No summary available.
ታህሳስ 12 ቀን 2003ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጎስ ወልደ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ ነ/ፈጅ ፅዮን በላይ ቀረቡ ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትና የከፍተኛው ፍ/ቤት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ስላመለከቱ ነው። የክርክሩ ፍሬ ጉዲይ በባህር ላይ እቃ ሲጓጓዝ ለደረሰ ጉዲት የካሳ አከፊፈልን የሚመለከት ነው። አመልካች ተጠሪ የደንበኛቸው ንብረት የሆነና የመድን ሽፊን የሰጠባቸውን ሀምሳ ሳጥን መስታወት ከቻይና በመጫን ጅቡቲ ወደብ ለማድረስ በተዋዋለው ውል መሰረት ጅቡቲ ወደብ ካደረሳቸው አምሳ ሳጥን መስታወት ውስጥ አስር ሳጥን መታወት ላይ በአኗኗር ችግር ምክንያት ጉዲት ደርሶበታል። እኔ ለደንበኛያ የመስታወቱን ዋጋ ብር 101,465 /አንድ መቶ አንድ ሺህ አራት መቶ ስልሳ አምስት ብር/ የከፈልኩ በመሆኑ ይህንን ገንዘብ ተከሳሽ /የአሁን ተጠሪ/ እንዱተካ ውሳኔ ይሰጥልኝ ለማለት ክስ አቅርበዋል። ተጠሪ የእቃዋቹን ደህንነት በማረጋገጥ ያልጫንኩ በመሆኑ ሐላፉነት የለብኝም። ለእቃዎቹ ጉዲት ሐላፉ ነህ የምባል ከሆነ የእቃዎቹ ዋጋ ስለማይታወቅ በጥቅል ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ ታስቦ እንዱከፈለው ይወሰንልን በማለት ተከራክሯል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በእቃው ላይ ጉዲት የደረሰው በኮንቴነሩ ላይ በተደረገው ደካማ አያያዝ በመሆኑን በሰርቬይ ሪፕርት የተረጋገጠ በመሆኑ ተከሳሽ /ተጠሪ/ በእቃዎቹ ላይ ለደረሰው ጉዲት ሐላፉነት አለበት በማለት ውሳኔ ሰጥቷል። የካሳውን መጠን በተመለከተ የእቃው ዋጋ ያልታወቀ በመሆኑ በባህር ህግ አንቀጽ 198 ንዐስ አንቀጽ 1 መሰረት ለአንድ ሳጥን ብር 500 /አምስት መቶ ብር ሑሳብ ለአስሩ ብር 5000 /አምስት ሺህ ብር/ ተጠሪ ለአመልካች ይክፈል በማለት ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለከፍተኛው ፍ/ቤት አቅርበዋል። የከፍተኛው ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የስር ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ አጽንቷል። አመልካች የካቲት 8 ቀን 2002ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ የአመልካች ደንበኛ ለተጠሪ የጭነት ትዕዛዝ የሰጠው የእቃውን ትክክለኛ ዋጋ፣ ከባንክ "በላትር ኦፍ ክሬዱት" ክፍያ የተፈፀሙትን ሰነድ በመግለጽና ሰነድን በማያያዝ ነው። ለመስተዋቱ 21,499.94 የአሜሪካን ድላር የተከፈለ መሆኑን ተጠሪ ያውቃል። ተጠሪም በሰጡት ቢል ኦፍ ላዱንግ የኤል ሲ ቁጥር /L/C No.NIB /HGB/ 044/2007/ ክፍያ የተፈፀመበት እቃ መሆኑን ገልጿል። በመሆኑም ተጠሪ እቃውን ሲጭኑ በባንክ በኩል በተከፈተ "ኤል ሲ" ለእያንዲንደ መስተዋት ምን ያህል የውጭ ምንዛሬ እንደተከፈለት ያውቅ ስለነበር ለጉዲዩ አግባብነት ያለው የባህር ህግ 198 ንዐስ አንቀጽ 3 ሆኖ እያለ የበታች ፍርድ ቤቶች የባህር ህግ ቁጥር 198 ንዐስ አንቀጽ 2ን በመጥቀስ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልን በማለት አመልክተዋል። ተጠሪ በበኩላቸው የአመልካች ደንበኛና የእኛ ግንኙነት በባህር ላይ እቃ ማጓጓዥን የሚመለከት ነው። የበታች ፍ/ቤቶች የባህር ህጉን መሰረት በማድረግ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት መልስ ሰጥቷል።
ከስር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም መዝገቡን መርምረናል። መዝገቡን እንደመረመርነው የአመልካች ደንበኛ ለተጠሪ የሚጭነው እቃ በውጭ ምንዛሬ በባንክ በኩል ክፍያ የተፈፀመበትን የኤል.ሲ ድክመንት የሰጠውና ተጠሪም ለአመልካች ደንበኛ በሰጠው የባህር እቃ መጫኛ ሰነድ /ቢል ኦፍ ላዱንግ/ ለእቃዎቹ በባንክ በኩል ክፍያ የተፈፀመበትን የኤል. ሲ ቁጥር ማለትም /L/C No.NIB /HGB/ 044/2007/ የጠቀሰ መሆኑን አመልካች በሰበር አቤቱታው የገለፀ ሲሆን ተጠሪ ለአመልካች የሰጠሁት /ቢል ኦፍ ሉዱንግ/ ለእቃው የአመልካች ደንበኛ በንብ ባንክ በኩል የውጭ ምንዛሬ የከፈለበትን "ላተር ኦፍ ክሬዱት" ቁጥር አይጠቅስም፣ የባንክ ላተር ኦፍ ክሬዱት ሰነድ ከጭነት ማዘዣው ጋር አልተሰጠንም የሚል መልስ አላቀረበም። ይህም የአመልካች ደንበኛ በንብ ባንክ በኩል ለእቃዎቹ በውጭ ምንዛሬ የከፈልኩትን የላተር ኦፍ ክሬዱት ለተጠሪ የቀረበለት መሆኑን እንዲመነ የሚያስቆጥረው መሆኑ በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት 234 ንዐስ አንቀጽ 1 /ሰ/ የተደነገገ በመሆኑ ተጠሪ የአመልካች ደንበኛ የሆነውን አምሳ ሳጥን መስታዎት ስጭን የእያንዲንደ ሳጥን መስታወት ዋጋ በነጠላና የእቃው ዋጋ በጥቅል ስለማላውቀው ለእቃው መክፈል የሚገባኝ ካሳ በጥቅል ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ መሆን ይገባዋል በማለት የሚያቀርበው ክርክር ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም።
የአመልካች ደንበኛ በተጠሪ የጭነት ትዕዛዝ ለሰጠበት እቃ የተከፈለው ዋጋ በውጭ ምንዛሬና በንብ ባንክ በኩል በተከፈተ ላተር ኦፈ ክሬዱት እንደሆነ ይህንንም ተጠሪ በቢል ኦፍ ላዱንግ ላይ የገለፀ መሆኑ ያልተስተባበለና ያልተካደ ፍሬ ጉዲይ ነው። ለእቃው በባንክ በኩል በውጭ ምንዛሬ ክፍያ የተፈፀመበትን ሰነድ ተጠሪ የማያውቀውና በባህር ማጓጓዥያ ሰነድ ላይ የባንኩን "ላተር ኦፍ ክሬዱት ቁጥር" የተገለፀው ከሆነ የባህር ህግ አንቀጽ 198 ንዐስ አንቀጽ 1 ለጉዲዩ አግባብነትና ተፈፃሚነት ያለው ድንጋጌ አይደለም። ለዚህ ጉዲይ አግባብነትና ተፈፃሚነት ያለው ድንጋጌ በባህር ህግ አንቀጽ 198 ንዐስ አንቀጽ 3 ድንጋጌ ነው። በመሆኑም የስር ፍ/ቤት ተጠሪ ለእቃዎቹ በንብ ባንክ በኩል በተከፈተ "ላተር ኦፍ ክሬዱት" የተከፈለውን የውጭ ምንዛሬ ክፍያ አውቆና "የላተር ኦፍ ክሬዱቱን" ቁጥር ለአመልካች ደንበኛ በሰጠው "ቢል ኦፍ ሉዱንግ" የእቃ መጫኛ ሰነድ ገልጾ እያለ የባህር ህግ ቁጥር 198 ንዐስ አንቀጽ 1ን በመጥቀስ የእቃው ዋጋ ስለማይታወቅ የአንድ ሳጥን መስታዎት ዋጋ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ ሑሳብ ተጠሪ ለአመልካች ብር 5000 /አምስት ሺህ ብር/ ይክፈል በማለት የሰጠውን ውሳኔና ከፍተኛው ፍ/ቤት ሳያርም ማጽናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትና የከፍተኛው ፍ/ቤት ውሳኔ ተሽሯል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአመልካች ደንበኛ በንብ ባንክ በኩል በከፈቱት "ላተር ኦፍ ክሬዱት" በእቃዎቹ የከፈለትን ዋጋ በማጣራትና ላልች አግባብነት ያላቸውን ማስረጃዎች አስቀርቦ በመመርመር ተጠሪ ለአመልካች ሉከፈለው የሚገባውን የካሳ መጠን እንዱወስን ጉዲዩን በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 343/1/ መሰረት መልሰን ልከንለታል።
በዚህ ፍ/ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሳራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.