No summary available.
ግንቦት 16 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጏስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡-
በዚህ መዝገብ የተያዘው ጉዲይ በመ/ ከቀረቡት ጉዲዮች ጋር ተመሳሳይ የሕግ ጥያቄ ያለበት በመሆኑ መዝገቦችን አንድ ላይ አጣምረን በመመርመር ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሰራተኞች አስተዲደር የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 155/2000 አንቀጽ 37/1/ መሰረት ሰራተኛን በልዩ ሁኔታ ከሥራ ስለማስናበት የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል ሲቪል ሰርቪስ ኤጄንሲ አስተዲደር ፍርድ ቤት ሲሆን በዚሁ ፍርድ ቤት አቤቱታ ያቀረቡት የአሁኑ አመልካቾች ናቸው። የአመልካቾች አቤቱታ ይዘት የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን እየተገበረ ባለው የመሰረታዊ አሰራር ሂደት ለውጥ ምክንያት ምደባ ሳያገኙ የቀሩ በመሆኑ እረፍት እንዱወስደ መደረጉንና ለአስራ አንድ ወራት ደመወዝ ሲከፍላቸው ቆይቶ ሐምል 01 ቀን 2001 ዓ.ም ጀምሮ የስራ ውላቸው ተቋርጦ ከስራ መሰናበታቸው ከሕግ ውጪ መሆኑን ገልፀው ወደ ስራ እንዱመለሱ፣ ይህ የማይሆን ከሆነ ከስራቸው የተሰናበቱበትን ምክንያት በአግባቡ በመግለፅ የአመልካችን የመሰማት መብት ተግባራዊ በማድረግ ተገቢውን ውሳኔ እንዱሰጣቸው ይወሰንላቸው ዘንድ የይግባኝ አቤቱታውን ማቅረባቸውን የሚያሳይ ነው። በአስተዲደር ፍርድ ቤቱ በተደረገለት ጥሪ መሰረት የአሁኑ ተጠሪ ቀርቦም እርምጃው በአዋጅ ቁጥር 578/2000 አንቀፅ 19/1/ለ/ እና በደንብ ቁጥር 155/2000 አንቀጽ 37/1/ መሰረት የተከናወነ በመሆኑ ተገቢ ነው በማለት የአመልካች ይግባኝ ውድቅ እንዱሆን ገልፆ ተከራክሯል። ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት የአስተዲደር ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ የአመልካቾችን ይግባኝ በድምጽ ብልጫ ውድቅ አድርጓል። በዚህ ውሳኔ አመልካቾች ቅር በመሰኘት ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኛቸውን በተለያዩ መዛግብት ቢያቀርቡም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ/337 መሰረት ይግባኛቸው ተሰርዞባቸዋል የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
ከላይ በተጠቀሱት መዛግብት አመልካቾች የሰበር አቤቱታቸውን ያቀረቡ ሲሆን የአቤቱታቸው መሰረታዊ ይዘትም አመልካቾች የኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ ሕገ መንግስት ያረጋገጠልን የመደመጥ መብት ሳይከበር የተሰጠ የባለስልጣኑ መስሪያ ቤት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ጉዲያቸው ባግባቡ እንዱጣራ ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታቸው ተመርምሮም የፋዳራል መንግስት ሰራተኞች አስተዲደር ፍርድ ቤት አመልካቾች የተሰናበቱት በሕጉ አግባብ ነው በማለት የሰጠው ውሳኔ ከሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 155/2000 አንቀጽ 37/1/ እና /2/ አንጻር ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን የግራ ቀኙ የቃል ክርክር መጋቢት 10 ቀን 2002 ዓ/ም በዋለው ችልት በተወሰኑ መዛግብት ሲያሰሙ በተወሰኑ መዛግብት ደግሞ የጽሐፍ ክርክር ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም ጉዲዩን ለሰበር ችልቱ ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው የፋዳራል አገር ውስጥ ገቢና ጉምሩክ ባለስልጣን ሰራተኞች መስሪያ ቤቱ በአዱስ መልክ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ተብል ሲዋቀር የባለስልጣኑ መስሪያ ቤት የሰራተኞችን መተዲደሪያ ደንብ ቁጥር 155/2ዐዐዐ አንቀጽ 37/1/“ን“ በመጥቀስ አመልካቾችን ከስራ ያሰናበታቸው መሆኑን ሲሆን አመልካቾች ይህ የተጠሪ እርምጃ ሕጋዊ አይደለም፣ በሕገ መንግስቱ የተከበረውን የመሰማት መብት የሚጥስ ነው በማለት የሚከራከሩ መሆኑን ተገንዝበናል።
በመሰረቱ ማንኛውም ሰው በፍርድ ሉወሰን የሚገባውን ጉዲይ ለፍርድ ቤት ወይም ለላላ በሕግ የዲኝነት ስልጣን ለተሰጠው አካል የማቅረብና ውሳኔ ወይም ፍርድ የማግኘት መብት ያለው ስለመሆኑ የኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 37/1/ ድንጋጌ በግልፅ የሚያሳየው ጉዲይ ነው። ከዚሁ የሕገ መንግስት ድንጋጌ መገንዘብ የሚቻለው ደግሞ ፍርድ ቤቶች አንድን ጉዲይ (አቤቱታ) ተቀብለው ውሳኔ መስጠት የሚችለት ዲኝነት የተጠየቀበት ጉዲይ በሕግ ለላላ አካል ያልተሰጠ ጉዲይ በሚሆንበት ጊዜ እንደሆነ መሆኑን ነው። በህግ ተለይተው በአስተዲደራዊ ውሳኔ እንዱቋጩ በተባለ ጉዲዮች ላይ መደበኛ ፍርድ ቤት የመዲኘት የስረ ነገር ስልጣን ስለላለው በሕጉ መሰረት ለአንድ አስተዲደር አካል ቀርቦ አስተዲደራዊ ውሳኔ የተሰጠበትን ጉዲይ ወይም ለአስተዲደር መቅረብ የሚገባውን ጉዲይ ፍርድ ቤት ሉያሰተናግደውም ሆነ አከራክሮ ውሳኔ ላሰጥበት አይችልም። ለአንዲንድ የመንግስት አካላት በተወሰኑ ጉዲዮች ላይ የመወሰን ስልጣን የሚሰጡት ሕጎች መጠበቅና መከበር ያለባቸው ሲሆን የዲኝነት አካል ስልጣንም በሕግ የተወሰነ ስለሆነ ሕግ የመተርጎም ስራው በሕጉ በተመለከተው አድማስ የሚመራ ይሆናል። የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 4 ድንጋጌ የሚያሳየውም ፍርድ ቤቶች በልላ ህግ በግልጽ በታገደ ጉዲዮች ላይ አከራክሮ የመወሰን ስልጣን የላላቸው መሆኑን ነው። በመሆኑም በአስተዲደራዊ ውሳኔ የመጨረሻ እልባት እንዱያገኙ በህግ ተለይተው የተቀመጡት ጉዲዮችን ፍ/ቤቶች የመዲኘት ስልጣን የላላቸው መሆኑ ሉስተዋል የሚገባው ጉዲይ ነው። በዚህም መሰረት የሕገ መንግስቱ አንቀፅ 79/1/ እና 37 ድንጋጌዎች አንድ ላይ ሲታዩ ፍ/ቤቶች አንድን ጉዲይ ተቀብለው ለማየትና ለመወሰን ሥልጣን የሚኖራቸው ጉዲዩ በፍርድ ሉወሰን የሚገባው (Justiciable matter) ሆኖ ከተገኘ ብቻ መሆኑን ያስገነዝባለ።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስ አዋጅ ቁጥር 578/2000 የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣንን ያቋቋመ ሕግ ሲሆን በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 19/1/ለ/ ድንጋጌ የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 515/1999 ቢኖርም የባለስልጣኑ ሰራተኞች አስተዲደር የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ መሰረት ይመራል በሚል በኃይለ ቃል ተደንግጎ ይገኛል ። በዚሁ ሥርዓት መሰረትም የሚኒስሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 155/2000 ያወጣ ሲሆን በዚህ ደንብ አንቀጽ 37/1/ ስር በደንቡ በልላ ሁኔታ የተደነገገ ቢሆንም ዋና ዲይሬክተሩ በሙስና የተጠረጠረውንና እምነት ያጣበትን ማንኛውንም ሰራተኛ መደበኛውን የዱስኘሉን እርምጃ አፈጻጸም ሥርዓት ሳይከተል ከሥራ ማሰናበት እንደሚችል የተደነገገ ሲሆን የዚሁ አንቀጽ ንዐስ ቁጥር ሁለት ድንጋጌ ደግሞ ከላይ በተመለከተው ስርዓት መሰረት ከስራ የተሰናበተ ሰራተኛ በየትኛውም የፍርድ አካል ውሳኔ ወደ ስራ የመመለስ መብት እንደማይኖረው አስገዲጅነት ባለው መልኩ አስቀምጧል።
በመሆኑም የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሰራተኞች የሚተዲደሩት አዋጅ ቁጥር 578/2000 ‛ን“ ተከትል በወጣው ደንብ ቁጥር 155/2000 መሰረት እንደሆነ በግልጽ ተመልክቷል። በደንቡ አንቀፅ 37/1/ መሰረት የሥራ ስንብት ቢፈፀም በዲኝነት በፍ/ቤት እንደማይታይ በተጠቀሰው ድንጋጌ በንዐስ ቁጥር ሁለት ድንጋጌ በግልፅ ተመልክቷል። በመርህ ደረጃ ሕግ የማውጣት ሥልጣን በሥልጣን ክፍፍል መርህ መሰረት የሕግ አውጪው አካል ስለመሆኑ ግልፅ ነው። በሕግ አውጪው የመንግስት አካል የሚወጡ ሕጎች ቀዲሚዊ (primary legislations) ተብለው የሚታወቁ ሲሆን ላልቹ እንደአስፈላጊነታቸው አግባብ ባለው አካል የሚወጡ ሕጎች የበታች ህጎች (subsidiary legislations) ተብለው የሚታወቁ ናቸው። ሕግ አውጪው የመንግሥት አካል በተለያዩ ቴክኒካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ምክንያቶች ቀዲሚውን ሕግ ለማስፈጸም የሚያስችለ ዝርዝር ሕጎች ያስፈልጋለ ብል ባመነ ጊዜ ተገቢ ነው ላለው አካል የበታች ሕጎችን እንዱያወጣ ሥልጣን ሲሰጥ ይስተዋላል። ይህ አሰራር በሕግም በምክንያትም የተደገፈ እና የዲበረ ልምድ ስለመሆኑ ግልፅ ነው። በሚኒስትሮች ምክር ቤት የወጣው ደንብ ቁጥር 155/2000 ሕግ አውጪው በሰጠው ስልጣን መሰረት የወጣ ሲሆን በደንቡ አንቀጽ 37 መሰረት ደግሞ ሰራተኛው ከስራ የሚሰናበትበትን አግባብ ደንግጓል። በመሆኑም ወደ ስራ የመመለስ ወይም የመደመጥ መብት በፍርድ የሚያልቅ ጉዲይ አለመሆኑን የተጠቀሱት ድንጋጌዎች ያሳያለ።
ከላይ እንደተገለጸው አንድ ጉዲይ በፍርድ ሉያልቅ የሚችለው ዲኝነት የተጠየቀበት ጉዲይ በሕግ ለላላ አካል ያልተሰጠ ጉዲይ በሚሆንበት ጊዜ እንደሆነ ነው። በተያዘው ጉዲይ ግን አመልካቾች የተሰናበቱት ሕግ አውጪው በዘረጋው ሥርዓት መሰረት ሲሆን አመልካቾች ከጠየቁት ዲኝነት አንጻር (ወደ ስራ መመለስ ወይም የመደመጥ መብት መከበር) ሲታይ ጥያቄው በፍርድ ሉያልቅ የሚችል (justiciable matter) አይደለም።
በመሆኑም የአስተዲደር ፍርድ ቤት ጉዲዩ በፍርድ ቤት ላታይ የሚችል አይደለም በሚል ምክንያት የአመልካቾችን የይግባኝ ቅሬታ በአብላጫ ድምፅ ውድቅ ማድረጉ በአመልካቾች ከተጠየቀው ዲኝነት (ወደ ስራ እንድንመለስ ወይም የመደመጥ መብታችን ይጠበቅልን ከሚለው) አንፃር ሲታይ በአዋጅ ቁጥር 578/2000 አንቀጽ 19/1/ለ/ እና ከሚኒስተሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 155/2000 አንቀጽ 37(1 እና 2) ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ እንዱሁም አላማን የተከተለና ለአስተዲደር አካለ በሕጉ አግባብ የተሰጠውን ስልጣን (executive prerogative) ያከበረ ነው ከሚባል በስተቀር መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ለማለት የሚያስችል ሕጋዊ ምክንያት ያለ ሆኖ አልተገኘም። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራል ሲቪል ሰርቪስ ኤጄንሲ አስተዲደር ፍርድ ቤት በይ/መ//2001 ነሐሴ 18 ቀን 2001 ዓ/ም ጳጉሜ ዐ2 ቀን 2001፣ በይ/መ//2001 ነሐሴ 18 ቀን 2001 ዓ/ም በይ/መ//2001 ነሐሴ 26 ቀን 2001 ዓ./2001 ነሐሴ 26 ቀን 2001 ዓ.ም፣ በይ/መ//2001 ነሐሴ 21 ቀን 2001 ዓ.ም እና በይ/መ//2001 ነሐሴ 13 ቀን 2001 ዓ/ም እና በይ/መ//2001 መጋቢት 08 ቀን 2002 በአቶ አሸናፉ አማረና በአቶ አወቀ ተሻለ ጉዲይ ተሰጥተው በፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በትዕዛዝ የፀኑት ውሳኔዎች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ/ 348(1) መሰረት ጸንተዋል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
የዚህ ውሳኔ ግልባጭ ተጣምረው እንዱታዩ ከተባለት መዛግብት ጋርም ይያያዝ ብለናል።
No topics extracted.