩ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - ነ/ፈጅ ሰለሞን ፍቅሬ ቀረቡ ተጠሪ፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 418 መሰረት በተያዘ ወይም በተከበረ ንብረት ላይ መብት አለን ባዮች አቤቱታ የሚያቀርቡበትንና አቤቱታው የሚመረመርበትን አግባብ የሚመለከት ነው።
ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች የፍርድ ባለመብት በመሆን ባሁኑ 1ኛ ተጠሪ ላይ በፍርድ ባለእዲነታቸው የአፈፃጸም ማመልከቻ በጉጂ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከአስከፈተ በሁዋላ ነው።የአሁኑ አመልካች በአሁኑ 1ኛ ተጠሪ በፍርድ ያገኘው ገንዘብ እንዱፈፅምለት አቤቱታ አቅርቦና የፍርድ ባለእዲውም ፍርደ የማይፈጸምበትን ምክንያት ያላስረደ በመሆኑ የፍርድ ባለመብት የሆነው አመልካች ከአክሲዮን ማህበሩ ንብረት ንብረቱ ተገምቶ የባለእዲው ድርሻ በጨረታ ተሽጦ ለእዲው ገቢ እንዱሆን አፈፃጸሙን ለያዘው ፍርድ ቤት አመልክቶ አፈፃጸሙ በቀጠለበት ሁኔታ የአሁኑ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ተራ የተጠቀሱት ተጠሪዎች አፈፃጸሙ በአክሲዮን ማህበሩ ሉቀጥል የማይገባበት ምክንያት ዘርዝረው አፈጻጸሙ እንዱቆም ከላይ በተጠቀሰው ስነ ስርዓት መሰረት አቤቱታቸውን አቅርበዋል።የስር ፍርድ ቤት በእነዚህ ተጠሪዎች የቀረበውን ተቃውም ለአመልካችና ለፍርድ ባለእዲ(የአሁኑ 1ኛ ተጠሪ) እንዱደርስ አድርጎአል።አመልካችና የፍርድ ባለእዲም የተቃውሞ አቤቱታ አቅራቢዎች ተቃውሞ ለማቅረብ የሚያስችል መብት ወይም ጥቅም የላላቸው መሆኑንና የተቃውሞ አቤቱታውም የቀረበው የአፈጻጸም ሂደቱን ለማስናከል ስለመሆኑ ጠቅሰው አቤቱታው ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
ጉዲዩ በመጀመሪያ ደረጃ የቀረበለት የጉጂ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የተቃውሞ አቤቱታ አቅራቢ የሆኑት የአሁኑ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ተራ የተጠቀሱት ተጠሪዎች የአክሲዮን ማህበሩ አባል መሆናቸውን መስከረም 18 ቀን 1999 ዓ/ም የማህበሩ አባላት ከአካሄደት ስብሰባ ቃለ ጉባኤ ላይ መረዲት ይቻላል በሚል ምክንያት አመልካችና 1ኛ ተጠሪ ያቀረቡትን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አልፍ በዋናው ጉዲይ ላይ ብይን ሰጥቷል። በዋናው ጉዲይ ላይ የሰጠው ብይንም ሰላም እሸት የተባለ ፊብሪካ በአንድ አባል ድርሻ ምክንያት ሉሸጥ ይችላል ወይስ አይችልም? የሚል ጭብጥ ተይዞ ፊብሪካው የጋራ ንብረት ነው፣የ1ኛ ተጠሪ እዲ የግለ ሁኖ በግለ የሚጠየቅበት እንጂ የማህበሩ አባለት ሁለ የሚጠየቁበት ጉዲይ አይደለም፣ለግለሰብ እዲ ደግሞ መያዝ የሚቻለው የባለእዲውን ድርሻ ብቻ ስለመሆኑ በንግድ ሕጉ ተመለክቷል የሚለትን ምክንያቶችን በመዘርዘር ንብረቱ በጨረታ ሉሸጥ የሚገባው ሁኖ አልተገኘም፣ሆኖም የቀረበው የፊብሪካ ግምት ብር 582,637.20 (አምስት መቶ ሰማኒያ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ሰላሳ ሰባት ብር ከሃያ ሳንቲም) መነሻ ሁኖ ለማህበሩ አባላት ተከፊፍል የፍርድ ባለእዲው በፊብሪካው ያላቸውን ድርሻ የማህበሩ አባላት ለፍርድ ባለመብት ሰጥተው ፊብሪካውን ሉያስቀሩት ይገባል በማለት የጨረታ ሂደቱ እንዱቆም ወስኗል።በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ቢያቀርብም ይግባኙ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞበታል።የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ተጠሪዎች ሕጋዊ የማህበሩ አባላት ናቸው ተብል የተወሰነው ተቀባይነት ባለው ማስረጃ አይደለም፣የማህበሩ አባላት ቁጥርም አራት እንጂ አምስት አይደለም፣የፊብሪካው የመሃንዱስ ግምት መነሻ ተደርጎ የፍርድ ባለእዲ ድርሻን የማህበሩ አባላት ለአመልካች ከፍለው ፊብሪካውን ያስቀሩ ተብል መወሰኑንም የወቅቱን የገበያ ዋጋ ባላገናዘበ መልኩ ከመሆኑም በላይ የአመልካችን ፍርድ ይፈጸምልኝ መብቱን የሚያጣብብ ነው በማለት መከራከሩን የሚያሳይ ነው።አቤቱታው ተመርምሮም ከ2ኛ እስከ 5ኛ ተራ የተጠቀሱት ተጠሪዎች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 418 መሰረት በጉዲዩ ላይ ጣልቃ ገብተው ለመከራከር የሚያስችላቸው መብት አላቸው ተብል መወሰኑ ባግባቡ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለውንና ተያያዥ ነጥቦችን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጓል።በዚህም መሰረት ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው መልሳቸውን በጹሐፍ ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን ለሰበር ችልት ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
በቅድሚያ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ተራ የተጠቀሱት ተጠሪዎች ጠበቃ የአመልካች ክርክር በፍሬ ነገር ላይ የተመሰረተ እንጂ በሕግ ስህተት ላይ ያልተመሰረተ በመሆኑ በሰበር ችልቱ ላታይ የሚገባው አይደለም በማለት ያቀረቡትን ተቃውሞ ተመልክተናል።ይህ ሰበር ችልት በኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80(3(ሀ)) እና በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 መሰረት የተሰጠው ሥልጣን በማናቸውም የመጨረሻ ፍርድ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት መፈፀሙ ሲረጋገጥ ማረም መሆኑ የሚታወቅ ነው።ከእነዚህ ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ መገንዘብ የሚቻለውም ሰበር ችልቱ የፍሬ ነገርና የማስረጃ ምዘና ክርክርን መሰረት ያደረገ ጉዲይ መመልከትና ማረም የማይችል መሆኑን ነው።ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም አመልካች መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል በማለት ክርክር እያቀረበ ያለው ለጉዲዩ የቀረበው ማስረጃ ተቀባይነት የላለው ነው፣የአከራካሪው ንብረት የጋራ ባለሃብቶች እነማን እንደሆኑ በሕጉ አግባብ ላቀርብ የሚችል ማስረጃ አይደለም በሚል እንጂ ማስረጃው ታዓሚነነት የላለው ነው በሚል አይደለም።እንዱህ ከሆነ ለጉዲዩ በሕጉ ተለይቶ የተቀመጠ ማስረጃ መቅረብ ያለመቅረቡና የንብረቱ የጋራ ባለሃብቶች እነማን ናቸው? የሚለው ጥያቄ የማስረጃ ምዘና ሳይሆን በሕገ መንግስቱ ፣በንብረትና በንግድ ሕጎች እንዱሁም ላልች አግባብነት ባላቸው አዋጆች መሰረት ታይቶ ምላሽ የሚያገኝ የሕግ ጥያቄ በመሆኑ በሰበር ችልት የሚታይ ስለሆነ በዚህ ረገድ የቀረበው ተቃውሞ ተቀባይነት ያለው ሁኖ አላገኘነውም።
ወደዋናው ጉዲይ ስንመለስም ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ በቀዲሚነት የተያዘው ጭብጥ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ተራ የተጠቀሱት ተጠሪዎች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 418 መሰረት በጉዲዩ ጣልቃ ገብተው ለመከራከር የሚያስችላቸው መብት አላቸው ሲል የስር የጉጂ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወሰነው ተቀባይነት ያለውን ማስረጃ መሰረት በማድረግ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለው ነው።የስር ፍርድ ቤት በዚህ ረገድ አመልካችና 1ኛ ተጠሪ ያቀረቡትን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያን ውድቅ ያደረገው ተጠሪዎች የማህበሩ አባል ስለመሆናቸው ማህበሩ መስከረም 18 ቀን 1999 ዓ/ም ከአደረገው ስብሰባ ቃለ ጉባኤ ተገንዝቤአለሁ በሚል ምክንያት መሆኑን በውሳኔው ላይ በግልፅ አስፍሯል።አከራካሪው ፊብሪካ በአክሲዮን የተቋቋመ ኃላ.የተ.የግል ማህበር መሆኑ በክርክሩ ሂደት የተረጋገጠ ነው።አክሲዮን ማህበሩ ሲቋቋም ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተራ ከተጠቀሱት ተጠሪዎች ጋር በመሆን አባል የነበሩት አቶ ጸጋዬ ሐጎስ የተባለ ሰው መሆናቸው ያላከራከረ ሲሆን ግራ ቀኙ እየተከራከሩ ያለት የማህበሩ የጋራ ባለሃብቶች ቁጥር፣አቶ ጸጋዬ በማህበሩ ያላቸው የአክሲዮን መጠንና ለ4ኛ እና ለ5ኛ ተጠሪዎች አክሲዮናቸውን ማስተላለፍ አለማስተላለፊቸው እንዱሁም እነዚህ ተጠሪዎች እያንዲንዲቸው ከአቶ ጸጋዬ የገዙት የአክሲዮን መጠን፣ይኸው የአክሲዮን ማስተላለፍ ሁኔታ በሕጉና በማህበሩ መመስረቻ ፁሐፍና መተዲደሪያ ደንብ መሰረት የተከናወነ መሆን ያለመሆኑን ጉዲይ ነው።
በመሰረቱ የአክሲዮን ድርሻ አንድ የተፈጥሮ ወይም ሕግ ወለድ ሰው ካፑታለ አስቀድሞ በታወቀ በአክሲዮን በተከፍፈለና ለዕዲውም ንብረቱ ብቻ ዋስትና በሆነ የአክሲዮን ማህበር ውስጥ ያለትንና በባለቤትነት የያዛቸውን አክሲዮኖች ብዛትና ዋጋ የሚያረጋግጥ ነው። አንድ ባለአክሲዮን በአክሲዮን ማህበሩ ውስጥ በባለቤትነት የያዛቸው አክሲዮኖች የራሣቸው ልዩ ባህሪና ውጤት ያላቸው ግዙፍ ያልሆኑ ሃብቶች ናቸው። በአገራችን ዕውቅና እና ጥበቃ የተሰጣቸው ሁለት አይነት አክሲዮኖች የራሣቸው ልዩ ባህሪና ውጤት ያላቸው እንዲለ የንግድ ሕግ ቁጥር 325 (1) ይደነግጋል።
የመጀመሪያው አይነት አክሲዮኖች ‛ለአምጭው ተብል የተፃፈባቸው አክሲዮኖች ናቸው።
ለአምጭው ተብል የተፃፈበት አክሲዮን እንደማንኛውም ተላላፉ የንግድ ሰነድች ናቸው። ለአምጭው ተብል የተፃፈባቸውን አክሲዮኖች ለላላ ሰው ለማስተላለፍ እንደማንኛውም ተላላፉ የንግድ ሰነድ የአክሲዮን ድርሻ ማረጋገጫ ሰነደን /ሼር ሰርተፉኬቱን/ አሳልፍ በመስጠት ያለአንዲች አይነት አሰራር /ፍርማሉቲ/ ማከናወን እንደሚቻል ከንግድ ሕግ ቁጥር 340(1) ድንጋጌ ለመረዲት ይቻላል።
ሁለተኛዎቹ አይነት አክሲዮኖች የባለአክሲዮኑ ስም የተፃፈባቸው አክሲዮኖች ናቸው።
የባለአክሲዮኑ ስም የተፃፈበቸው አክሲዮኖች እንደማንኛውም ተላላፉ የንግድ ሰነድ የአክሲዮን ድርሻ ማረጋገጫ ሰነደን /ሼር ሰርተፉኬቱን/ አሳልፍ በመስጠት ብቻ ለላላ ሰው ለማስተላለፍ አይቻልም።
ስም የተፃፈባቸውን አክሲዮኖች ለማስተላለፍ አክሲዮኖቹ ለላላ ሰው የተላለፈ መሆኑን በአክሲዮን ማህበሩ ዋና መሥሪያ ቤት በሚገኘው የአክሲዮን መዝገብ ማስመዝገብ አስፈላጊ እንደሆነ ከንግድ ሕግ ቁጥር 341 ንዐስ አንቀፅ 2 ድንጋጌዎች ለመገንዘብ ይቻላል።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስ ክርክር የቀረበበት የንግድ ድርጅት አይነቱ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሲሆን የዚህ አይነት ማህበር አክሲዮኖች ለላላ ሰው የሚተላለፈበት አግባብ በንግድ ሕጉ ከቁጥር 522 እስከ 524 ድረስ ባለት ድንጋጌዎች ተመልክቷል።የን/ሕ/ቁጥር 522 በተለይ ሲታይም የአክሲዮኖቹ መተላለፍ በጹሐፍ የተረጋገጠ መሆን እንዲለበት፣መተላለፈም በአክሲዮኖቹ መዝገብ ላይ ካልተጻፈ በቀር ለማህበሩና ለሶስተኛ ወገኖችን መቃወሚያ ላሆን እንደማይችል በሕጉ በአስገዲጅነት ተደንግጓል።የን/ሕ/ቁጥር 523 በመተዲደሪያ ደንቡ ተቃራኒ ቃል ከላለ በቀር አክሲዮኖች በማህበተኞቹ መካከል ያለገደብ ሉተላላፈ የሚችለ መሆኑን፣አክሲዮን ለባእድ ሰው የሚተላለፍበትን አግባብም የተወሰነ ስለመሆኑ ያሳያል።የዚሁ ድንጋጌ ንዐስ ቁጥር ሶስት ደግሞ ማህበርተኞቹ አክሲዮኑ እንዱተላለፍ የተስማሙበት ውሳኔ በንግድ መዝገብ ላይ እንዱመዘገብ የሚያስፈልግ ስለመሆኑ ኃይለ ቃል ባለው አገላለፅ አስቀምጧል።እንግዱህ በህጉ ረገድ ኃላ.የተ.የግል ማህበር የአክሲዮን ድርሻ የሚተላለፍበት አግባብ በግልፅ ከተቀመጠ የአንድ የማህበሩ አባል የአክሲዮን ድርሻ ለላላ መተላለፍ አለመተላለፈ መረጋገጥ ያለበት በሕጉ የተመለከቱት ሁኔታዎች መሟላታቸውን በሚያሳይ ማስረጃ ነው።በተያዘው ጉዲይ የአቶ ጸጋዬ የአክሲዮን ድርሻ ለ4ኛ እና ለ5ኛ ተጠሪዎች መተላለፈን ያሳያል የተባለው መስከረም 18 ቀን 1999 ዓ/ም የማህበሩ አባላት ያደረጉት ቃለ ጉባኤ ነው።ሆኖም ይኸው ማህበረተኞቹ የተሰማሙበት ውሳኔ በንግድ ሕግ ቁጥር 523(3) አግባብ በንግድ መዝገብ ላይ እንዱመዘገብ የተደረገ መሆን ያለመሆኑን የስር ፍርድ ቤት በተገቢው መንገድ አላረጋገጠም።ከ2ኛ እስከ 5ኛ ተራ የተጠቀሱት ተጠሪዎች የአክሲዮኑ መተላለፍ የማህበሩን መመስረቻ ጹሁፍና መተዲደሪያ ደንብ ባገናዘበ መልኩ የተከናወነ መሆኑን ገልጸው ቢከራከሩም የመስከረም 18 ቀን 1999 ዓ/ም ቃለ ጉባኤ ግን በሕጉ አግባብ እንዱመዘገብ የተደረገ ስለመሆኑ ተረጋግጧል የሚል ክርክር በዚህ ሰበር ችልት በሰጡት መልስ ላይ ያነሱ ሲሆን አመልካች ደግሞ ይህ እውነትነት የላለው መሆኑን ጠቅሶ የመልስ መልስ ሰጥቷል።እንዱህ ከሆነ የስር ፍርድ ቤት ቃለ ጉባኤውን በሕጉ አግባብ የተመዘገ መሆኑን ሳያጣራ ማስረጃነቱን ዋጋ ሰጥቶ ውሳኔ መስጠቱ የፍርድ አካሄደን የተሟላ ባደረገ መልኩ አይደለም።በማህበሩ መተዲደሪያ ደንብ የሚገለጸው እንደተጠበቀ ሁኖ ቃለ ጉባኤው በማስረጃነቱ ሕጋዊ ዋጋ ሉሰጠው የሚችለው በማህበርተኞቹ ስምምነት የተደረሰበት በመሆኑ ብቻ ሳይሆን በንግድ መዝገብ መመዝገቡም በሚገባ ሲረጋገጥ ነው።አንድ ፍርድ ቤት በተከራካሪ ወገኖች የሚቀርበውንና ለጉዲዩ አግባብነት ያለውን ማስረጃ በመቀበል ፍትሒዊ ዲኝነት መስጠት ያለበት መሆኑን በፍትሒ ብሓር ሥነ ሥርዓት ሕጉ ላይ ስለማስረጃ አቀራረብና አቀባብል እንዱሁም ስለፍርድ አሰጣጥ የተመለከቱት ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የሚያስገነዘቡን ሐቅ ሲሆን አግባብነት ያለው ማስረጃ ሳይቀርብና ጉዲዩ በአግባቡ ሳይጣራ የሚሰጠው ውሳኔ የፍርድ አካሄደን የተሟላ የማያደርግና በዲኝነት አሰጣጥ ሥርዓት ተቀባይነት የላለው አካሄድ ነው።በመሆኑም ማስረጃ የማቅረብ ግዳታ የተከራካሪ ወገኖች ሲሆን ለጉዲዩ አግባብነት ያለው ማስረጃ መቅረብን ማረጋገጥና ወደ እውነት መድረስ ደግሞ ፍርድ ቤቱ ራሱ በማስረጃ አቀራረብ ረገድ ተካራካሪ ወገኖችን ማገዝና ተገቢውን ማጣራት ማድረግ ያለበት መሆኑ የዲኝነት አሰጣጥ ስርዓቱ የግድ የሚለው ጉዲይ ነው።ስለሆነም መስከረም 18 ቀን 1999 ዓ/ም የማህበሩ አባለት አደረጉ የተባለው ቃለ ጉባኤ የተመዘገበ መሆን ያለመሆኑ በተገቢው መንገድ ሳይጣራ ቃለ ጉባኤው መኖሩ ብቻ በመረጋገጡ ይኸው የሰነድ ማስረጃ እንዲለ የማስረጃነት ዋጋ በበታች ፍርድ ቤቶች መሰጠቱ በማስረጃ አቀራረብና አቀባበል ረገድ የተፈፀመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ሁኖ አግኝነተናል።በዚህም ምክንያት ይህ ሰነድ ሕጋዊ መሆን ያለመሆኑ በስር ፍርድ ቤት እንደገና ተጣርቶ በዚህ ረገድ አመልካች ያቀረበው መቃወሚያ እንዱታይ ማድረጉ ተገቢ ሁኖ አግኝተናል።
በዚህ ረገድ የስር ፍርድ ቤት አጣርቶ የሚደርሰው ውጤት ከዚህ በፉት የደረሰበትን ድምዲሜ የማያስለውጠው ከሆነ የስር ፍርድ ቤት የፊብሪካውን የመሃንዱስ ግምት መነሻ ተድርጎ በማህበሩ አባላት እንዱከፊፈልና የፍርድ ባለእዲውን ድርሻ የሥር ተቃውሞ አቅራቢ የሆኑ የማህበሩ አባላት ለአመልካች ከፍለው ፊብሪካውን እንዱያስቀሩ ተብል የጨረታው ሂደት እንዱቆም የመደረጉን አግባብነትም ከወዱሁ መመልከቱ አስፈላጊ ሁኖ አግኝተናል።የስር ፍርድ ቤት የፍርድ ባለእዲው አክሲዮን ድርሻ በማህበሩ አባላት ለአመልካች እንዱከፊፈልና ፊብሪካውን እንዱያስቀሩ ብል መወሰኑ ማህበሩ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እንደመሆኑ መጠን ሉቋቋም የሚችለው የመቀራረብና የመተማመን ሁኔታዎች ባላቸው ሰዎች መካከል ነው የሚለው እሳቤ ሲያዝ ከዚሁ የማህበሩ ልዩ ባሕርይ አንፃር ሲታይ ተገቢ ነው ቢባል እንኳ የፊብሪካ ዋጋ ላሆን የሚችለው ግን የመሐንዱሱ ግምት ሳይሆን የወቅቱ የገበያ ዋጋ ነው።በመሆኑም ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር አባል የሆነ የአንድ የማህበር አባል የግል እዲ ከአለበት አክሲዩኑ ለእዲው እንዲይሸጥ የሚከለክል ሕግ የላለ መሆኑ ከን/ሕ/ቁጥር 522፣523 እና 524 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ነው።እነዚህ ድንጋጌዎች ከማህበሩ ልዩ ባሕርይ አንፃር የአንድ የማህበሩ አባል አክሲዮን ሲሸጥ ቅድሚያ መብት ለማህበሩ አባላት እንዱሰጥ ከሚያሳዩ በቀር የማህበሩ አባላት አክሲዩኑን ወይም የማህበሩ ንብረት በመሐንዱስ ግምት መሰረት እንዱያስቀሩት መብት የሚሰጡ አይደለም።የአንድ ንብረት ሕጋዊ ባለቤት መሆኑ የተረጋገጠ ሰው ንብረቱ በእዲ ምክንያት ሲሸጥ የወቅቱን የገበያ ዋጋ እንዲያገኝ የሚደረግበት የሕግ አግባብ የለም።የፍርድ ባለእዲ ንብረት በጨረታ የሚሸጥበት አግባብ በፍትሒ ብሓር ሥነ ሥርኣት ሕጋችን የመደንገጉ አንደ ዓላማም የንብረቱን የገበያ ዋጋን በማረጋገጥ የፍርድ ባለመብትና የፍርድ ባለእዲን መብት ለመጠበቅ ነው።የአንድን ንብረት የመሐንዱስ ግምት እንደትክክለኛ የገበያ ዋጋ መውሰድ የማይቻል ሲሆን በመሐንዱሱ ግምት ብቻ ንብረቱ እንዱሸጥ ማድረግ የንብረቱ ባለቤትን መብት ከማጣበቡም በላይ የንብረቱ ግምት ከፍርድ ባለእዲው ከሚፈለገው ገንዘብ ያነሰ ከሆነ የፍርድ ባለመብትን መብት ጭምር የሚያጣብበት አጋጣሚ ሰፉ እንደሚሆን ይታመናል። በመሆኑም የስር ፍርድ ቤት የፊብሪካውን ግምት መነሻ በአደረገ መልኩ ፊብሪካው ለማህበርተኞቹ እንዱከፊፈልና የፍርድ ባለእዲውን ድርሻ ተጠሪዎች ከፍለው ፊብሪካውን ያስቀሩ በማለት የደረሰበት ድምዲሜም ሕጋዊ መሰረት የላለው ነው።በአጠቃላይ ከላይ በተመለከቱት ዝርዝር ምክንያቶች በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በጉጂ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ የካቲት 26 ቀን 2002 ዓ/ም ተሰጥቶ በኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ መጋቢት 21 ቀን 2002 ዓ/ም በትእዛዝ የፀናው ብይን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
ክርክር ያስነሳው ማህበር አባላቱ ስንት እንደሆኑ፣እንያንዲንደ አባል ያለውን የአክሲዮን ብዛት፣4ኛ እና 5ኛ ተጠሪዎች የማህበሩ አባል መሆን ያለመሆናቸውን፣በሕጉ አግባብ ተቀባይነት ያለው ቃለ ጉባኤ መኖር ያለመኖሩን(የ
No topics extracted.