No summary available.
ጥቅምት 4 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢትዮጵያ መድህን ድርጅት - ጽጌረዲ ተሻገር ቀረበች ተጠሪዎች፡-
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፍዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ በማጽናት በመ.ቁ. 65456 ግንቦት 17 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በሰጠው ውሣኔ ላይ ነው።
ጉዲዩ 1ኛ ተጠሪ ያለበትን የብር 1ዐ7,44ዐ ዕዲ ለመክፈል እንዱያስችለው በ2ኛ ተጠሪ አማካይነት የቃል ኪዲን ሰነድ ፈርሞ ቢሰጠኝም በገባው ቃል መሰረት አልከፈለኝም በማለት አመልካች የመሰረተውን ክስ መነሻ ያደረገውን ክርክር የሚመለከት ነው። 2ቱም ተጠሪዎች ባልተነጣጠለ ኃላፉነት ዕዲውን እንዱከፍለ ወይም ፍ/ቤቱ ኃላፉነቱ የማን እንደሆነ ለይቶ ገንዘቡ እንዱከፈለው እንዱወስንለት ሰለመጠየቁም ከመዝገቡ ተመልክተናል። ተጠሪዎችም ለክሱ በሰጡት መልስ ክሱ በይርጋ ቀሪ ሆኖአል። በውክልና ሰነደ ላይ ያለው ፊርማ የ2ኛ ተጠሪ አይደለም። ስለዚህ በቀረበው ክስ በኋላፉነት ልንጠየቅ አይገባም በማለት በጋራ ሲከራከሩ፤ 2ኛ ተጠሪ ደግሞ በተለይ ባቀረበው ክርክር በውክልና ሰርተሃል እየተባልኩ ለገንዘቡ አከፊፈል ተጠያቂ የምሆንበት ምክንያት የለም ብልአል። ከዚህ በኋላ ፍ/ቤቱ 2ኛ ተከሣሽ ፊርማውን በመካደ ፊርማው እንዱመረመር ቢታዘዝም፤
ከሣሽ ዋናውን ሰነድ ሉያቀርብ አልቻለም የሚል ምክንያት በመስጠት ክሱን ውድቅ አድርጎአል።
ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም በበኩለ ክርክሩን የሰማ ሲሆን፣ በመጨረሻም ይግባኝ የተባለበትን ውሣኔ አጽንቶአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
አመልካች ነሐሴ 4 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በፃፈው ማመልከቻ በሥር ፍ/ቤቶች የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል የሚልበትን ምክንያት በመግለጽ አቤቱታውን አቅርቦአል።
በበኩላችንም ይህን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪዎችን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል።
አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተደረገው አመልካች ዋናውን የውክልና ሰነድ አላቀረበም በማለት ክሱ ውድቅ የመደረጉን አግባብነት ለመመርመር ነው። በልላም በኩል ተጠሪዎች ክሱ በይርጋ ቀሪ ሆኖ እያለ መቃወሚያችን ውድቅ በመደረጉ በሕጉ አተረጓጏም መሰረታዊ ስህተት ተፈጽሞአል በማለት መስቀልኛ አቤቱታ በማቅረባቸው በዚህ ረገድም የግራ ቀኝ ወገኖችን ክርክር ሰምተናል። በመቀጠልም ክርክሩን አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ተጠሪዎች ክሱ በይርጋ ቀሪ ሆኖአል በማለት አቅርበውት የነበረው መቃወሚያ የሥር ፍ/ቤቶች ያልተቀበለት ቢሆንም፤ተጠሪዎች ግን መቃወሚያው ውድቅ የተደረገው ከሕጉ ውጪ ነው በማለት እየተከራከሩ ነው። የሥር ፍ/ቤቶች ለጉዲዩ አግባብነት የላለውን የንግድ ሕግ ድንጋጌ መሰረት አድርገው ወስነዋል የሚል የመከራከሪያ ነጥብም አንስተዋል። አመልካች ደግሞ ለጉዲዩ አግባብነት ያለው ድንጋጌ የንግድ ሕግ ቁ. 817/1/ ነው። በዚህ ድንጋጌ የተወሰነው የክስ ማቅረቢያ ጊዜ ሦስት ዓመት ሲሆን ክሱ የቀረበው ደግሞ ይህ ጊዜ ከማለፈ በፉት በመሆኑ የተጠሪዎች የይርጋ መቃወሚያ ውድቅ መደረጉ በአግባቡ ነው በማለት ተከራክሮአል።
ለክሱ መነሻ የሆነው የቃል ኪዲን ሰነድ ተፈርሞ በተሰጠበት ጊዜ እና ክሱ በቀረበበት ጊዜ መሐል ያለው ጊዜ ሲታይ የሦስት ዓመት ጊዜ አለማለፈ እርግጥ ነው። አከራካሪ የሆነው የይርጋው መቃወሚያ ለመወሰን ተገቢ የሆነው ድንጋጌ የትኛው ነው? የሚለው ነጥብ ነው። የተስፊ /ለመክፈል ቃል የሚሰጥበት/ ወረቀትን ወይም ሰነድን በሚመለከት በንግድ ሕጉ አራተኛ መጽሐፍ በአንቀጽ 2 ሥር ያለት ድንጋጌዎች አግባብነት እንደሚኖራቸው በንግድ ሕግ ቁ. 825 በመመልከቱ ተጠሪዎች ወደ ቁ. 817 በመሄድ እና አግባብነት ያለው ድንጋጌ ንዐስ ቁ. /2/ እንደሆነ በመግለጽ ተከራክረዋል። ለዚህ ክርክራቸው ምክንያት ያደረጉት የሰነደ አውጪ ነን፤ በሰነደ አውጪ ላይ የሚቀርበውን ክስ በሚመለከት ግልጽ ድንጋጌ ያለው በንዐስ ቁ. /2/ ላይ ነው የሚል ነው።
ለተያዘው የይርጋ ክርክር አወሳሰን ተገቢነት አለው በማለት በግራ ቀኝ ወገኖች የተጠቀሰው የንግድ ሕግ ቁ. 817 የሃዋላ ወረቀትን መሰረት በማድረግ የሚቀርበው ክስ በይርጋ ቀሪ ስለሚሆንበት ሁኔታ የሚደነግግ ነው። ንዐስ ቁ. /1/ ክሱ በሦስት ዓመት ይርጋ ቀሪ እንደሚሆን ሲያመለክት፤ ንኡስ ቁ. /2/ ደግሞ ክሱ በአንድ ዓመት ይርጋ ቀሪ እንደሚሆን ያመለክታል። እዚህ ላይ በጥንቃቄ መታየት ያለበት የጊዜዎቹ መርዘም ወይም ማጠር ሣይሆን፣ በሁለቱ ድንጋጌዎች /ንኡስ ቁጥሮች/ መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው? የሚለው ነው። የመጀመሪያው ክሱ በእሺ ባዩ ላይ የሚቀርብ እንደሆነ ገልጾ መቅረብ ያለበት ከመክፈያው ቀን አንሰቶ በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደሆነ ያመለክታል። ሁለተኛው ማለትም ንኡስ ቁ. /2/ ደግሞ ክሱ የሚቀርበው በጀርባ በፈረሙ ሰዎችና በአውጪ ላይ መሆኑን በአንድ በኩል ሲገለጽ፤ በልላ በኩል ደግሞ የሐዋላ ወረቀቱ / ሰነደ/ በሚገባው ጊዜ እንቢታ ማስታወቂያ የተደረገበት ወይም ‛ያለኪሣራ የሚመለስ“ የሚል ቃል ያለበት እንደሆነ ያመለክታል። እነዚህ በንኡስ ቁ./2/ የተጨመሩ ሁኔታዎች በንኡስ ቁ./1/ የለም።
No topics extracted.
ወደያዝነው ጉዲይ ስንመለስ ተጠሪዎች የተከሰሱት የሰነደ አውጪ በመሆናቸው እንደሆነ ግልጽ ነው። በዚህ ሰነድ መሰረት ግንኙነት የተፈጠረው በተጠሪዎች እና በአመልካች መካከል ብቻ እንደሆነ ግን ልብ ልባል ይገባል። በሰነደ የተመለከተውን ገንዘብ ለመክፈል“እሺ“ ባዮች ተጠሪዎች እንደሆኑም መታወቅ አለበት። በሰነደ ላይ በንግድ ሕግ ቁ. 817/2/ የተመለከቱት ሁኔታዎች አለበት አልተባለም። በመሆኑም ተጠሪዎች ከእነሱ ውጪ ላላ ሰው ያለ ይመስል የይርጋ መቃወሚያችን መታየት ያለበት በንኡስ ቁ./2/ መሰረት ነው በማለት መከራከራቸው አግባብ አይደለም። በመሆኑም ክሱ የቀረበው በይርጋ ቀሪ ከሆነ በኋላ ነው በማለት ያቀረቡት መቃወሚያ በሥር ፍ/ቤቶች ውድቅ መደረጉ በአግባቡ ነው ብለናል።
በመቀጠል የተመለከትነው አመልካች ባቀረበው አቤቱታ መነሻነት የተያዘውን ጭብጥ ነው።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአመልካችን ክስ ውድቅ ያደረገው በ2ኛ ተጠሪ የተካደው በውክልና ማስረጃ ላይ ያለውን ፊርማ ለማስመርመር አመልካች ዋናውን የውክልና ሰነድ ለማቅረብ አልቻለም በማለት ነው። እንደሚታወቀው የውክልና ማረጋገጫ ሰነድ የሚመለከተው ወካዩንና ተወካይን ብቻ ነው። አመልካች በዚህ ጉዲይ ወካይም ተወካይም አይደለም። በመሆኑም የውክልናው ሰነድ ዋናውን አቅርብ ልባል የሚገባው ወካይ ወይም ተወካይ እንጂ ሦስተኛ ወገን የሆነውን አመልካችን አይደለም። በሥር ፍ/ቤት ከተደረገው ክርክር ይዘት መገንዘብ እንደቻልነው ፍ/ቤቱ የውክልናውን ዋና ሰነድ አመልካች ማቅረብ አልቻለም ከማለት አልፍ ውክልናውን አረጋግጦ ሰነደን ከሰጠው የመንግሥት መሥሪያ ቤት በተጠሪዎች መካከል የውክልና ግንኙነት የለም የሚል ማረጋገጫ አላገኘም። ይልቁንም ዋናው የውክልና ሰነደ የሚገኘው በተጠሪዎች ዘንድ እንደሆነ የሚመለከተው መንግሥታዊ አካል እንደገለፀለት በአመልካች ክርክር ተመልክቶ እያለ ይህንኑ በዝምታ ማለፈን ነው የተገነዘብነው ከሁለ በላይ ደገሞ ተጠሪዎች ዋናውን ሰነድ በማቅረብ የማስረዲት ሸክማቸውን ሣይወጡ የማስረዲት ሸክሙን ወደአመልካች በማዞር ወደብይን በማምራቱ በሕጉ አተገባበር ረገድ መሰረታዊ ስህተት መፈፀሙን ነው መገንዘብ የቻልነው። ስለዚህም ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ 1/ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ. 7593ዐ ታህሣሥ 22 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ. 65456 ግንቦት 17 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
2/ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአመልካችን ክስ ውድቅ ያደረገው ተጠሪዎች የውክልና ስልጣኑን በተመለከተ የማስረዲት ሸክማቸውን ባልተወጡበት ሁኔታ መሆኑን ተገንዝቦ ወደ ክሱ ሥረ- ነገር በመግባት ተጠሪዎች ክስ የቀረበበትን ገንዘብ የማይከፍለበት አግባብ አለ ወይስ የለም በሚለው ጭብጥ ላይ ግራ ቀኝ ወገኖች ካከራከረ በኋላ ተገቢውን ይወሰን ዘንድ ጉዲዩ ይመለስለት ብለናል።