No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 4ዐ173 ጥቅምት 5 ቀን 2ዐዐ3 ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ተሻገር ገ/ሥላሴ አብደራሂም አህመድ ብርሃኑ አመነው ሡልጣን አባተማም አመልካች፡- አምባሰል የንግድ ሥራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር የቀረበ የለም ተጠሪ፡- አቶ አብደልቃድር ጁሀር የቀረበ የለም **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ የቀረበው ክርክር ያለአግባብ መበልፀግ በሚል መነሻ አመልካች ያቀረበው ክስ በይርጋ ቀሪ ሆኗል በሚል የሥር ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ የሕግ ስህተት አለበት በማለት አቤቱታ ስለቀረበበት ነው።
የክርክሩ አጀማመር ሲታይ በአመልካች እና በተጠሪ መካከል በተደረገ የሰሉጥ ሽያጭ ውል መነሻ ተጠሪ ለአመልካች የገንዘብ ክፍያ የሰጠው ቼክ ከፊይ ባንክ ዘንድ ቀርቦ በቂ ስንቅ የላለው መሆኑ ተረጋግጦ በቼኩ መሰረት በአመልካች በኩል ቀርቦ የነበረው ክስ በንግድ ሕግ ቁጥር 881 መሰረት በይርጋ ጊዜ ገደብ ቀሪ በመባለ በንግድ ሕግ ቁጥር 799 መሰረት ተጠሪ በአመልካች ሀብት ያለአግባብ በልጽጓል በሚል መነሻ ብር 2,448,25ዐ ከጥር 1ዐ ቀን 1989 ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ 14% ወለድ ጋር እንዱከፍል እንዱወስን ሲል አመልካች ክስ መመሥረቱን መዝገቡ ያስረዲል።
ክሱን በመጀመሪያ የዲኝነት ሥልጣን የተመለከተው የአማራ ብ/ክ/መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት ክሱን በብይን ውድቅ አድርጓል። ለብይኑ የሰጠው ምክንያትም በአንድ በኩል አመልካች ቀደም ሲል በቼክ መነሻ ያቀረበው ክስ በይርጋ ታግዶል ከተባለ በኋላ ይህንኑ ቼክ መሰረት አድርጎ ያለአግባብ መበልፀግ በሚል የክስ ምክንያት በንግድ ሕግ ቁጥር 799 መሰረት ክስ ማቅረቡ ቀድሞ ከቀረበው ክስ ጋር ተመሣሣይ በመሆኑ ፍ/ቤት በይርጋ ቀሪ ነው ባለው ጉዲይ እንደገና ክስ ማቅረቡ ተገቢነት እንደላለው፣ በልላ በኩል ክስ የቀረበበት ገንዘብ መክፈያ ጊዜ ጥር 1ዐ ቀን 1989 ዓ.ም ሆኖ ክስ የቀረበው ጥር 25 ቀን 1999 ዓ.ም መሆኑን በመጥቀስ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1845 መሰረት 1ዐ /አሥር ዓመት/ ጊዜ አልፍበታል የሚለ ናቸው።
አመልካች በዚህ ቅር ተሰኝቶ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርቦ ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን አስቀርቦ ካከራከረ በኋላ የሥር ፍ/ቤት ውሣኔን አጽንቷል።
የሰበር አመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘት ባጭሩ የሥር ፍ/ቤት ለንግድ ሕግ አንቀጽ 799 የተሣሣተ ትርጉም እንደሰጠ፣ የክሱ አቀራረብ ጊዜን በተመለከተ በመ/ቁ. 5ዐ554 ፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ቀርቦ ፍ/ቤቱም በጉዲዩ ላይ ሥልጣኑ በውክልና ለአማራ ብ/ክ/ጠቅላይ ፍ/ቤት የተሰጠ መሆኑን ጠቅሶ ጥር 23 ቀን 1999 ዓ.ም በብይን መዝገቡን የዘጋ ስለሆነ የይርጋ ጊዜው አቆጣጠር በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1851/2/ መሰረት ተቋርጧል፤ ከዚህም በተጨማሪ የቼኩ መክፈያ ቀን የካቲት 2ዐ ቀን 1989 ዓ.ም ቢሆንም ቼክ ቆርጦ ከሰጠ በኋላ ተጠሪው ከዚሁ በቼክ ከተሰጠው ገንዘብ ውስጥ ሚያዝያ 21 ቀን 1989 ዓ.ም ብር 7ዐ,ዐዐዐ /ሰባ ሺህ ብር/ እና ሰኔ 1ዐ ቀን 1989 ዓ.ም ብር 6ዐ,ዐዐዐ /ስልሣ ሺህ/ ለአመልካች የከፈለ መሆኑን በመጥቀስ ይርጋ ጊዜው መታሰብ ያለበት ከዚህ ጊዜ ጀምሮ መሆን እንዲለበት በመዘርዘር የሥር ፍ/ቤት ክሱ በይርጋ ይታገዲል በማለት የሰጠው ብይን እንዱሻር አመልክቷል።
ይህ ሰበር ችልትም የአመልካችን አቤቱታ መርምሮ አመልካች አለአግባብ መበልፀግን መሰረት በማድረግ ያቀረበው ክስ በንግድ ሕግ ቁጥር 799 መሰረት በድጋሚ የቀረበ ነው ሲል የሥር ፍ/ቤት የሰጠው ትርጉም እና ብያኔ ተገቢነትን ለመመርመር ሲባል ተጠሪ መልስ እንዱሰጥ ትእዛዝ ሰጥቷል።
የተጠሪ ጠበቃ ሐምል 16 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርቧል። ይ/ባይም በቼክ ክስ ቀርቦ በይርጋ ከታገደ በኋላ በንግድ ሕግ ቁጥር 799 ላላ ክስ እንዱቀርብ መፍቀድ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 5 አኳያ የተከለከለ ስለመሆኑ የክፍያ ጊዜንም በሚመለከት ክፍያ የሚፈፀመው ጥር 1ዐ ቀን 1989 ዓ.ም ሆኖ ክስ የቀረበው ጥር 24 ቀን 1999 ዓ.ም በመሆኑ የአሥር /1ዐ/ ዓመት ጊዜ ያለፈ ስለመሆኑና በመ/ቁ. 5ዐ554 የቀረበውን ክስ ፍ/ቤቱ ሥልጠን የለኝም በሚል የተዘጋ ስለሆነ በሰበር መ/ቁ. 16648 በተሰጠው ውሣኔ መሰረት ይርጋ ማቋረጫ ምክንያት ላሆን አይችልም የሚል ክርክር አቅርቧል።
የአመልካች ጠበቃ አቤቱታውን አጠናክሮ የመልስ መልስ ሰጥቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኙ ክርክር ከፍ ሲል የተመለከተ ነው። ችልቱም የተያዘውን ጭብጥ መሰረት በማድረግ ከሕጉ አገናዝቦ መርምሮታል።
እንደመረመርነውም በዚህ ችልት ውሣኔ እንዱሰጥበት የተያዙት ጭብጦች ሁለት ናቸው።
እነዚሁኑ በየተራ እንደሚከተለው ተመልክተናል።
የመጀመሪያው ጭብጥ የሥር ፍ/ቤት የንግድ ሕግ ቁጥር 799 አፈፃፀምን አስመልክቶ የሰጠው ትርጉም አግባብ መሆኑን ወይም አለመሆኑን በተመለከተ ነው።
በዚህ ረገድ ከመዝገቡ መረዲት የተቻለው ተጠሪ ለአመልካች ቆርጦ የሰጠው ቼክ ለባንክ ቀርቦ በቂ ስንቅ የለውም ከተባለ በኋላ ይህንኑ ገንዘብ ተጠሪ እንዱከፍል እንዱወስን አመልካች በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ክስ መሥርቶ ፍ/ቤት ግራ ቀኙን አከራክሮ የቼኩ የክፍያ ቀን የካቲት 2ዐ ቀን 1989 ዓ.ም ሆኖ በቼኩ ክስ የቀረበው ነሐሴ 21 ቀን 1989 ዓ.ም በመሆኑ ክሱ በንግድ ሕግ ቁጥር 881 መሰረት የስድስት /6/ ወር የጊዜ ገደብ ካለፈ በኋላ የቀረበ ነው በሚል በመ/ቁ. 11774 በ4/1ዐ/96 ውሣኔ መሰጠቱን ከዚያም በኋላ ያለአግባብ መበልፀግ በሚል የክስ ምክንያት ለቼኩ መሰጠት ምክንያት የሆነውን ውል እና ያልተከፈለ ቼክ ማስረጃ በማድረግ አመልካች በመ/ቁ.
5ዐ554 በ19/3/99 ዓ.ም ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ክስ ማቅረቡን እና ፍ/ቤቱም የተጠሪን መልስና መቃወሚያ ከተቀበለ በኋላ በ23/5/99 ዓ.ም ጉዲዩን ለመዲኘት ሥልጣን የላለው ስለመሆኑ ጠቅሶ በብይን መዝገቡን መዝጋቱን ነው።
ከዚህ በኋላ ነው እንግዱህ አመልካች በአማራ ብ/ክ/መ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ክስ የመሰረተው የክሱ ምክንያትና ይዘትም ከፍ ሲል ከተጠቀሰው ከመ/ቁ. 5ዐ554 ጋር ተመሣሣይና አንድ ነው።
በዚህ መልክ የቀረበውን ክስ የተመለከተው የአማራ ብ/ክ/መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት የአመልካችን ክስ ላለመቀበል የሰጠው ምክንያት በቼክ ክስ ቀርቦ በይርጋ ቀሪ ነው ከተባለ በኋላ ይህንኑ የክስ ምክንያትና የገንዘብ መጠን መሰረት በማድረግ ያለአግባብ መበልፀግ የሚል ክስ ማቅረብ እንዱቻል የንግድ ሕግ ቁጥር 799 ድንጋጌ የሚፈቅድ አይደለም የሚል ነው።
የዚህ ዓይነት ድምዲሜ የሕጉን ይዘትና ግላማ ያገናዘበ መሆን ወይም አለመሆኑን ለመረዲት የድንጋጌውን ይዘት እንመለከታለን።
የአንቀጽ 799ን ይዘት ከማየታችን በፉት ግን አጠቃላይ ስለቼክ የተመለከቱ ጉዲዮችን በአጭሩ እንዲስሣለን።
በመሰረቱ ቼክ የተወሰነ ገንዘብ ለመክፈል ሐተታ የላለበት ትእዛዝ የያዘና ቼኩም እንደቀረበ የሚከፈል ስለመሆኑ በንግድ ሕግ ቁጥር 827/ሀ/ እና 854 ሥር ተመልክቷል።
እንዱሁም ቼኩ የወጣበት ቀን ከግምት ሣይገባ ቼኩ ከተፃፈበት ቀን አንስቶ በሚከተለት ስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ለክፍያ መቅረብ እንዲለበት አልፍም በቼኩ አውጭውና ላልች ተገዲጆች ላይ አምጪው ክስ ለመመሥረት የሚችለው ቼኩን ለማቅረብ ከተወሰነው ጊዜ ባለት ቀጣይ ስድስት ወራት ጊዜ ስለመሆኑ የንግድ ሕጉ ድንጋጌ ቁጥር 854 እና 881/1/ ይዘት ያስገነዝባለ። እነዚህ ጥያቄዎች የሚቀርቡት በንግድ ሕጉ አንቀጽ 64ዐ እና 868/ሐ/ በተመለከተው መሰረት የቼኩ አውጪና ላልች የጀርባ ፉርሚና እሺ ባይ በቼኩ ለተመለከተው ገንዘብ አከፊፈል ኃላፉ መሆናቸው የተደነገገውን ተከትል ስለመሆኑ መረዲት ይቻላለ።
እነዚህን የሕጉ ድንጋጌዎች ተከትል ክፍያ ያልተፈፀመ እንደሆነ የአምጪው መብት ምን ላሆን ይገባል የሚለውን ጥያቄ በተመለከተ ምላሽ የሚሰጠን የንግድ ሕጉ አንቀጽ 799 ነው። ይህ ድንጋጌ ስለሐዋላ ወረቀት በተመለከተ የተደነገገው ክፍል ውስጥ የሚገኝ ቢሆንም በቼክ ላይም ተፈፃሚነት እንዲለው የንግድ ሕጉ አንቀጽ 886 በግልጽ ያመለክታል።
ስለሆነም የንግድ ሕጉ አንቀጽ 799ን ይዘት ለመረዲት ይቻል ዘንድ እንጠቅሣለን።
799፡ ያላግባብ ስለመበልፀግ የሚቀርብ ክስ፡- 799/1/ በሐዋላ ወረቀት ላይ የተመሰረቱት ግዳታዎቸቸው ጊዜያቸው በማለፈ ወይም በይርጋ ምክንያት የቀሩ ቢሆኑም እንኳ አውጪውና እሺ ባዩ ሕግ በማይፈቅደው አኳኋን ያለአግባብ በመበልፀግ ባገኙት ጥቅም መጠን ለአምጪው ኃላፉዎች ናቸው“ ይላል።
ድንጋጌው ንዐስ ቁጥሮች ቢኖሩትም ለተያዘው ጉዲይ አግባብነት ያለው ይኸው ነው።
ከዚህ ድንጋጌ በግልፅ መረዲት የሚቻለው በቼኩ የተመለከተው ክፍያ ሣይፈፀም ጊዜ ያለፈበት እንደሆነ ወይም በይርጋ ቀሪ ነው የተባለ እንደሆነ የቼኩ አምጪ የቼኩ አውጪ ወይም እሺ ባይ ያለአግባብ በበለፀጉበት መጠን ኃላፉ ስለመሆናቸው ነው።
ይህ ድንጋጌ ግልጽ ነው። የሥር ፍ/ቤት ይህንኑ ግልጽ የሆነውን የሕጉ ድንጋጌ ከንግድ ሕግ ቁጥር 881/ረ/ በማጣቀስ የሰጠው ትርጓሜ አግባብነት ያለው ሆኖ አልተገኘም።
አንድ የሕግ ድንጋጌ ግልጽ ሆኖ በተገኘ ጊዜ ትርጓሜ እንደማያሻው የሕግ አተረጓጎም መርህ ያስረዲል። ስለሆነም ቼኩን መሰረት አድርጎ በሕጉ በተቀመጠው ጊዜ ክፍያ ያልተጠየቀበት ወይም በይዞታ የታገደ የሆነ እንደሆነ ይህንኑ ቼክ እንደተራ ሰነድ በማስረጃነት በማቅረብ ያለአግባብ መበልፀግ በሚል የክስ ምክንያት መክሰስ የሚቻል መሆኑ ግልጽ ነው። አመልካችም የዚህን የንግድ ሕግ ቁጥር 799 መሰረት በማድረግ ክስ የመሰረተ ስለመሆኑ ከመዝገቡ ይዘት መረዲት ተችሎል።
ስለዚህም ክሱን በመጀመሪያ የተመለከተው የሥር ፍ/ቤት የንግድ ሕግ ቁጥር 799ን አስመልክቶ የተሣሣተ ትርጉም የሰጡ መሆኑን መገንዘብ ተችሎል።
ሁለተኛውን ጭብጥ በተመለከተ አመልካች በመ/ቁ. 5ዐ554 በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበው ክስ የይርጋ ጊዜ ያቋርጣል ወይንስ አያቋርጥም? የሚለው ነው።
በዚህ ረገድ የአማራ ብ/ክ/ጠ/ፍ/ቤት ለውሣኔው የሰጠው ምክንያት የፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት መ/ቁ.5ዐ554ን የዘጋው ጉዲዩን ለመዲኘት ሥልጣን የለኝ በሚልም ምክንያት መሆኑን በመጥቀስ ሥልጣን ባለው ፍ/ቤት የቀረበው ክስ የይርጋ ጊዜን ለማቋረጥ የሚያስችል አይደለም በሚል ስለመሆኑ ከመዝገቡ ተመልክተናል።
አመልካች የይርጋ ጊዜው በከፍተኛው ፍ/ቤት በቀረበ ክስ ምክንያት ስለመቋረጡ እና የጊዜውም ስላት ቼኩ ሉከፈል ከሚገባበት የካቲት 2ዐ ቀን 1989 ዓ.ም ጀምሮ መታሰብ እንዲለበት አጥብቆ ተከራክሯል። በዚህ ነጥብ ላይ የተጠሪ ጠበቃ በሰጡት መልስ የይርጋ ጊዜ መታሰብ ያለበት ከጥር 1ዐ ቀን 1989 ጀምሮ ስለመሆኑ ጠቅሰው ይህ ደግሞ ክስ እስከቀረበበት ጥር 24 ቀን 1999 ዓ.ም የአሥር ዓመት ጊዜ ያለፈው መሆኑና ሥልጣን በላለው ፍ/ቤት የቀረበው ክስ ይርጋ ጊዜ አቆጣጠር ማቋረጫ ምክንያት ላሆን እንደማይገባ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በሰበር መ/ቁ. 16648 ታህሣሥ 2ዐ ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠውን ፍርድ በመጥቀስ የሥር ፍ/ቤት ውሣኔ በአግባቡ ነው ሲል ተከራክሯል።
እኛም ይህንኑ የግራ ቀኙን ክርክር ከሕጉ አገናዝበናል። በመሰረቱ የክፍያው ጊዜ ጥር 1ዐ ቀን 1989 ዓ.ም ስለመሆኑ የሥር ፍቤት በውሣኔው አረጋግጧል። ይህ ከሆነ አመልካች በመ/ቁ.
5ዐ554 በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የመሰረተው ክስ ፍ/ቤቱ ሥልጣን የለውም ሲል ክሱን መዝጋቱ የይርጋ ጊዜ ያቋርጣል ወይንስ አያቋርጥም የሚለውን ጭብጥ በተመለከተ ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ. 3673ዐ የሰጠውን አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ማገናዘብ ተገቢ ይሆናል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቀደም ሲል በመ/ቁ. 16648 የሰጠውን አስገዲጅ የሕግ ትርጉም በአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2/4/ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት በመለወጥ በመ/ቁ. 3673ዐ አስገዲጅ ውሣኔ ሰጥቷል። በይዘቱም ጉዲዩ የቀረበለት ፍ/ቤት ሥልጣን የለኝም በሚል ክሱን ቢዘጋውም የይርጋ ጊዜ ማቋረጫ ላሆን እንደሚባ ለዚህም የሕግ መሰረቱ የሥልጣን ጉዲይ መለየት በዋነኛነት የፍ/ቤቱ ኃላፉነት ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር አንቀጽ 9፣ 23/1/ለ እና 231/1/ለ ድንጋጌዎችን እንዱሁም ሕገ መንግሥታዊ መብት የሆነውን ፍትህ የማግኘት መብት መሰረት በማድረግ ነው።
ስለሆነም የዚህ ሰበር ችልት ውሣኔ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ለዚህ ጉዲይም ተፈፃሚነት ያለው ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2/4/ን ይዘት መሰረት በማድረግ ስንመለከተው የሥር ፍ/ቤት የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1851/ለ/ ጠቅሶ የሰጠው ውሣኔ አግባብነት የለውም።
በመሆኑም አመልካች በመ/ቁ. 5ዐ554 ያቀረበው ክስ ህዲር 19 ቀን 1999 ዓ.ም ሲሆን ፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ በብይን የዘጋው ጥር 23 ቀን 1999 ዓ.ም ስለመሆኑ ከመዝገቡ ተረድተናል።
ከዚህ መረዲት እንደሚቻለው ክሱ የ1ዐ ዓመት ጊዜ ገደብ ጥር 1ዐ ቀን 1999 ዓ.ም ቢሆንም አመልካች አስቀድሞ ህዲር 19 ቀን 1999 ዓ.ም በመ/ቁ. 5ዐ554 የመሰረተው ክስ የይርጋ ጊዜውን አቋርጧል።
ስለሆነም አመልካች በአማራ ብ/ክ/ጠቅላይ ፍ/ቤት
No topics extracted.