No summary available.
መጋቢት 6 ቀን 2003 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች- ኤም. ኤ. ሸሪፍ ኃ/የተ/የግል ማህበር - ጠበቃ ይማጅ ዩኒስ - ቀረቡ ተጠሪ- ታይስ ኃ/የተ/የግል ማህበር - የቀረበ የለም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ ለቀረበው የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዲይ የማይገባ የንግድ ውድድር ተፈጽሞአል በማለት የአሁኑ ተጠሪ የመሰረተውን ክስ የሚመለከት ነው። ክሱ የቀረበው ለንግድ አሰራር አጣሪ ኮሚሽን ጽ/ቤት ሲሆን፣ ኮሚሽኑ ከሣሽ እና በወቅቱ ተከሣሾች የነበሩት የአሁኑን አመልካች እና አቶ መሐመድ አደም የተባለውን ግለሰብ አከራክሮአል። በመጨረሻም ተከሣሾች ከከሣሽ የንግድ ምልክት ጋር ተመሣሣይነት ያለውን ምልክት በመጠቀም ምርታቸውን ሲሸጡ ተገኝተዋል። ይህ ደግሞ ተጠቃሚውን ህብረተሰብ ግራ የሚያጋባና የሚያደናግር ተገቢ ያልሆነ የንግድ ውድድር ነው እሚል መደምደሚያ ላይ ደርሰናል። በዚህ መሰረትም ተከሣሾች ድርጊቱን እንዱያቆሙ፣ 1ኛ ተከሣሽ የነበረው /የአሁኑ አመልካች/ ብር 15,000 መቀጫ እንዱከፍል፣ 2ኛ ተከሣሽ የነበረው ግለሰብ ደግሞ በማስጠንቀቂያ እንዱታለፍ በማለት ወስኖአል። በልላ በኩል ደግሞ አመልካች ውሣኔውን በመቃወም ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ በማቅረቡ ክርክሩ የተሰማ ሲሆን፣ ፍ/ቤቱም ኮሚሽኑ ጉዲዩን ለማየት የዲኝነት ሥልጣን የለውም በማለት ይግባኝ የተባለበትን ውሣኔ ሽሮአል። በመጨረሻም ተጠሪ በበኩለ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ በማቅረቡ በዚህ ደረጃም ክርክሩ ተሰምቶአል። በመቀጠልም ፍ/ቤቱ የንግድ አሰራር አጣሪ ኮሚሽን ጉዲዩን ያየው በንግድ አሰራር አዋጅ ቁጥር 329/95 በተሰጠው ሥልጣን ነው የሚል ምክንያት በመስጠት በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሣኔ ሽሮአል። የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚህ ላይ ነው።
አመልካች ሐምል 21 ቀን 2001 ዓ.ም. በጻፈው ማመልከቻ በሥር ፍ/ቤት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞአል የሚልበትን ምክንያት በመግለጽ አቤቱታውን አቀርቦአል።
በበኩላችንም አቤቱታውን መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። ክርክሩ የተሰማው የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ በሕጉ አግባብ የተሰጠ ነው ወይ? በሚለው ጭብጥ ላይ ነው። በሆኑም ግራ ቀኝ ወገኖች በጭብጡ መሰረት ያሰሙትን ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ከሥር ጀምሮ የተደረገውን የግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር እና የተሰጡትን ውሣኔዎች ይዘት በዝርዝር ተመልክተናል። ከዚህም በቅድሚያ ልንገነዘብ የቻልነው ተጠሪ ክስ የመሰረተው የንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ መብትን ለማስከበር ወይም የንግድ ባለቤትነት መብትን ለማረጋገጥ ሳይሆን፣ ከሕግ አግባብ ውጪ ተፈጽሞብኛል ያለውን የማይገባ ውድድር /የንግድ ውድድር/ እንዱገታለት እና አመልካችም ለዚህ ድርጊቱ ተገቢው እርምጃ እንዱወሰድበት በመጠየቅ እንደሆነ ነው። ክሱን የሰማው የንግድ አሰራር አጣሪ ኮሚሽንም ባቀረበለት የዲኝነት ጥያቄ የተፈፀመውን እና በመፈፀም ላይ ያለውን ያልተገባ የንግድ ውድድር እንዱቆም፤ አመልካችም በአዋጁ መሰረት እርምጃ ይወሰድበት የሚል እንደሆነ በመገንዘቡ የንግድ ምልክት ጥበቃን /አዋጅ ቁ. 501/98/ በሚመለከት የሚነሳውን ክርክር የመዲኘት ሥልጣን የለህም በማለት ከአመልካች ቀርቦ የነበረውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ውድቅ በማድረግ በጉዲዩ ሥረ ነገር ላይ አከራክሮ ውሣኔ ሰጥቶአል። የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ደግሞ የሥር ከሣሽ /የአሁኑ ተጠሪ/ ክስ የንግድ ምልክት ባለቤትነትን ማዕከል ያደረገ ነው የሚል ምክንያት በመስጠት ጉዲዩ በኮሚሽኑ የዲኝነት ሥልጣን ሥር አይወድቅም በማለት ወስኖአል። የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት በከፍተኛ ፍ/ቤት ውሣኔ ባለመስማማቱ በአዋጅ ቁ.
329/95 እና በአዋጅ ቁጥር 501/98 መካከል ያለውን ልዩነት በዝርዝር በማመልከት ጉዲዩ በንግድ አሰራር አጣሪ ኮሚሽን የዲኝነት ሥልጣን ሥር የሚወድቅ ነው እሚል መደምደሚያ ላይ ደርሶአል።
በበኩላችንም እንዲየነው የኮሚሽኑ ውሣኔ የተመሰረተው በንግድ አሰራር አዋጅ ቁ.
329/95 አንቀጽ 10 እና 15 በተቀመጡት ድንጋጌዎች ላይ ነው። ተጠሪም ክሱን የመሰረተው በእነዚህ ድንጋጌዎች የተመለከተውን መሰረት በማድረግ ሲሆን ተፈፀመ ወይም እየተፈፀመ ነው ያለውን ድርጊትም በዝርዝር ገልጾ አቅርቦታል። የንግድ አሰራር አጣሪ ኮሚሽን ያልተገባ የንግድ ውድድርን በሚመለከት የሚነሳውን ክርክር የመዲኘት ሥልጣን ያገኘው በንግድ አሰራር አዋጅ ቁ.
329/95 አንቀጽ 15 መሰረት ነው። በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ 1/ሀ/ እና /ሰ/ እንደተመለከተው ኮሚሽኑ ከማንኛውም ወገን የሚቀርቡለትን አቤቱታዎች የአዋጁ ድንጋጌዎችን የመተላለፍ ድርጊት ተፈጽሞአል በሚል እስከቀረቡ ድረስ አቤቱታዎቹን የመመርመር እና /ወይም የቅጣት ውሣኔ የመስጠት ሥልጣን ተሰጥቶታል። በዚህ ረገድ አግባብነት ያላቸው ማለትም ለአቤቱታ መቅረብ መሰረት ሉሆኑ የሚችለት የአዋጁ ድንጋጌዎችም ተገቢ ያልሆነ የንግድ ውድድርን በተመለከተ ዝርዝር ነገሮችን የያዘው አንቀጽ 10፣ ገበያን በበላይነት ያለ አግባብ ስለመጠቀም በሚል የተደነገገው አንቀጽ 11“ን“ መጥቀስ ይቻላል። ከዚህም በተጨማሪ የአዋጁን ዓላማ በዝርዝር ያስቀመጠው አንቀጽ 3 ‛ንም“ መመልከቱ ተገቢ ይሆናል። የአዋጁ ዓላማ፡-
በሚል በዝርዝር ተቀምጦአል።
ቀደም ሲል እንዲመለከትነው አመልካች በአዋጅ ቁጥር 329/95 አንቀጽ 10/2/ሀ/ የተቀመጠውን ድንጋጌ ስለመተላለፈ በተጠሪ ክስ በዝርዝር ተመልክቶአል። የድርጊቱ አፈፃፀም ምን እንደሚመስልም በክሱ ተገልጾአል። በዚህ ረገድ የተጠቀሰው አንቀጽ 10/2/ሀ/ በልላው የንግድ ድርጅት ወይም በንግድ ድርጅቱ ተግባሮች በተለይም ድርጅቱ ከሚያቀርበው ምርት ወይም አገልግልት ጋር በተገናኘ ሁኔታ ማደናገርን ያስከተለ ወይም ሉያስከትል የሚችል ማናቸውም ድርጊት ተገቢ ያልሆነ የንግድ ውድድር ሆኖ እንደሚቆጠር ያመለክታል። አመልካች ፈጽሞታል ወይም እየፈጸመው ነው ተብል በተጠሪ ክስ የተነገረውም ይኸው በድንጋጌው የተመለከተው ድርጊት ነው። የተጠሪ የክስ መነሻ አመልካች እኔ የምጠቀምበትን የንግድ ምልክት አመሳስል በመጠቀም ምርቱን ለገበያ እያቀረበነው የሚል ነው። በአጠቃላይ የተጠሪ ክስ በንግድ አሰራር አዋጅ ቁ.
329/95/ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች የመተላለፍ ድርጊት ተፈጽሞብኛል በሚል ብቻ የሚያቆም ሳይሆን ተፈጸመ /እየተፈጸመ ነው/ የሚለው ድርጊት ከሕጉ ጋር ያለውን ግንኙነት /አግባብነት/ም በግልጽ በዝርዝር የሚያሳይ ነው። አመልካች ጉዲዩ ከንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ መብት አከባበር አንፃር በማየት ነው ኮሚሽኑ ሥልጣን የለውም በማለት እየተከራከረ የመጣው።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም አመልካች የተጠሪን የንግድ ምልክት አመሳስል በመጠቀም ምርቱን ለገበያ እያቀረበ ነው የሚለውን በተጠሪ ክስ የተቀመጠውን አባባል ብቻ አጉልቶ በማውጣት ጉዲዩ ከንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ አዋጅ ቁ. 501/98 አንፃር ነው መታየት ያለበት እሚል መደምደሚያ ላይ ሉደርስ እንደቻለ ከውሣኔው ይዘት ለመገንዘብ ችለናል።
በእርግጥም የክርክሩ አነሳስ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ወደያዘው መደምደሚያ ላይ የሚያደርስ ከሆነ ጉዲዩን ለመዲኘት ሥልጣን የሚኖረው የንግድ አሰሪር አጣሪ ኮሚሽን ሳይሆን የፋዳራል መደበኛ ፍ/ቤት እንደሆነ ከአዋጅ ቁ. 501/98 አንቀጽ 49 መገንዘብ ይቻላል። ይሁንና ወደ ድምዲሜ ከመደረሱ በፉት የተያዘውን ክርክር አጠቃላይ ይዘት እና ተጠሪ በክሱ የጠየቀውን ዲኝነት በአግባቡ መመልከት ተገቢ ይሆናል። በበኩላችን እንደምንገነዘበው በተያዘው ጉዲይ የንግድ አሰራር አጣሪ ኮሚሽን የዲኝነት ሥልጣን አለው ወይስ የለውም? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ በዋናነት መታየት ያለበት የተጠሪ የክስ ምክንያት /መነሻ/ እና በመጨረሻ የተጠየቀው ዲኝነት ነው።
ላላው በመቀጠል መታየት ያለበት ጉዲይ አመልካች እና ተጠሪ በንግድ ሥር ላይ የተሰማሩ ብቻ ሳይሆኑ ተመሣሣይነት ያለው ዕቃም ለገበያ እያቀረቡ ናቸው የሚለው ነው። ተጠሪ ተገቢ ያልሆነ የንግድ ውድድር ተፈጽሞብኛል የሚለውም አመልካች የሱ ያልሆነውን የንግድ ምልክት /ተጠሪ ባለቤት የሆነበትን/ አመሳስል በመጠቀም ምርቱን ለገበያ እያቀረበ /እየሸጠ/ ነው በማለት ነው።
ድርጊቱ ያልተገባ ውድድር ነው እየተባለ ያለውም ተጠሪ ከሚያቀርበው ምርት ጋር ማደናገርን አስከትልአል ስለተባለ ወይም ሉያስከትል የሚችል ሆኖ በመታየቱ ነው። በመሆኑም በክርክር ሂደት ወይም በክሱ አቀራረብ ስለ ንግድ ምልክት በመነሳቱ ጉዲዩ የንግድ ምልክት ባለቤትነት መብት ወይም ምዝገባ ጥበቃን የሚመለከት ጉዲይ ነው ለማለት አይቻልም። በመሆኑም በዚህ ረገድ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የአመልካችን ክርክር መቀበለ ትክከል አይደለም። የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የደረሰበት መደምደሚያ ግን የጉዲዩን ይዘት ከሕጉ ጋር ያገናዘበ የሕግ መሰረት ያለው ነው። ጉዲዩ በእርግጥም በንግድ አሰራር አጣሪ ኮሚሽን የዲኝነት ሥልጣን ሥር የሚወድቅ ነው።
በመጨረሻም የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የዲኝነት ሥልጣንን በመሚመለከት የተነሳውን ክርክር ከወሰነ በኋላ በሥረ ነገር ረገድ ያለውን ክርክር በሥር ፍ/ቤት እንዱታይ አለማድረጉ ተገቢ ነው ወይ? የሚለውን ነጥብ ተመልክተናል። የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በጉዲዩ የመጨረሻ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት እንደመሆኑ ከንግድ አሰራር አጣሪ ኮሚሽን ጀምሮ የተካሄደውን ክርክር ነው የመረመረው። በአጣሪ ኮሚሽኑ እና በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የተሰጡት ውሣኔዎችም በዚህ ሂደት ይመረመራለ። በእርግጥ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ትኩረት አድርጎ የወሰነው በዲኝነት ሥልጣን ረገድ የተነሳውን ክርክር ብቻ በመያዝ በመሆኑ ወደ ጉዲዩ ሥረ ነገር አልገባም። የንግድ አሰራር አጣሪ ኮሚሽን ግን በሥረ ነገር ረገድ የተነሳውን ክርክር ጭምር በመመርመር ውሣኔ ሰጥቶአል። የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤትም በተመሣሣይ ሁኔታ በሁለቱም ነጥቦች ላይ ውሣኔ ሰጥቶአል። ለዚህም ነው የንግድ አሰራር አጣሪ ኮሚሽን የሰጠውን ውሣኔ ማፅናቱን በግልጽ በውሣኔው ላይ የገለጸው። በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 342 እንደተደነገገው ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ይግባኝ በተባለበት መዝገብ ውስጥ የሰፈረው ማስረጃ በቂ ነው የሚል ግምት ከያዘ የነገሩን ጭብጥ በማሻሻል ወይም በመለወጥ ተገቢ መስል የታየውን የመጨረሻ ፍርድ ላሰጥ ይችላል። በያዝነው ጉዲይ የሆነውም ይኸው ነው። የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በይግባኝ ሰሚነቱ ከንግድ አሰራር አጣሪ ኮሚሽን ጀምሮ የተደረገውን ክርክር የተሰማውን ማስረጃ በመመርመር የመጨረሻ ውሣኔ ሰጥቶአል።
የንግድ አሰራር አጣሪ ኮሚሽን በመቃወሚያውም ሆነ በጉዲዩ ሥረ ነገር ላይ የሰጠው ውሣኔ ትክክል ሆኖ ስላገኘውም ሙለ በሙለ አጽንቶታል። በመሆኑም ውሣኔው በሕጉ አተገባበር ረገድ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት የሚያስችል ምክንያት የለም። ስለዚህም ተከታዩን ወስነናል።
ውሣኔ
የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 41022 ሚያዚያ 26 ቀን 2001 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ፀንቶአል።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተቀባይነት የለውም ብለናል።
በዚህ ሰበር ችልት ለተደረገው ክርክር ግራ ቀኝ ወገኖች ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ።
No topics extracted.