No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 55ዐ77 ኀዲር 28 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ሥላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ጥሩወርቅ ዘገኑ - ጠበቃ አቶ በጋሻው ኃ/ገብርኤል ቀረቡ።
ተጠሪ፡- አቶ ግደይ አብርሃ - ጠበቃ አቶ ተስፊዬ ወረደ - ቀረቡ።
መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን፣ መርምረን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዲይ በቼክ ምክንያት የተነሣን ክርክር የሚመለከት ሆኖ ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቼክ ቼኩን ለመስጠት ምክንያት ከሆነውና ግራ ቀኙ የካቲት ዐ9 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. ካደረጉት ውል አንፃር ተገናዝቦ ላታይ የሚገባው ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን አከራካሪ ነጥብ በመለየት የሥር ፍ/ቤት የሰጡትን ዲኝነት አግባብነት ለማየት ሲባል የቀረበ ነው።
ምንም እንኳ የአሁን አመልካች በሰበር አቤቱታቸው ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ በዋስትና በተሰጠውና ፊርማው የእኔ ባልሆነ ቼክ በሚል እንደ አዱስ የፍሬ ነገር ክርክር ያቅረቡ እንጂ ይኸው ቼክ በእርሳቸው ለተጠሪ የተሰጠ ስለመሆኑ ከሥር ፍ/ቤት ጀምሮ የተደረገው ክርክርና የሥር ፍ/ቤቶች ውሣኔ አስረጅ ናቸው።
ሆኖም ለቼኩ ምክንያት የሆነው ግራ ቀኙ የካቲት ዐ9 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. ከግንባታ ሥራ ጋር በተያያዘ ያደረጉት ስምምነት ስለመሆኑ በግራ ቀኙ የተካደ ጉዲይ አይደለም።
አከራካሪ የሆነውና የሥር ፍ/ቤቶችን ዲኝነት አግባብነት ለማየት ያስፈለገው ቼኩ በክፍያ ሰነድነቱ ብቻ ተለይቶ የሚታይ ነው ወይስ ለቼኩ መሰጠት መነሻ ከሆነው የግራ ቀኙ ስምምነት ጋር የሚለውን ከንግድ ሕግ ቁጥር 717 አንፃር ለማየት በሚል ነው።
ይህንን ጉዲይ በሚመለከት የሥር ፍ/ቤት መመርመር ሳያስፈልገው ቼኩ በላዩ ላይ የያዘውን የገንዘብ መጠን እና ከቼኩ መስጠት በኋላ አመልካች በተለያየ ጊዜ የፈፀሙትን ክፍያ አቀናንሶ ቀሪውን ብር 18ዐ,ዐዐዐ.00 /አንድ መቶ ሰማንያ ሺህ/ ብር ከህጋዊ ወለድ ጋር አመልካች ይክፈለ ሲል ወስኗል።
ሆኖም ለዚህ ቼክ ምክንያት የሆነው የግራ ቀኙ ያደረጉት ውል መሆኑን የአሁን አመልካች በመከላከያነት ያቀረቡት ሲሆን ተጠሪ ይህንኑ የካደት አይደለም ይህም ከሆነ ከቼኩ በስተጀርባ ያለው የስምምነት ጉዲይ ከቼኩ ጋር ተገናዝቦ ላታይ የሚገባው ሆኖ ሳለ የሥር ፍ/ቤት በቼኩ ላይ ብቻ ተወስኖ የሰጠው ዲኝነት በንግድ ሕግ ቁጥር 717 የተመለከተውን ድንጋጌ መሰረት ያደረገ አለመሆኑን ተገንዝበናል።
በዚሁ መሰረት የተሰጠው ዲኝነት አግባብ አለመሆኑን ጠቅሰው ቼኩ ከውለ ጋር ተጣቅሶ ላታይ ይገባዋል የሚለውን ክርክር በሚመለከት አመልካች ቼኩ የተሰጠው ተጠሪ እንደውለ ግዳታውን የሚፈጽሙ መሆኑን ታሳቢ በማድረግ ነው። ነገር ግን ተጠሪ በውለ መሰረት ግዳታቸውን አልተወጡም፣ ሥራው ግድፈት አለበት ይህንኑ ከግንባታ ፈቃድ ውጭ የሚለውን አላስተካከለም በማለት ያቀረብኩት ሳይታይልኝ ታልፎል በማለት ላቀረቡት ክርክር ተጠሪ በተራው በውለ መሰረት የግንባታ ሥራው ተፈጽሞ የአማካሪ መሐንዱሱ ባለበት በ22/6/2ዐዐ2 አመልካች ፈርመው ተረክበዋል። ለዚህም በማስረጃነት ሰነደ ቀርቧል በማለት መልስ ሲሰጥ አመልካች ለዚሁ ማስተባበያ የሚሆን የፍሬ ነገር ክርክር ኀዲር 28 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም. የተፃፈ የመልስ ልስ ያቀረቡ ሲሆን የክርክሩ ይዘት ቼኩ ዋጋ እንዲይኖረው የሚያደርግ ሆኖ አላገኘነውም። እንደ አባባላቸው ከሆነም እንደውለ ባለመፈፀሙ ምክንያት እራሱን የቻለ አቤቱታ እንዱያቀርቡ ከሚረዲ በቀር ክርክር ያስነሳውን የቼክ ጉዲይ ከንግድ ሕግ ቁጥር 717 አንፃር እንዱታይ በማድረግ በዚህ ነጥብ ላይ በሥር ፍ/ቤት ታይቶ ውሣኔ እንዱሰጥበት ለማድረግ የሚያበቃ ክርክር አይደለም። ይኸው ጉዲይ ተጣርቶ እንዱወሰን ወደ ሥር ፍ/ቤት ለመመለስ የሚቻልበት ምክንያት ካልተገኘ ደግሞ የሥር ፍ/ቤት ይህንኑ ማጣራት ሳያስፈልገው በቼኩ ላይ ተመርኩዞ ውሣኔ መስጠቱ ከውጤት አንፃር የሕግ ስህተት ፈጽሟል ለማለት የሚያስችል አይደለም። ይህንን ሁለ በማየት የሚከተለውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት እና የከፍተኛው ፍ/ቤት እንደቅደም ተከተለ በኮ/መ/ቁ. 144516 በ28/9/2ዐዐ1 ዓ.ም. እና በመ/ቁ. 85254 የካቲት 24 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. የሰጡትን ፍርድ እና ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት አጽንተናል።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተቀባይነት ያለው ነው ብለናል።
የዚህ ክርክር ሁኔታ እስከሚታወቅ ድረስ የሰበር መ/ቁ. 55ዐ77 አፈፃፀሙ ታግድ እንዱቆይ በሚል ተሰጥቶ የነበረው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል፤ ይፃፍ።
No topics extracted.
ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ።