No summary available.
ጥቅምት 17 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡-
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ስላመለከቱ ነው። ክርክሩ የአክሲዮን ድርሻን የሚመለከት ነው።ተጠሪ 148,ዐዐዐ /አንድ መቶ አርባ ስምንት ሺህ ብር/ ዋጋ ያለው አክሲዮን ባለቤት እንዲልሆንኩ የወሰኑበት ውሣኔ ተሰርዞ የአክሲዮን ባለመብት መሆኔ ይወሰንልኝ በማለት ክስ አቅርቧል። አመልካች ይህንን ገንዘብ ተጠሪ በአይነት ወይም በገንዘብ ገቢ አላደረገም በማለት ተከራክረዋል። የሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ ብር 1ዐዐ,ዐዐዐ, የከፈለ መሆኑ በመመሥረቻ ጽሐፍ የተገለፀ ሲሆን ብር 95,ዐዐዐ የከፈለ ስለመሆኑ ደግሞ ለሲ ኮላጅ አክስዮን ማህበር የሰጣቸው ማስረጃ ቀርቧል። ይህንን ድርሻ በቃለ ጉባዔ እንዲልተከፈለ ለመቀየር መሞከራቸው ሕጋዊ ውጤት የለውም በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
አመልካች ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅርበዋል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ተጠሪ የአክሲዮን ማህበሩ ሲቋቋም ከጠቅላላ ካፑታል ብር 1ዐዐ,ዐዐዐ ከዚያ በኋላ ብር 95,ዐዐዐ መክፈላቸው ተረጋግጧል። ይህንን መብት ለማሻሻል የተሰጠው ውሣኔ የሕግ መሰረት የለውም በማለት የሥር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ አጽንቶታል።
አመልካች ተጠሪ ክስ ያቀረበው ውሣኔ ከተላለፈ በኋላ አንድ ዓመት አሣልፍ ነው። እኛ ያነሣነውን የይርጋ መቃወሚያ አላግባብ ውድቅ ተደርጎብናል። ስለዚህ የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ እንዱሻርልን በማለት አመልክተዋል።
ተጠሪ በበኩለ የአክሲዮን ማህበር ቃለ ጉባዔ ጉዲዩን በአጀንዲነት ይዞ ያስተላለፈው ውሣኔ የለም።
የእኔን አክሲዮን ድርሻ ዝቅ አድርጎ በቃለ ጉባዔው መመዝገቡ የሚያስከትለው ሕጋዊ ውጤት የለም የበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት መልስ ሰጥቷል።
የአመልካችን የይርጋ መቃወሚያ በተመለከተም የራሱን የመከራከሪያ ነጥብ አቅርቧል። አመልካች የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከስር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው የግራ ቀኙ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም መዝገቡን መርምረናል። መዝገቡን እንደመረመርነው አመልካች ለመመሥረቻ ጽሐፍና በአክሲዮን ሼር ሰርቲፉኬት የተገኘውን መብት በማስመልከት ዝቅ ለማድረግ የአክሲዮን ማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ የተሰጠው ውሣኔ በአንድ ዓመት ይርጋ ይገደባል በማለት ያቀረቡትን ክርክር የበታች ፍርድ ቤቶች ያለፈት በመዝገቡ ዋና የመከራከሪያ ጭብጥ የሆነውን ነጥብ አጠቃላይ ባህሪና የንግድ ሕግ ቁጥር 359/1/ ድንጋጌ ይዘት መንፈስና ዓለማ በማገናዘብ መሆኑን ለመረዲት ችለናል።
ተጠሪ በዚህ መዝገብ ያቀረቡት ክስ የባለአክስዮኖች ጉባዔ የሰጠው ቃለ ጉባዔ እንዱሻሻልን ወይም ቀሪ እንዱሆን ሣይሆን በመሰረታዊነት የአክሲዮን ማህበሩ መሥራችነታቸውና ለአክሲዮን ማህበሩ በተረጋገጠ ማስረጃ ክፍያ የፈፀሙባቸው የአክሲዮን ድርሻ የሚጎዲ ተግባር ባአክሲዮን ማህበሩ እየተፈፀመ ስለሆነ ይህንን መብታቸውን ለማስከበር ነው። በዚህ መንገድ የሚቀርብ ክስ በንግድ ሕግ ቁጥር 416/2/ የሚሸፈንና ቀሪ የሚሆን አይደለም በማለት የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠው የሕግ ትርጉምና ውሣኔ ተገቢ ሆኖ ስላገኘነው በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348/1/ መሰረት አጽንተነዋል።
ው ሣ ኔ
የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት የተሰጠው የእግድ ትእዛዝ ተነስቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት የወጣውን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሣቸው ይቻለ።
No topics extracted.