No summary available.
ጥር 27 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፣ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ስላሴ ብርሃኑ አመነው በላቸው አንሺሶ አሉ መሐመድአመልካች - የአቶ መሐመድ ሁሴን ወራሾች
ይህ የሰበር ጉዲይ የቀረበው የግራቀኙን ጉዲይ የፋዳራል ፍ/ቤቶች ተቀብለው ለማየት ሥልጣን የላቸውም በጉዲዩም ላይ ቢሆን የአሁን አመልካቾች ክስ የማቅረብ መብት የላቸውም በሚል ይግባኝ ሰሚው የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጠውን ፍርድ አግባብነት ለጉዲዩ ተፈፃሚነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ተገቢውን ዲኝነት ለመስጠት ሲባል ነው።
ይህንን ጉዲይ ፍ/ቤቶች ተቀብለው ለማስተናገድ የሚያስችላቸው ሥልጣን አላቸው ወይስ የላቸውም? እንዱሁም አመልካቾች በጉዲዩ ላይ ክስ ለማቅረብ የሚያስችል መብት አላቸው ወይስ የላቸውም? የሚለትን ሁለት አከራካሪ ነጥቦች ለመለየት ከእነዚህ ጭብጦች ጋር ተያያዥነት ያላቸውን የፍሬ ነገርም ሆነ የህግ ክርክሮች በእነዚህ ጭብጦች ላይ ከታች ባለት ፍ/ቤቶች በየደረጃው የሰጡት ውሣኔዎች እና ግራቀኙም በጉዲዩ ላይ በሰበር ደረጃ ያቀረቡትን ክርክር ባጭር ባጭሩ ለመጥቀስ ያህል የአሁን አመልካቾች በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በከሣሽነት ያቀረቡት የክስ አቤቱታ የአውራሻችን ንብረት የሆነው በኪራይ ቤቶች አስተደደር ድርጅት በቁጥር 785 በቀበላው ቁጥር 786 ከሚታወቀው ቤት ውጭ ላላ ቤት ስላልነበራቸው አዋጅ ቁጥር 47/67 በወጣበት ጊዜ በቅጽ 004 ተረክበው እያለ ከዚህ ዓለም በሞት በተለዩበት ጊዜ በ1970 ዓ.ም አስረክባችሁ እንደገና ትጠይቃላችሁ በሚል በማስገደድ ቅጽ 003 እንዱሞላ አድርገው እንደ አዋጁ ያልተወረሰውን ንብረት ወስደውብናል ይህንኑ የንብረት ባለቤትነት መብት ለማስከበር ለፔራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ጥያቄ ብናቀርብም እነዚህን ቅጾች መነሻ በማድረግ ጉዲዩ በእኔ ሥልጣን ሥር የሚወድቅ አይደለም በማለት አሰናብቶናል ስለሆነም በአዋጁ መሰረት ያልተወረሰውን ንብረት በጥንቃቄና በኃይል ወስድ ከህግ ውጭ ለ3ኛ ተጠሪ አሳልፍ የሰጠ ስለሆነ ከ1968 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 1994 ዓ.ም ድረስ ያለውን የቤት ኪራይ ብር 390‚000 ከ1995 ዓ.ም ጀምሮ ያለውን ደግሞ የመጠየቅ መብታችንን ከማስጠበቅ ጋር ንብረቱን እንዱያስረክቡ ይድረግልን የሚል ነው።
የአሁን 1ኛ ተጠሪ የቤቱ ባለቤት ስለመሆናቸው ማስረጃ ያላቀረቡ ስለሆነ በጉዲዩ ላይ የመክሰስ መብት የላቸውም ቅፅ 004 ከተሞላ በኃላ መልሰው በቅፅ 003 አስረክበዋል። ቅጽ 004 እንደቋሚ የባለቤትነት ማስረጃም አያገለግልም። ፔራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ በቅፅ 003 በትርፍነት ተሞልቶ ማስረከባቸውን አረጋግጦ አቤቱታውን አልተቀበለውም። በመሆኑም ቤቱ ሉመለስላቸው አይገባም በማለት መልስ ሰጥቷል።
የአሁን 2ኛ ተጠሪም በበኩለ ከከሣሾች ጋር የውል ግንኙነት ስለላለኝ እኔን የመክሰስ መብት የላቸውም ጉዲዩን ማየት የሚችለው ፔራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ነው ኤጀንሲው በሰጠው ውሣኔ ቅር ከተሰኙ ለኤጀንሲው ሥራ አመራር ቦርድ ያቀርባለ እንጂ ፍ/ቤቱ ሉመለከት አይችልም ቤቱ በአዋጅ የተወረሰ ነው በአዋጁ መሰረት ተገቢውን ካሣ ከሚጠይቁ በቀር እኔን ከቤቱ ለማስወጣት የሚያስችል መብት የላቸውም የንግድ ድርጅቱንም በህግ አግባብ ገዝቻለሁ በማለት ተከራክረዋል።
ክሱ የቀረበበት የከፍተኛው ፍ/ቤትም ጉዲዩን ተመልክቶ ጉዲዩን ለማየት ሥልጣን ያለው የፔራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ እንጂ ፍ/ቤት አይደለም በሚል የቀረበውን ክርክር አስመልክቶ የፔራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ሥልጣን በአዋጅ ቁጥር 110/87 መሰረት ከአዋጅ ውጭ በትዕዛዝና በቀላጤ የተወረሱ ንብረቶችን እንጂ ከሣሽ ያቀረቡትን ከህግ ውጭ ቤት ተወርሶብኛል የሚልን ጥያቄ ለመመልከት ሥልጣን የላለው በመሆኑ ተቃወሟቸው ተቀባይነት የለውም።
ዋናውን ጉዲይ በሚመለከት ቤቱ በተወረሰበት ወቅት ላላ ቤት የላላቸው መሆኑን 1ኛ ተከሣሽ የአሁን 1ኛ አመልካች በ18/10/72 ዓ.ም ለከሣሾች የኪራይ ቅድሚያ እንዱሰጣቸው ከፃፈው ደብዲቤ ለመረዲት ተችሎል። የከሣሾች አውራሽ ክስ የቀረበበትን ቤት ላላ ቤት ስለላላቸው በአዋጁ መሰረት ቤቱ ተፈቅድላቸዋል ተብል በ21/3/68 ዓ.ም ቅፅ 004 የሞለ ሲሆን በልላ በኩል በ1970 ዓ.ም ቤቱ ትርፍ ነው ተብል ቅፅ 003 ተሞልቷል። ነገር ግን በዚሁ ቅፅ 003 በተሞላበት ፍርም ላይ ክስ የቀረበበት ቤት ትርፍ ነው ተብል ከተሞላው ቤት ላላ የመረጡት ቤት አልተገለፀም ይህም ከሣሾች አንድ ቤት ብቻ ያላቸው መሆኑን ያመለክታል ተከሣሾች ከሣሾች ቤቱን በቅፅ 003 ሞልተው ቤቱ በትርፍነት ተወርሷል በማለት ይከራከሩ እንጂ አዋጁን አስፈፃሚ እንደመሆናቸው መጠን የአዋጁን መንፈስ የሚቃረኑ ከሆነ ህገወጥ ናቸው የማይባለበት ምክንያት አይኖርም ተከራይ ነኝ የሚለው የአሁን አመልካች ድርጅቱን ከ1ኛ መልስ ሰጭ ተከራይቼ እየተገለገልኩበት እገኛለሁ የሚለው ክርክሩ ክርክር ከተነሳበት ቤት ጋር የሚገናኝ ባለመሆኑ ተቀባይነት የለውም በመሆኑም ከላይ በተገለፁት ምክንያቶች በአዋጁ መሰረት ሉወረስ የሚገባው ትርፍ ቤት ከሆነ ብቻ ስለሆነ ቅጽ 003 ተሞልቶ ተወርሷል የሚለው ክርክር ህጋዊ መሰረት ስለላለው እና ከህግ ውጭ መወረሱን ስለሚያስረዲ ተከሣሾች ቤቱን ሉመልሱ ይገባል ቤቱ በኪራይ ያስገኘውን የገንዘብ መጠን አስመልክቶ የቀረበ ክርክር ስለላለም ከብር 390‚000 /ሶስት መቶ ዘጠኛ ሺህ/ ጋር ለከሣሾች ያስረክቡ በማለት ወስኗል።
የአሁን 1ኛ ተጠሪ እና 2ኛ ተጠሪዎች በተናጠል ያቀረቡትን የይግባኝ መዝገብ አጣምሮ የተመለከተው የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በበኩለ በፍ/ብ/ይ/መ/ የካቲት 28 ቀን 2000 በዋለው ችልት ከሣሾች በአዋጅ ቁጥር 110/87 መሰረት ሥልጣን ላለው ለፔራይቬይታይዜሽን ኤጀንሲ ቤቱ እንዱመለስላቸው ጠይቀው ቤቱ በቅጽ 003 ተሞልቶ በመሰረዙ ምክንያት ጥያቄያቸው ተቀባይነት ማጣቱን የክስ ማመልከቻቸው እያስረዲ ሥልጣን ያለው አካል ውሣኔ ያሰፈረበትን ነጥብ ቤቱ ከህግ ውጭ የተወረሰ ነው በማለት ከፍተኛው ፍ/ቤት መወሰኑ በላለው ሥልጣን ነው፣ ከዚህም በተጨማሪ በአዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት ቤቱ ትርፍ ነው አይደለም ሉወረስ ይገባል አይገበም? ብል የመወሰን ሥልጣን ያለው የሥራና ከተማ ቤቶች ሚ/ር ስለመሆኑ በአዋጁ ተጠቅሶ እያለ ከሣሾች ትርፍ ቤት ሳይኖራቸው የተወረሰባቸው ያለአግባብ ነው ማለቱ በላለው ሥልጣን በመሆኑ እንዱሁም ቤቱ ከተወረሰ በኃላ በአዋጅ ቁጥር 47/67 ሆነ ይህንኑ አዋጅ ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 292/18 መሰረት ቤቱ እንዱመለስላቸው በወቅቱ አጠራር ለሥራና ቤቶች ሚ/ር አመልክተው እንዱመለስላቸው ተወስኖ ውሣኔው በሚ/ሩ የፀደቀበትን ማስረጃና በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1195/1/ መሰረት የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነታቸውን ለማወቅ የተሰጣቸው የባለቤትነት የምስክር ወረቀት ስላላቀረቡ ከሣሾች ከመነሻውም ቢሆን ክስ በቀረበበት ሐብት ላይ ጥቅም ወይም መብት ያላቸው መሆኑን ስላላረጋገጡ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 33/2/መሰረት በቤቱ ላይ ክስ የማቅረብ መብት የላቸውም።
ስለሆነም በእነዚህ ነጥቦች ላይ ያቀረበውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ መቀበል ሲገባው አልፍ በፍሬ ጉዲዩ ላይ ውሣኔ መስጠቱ ተገቢ አይደለም በማለት የሥር ፍ/ቤትን ውሣኔ ሽሮታል።
ለዚህ የሰበር ጉዲይ መነሻ የሆነው የአሁን አመልካቾች በዚህ የጠቅላይ ፍ/ቤት ውሣኔ ላይ ተፈፅሟል የሚለትን የህግ ስህተት ለማሳየት ዝርዝር የሰበር አቤቱታ በማቅረባቸው ሲሆን ፍሬ ቃለም ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በቤቱ ላይ ክስ ለማቅረብ የሚያስችላቸው መብት የላቸውም በማለት የሰጠው ውሣኔ ያቀረብነውን የፍሬ ነገር ክርክርና ማስረጃ መሰረት ያደረገ አይደለም።
እንዱሁም የፔራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ማስረጃዎችን አጣርቶ ቅጽ 003 የተሞላው ከህግ ውጭ መሆኑን በኤክስፏርቶች ካረጋገጡ በኃላ ቤቱ ሉመለስ ይገባል በማለት ወስኗል። ሆኖም የኤጀንሲው ሥራ እስኪያጅ ቅጽ 003 በህግ አግባብ ያልተሞላ ቢሆንም ሰነደ ህጋዊነት አለው ወይስ የለውም የማለት ሥልጣን ለኤጀንሲው አልተሰጠውም ስለዚህ ሰነደ በህግ ውጤት የለውም ቤቱ ሉመለስ ይገባል ለማለት አይችልም ከማለት ውጭ ቅፅ 003 በህግ አግባብ የተሞላ እና ቅጽ 004ን የሻረ ነው አላለም ስልጣን የለኝም ማለት በጉዲዩ ላይ ውሣኔ ተሰጠ ማለት አይደለም ስለሆነም ማንኛውም ሰው በህገ መንግስቱ የተረጋገጠለትን መብት ያለህግ የግል ንብረቴን ማጣት የለብኝም በማለት መብቱን ማስከበር የሚችለው በፍ/ቤት ዲኝነት በመጠየቅ በመሆኑ ኤጀንሲው የመጨረሻ ውሣኔ ባልሰጠበት ጉዲይ የቀረበውን የዲኝነት ጥያቄ ፍ/ቤት የማየት ሥልጣን አለው የሚል ነው።
ተጠሪዎችም በየፉናቸው ለሰበር አቤቱታው መልሳቸውን አቅርበዋል። በይዘቱም በሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት እና በይግባኝ ሰሚው ጠቅላይ ፍ/ቤት ያቀረቡትን መልስና ቅሬታ የሚያጠናክር የጠቅላይ ፍ/ቤቱ የሰጠውን ዲኝነት ትክክለኛነት የሚያስገነዝብ በመሆኑ በድጋሚ ማስፈሩ አስፈላጊ ሆኖ አላገኘነውም።
አመልካቾችም በመልስ መልሳቸው በፅሐፍ ያቀረቡት ክርክር በየደረጃው ባለት ፍ/ቤቶች የቀረበውን የሚያብራራ እና የሚያጠናከር ነው።
እንግዱህ የጉዲዩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምረናል።
ይህንን ጉዲይ የከፍተኛው ፍ/ቤት ተመልክቶ ለመወሰን ሥልጣን የለውም በሚል ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የሰጠውን ዲኝነት በማስቀደም ተመልክተናል።
በኢት/ያ ፋዳራላዊ ዱሞክራሲያዊ ሪፐብላክ ህገመንግስት አንቀጽ 37 እንደተደነገገው አንድን ጉዲይ ተመልክቶ ዲኝነት ለመስጠት ሥልጣን የተሰጠው ለላላ የዲኝነት አካል ከሆነ ፍ/ቤቶች ጉዲዩን የማየት ሥልጣን የላቸውም ለላላ በህግ የዲኝነት ሥልጣን ለተሰጠው አካል መቅረብ የሚገባው ጉዲይ ለፍ/ቤቶች በቀረበ ጊዜ ጉዲዩ በየትኛው የክርክር ደረጃና በየትኛውም የፍ/ቤት እርከን ቢገኝም በሥልጣን ምክንያት ክርክሩ ሉቋረጥ እና ቀሪ ላሆን እንደሚገባ ይኸው ህገ መንግስታዊ ድንጋጌ ሆነ በዝርዝር ህጉ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 231/1/ /ለ/፣ 9/2/፣ 244/3/ እና 328/3/ ተመልክቷል።
በዚህም መሰረት ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በይግባኝ የቀረበለትን ጉዲይ ከፍ/ቤቶች ሥልጣን አንፃር መመርመሩ አግባብ ቢሆንም ይህ ጉዲይ ቀደም ሲል ለፔራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ቀርቦ የታየና ውሣኔ ያገኘ ጉዲይ ስለሆነ ፍ/ቤቶች ተቀብል ለማስተናገድ የሚያስችላቸው ሥልጣን የለውም በሚል የሰጠው ዲኝነት ስለጉዲዩ ግራቀኙ በፍሬ ነገር ረገድ ያቀረቡትን ክርክር መሰረት ያደረገ ሆኖ አላገኘነውም ይኸውም ለዚሁ ውሣኔ እንደመነሻ ያደረገው ጉዲዩ ለፔራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ቀርቦ ውሣኔ ያገኘ ስለመሆኑ የከሣሾች የክስ ማመልከቻ በግልፅ ያስረዲል የሚለውን በመያዝ ነው ይሁን እንጂ የከሣሾች የክስ ማመልከቻ ክሱ ቀርቦለት የነበረው የፔራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ መምሪያ ቤቱ በአዋጁ መሰረት ያልተወረሰ መሆኑን አረጋግጦ እንዱመልስልን የወሰነልን ቢሆንም ዋና ስራ አስኪያጅ ጉዲዩ በኤጀንሲው ሥልጣን ሥር የማይወድቅ መሆኑን ጠቅሶ ሥልጣን የለኝም ብለናል የሚለውን የሚጠቅስ እንጂ እንደይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ውሣኔ የሚናገር አይደለም።
አመልካቾችም ይህንኑ የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ውሣኔ በመንቀፍ በሰበር አቤቱታቸው ገፅ 4 የመጨረሻ ክፍል ላይ ኤጀንሲው ጉዲዩን ተመልክቶ ውሣኔ የሰጠበት ጉዲይ ሳይሆን ሥልጣን የለኝም በማለት ነው ያሰናበተን በማለት ላቀረቡት ቅሬታ 1ኛ መልስ ሰጭ በሰጠው መልስ ገፅ 3 የመጨረሻ ክፍል የፔራይቨታይዜሽን ኤጀንሲም ቢሆን ይህን የማጣራትም ይሁን ትክክለኛነቱን ወይም ህገ ወጥነቱን የመመርመር ሥልጣን የላለው መሆኑን በመግለፅ መዝገቡን ዘግቶታል ቤቱ የተወረሰው ከአዋጁ ውጭ ነው በማለት ቤቱ እንዱመለስላቸው በኤጀንሲው የተሰጠ ውሣኔ የለም በማለት ጉዲዩ በኤጀንሲው በኩል ቀርቦ ክርክር ተደርጏ ማስረጃ ተመርምሮ ተገቢውን ዲኝነት ያረፈበት ሳይሆን ጉዲዩን ለማየት ሥልጣን የለኝም በማለት የዘጋው መሆኑን ሁለ አረጋግጧል ይህ ሆኖ እያለ ይግባኝ ሰሚው ጠቅላይ ፍ/ቤት በጉዲዩ በኤጀንሲው ታይቶ ዲኝነት ያረፈበት ጉዲይ ነው የሚለውን መነሻ አድርጎ ጉዲዩን የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የማየት ሥልጣን አልነበረውም በማለት የሰጠው ዲኝነት የግራቀኙን ክርክር መሰረት ያደረገ ባለመሆኑ የተነሣ የተሳሳተ ሆኖ አግኝተነዋል።
ጉዲዩ በአዋጅ ቁጥር 110/87 እንደተመለከተው ጉዲዩ በፔራይቬታዜሽን ኤጀንሲ ሥልጣን ሥር የሚወድቅ አይደለም ተብል መመለሱ ከተረጋገጠ እና አሁንም ቢሆን ይህን ጉዲይ አይቶ ለመወሰን ሥልጣኑ ለላላ የዲኝነት አካል የተሰጠ ነው የሚል የህግ ክርክር እስካልቀረበ ድረስ የህገ መንግስቱ አንቀጽ 37 ድንጋጌ ይህንኑ ጉዲይ በፍ/ቤት ቀርቦ እንዲይታይ የሚከለክል አይደለም በዚህ ረገድ የሥር ጠቅላይ ፍ/ቤት ሥልጣኑን አስመልክቶ የሰጠው ትርጓሜ የግራቀኙን ክርክር ይዘት ካለማገናዘብም ሆነ ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ድንጋጌ አንፃር ሲታይ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
እንዱሁም ትርፍ ቤት ነው ወይስ አይደለም? ሉወረስ ይገባል ወይስ አይገባም?
የሚለውንም ጉዲይ በአዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት አዋጁን ለማስፈፀም ሥልጣን በተሰጠው አካል ከሚታይ በቀር የፍ/ቤቶችን ዲኝነት የሚጠይቅ ጉዲይ ባለመሆኑ ፍ/ቤቱ ሥልጣን የለውም በሚል በሁለተኛ ደረጃ የሰጠውንም ትርጉም እንደተመለከትነው ከሣሾች ያቀረቡትን የክርክር ይዘት ያገናዘበ አይደለም የከሣሾች የክስ መነሻ አውራሻችን አዋጅ ቁጥር 47/67 በወጣበት ጊዜ ከዚህ ክርክር ካስነሳው ቤት ላላ ትርፍ ቤት የላላቸው መሆኑን በማረጋገጥ አዋጁን ለማስፈፀም ሥልጣን በተሰጠው አካል ተረጋግጦ በ21/03/68 ዓ.ም ቅፅ 004 ተሞልቶ ቤቱ ሳይወረስ በአባታችን ባለቤትነት ዘልቆ ቆይቷል በባለቤትነት መብታቸውም እየተገለገለበት እያለ በ1970 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ምክንያት በማድረግ እኛን ወራሾችን ከቤት አስመጥተው እንደተወረሰ አድርገው ቅጽ 003 በመሞላት ያልተወረሰን ንብረት ተወስድብናል በማለት ቤቱን ለማስመለስ አዋጁን ለማስፈፀም ሥልጣን የተሰጠው አካል ያደረገውን የፈቃድ ተግባር መነሻ በማድረግ የሚከራከሩ መሆኑን ያገናዘበ አይደለም በእነዚህ ፍሬ ነገሮች በመመሥረት የቀረበው የቤት ይመለስልኝ አቤቱታ ከመነሻውም በፍርድ ሉያልቅ የሚችል አይደለም ከሚል መደምደሚያ ለመድረስ የሚያስችል የህግ መሰረትም አላገኘንበትም ከዚህም ነጥብ አንፃር ቢሆን ፍ/ቤቶች ጉዲዩን ተቀብለው ለመወሰን የሚያስችል ሥልጣን የላቸውም የሚለው ትርጉም ህጋዊ መሰረት ያለው ሆኖ አልተገኘም።
ሶስተኛውና ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትን ውሣኔ ለመሻር በምክንያትነት የጠቀሰውን የክስ ምክንያት የላቸውም የሚለውንና የዲኝነት አግባብነት የአሁን አመልካቾች በክስ ማመልከቻቸው ላይ ከገለፁት የክስ ምክንያት እና የማስረጃ ዝርዝር ጋር ተገናዝቦ ላታይ ይገባዋል።
አመልካቾች በሥር ፍ/ቤት ባቀረቡት የክስ ማመልከቻና የማስረጃ ዝርዝር ላይ ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት ከአዋጅ ቁጥር 47/67 በፉት ሀብትነቱ የአባታቸው የአውራሻቸው የነበረ መሆኑን አዋጁ እንደወጣም በአዋጁ መሰረት ትርፍ ቤት የላላቸው መሆኑ ሥልጣን በተሰጠው አካል በቅፅ 004 ተረጋግጦ ህዲር 21 ቀን 1968 ተሞልቶ ተሰጥቷቸው በባለቤትነት በይዞታቸው እያለ በ1970 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን በ1970 ዓ.ም የቤቱ ባለቤት ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለዩ በተደራቢ ቅፅ 003 የአሁን 1ኛ ተጠሪ እንደተረከበው ጠቅሰዋል ይህም ስለመሆኑ በየደረጃው የተሰጠው ውሣኔም ያስረዲል።
እንዱሁም አመልካቾች በክስ ማመልከቻቸውና በሰበር ደረጃ በተደረገው ክርክር እንደገለፁት በፔራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ የተደረገው ክርክርና ማስረጃ ከተሰማ በኋላ መምሪያው የሰጠው ውሣኔ በሥልጣን ምክንያት ቀሪ ይሁን እንጂ የቤቱ አወራረስ እንደ አዋጁ ነው ወይስ አይደለም?
የሚለውን አስመልክቶ የኤጀንሲው ኤክስፏርቶች አረጋግጠው መምሪያው እንዱመለስ አድርጎ ነበር ለሚለው ክርክራቸው ተጠሪውም ይህ ውሣኔ የመ/ቤቱ የበላይ ውሣኔ አይደለም ተፈፃሚነት የለውም የተቋም ውሣኔ እንደሆነ አይቆጠርም በሚል ተከራከሩ እንጂ በፍሬ ነገር ረገድ ሐሰት ነው አልተባለም የሚል ማስተባበያ አላቀረቡበትም ስለጉዲዩ በልላ የዲኝነት ሰጭ አካል በተደረገ ክርክር የተረጋገጠ ጉዲይ ሥልጣን ባለው ፍ/ቤት ክርክር በቀረበ ጊዜ ያለው ተቀባይነት ምን ያህል ነው?
የሚለው አከራካሪ ነጥብ እንዲለ ሆኖ አሁን ለተያዘው የመክሰስ መብት አላቸው ወይስ የላቸውም የሚለውን ለመለየት ግን አግባብነት ያለው በመሆኑ እነዚህ ፍሬ ነገሮችና የከሣሾች የማስረጃ ዝርዝር በጉዲዩ ላይ ክስ የማቅረብ መብት ያላቸው ለመሆኑ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 33/2/ አንፃር ሲታዩ በቂ መነሻዎች ናቸው።
የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ መብትና ግዳታን ወደ ተግባር ለመለወጥ የሚረዲ መሣሪያ እንደመሆኑ ክስ የሚያቀርብ ወገን ክስ የሚያቀርብበት ጉዲይ ከህግ በመነጨ መብት የተደገፈ ተከሣሹም መብቱን ለማሟላት በህግ ግዳታ የተጣለበት መሆኑን ሉያሳይ ይገባዋል በሚል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 33/2/ እና /3/ የተቀመጡት ድንጋጌዎች ተገቢ ያልሆነ ክስ እንዲይቀርብ መገደቢያዎች ከመሆኑ አንፃር ስታይ በዚህ ጉዲይ ከሣሾች በጉዲዩ ላይ ክስ ለማቅረብ የሚያስችል መብት ያላቸው ስለመሆኑ በክሳቸው የገለፁት የክስ ዝርዝር እና ማስረጃ አረጋገጭ ናቸው ጉዲዩን ለማስረዲት በብቸኝነት መቅረብ የሚገባው የባለቤትነት የምስክር ወረቀት ነው ለማለትም አያስችልም።
ከዚህ ጋር በተያያዘ በተመሳሳይ ጉዲይ ይህ የሰበር ሰሚ ችልት ተመልክቶ ከዚህ በፉት የመክሰስ መብት የለም በሚል ስለተረጋገጠው በዚያው አንፃር ይታይልን በማለት በሰበር መ/ በአመልካች የኪራይ ቤቶች አስተዲደር ድርጅት እና በአቶ ሰለሞን ወረደ መካከል የነበረውን ጉዲይ በመጥቀስ ሁለተኛ አመልካች ያቀረበውን ክርክር ተመልክተናል። በተመሳሳይ ጉዲይ የሰበር ሰሚ ችልት የሰጠው የህግ ትርጉም በየትኛውም ደረጃ ላለ ፍ/ቤት የአስገዲጅነት ባህሪ የሚኖረው ጉዲዮች በፍሬ ነገር እና በማስረጃ አቀራረብ ተመሳሳይ ሆነው በተገኙ ጊዜ ለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 454/97 አስረጂ ነው በሰበር መ/ በተነሳው ጉዲይ ቤቱን በውርስ ይገባኛል ሲል ክስ ያቀረበው ወገን ከአዋጅ ቁጥር 47/67 በፉት የነበረን ካርታና የቤት ሥራ ፈቃድ መሰረት በማድረግ የቀረበ ከመሆኑ በቀር በአዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት ሉወረስ የማይገባበትን ምክንያት አዋጁን መሰረት በማድረግ ያቀረበው ክርክርም ሆነ ማስረጃ የለም ከአዋጁ አፈፃፀም ጋር በተያያዘ የህግ ጥያቄ ሉያስነሳ የሚችል ለመሆኑ መነሻ የሚሆኑ የፍሬ ነገሩና የማስረጃ ጉዲይ የቀረበበት አይደለም በክርክርና በማስረጃ ረገድ ሁለቱም የተለያዩ ናቸው ስለሆነም በተመሳሳይነት የሚወሰንበት አግባብ አላገኘንበትም በዚህ ሁለ ምክንያት ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ክስ የቀረበለት ፍ/ቤት ጉዲዩን ለመመልከት የሚያስችለው ሥልጣን የለውም በሚል እና በጉዲዩም ቢሆን አመልካቾች ክስ ለማቅረብ የሚያስችል መብት የላቸውም በሚል የሰጠው ትርጉም የግራቀኙን የክርክር ይዘትና ለጉዲዩ አግባብነት ያላቸውን ድንጋጌዎች ባለማገናዘብ የተሰጠ ትርጉም በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል። በመሆኑም የሚከተለውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
ይግባኝ ሰሚው ጠቅላይ ፍ/ቤት በፍ/ብ/መ/ የካቲት 28 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
አመልካቾች ክስ ባቀረቡበት ጉዲይ ክስ የማቅረብ መብት አላቸው ጉዲዩንም ተመልክቶ የፋዳራል ከፍተኛው ፍ/ቤት ውሣኔ የሰጠው በሥልጣኑ ስር የሚወድቅ ሆኑ በመገኘቱ ነው ብለናል።
ጉዲዩ የሚያስከስስ እና በስር ፍ/ቤት ስልጣን ስር የሚወድቅ በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 33/2/ ሆነ በሥልጣን ምክንያት ጉዲዩ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የሚቋጭ ስላልሆነ በቀሪው ጉዲይ ላይ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በይግባኝ ሥልጣኑ ተመልክቶ ተገቢውን ዲኝነት ይሰጥበት ዘንድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁ 341 መሰረት ጉዲዩን መልሰናል።
በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ግራቀኙ ላደረሱት ክርክር ወጭና ኪሣራ ይቻቻለ መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.